Hakim
53.3K subscribers
24.4K photos
248 videos
505 files
4.59K links
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Download Telegram
የኮሌስትሮል መዛባት፤ መቼ ነው ሪፈር ማድረግ ያለብን?

በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም (የፋሚሊያል ሃይፐርኮሌስትሮሌሚያ, Familial Hypercholesterolemia, FH) በጣም ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት የሚያመጣና ለልብ ህመም የሚያጋልጥ የተለመደ በዘር የሚወረስ በሽታ ነው።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከ300 ሰዎች አንዱን እንደሚያጠቃ የተረጋገጠ ሲሆን በዘር ከሚወረሱ የሜታቦሊክ ህመሞች በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። በሃገራችን ኢትዮጵያም ይህ በሽታ እንዳለ ማረጋገጫዎች ቢኖሩም የህመሙን ስፋት ከ100 ሺህ በላይ ሰዎችን ሊይዝ እንደሚችል ከመገመት ውጭ በውል አይታዎቅም።

ነገር ግን ይህን ህመም አስቀድሞ ማወቅ ሕይወትን ከከፋ የልብ ህመም የሚታደግ ነው። የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ተጠቂዎች በጊዜ አስፈላጊውን ምርመራ እና ህክምና ያገኙ ዘንድ መቼ ነው ወደ ህመሙን መጠርጠር እና የኮሌስትሮል ስፔሻሊስት ሪፈር መደረግ ያለብን?

ከዚህ እንደሚከተለው በጣም ከፍ ያለ በተለይም ኮሌስትሮል አምጭ ግልጽ ምክንያቶች (secondary dyslipidemia) ከሌለ በዘር የሚተላለፍ የኮሌስትሮል ህመም ሊሆን ስለሚችል መለየትና በጊዜ ሪፈር ማድረግ ይመከራል።
1️⃣ Total cholesterol >300 mg/dl
2️⃣ LDL-C >200 mg/dl
3️⃣ በህክምና ሊስተካከል ያልቻለ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መብዛት
4️⃣ በቆዳና ጅማት ላይ የሚወጡ ቢጫማ እብጠቶች (xanthoma) ዋነኛ የህመሙ ምልክቶች ናቸው። እነዚህ እባጮች በቁርጭምጭሚት አካባቢ የተረከዝ ጅማት (ቋንጃ) ላይ፣ በጉልበት፣ በእጆች ወይም ክርን ላይ ሊወጡ ይችላሉ። በአይን ዙሪያም (xanthelasma) ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ እብጠቶች በቀላሉ የሚታዩ ቀለማቸው ቢጫማ ሲሆን ኮሌስትሮል በቆዳና ጅማት ውስጥ ሲከማች የሚመጡ ናቸው።
5️⃣ የአይን መስታውት ዙሪያ ላይ የሚወጣ ቀለበቶች (arcus cornealis) ሌላኛው የኮሌስትሮል ህመም መገለጫ ሊሆን ይችላል። ይህ ነጭ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ክብ መሰል ሲሆን ኮሌስትሮል በአይን መስታወት ዳርቻ ላይ ሲከማች የሚፈጠር ነው። በአብዛኛው በአረጋውያን ላይ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚታይ ሲሆን ከ45 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ ሲታይ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ነው።
6️⃣ከቤተሰብ አባላት ውስጥ በወጣትነታቸው ከ50 አመት እድሜ በፊት ድንገተኛ የልብ ድካም (heart attack) ወይም ስትሮክ (stroke) ያጋጠመው ካለም እንዲሁ የዚህ የኮሌስትሮል ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።

እንደዚህ በጣም ከፍ ያለ የኮሌስትሮል ምርመራ ውጤት ያላቸውን ሰዎች ቶሎ ወደ ስፔሻሊስት የኮሌስትሮል ሃኪም ሪፈር በማድረግ ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ወሳኝ ነው።

ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ግብረ መልስ ካሉዎት የዚህን መረጃ ያሰናዳዉን ዶ/ር መላኩ ታዬ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የስኳር ህክምና ክፍል ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ ተግባራዊ ምክሮችን በዶ/ር መላኩ ድህረ ገጽ www.melakutaye.com እና ማህበራዊ ሚዲያዎች @hakimmelaku ይከታተሉ!

telegram https://t.me/hakimmelaku

write me feedback at https://maps.app.goo.gl/twmS9fq7LiG1eRnq9

WhatsApp +251921720381

Dr. Melaku Taye (Endocrinologist, Lipidologist)

Get social with Hakim on Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207

@HakimEthio
Prevalence of group B Streptococcus colonisation in Afroasia.pdf
461.9 KB
Prevalence of group B Streptococcus colonisation in mother – newborn dyads in low-income and middle-income south Asian and African countries: a prospective, observational study

