Hakim
52.3K subscribers
23.5K photos
228 videos
466 files
4.33K links
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Download Telegram
Vacancy announcements: -

Organization: Eban speciality center 

Work place: Jimma

Positions
Position 1:- Nurse
1.1 Education: Diploma Nursing
Quantity  Required: 1
Experience: 0 year
1.2 Education:  Diploma Nursing
Quantity  Required: 2
Experience: above 2 years
1.3 Education:  BSc Nursing
Quantity  Required: 1
Experience: 0 year
1.4 Education:  BSc Nursing
Quantity  Required: 2
Experience: above 2 years with License

Position 2:- Midwifery
2.1Education:  BSC Degree in Midwifery
Quantity  Required: 1
Experience: Above 2 years
2.2 Education: diploma  in Midwifery
Quantity  Required: 2
Experience: Above 2 years

Position 3- pharmacy
3.1Education: Bsc pharmacy
Quantity  Required: 1
Experience: Above 2 years
3.2 Education: diploma in pharmacy
Quantity  Required: 1
Experience: Above 2 years

Position 4- Laboratory
4.1 Education: diploma in Laboratory
Quantity  Required: 1
Experience: Above 2 years
4.2 Education: Bsc  in Laboratory
Quantity  Required: 1
Experience: Above 2 years
4.3 Education: Bsc in Laboratory
Quantity  Required: 1
Experience: 0 years

Position 5- Radiographer
5.1 Education level 4
Quantity  Required: 1
Experience: above 2 years

Position 6- General Practitioner
6.1Education: MD
Quantity  Required: 1
Experience: Above  2years

Position 7- Porter
7.1 Education:10+
Quantity  Required: 2
Experience: Above 2  years

Position 8- cleaner
8.1 Education: 10+
Quantity  Required: 6
Experience: above 2  years

Position 9- laundry
9.1Education: 10+
Quantity  Required: 2
Experience: above 2years

Position 10- guard
10.1 Education: above 8
Quantity  Required: 2
Experience:0 year

Position 11- human resource manager
11.1 Education: BA in management
Quantity  Required: 1
Experience: above 4 years preferable if worked in health sector

Position 12- accountant
12.1 Education: BA in accounting
Quantity Required: 1
Experience: above 2 years

Position 13- runner
13.1 Education:10+
Quantity  Required: 1
Experience:

Position 14- secretary
14.1 Education: diploma in IT/computer science
Quantity  Required: 1
Experience: above 2 years

Deadline: May 27, 2024
How To Apply: Submit your application letter, updated CV, and renewed professional license via email: ebanhealthjimma@gmail.com bring in person Eban specialty center near Lina international hotel office no 011

For furtuer information call 0912222843 / 0928302555 / 0717019944

@HakimEthio
"ምግብ የሚያስቸግሩ ልጆችን እንዴት እንመግባቸው" - ዶ/ር ንጉሤ ጫኔ ፤ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም

ከአንድ እስከ ሦሥት ዓመት ያሉ ልጆች መደበኛ አመጋገብ የላቸውም። አንድ ቀን በድንብ ይበላሉ ሌላ ቀን ደግሞ ፈጽመው ምግብ መንካት አይፈልጉም። ቁርስ በደንብ በልተው ምሳ ላይፈልጉ ይችላሉ። ይህ የተለመደ ፀባያቸው ስለሆነ አይጨነቁ። ግን ምግብ በደንብ የሚበላ ልጅ ምግብ በተደጋጋሚ ከቀነሰ ያን ጊዜ የልጅውዎን ሀኪም ያማክሩ።

አንዳንዴ ምግብ መብላት ለልጆች እንደ ስራ ከባድ ይሆንባቸዋል። እንዴት እንደምናስተካክለው ቀጥሎ ይመልከቱ።

1. የህጻናትን የምግብ ፍላጎት ያክብሩ፥ ሳይፈልግ ምግብ እይስጡ

ህፃናት አዲስ ምግብ እንዲለምዱ እድል ይስጡ። ሳይቀምሱ አልወድም ወይም ያስጠላል ስለሚሉ መጀመሪያ ጣእሙን እና ቀለሙን እያደነቁ ይቅመሱላቸው ከዚያ እንዲሞክሩ ይጋብዙ።

አስገድደው ውይም ደልለው ለመመገብ አይሞክሩ ምክንያቱም በምግብ ሰአት ሁልጊዜ እንዳይጨነቁ።
ልጅዎ የማይወደውን ምግብ በራበው ሰዓት ለመስጠት ይሞክሩ። ምግቦችን በተለያየ ቀልም እና ጣእም ያለማምዱ።

