ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
7.08K subscribers
1.29K photos
8 videos
37 files
262 links
የዲ.ን ዮርዳኖስ አበበ ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
ከመላእክትም አንዱ ከሀዲ ጉዝፋር ከዚህ ለምን ቆምክ አለው። እርሱም ወዳጁ መርቀፀ ለክብር ባለቤት #ለጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ እንጂ ለሌላ እንዳይሰጥ ብሎ እንዳማለው ነገረው። መልአኩም የክብር ባለቤት የሕያው #እግዚአብሔር_ልጅ_ጌታ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ይህ ነውና ና ስገድ አለው።

ጉዝፋርም ሰገደ ደብዳቤውንም ሰጠው።እየተንቀጠቀጠም የክብር ባለቤት #ጌታዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ አመንኩብህ አለ። ጌታም ያንን ወርቅ ይመዝኑ ት ዘንድ አዘዘ። አርባ ልጥርም ሆነ ጉዝፋርንም ከቀሲስ ታዴዎስ ዘንድ እንዲጠመቅ አዘዘው። ከቤተሰቡ ሁሉ ጋር ተጠመቀ የተጠመቁትም ሰባ አምስት ነፍስ ሆኑ።

ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ለዘለዓለሙ ይሁን አሜን፡፡

#የዕለተ_ሐሙስ_ፍጥረታት

#ሐሙስ፡- የሚለው የዕለቱ ስም ሀምሰ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው #አምስተኛ ማለት ነው፡፡ አምስተኛነቱም እግዚአብሔር ፍጥረታትን መፍጠር ከጀመረበት ከዕለተ እሑድ ጀምሮ ያለው ቀን ማለት ነው፡፡

  #የሐሙስ_ፍጥረታት
እግዚአብሔር ሐሙስ በቀዳማይ ሰዓት ለሊት “#ውሃ_ሕያው_ነፍስ_ያላቸው_ተንቀሳቃሾች_ታስገኝ” ብሎ በማዘዝ ሦስት አይነት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ዘፍ 1፡20 በዕለተ ሐሙስ የተፈጠሩት ሦስት ፍጥረታት ዘመደ እንስሳት የሚባሉት አሣዎች፣ ዘመደ አራዊት የተባሉት ኣዞ፣ጉማሬ፣ አሳነባሪ፣ ዘመደ አዕዋፍ የሚባሉት ደግሞ ዳክዬዎች ናቸው፡፡ 
#በዕለተ_ሐሙስ_የተፈጠሩት_ፍጥረታት_ተፈጥሮአቸው_ከአራቱ_ባሕሪያተ_ስጋ /መሬት፣ ውሃ ፣ነፋስና፣ እሳት/ ነው፡፡ አካላቸው ሥጋና ደም፣ አፅምና ጅማት ሲሆን በደም ነፍስ ይንቀሳቀሳሉ የደመ ነፍስ እውቀት አላቸው ደመነፍስ ማለትም በደም ነፍስነት፣ ኃይልነት የሚንቀሳቀሱ፣ የደም ነፍስ ያላቸው፣ ደማቸው ሲቆም እንቅስቃሴያቸውም የሚቆም ማለት ነው፡፡
   #የሐሙስ_ፍጥረታት_በአካሄዳቸው_በአኗኗራቸው_አንፃር_በሦስት_ይከፈላሉ በአካሄዳቸው በልብ የሚሳቡ፣ በእግር የሚሽከረከሩ፣ /የሚሄዱ/፣ በክንፍ የሚበሩ ይባላሉ፡፡

#በአኗኗራቸውም አንጻር በባህር ውስጥ ተፈጥረው በረው ወደ የብስ፣ ወደ ደረቁ መሬት የወጡ፣ በዚያው በተፈጠሩበት በባህር ውስጥ የቀሩ፣ ወጣ ገባ እያሉ ማለት ከባህር ወደ የብስ፣ ከየብስ ወደ ባሕር ወጣ ገባ እያሉ የሚኖሩ ይባላሉ፡፡ ከእነዚህም ፍጥረታት የሚበሉና የማይበሉ ለሰው የሚገዙና፣ የማይገዙም አሉ፡፡
    
