Hakim
53.3K subscribers
24.4K photos
248 videos
503 files
4.58K links
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Download Telegram
ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት የደም ልገሳ መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡
በደም ልገሳ መርሀ ግብሩ የላንሴት ሰራተኞች ፣በማዕከሉ የሚገኙ አስታማሚዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ከተመሰረተ ወደ አራተኛ ዓመት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን ከተመሰረተ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በየሶስት ወሩ የደምልገሳ ፕሮግረም ያካሂዳል፡፡
ላንሴት አጠቃለይ ሆስፒታል በግሉ ዘርፍ አንቱታን ያተረፈ የመዲናችን ትልቅ የጤና ማዕከል ነው፡፡

ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል
በሀኪምች ህብረት ለህብረተሰብ ጤና የቆመ
ስልክ ፡ 9171 ወይም 0977 71 71 71
አድራሻ ፡ መገናኛ አደባባይ ፣ አፋረንሲስ ህንፃ

Get in touch:
Telegram | Facebook | Instagram | TikTok | Website |
The 3rd Annual Meeting and Scientific Conference of the Association of Ethiopian Pediatric Surgeons (AEPS) concluded on May 19th at the Elilly International Hotel.

This event served as a dynamic platform for knowledge exchange and discussions on the state of pediatric surgery in Ethiopia, as well as the path forward.

The pre-conference workshop on May 18th featured two distinctive training courses: “Resuscitation and Transfer of Pediatric Surgery Patients” and “Soft Skill Training in Pediatric Surgery”. These courses provided valuable insights for health professionals across the country.

The conference brought together pediatric surgeons and health professionals from across Ethiopia, fostering a robust professional network. It featured insightful abstract presentations and updates on pediatric surgical treatments.

Additionally, it highlighted the need for support in key areas to enhance pediatric surgical care in low- and middle-income countries.

#AEPS2024 #PediatricSurgery #HealthcareInEthiopia

@HakimEthio
Soviet Red Cross Hospital, now Balcha Hospital, in Addis Ababa, 1979

📷 ታሪካችን

@HakimEthio
4.7kg የሚመዘን የኩላሊት ዕጢ | Dhiitoo kalee kiiloo 4.7kg madaalu

ከታች የምትመለከቱት ፎቶ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ከ38 አመት ሴት ታካሚ ከቀኝ ኩላሊት ላይ  የወጣ ዕጢ ነው።

ታካሚዋ ለ5 ዓመታት የቆየ የሆድ እብጠት በቀኝ በኩል ይዛ ነው የመጣችው። እሷን በጥንቃቄ ከገመገምን እና ሲቲ ስካንን ጨምሮ አስፈላጊ ምርመራዎችን ካደረግን በኋላ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ወሰንን።

እንዲህ ዓይነቱ ቀዶ ጥገና በሆስፒታላችን የመጀመሪያ ጊዜ ነው የተሰራው:: ቀዶ ጥገናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ እና 4.7 ኪሎ ግራም ክብደትን ሚመዝን ዕጢም በተሳካ ሁኔታ  አወጣን:: በአሁኑ ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች::

ስለ ኩላሊት ካንሰር
- የኩላሊት ካንሰር ብዙ ጊዜ ምንም ምልክት አይታይበትም እና ብዙ ጊዜ በሌሎች የጤና እክሎች ምርመራ ወቅት ይገለጻል። ምልክቶችን ለመመርመር የአልትራሳውንድ ስካን ሲጠቀሙ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የአዋቂ የኩላሊት እጢዎች ተገኝተዋል

-አንዳንድ የኩላሊት ካንሰር ምልክቶች ግልጽ ያልሆኑ እና እንደ ዝቅተኛ የጀርባ ህመም፣ ሥር የሰደደ የሽንት በሽታ፣ ሥር የሰደደ ድካም ወይም ውጥረት ወይም መጨናነቅ ባሉ ሌሎች ችግሮች ሊታዩ ይችላሉ።
- የተለመዱ ምልክቶች የምንላቸዉ
- መመርመር ያለበት አስፈላጊ ምልክት በሽንት ውስጥ ያለው ደም ነው:: አንዳንድ ጊዜ ሊያዩት አይችሉም, ስለዚህ በሽንትዎ ቀለም ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች መታየት አለባቸው::

- በሽንት ውስጥ ያለው ደም የኢንፌክሽን፣ የኩላሊት ጠጠር፣ የፕሮስቴት ችግር ወይም አንዳንዴ የፊኛ ካንሰር ምልክት ነው። ስለዚህ፣ የካንሰር ምልክት የመሆኑ ዕድል ባይኖረውም፣ ካንሰርን እና ሌሎች ከባድ መንስኤዎችን ለማስወገድ ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማግኘት ሐኪምዎን ማየት አለብዎት።

-  በኩላሊትዎ አካባቢ እብጠት  ከተሰማዎት ወዲያውኑ ለሐኪምዎ መንገር አለብዎት

- በጎንዎ ላይ ይሔም በጎድን አጥንትዎ እና በዳሌዎ አጥንት (አንዳንድ ጊዜ ወገብ አካባቢ ይባላል) ሕመም ከተሰማዎት። ይህ ለብዙ ሌሎች ምክንያቶች ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህ ካለብዎ ለሐኪምዎ መንገር ጥሩ ነው::