2. የተለመደ የምግብ ሰዓት ያስለምዱ - ሁልጊዜ በተመሳሳይ ሰአት ይመግቡ።

ምግብ አልበላም ሲሉ ወተት ወይም ጭማቂ፣ ጣፋጭ ምግብ የሚሰጡ ከሆነ ይከልክሉ።

3. አዳዲስ ምግቦችን ለማስለመድ ትእግስተኛ ይሁኑ
ህፃናት አዲስ ምግብ ነክተው አሽትተው በምላስ ቀምሰው ተፍተው ነው የሚለምዱት። ግን ደጋግመው እንዲሞክሩ እድል ይስጧቸው ይሳካል።የምግቡን ቀለም፣ቅርፅ ሽታውን እየነገሩ እንዲወዱት ያድርጉ። አዳዲስ ምግቦችን ከለመዱት ጋር በማቀላቀል ይስጡ።

4. እንደ ምግብ ቤት የሚፈልጉትን ምግብ ብቻ እንዲያዙ እድል አይስጡ።

አንድን ምግብ እምቢ ሲሉ ወዲያው ተለዋጭ ምግብ ለመስራት አይቸኩሉ። ቢመገቡም ባይመገቡም የቀረበ መአድ እስኪነሳ ከገበታ ላይ እንዳይነሱ ያድርጉ። ይህም የመአድ ጊዜን ማክበር እንዲማሩ ያግዛል።

5. ምግብ ሲሰሩ የምግቦች ቅርፅ ልጅ ሳቢ እና አመራማሪ እንዲሆን አድርጉ። አንዳንዴ የቁርሱን ምግብ በራት ሰዓት የምሳውን ለቁርስ ሰዓት አድርገው ምግብን እንዲወዱ ማስደመም ይችላሉ።

6. አትክልት ስንገዛ ልጆች አብረውን ካሉ የሚፈልጉትን አትክልት እንዲመርጡ እድል ይስጡ።

7. ቤተሰቡ የሚመገበውን ምግብ በማፍራረቅ ለህፃናት አርአያ ይሁኑ።

8. ምግቦችን የፈጠራ ችሎታን ተጠቅሞ መስራት ልጆች በቀላሉ እያድነቁ እንዲበሉ ያደርጋል። የተፈጨ ብሮኮሊ ከሩዝ ወይም ከፓስታ ጋር ወይም የተፈጨ ጎመን ወይም ካሮት ከሾርባ ...ወዘተ

9. በምግብ ሰአት ሀሳብ የሚሰርቁ የኤሌክትሮኒክ መሳሪያዎችን ያጥፉ።

10. እባክዎ ይህን ከበላህ/ሽ ይህን እሰጥሀለሁ ብለው ምግቦችን አያበላልጡ። ከምግብ በኋላ ፍራፍሬ እንጂ ጣፋጭ አያስለምዱ።

11. የምግብ ሰዓትን የምግብ እና አመጋገብ መማሪያ ማድርግ እና ልጆች ስለሚመገቡት ምግብ አመጋገብ ዘዴ ፣ ምንነት እና ጥቅም እንዲያዉቁ ያድርጉ።

12. በምግብ ሰአት የሚያወሩት ገንቢ ሀሳብ እና አስደሳች ከሆነ ይህንን ጊዜ ቤተሰቡ ይናፍቀዋል።

13. ምግብ እኛ እናቅርብላቸው ወይስ ራሳቸውን ያስተናግዱ የሚለውን በየወቅቱ መለዋውጥ

14. ልጆች ምግብ እንዲሰሩ ወይም ሲሰራ እንዲያዪ እድል ይስጡ። ይህም ምግብን እየወደዱ እንዲመገቡ ያግዛል።

ይህ ሀሳብ ይጠቅማል ብለው ካሰቡ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ። ብንማርበት እርስዎንም ወዳጅዎንም ይጠቅማል ብለው የሚያስቡት ጉዳይ ካለ በአስተያየት (Comment) ያድርሱን።

@HakimEthio
📌 Real time Support
📌 Best quality
📌 Friendly service

BMY Diagnostic and Imaging Center, Perfecting Your Medical decision

📍Address - around Ras Desta Hospital next to Arbegnoch School at Gutter Building ground floor
Contact -9560 /0947868686 / 0947858585
Email: info@bmymedtech.com
Website: https://bmymedtech.com
Facebook: https://www.facebook.com/bmytechnologies?mibextid=LQQJ4d
Telegram: https://t.me/bmymedtech
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/bmymedicaltechnologies/
አጣዳፊ የሆነን ያልተጠበቀ (ለምሳሌ በምሽት ለሚከሰት) የጥርስ ህመም ፡ በጊዜያዊነት ለማስታገስ ፡ በቤት ውስጥ እኚህን ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል!

1. የህመም ማስታገሻ መዳኒቶች ፡ መዋጥ (መድኒቶችን ቦታው ላይ መንከስ ተገቢ አይደለም!)

2. ለብ ያለ 1 ብርጭቆ ውሀ ግማሽ ማንኪያ ጨው አሟሙቶ ፡ መጉሞጥሞጥ!