#የሐሙስ_ፍጥረታት_ምሳሌነት

#በባሕር_ውስጥ_የሚኖሩት_ምሌሳነታቸው፡-

በእግዚአብሔር አምነው በስሙ ተጠምቀው በዚያው ፀንተው የሚኖሩ ሰዎች፤
በሕገ እግዚአብሔር ፀንተው በትዳር ተወስነው በሀብት በንብረታቸው መልካም ስራ እየሠሩ ዓሥራት አውጥተው፣ በዓላትን አክብረው የሚኖሩ የሕጋውያ ሰዎች፤
ግብራችንን አንተውም ብለው ሲሰርቁ ሲቀሙ፤ ሲምሉና ሲገዘቱ የሚኖሩ የኃጥአን ምሳሌ ናቸው፡፡

#ወጣ_ገባ_እያሉ_የሚኖሩት_ምሳሌነታቸው
  አንድ ጊዜ ወደ ዓለም አንድ ጊዜ ወደ ገዳም ሲመላለሱ የሚኖሩ መነኮሳት፣
አንድ ጊዜ ወደ ሀይማኖት አንድ ጊዜ ወደ ክህደት የሚወላውሉ ሰዎች፤
#በባሕር_ተፈጥረው_በረው_ወደ_የብስ_የሄዱት
ከዘመድ አዝማድ ተለይተው ርቀው ከበረሃ ወድቀው ደምፀ አራዊቱን ፀብአ አጋንንቱን ግርማ ለሊቱን ታግሰው የሚኖሩ የመናንያን ምሳሌ ናቸው፡፡
አንድም በባህር ተፈጥረው በረው ወደ የብስ የሚኖሩት የከሀዲዎች ምሳሌ ነው በሀይማኖት ኖረው በኋላ ይክዳሉና
           
#አካሄዳቸውም 
#በልብ_የሚሳቡ፡- የመንግስት ምሳሌ ናቸው እነዚህ በልብ (በደረት) ተስበው ስራቸውን ፈቃዳቸውን እንዲፈፅሙ መንግስትም በልቡ ያሰበውን ይሠራል ይፈፅማል፡፡
#በእግር_የሚሽከረከሩ
“ያላችሁን ትታችሁ ተከተሉኝ” ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ሁሉን ትተው ከሴት ከወንድ እርቀው ድንግልናቸውን ጠብቀው ከትሩፋት ወደ ትሩፋት እየተሸጋገሩ የሚኖሩ የመናንያን ምሳሌ፡፡

#በክንፋቸው_የሚበሩት፡- ሥጋችሁን እንጂ ነፍሳችሁን ለመግደል የማይችሉትን አትፍሩ ባለው አምላካዊ ቃል ተመርተው ሳይፈሩ ዓላውያን ነገስታት ካሉበት ገብተው ሃይማኖታቸውን በመመስከር ሰማዕታትነታቸውን የሚፈፅሙ ሰማዕታት ምሳሌ ናቸው፡፡
  #ሰው_የሚባላቸውና_ለሰው_የሚገዙት፡- ለእግዚአብሔርና ለሰው በፍቅር በትሕትና የሚገዙ፣ የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚፈፅሙ የፃድቃን ምሳሌ ናቸው፡፡
#ሰው_የማይበላቸው_ለሰው_የማይገዙት ለእግዚአብሔርም ለሰውም የማይገዙ፣ አንገዛም አንታዘዝም ብለው በትዕቢት በዓመፅ የሚኖሩ የሃጣን ምሳሌ ናቸው፡፡
እግዚአብሔር ከአንድ ባሕር ሦስት ወገን የሆኑ ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ ከአንድ ማየገቦ ሦስት ትውልድ፡- ትውለደ ሴም፣ ትውልደ ያፌት፣ ትውልደ ካም ይጠመቁ ዘንድ መሰጠቱን  ያሳያል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ልጅነት በአብ‹ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቀው ለመሰጠቷም ምሳሌ ነው፡፡
  በዕለተ ሐሙስና በዕለተ ዓርብ የተፈጠሩት ፍጥረታት “እንስሳት” በመባል አንድ ቢሆኑም በአኗኗራቸውና በግብራቸው ይለያያሉ፡፡ የሐሙስ ፍጥረታት ከባሕር ተለይው በየብስ /በምድር/ መኖር አይችሉም የፀሐይ ሙቀት ሲነካቸው ይሞታሉ፡፡
  የግብር ፍጥረታትም ከምድር ተለይተው በባህር ውስጥ መኖር አይችሉም የባህር ውርጭ ቅዝቃዜ ይገድላቸዋልና፡፡