Suuraan armaan gadii kun hospitaala Riferaalaa Yuunivarsiitii Ambootti baqaqsanii yaaluun nama waggaa 38 kan taate irraa  kan ba’e dha.Yaalamtuun kun waggaa 5f garaan ishee gama mirgaatiin dhiita'ee dhufte. Dhiitoon kunis kalee ishee kan mirgaa irraa kan ka’e dha.Of eeggannoodhaan, madaallee CT-scan dabalatee qorannoo barbaachisaa erga goonee booda baqaqsanii yaaluuf murteessine. Baqaqsanii yaaluun gosa akkanaa yeroo jalqabaaf hospitaala keenya keessatti raawwatame.Baqaqsanii yaaluun kunis haala milkaa'inaan xumuramee. Dhiitoon kalee irraa ka’e kunis ulfaatina kiiloograama 4.7 madaalame. Yaalamtuun kun yeroo ammaa haala gaariirra jirti.

Hubannoo Kaansarii kalee
1. Kaansariin kalee yeroo baay’ee mallattoo kan hin qabnee fi  yeroo haalawwan fayyaa biroo adda baafaman kan mul'atudha. Dhibeen kalee akkasii ga’eessota keessaa walakkaa ol kan ta’an altiraasaawundii  fayyadamuun kan argamudha.

2. Mallattoolee waliigalaa kan jennu, fakkeenyaaf, dhiigni fincaan keessatti argamuu, yookaan boora'uu fincaanii.
Yeroo tokko tokko ija keenyaan arguu waan hin dandeenyeef jijjiiramni halluu fincaanii keessanii kamiyyuu qoratamuu qaba.

-Dhiigni fincaan keessatti argamu mallattoo infekshinii, cirracha kalee, rakkoo piroostaatii ykn yeroo tokko tokko kaansarii ujummoo fincaanii ti.

-Kanaaf mallattoo kaansarii ta’uun isaa hin oolu yoo ta’ellee, kaansarii fi sababoota ciccimoo biroo akka hin mudanneef qorannoo dabalataaf hakiima keessan ilaaluu qabdu.

3. Naannawaa kalee keetii dhiibbaan ykn dhiita'uun yoo sitti dhaga'ame hatattamaan dooktora keetti himuu qabda.Kunis milikkita kaansarii kalee ta'uu danda'a.

4. Dhukkubbiin cinaacha-kun sababoota biroo hedduudhaaf dhufuu danda'a, garuu kana yoo qabaatte doktora keetti himuun yaalamuun gaariidha.

Operating team
Surgeon : Dr. Ibsa Daba (Assistant Professor of Urology)
Assistants: Dr. Solomon (R-4 General surgery), Dr. Mokenin (R-4 General surgery), Dr. Tesfaye (R-3 General Surgery )

Scrub: Sr. Abigiya Runner: Bayisa
Anesthesia Team Leader: Gemechis

ኩላሊቶቻችሁ ከሁሉ የተሻለ እንክብካቤ ይገባቸዋል | Your kidneys deserve the best care

[Written consent for use of image and history has been obtained and will be presented upon request]

Prepared by: Dr. Ibsa Daba

@HakimEthio
የመንጋ ስነልቦና/Crowd Psychology
**

ሁላችንም  ግላዊ ፍላጎቶታችንን ከማህበራዊ ቅቡልነቶች ጋር አስማምተን እንድናኬድ የሚያስችለን የራሳችን(individual) የስነልቦና መዋቅር አለን::

በዘመናችን ፈቅደንም ይሁን ተገደን የተለያዩ ቡድኖች አባል መሆናችን አይቀርም::  ይህ ቡድንተኝነት አወንታዊም አሉታዊም ይዘት ሊኖረው ይችላል:: በሂደትም የቡድኑን ስነልቦና ተላብሰን እንደመንጋ ማሰብና መንቀሳቀስ እንጀምራለን:: የግል ስነልቦናችን አቅሙን ያጣና በመንጋነት ስነልቦና መተካት ይጀምራል:: 

የመንጋነት ስነ-ልቦና የሚከተሉት መገለጫዎች አሉት:-

▫️ መንጋ አሪፍ መደበቅያ ነው:: (Anonymity)

ለየብቻ የሚወሰድ ሃላፊነት አይኖርም:: ይህም ልቅ ፍላጎቶችን ተጠያቂ ሳይሆኑ በህቡዕ ለማስፈጸም እድልን ይሰጣል:: ለዚህ ነው በብሄር ታርጋ ስንቱ የልቡን መሻት የሚያራምድብን::

▫️መንጋነት የሚጋባ ስሜት(Contagion) አለው::

መንጋው በአንድ ልብ የሚያስብ ይመስል ለእኩይም ይሁን መልካም አድራጎቶች መተባበር ይጀምራል:: ልክ ቀፎው እንደተነካ ንብ ግርርር ማለት አንዱ የመንጋው መገለጫ ነው::