3. ቁሩንፉድ ለንቅጦ (የውስጥ ዘይቱን) ህመም ያመጥው ጥርስ ውስጥ ማስቀመጥ!

4. በረዶ ውሀ በፎጣ ጠቅልሎ ፡ በዙሪያው ማስደገፍ (በተለይ ስፍራው እብጠት ካለው!)

5. ዝንጅብል አድቆ ፡ መንከስ!

6. ህመም ያስከተለውን ነገር ከለዬ ማስወገድ (ቀዝቃዛ ውሀ ፣ ጣፋጭ ወይንም ምግብ ማኘክም ከሆነ መተው)

7. የተቦረቦረ ጥርስ ውስጥ የተሰገረ ምግብ ወይም ጣፋጭ ካለ ፡ በጥንቃቄ ማውጣት!

የተጠቀሱት ሁሉም መፍትሄዋች : ጊዜያዊ 'ማስታገሻዋች' ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው እንጂ ፡ ዘላቂ መፍትሄዎች አይደሉም! ሲመቻች ወዲያው ሀኪም ቤት በመሄድ መታየት እና ቋሚ መፍትሄ መፈለግ የግድ ይላል!

በቸልታ ህመሙን በተደጋጋሚ እያስታመሙ በሽተኛ ጥርስን በአፍ ወስጥ ሳያሳክሙ ማቆየት : መዘዙ የእትዬ ለሌ ነው!

ዶ/ር በረከት ማተያስ : Dental Surgeon
https://t.me/beckymatthiasdentalsurgeon

@HakimEthio
Ethiopian Physiotherapy Association is delighted to invite you to the upcoming panel discussion "Assistive Device and Technology Integration in Physiotherapy Practice."

The event, scheduled for May 25, 2024, from 2:00 PM to 11:00 PM at the Ethiopian Sport Academy,

Fill this form to secure your spot
https://forms.gle/TGMvTejZuR5ovFNu9

@HakimEthio
የኒው-ዮርክ የውስጥ ደዌ ልዮ ክሊኒክ የስነ-ደዌ ህክምና ክፍል የተለያዪ አገልግሎቶችን ይሰጣል ከእነዚህም ውስጥ የመቅኔ ምርመራ ፣ በአልትራሳውንድ የታገዘ የናሙና መውሰድ እና ምርመራ እንዲሁም በተለያዪ የሰውነት ክፍሎች ላይ ለሚወጡ እብጠቶች በቀጭን መርፌ ናሙና በመውሰድ የስነ-ደዌ ምርመራ እንዲሁም የማህፀን በር ቅደመ ካንሰር ምርመራ እናደርጋለን።

Newyork's Internal Medicine Specialty Clinic pathology department serves a fluid cytology, FNAC, Ultrasound guided FNAC, peripheral morphology, bone marrow aspiration and biopsy with histopathology service and Pap-smear test are available.

QUALITY CARE WITH COMPASSION!
ጥራትን ከርህራሄ ጋር!

☎️ +251462219119
📞 +251925636085
📞 +251916068121

📍 Infront of Hawassa Referral Hospital.

📍ከሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ፊት ለፊት።


Telegram - https://t.me/NEWYORKIM
"የእብድ ውሻ" በሽታ ሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?

- በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው።

- የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ ፣ ፈረስ ፣ ላም ፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

- ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።

መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?

- በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ (saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል (fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል።

- በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት (central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል (brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል።

- የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል።

ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?

-አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በኃላ ምልክት እስከሚያሳይ (incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3 ወር ሊቆይ ይችላል።

- ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ ፣ ትኩሳት ፣ እራስ ምታት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ፍራቻ ፣ ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር ፣ ለመዋጥ መቸገር ፣ ቅዠት ፣ ግራ መጋባት ፣ ዉሃን መፍራት (hydrophobia) ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል።

- ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።

እንዴት መከላከል እንችላለን?

- የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ
-ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን (post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን።

ህክምናውስ?

- የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም። ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ (Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም።

- ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው።

- በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ በመሆኑ ሁሉም ከውሻ በሽታ መጠበቅ ይገባል ያሰፈረውን አቅርበናል ። መልካም ቆይታ!

Dr. Tewdros Adisu

@HakimEthio
Clinical_Case_Reports_2024_Tukeni_Hypereosinophilic_syndrome_with1.pdf
2.4 MB
Hypereosinophilic syndrome with cardiac and cutaneous involvement: Missed treatment opportunity of a case from Ethiopia

Kedir Negesso Tukeni, Tadesse Dukessa Gemechu, Mohammed Abafogi, Amare Ashine, Tamirat Godebo Woyimo, Abdo Abafogi, Elsah Tegene Asefa

http://dx.doi.org/10.1002/ccr3.8844

@HakimEthio
To post your papers on the channel, use this link t.me/HakimAds to send your PDF

@HakimEthio