#ሚያዝያ_1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት፣
፩, ቅዱስ መርቄ ጻድቅ (ክርስቲያናዊ ነጋዴ)
፪, ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
፫, አባ ሚካኤል ዘእስክንድርያ
፬, #እግዚአብሔር በእግር የሚራመዱ በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታትን ፈጠረ

#ወርኃዊ_በዓላት
፩, በዓታ ለእግዝእትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪, ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫, ቅዱሳን ሊቀ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን)
፬, አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭, አቡነ ዜና ማርቆስ
፮, አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል

እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም። መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል። መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።(ማቴ. ፭÷፲፬-፲፮)

        ✝️ወስብሐት ለ#እግዚአብሔር✝️
#ጥቅምት_7

#አባ_ባውላ
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም
ጥቅምት ሰባት በዚች ቀን ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።

ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው። እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ #ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።

#መጀመሪያው ራሱን በዕንጨት ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደ ተሰቀለ ኖረ። ደሙም በአፍንጫው ፈሰሰ ነፍሱንም አሳለፈ #እግዚአብሔርም ከሞት አነሣው።

#ሁለተኛው ዓሣዎችና ዓንበሪዎች እንዲበሉት ራሱን ከባሕር ጨመረ እነርሱ ግን አልነኩትም በባሕርም ሠጥሞ ብዙ ወራት ኑሮ ሞተ። ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስም ዳግመኛ ከሞት አስነሣው።

#ሦስተኛም ጊዜ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ደፍኖ ሞተ #ጌታችንም አስነሣው።

#አራተኛም በውስጡ ስለታሞች ድንጋዮች ካሉት ረጅም ተራራ ላይ ወጥቶ ራሱን ከተራራው ላይ ወደ ታች ወርውሮ ተንከባለለ የተሳሉ ደንጊያዎችም በሥጋው ሁሉ ገብተውበት ሞተ። ረድኡም ያለቅስለት ነበረ #ጌታችንም መጥቶ ከሞት አሥነሣው አጽናናውም ።

#አምስተኛ ከረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ከስለታም ደንጊያ ላይ ራሱን ወረወረ ከሁለትም ተከፈለና ሞተ ያን ጊዜም #ጌታችን አስነሣው።

#ስድስተኛ ራሱን በእግሮቹ ውስጥ አሥሮ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት እንዲህ ሁኖ ሞተ #እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሞት አነሣው አጽናናውም።

#ሰባተኛ ከውኃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እጆቹን ዘርግቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት በመቆም ሞተ ክብር ይግባውና #ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።

አባ ባውላም ለ #መድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት #ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ። #ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።

ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ #ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።

ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች። ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች። እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።

#ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

በተጨማሪ በዚች ቀን #የአባ_ባውላ_ረድእ_አባ_ሕዝቅኤል መታሰቢያቸው፣ የቅዱሳን ሰማዕታት #የሚናስና_የሐናሲ_መታሰቢያቸው ነው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት_7)