▫️መንጋው የመሪውን ቃል ያለማመንታት ይፈጽማል(Suggestibility):: ይህም መሪዎቹ መንጋውን ለመንዳት ያመቻቸዋል::

▫️ መንጋው በዋናነት በደመነብሳዊ ልቦና(unconscious mind) የሚመራ እና አሰናሳይነት የጎደለው ነው:: ይህም ከእውነታው ይልቅ ለምናባዊ ነገሮች(illusion) ቦታ እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል:: መሪዎችም ይህን illusion ስለሚያውቁ በቃላት መሸንገልን ተክነውበታል::

በሃገራችንም አብዮት፣ ህዳሴ፣ ብልጽግና፣ እናሸንፋለን/እናቸንፋለን ቃላት በመንጋው ዘንድ ያላቸውን ቅቡልነት ማንሳት ይቻላል::

ሌላም መገለጫዎችን እንጨምር...

መንጋዎች....

▪️ግልፍተኞች፣ቁጡዎች እና ጨካኞች ናቸው::( አንዳንድ ቸር ቡድኖች ባይጠፋም):: ለውሳኔ ይቸኩላሉ: ጽንፍ መያዝ ይቀናቸዋል:: ነገሮችን ካላጋነኑ አይሆንላቸውም::

▪️ትዕግስት የላቸውም: የፈለጉት ነገር ወድያውኑ እንዲፈጸም ይፈልጋሉ

▪️የሚጣረሱ ነገሮችን ጎን ለጎን ሊያራምዱ ይችላሉ::

አማኞች እና ገዳይ/ሙሰኞች ፤ መግደል ሃጥያት ነው የሚል አስተምህሮ ያላቸው ግን ለበድናቸው ልዕልና ሲሆን መግደል ጀብደኝነት እንደሆነ የሚደሰኩሩ ፤  ሁሉም ሰው እኩል እንደሆነ የሚሰብኩ ግን ዘወር ብለው ስለ ብሄራቸው/መደባቸው የበላይነት የሚደነፉ ፤ አቃፊም አጥፊም መሆን የሚቻላቸው...ናቸው መንጋዎች!

▪️መደበኛ ነገሮች ደስታን አይሰጧቸውም:: ሁሌም አዲስ illusion እና አጀንዳን ይሻሉ.. መሪዎችም ይህን ካላደረጉ ከስረዋል😊

▪️ለመሪዎቻቸው ያጎበድዳሉ: ሳያጎበድዱ መኖሩን አይችሉበትም::

▪️ፍቅር እና ርህራሄ እምብዛም አይገዟቸውም:: እንዲያውም የድክመት እና የሞኝነት ምልክት ሁነው ይቆጠራሉ:: ይልቁንስ 'ቂጥ ቂጣቸውን በሳንጃ' እያለ ለሚገዛቸው ያደላሉ:: መሪዎቹም ይህን የመንጋ ባህርይ ስለሚያውቁ ሃይላቸውን ያለከልካይ ይጠቀማሉ::

በአንጻሩም እንደ የሃይማኖት ተቋማት መንጋዎቻቸውን በአግባቡ መያዙን ቢያውቁበት ሞራላዊ ልዕልናን መጎናጸፍ በተቻለ ነበር:: ግን የሃይማኖትን ካባ የለበሱ አንጃዎች መበጥበጣቸው አይቀርም:: እሱንም በተደጋጋሚ እያየን ነው::

ስለ መንጋ ስነልቦና የበለጠ ለማወቅ የ Le Bon ን ' crowd Psychology' ያንብቡ::

አሻም!

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው- የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት
https://t.me/DrEstif
https://www.facebook.com/DrEstif
https://t.me/HakimEthio
ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ | ቀን 14/09/2016ዓ.ም

ክብሩ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ ሠራተኛ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

የስራ መደብ-አዋላጅ ነርስ
ብዛት-1
ጾታ- አይለይም
የስራ ልምድ -ለዲግሪ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ
-ለዲፕሎማ አራት ዓመትና ከዚያ በላይ

የስራ ቦታ- ክብሩ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሀዋሳ
ደመወዝ- በስምምነት

ተፈላጊ ችሎታ -የነብሰጡር ሴት ክብካቤ
-የማዋለድ ችሎታ ያለው
-ከወሊድ በኋላ ክብካቤ
- የጨቅላ ህፃናት ክብካቤ
- የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት
-የስነ ተዋልዶ ጤና
-መደበኛ የሆነ የኮምፒውተር ክህሎት

በተጠቀሱት ዘርፎች በቂ የሆነ እውቀትና የተግባር ልምምድ ያለው/ያላት ለምዝገባ የሚያስፍልጉ ዶክመንቶችን ማለትም ቴምፖራሪ ፣የታደሰ የስራ ፈቃድ እና የስራ ልምድ ከCV ጋር አያይዞ/አያይዛ በ @tizeabe 📞0977729696 የቴሌግራም አካውንት በመላክ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት የስራ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

@HakimEthio