Gaurav Kwatra, Alane Izu, Clare Cutland, Godwin Akaba, Musa Mohammed Ali, Zabed Ahmed, Manisha Madhai Beck, Hellen Cherono Barsosio, James A Berkley, Tolossa E Chaka, Anélsio Cossa, Sowmitra Chakraborty, Nisha Dhar, Phurb Dorji, Maksuda Islam, Adama Mamby Keita,
StellaMwakio, Salim Mwarumba, NubwaMedugu, HelioMucavele, Viviana Mabombo, Stephen Obaro, Betuel Sigaúque, Samba O Sow, Samir K Saha, Sridhar Santhanam, Ragunath Sharma, Eric A F Simoes, Rani Diana Sahni, Milagritos D Tapia, Balaji Veeraraghavan, Shabir A Madhi

https://www.thelancet.com/journals/lanmic/article/PIIS2666-5247(24)00129-0/fulltext

To send your PDF use @HakimAds

@HakimEthio
As healthcare providers, we all want the best for our patients, especially when it comes to chronic conditions and elderly care. For many seniors, managing day-to-day health challenges requires more than just routine check-ups—it needs comprehensive, round-the-clock care that family members often can't provide at home.

That's where Grace Nursing Home Center steps in.

With years of experience, our facility is fully equipped with trained caregivers and medical professionals who specialize in managing chronic conditions and providing personalized care plans for elderly patients. At Grace Nursing Home, your patients receive:

24/7 medical supervision
Personalized treatment plans
Assistance with daily activities
Nutritious meals tailored to their health needs
A safe, comfortable environment for their well-being
Emotional support and social engagement

💡 By referring your chronic and elderly patients to us, you're not just treating their illness—you're ensuring their overall well-being. Together, we can give them the quality of life they deserve, while easing the burden on families who may be struggling with home care.

📞 Contact us today to discuss how we can collaborate for your patients' long-term health and comfort.

#GraceNursingHome #ChronicCare #ElderlySupport #DoctorsCare #ProfessionalCaregivers #SeniorCare #HealthcareCollaboration #WellBeingMatters #NursingHomeServices #PatientCare

@HakimEthio
የተዘጋ የአንጎል ደም-ስርን በመክፈት እስትሮክን ለማከም የሚውለው በመርፌ የሚሰጥ መድሐኒት :rTPA

በደም ስር በሚሰጥ መድሐኒት እስትሮክን በማከም ፈር ቀዳጁ የሀገራችን ሆስፒታል ጥቁር አንበሳ ህክምናውን በነፃ እየሰጠ ይገኛል ፤ በብዙ መቶ ሺ የሚሰጥ ህክምና መሆኑን አይዘንጉ ፤

ደም ስር ለአንጎል የኤልክትሪክ ገመድ ለቴሌቢዥን እንደ ማለት ነው ። የደም ስር ምግብና መጠጥ ከልብ ወደ ልዩ ልዩ ክፍለ አካሎች ወስዶ በምላሹ ከነሱ ዳግም ወደ ልብ የሚመላለስበት ማጓጓዣ መስመር ነው ። ክፍትና አስተማማኝ መሆን አለበት ። የኤሌክትሪክ ገመዱ የተቆረጠበት TV መስራት እንደማይችል ሁሉ የደም ስር ያላገኘ አንጎል ክፍልም አይሰራም ። አንጎል የደም ዝውውር መቋረጥን መቋቋም የማይችል የአካል ክፍል ነው ።

እስትሮክን በአመርቂ ሁንታ ማከም ካስቻሉ የህክምና ውጤቶች አንዱ በደም ስር የሚሰጥ ህክምና ነው ። መ'ዳኒቱን በደም ስር ሰጥቶ በአንጎል ውስጥ የተዘጉ ደም ስሮችን መክፈት የሚያስችል የህክምና አይነት ነው ። ከልብ ተነስቶ አለያም በአንጎል ደም ስር ውስጥ በተፈጠረ ደም መርጋት አማካኝነት የተዘጉ ደም ስሮችን መክፈት የሚችለው የጓጎሉና የረጉ ደም ውህዶችን በማሟሟት ነው ። መድሐኒቱ በረመጥ ላይ እንደተጣደ ሞራ እነዚያን የረጉ ደም ውህዶችን ያቀልጣል ፤ በዚህም የደም ስሮቹ ለደም ዝውውር ምቹና አስተማማኝ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ።

መድሐኒቱ ውድ በመሆኑ እና ስለ ገናናነቱ ወይም ፈዋሽነቱ ብዙም ባለመነገሩ (በቅርብ መታወቁ እና የህክምና ጉዟችን በማደግ ላይ በመሆኑም ጭምር ) በሀገራችን በደንብ የሚታወቅ አይደለም ። በሀገራችን ለመጀመሪያ ግዜ በመንግስት ሆስፒታል ይኸንን መድሐኒት ለእስትሮክ ታካሚዎች መስጠት የጀመረው ጥቁር -አንበሳ ሆስፒታል ነው ። ሆስፒታሉ ድንገተኛ የእስትሮክ መታከሚያ ማዕከል በማቋቋም ህክምናውን መስጠት ከጀመረ ሁለት አመታት ተቆጥረዋል ።

የማዕከሉ መከፈት የህክምናውን አመርቂ ውጤት በተግባር ማሳየት በመቻሉ ህክምናውን ማስፋፋት እንደሚገባ አሳይቷል ። እስትሮክ ሰፋ ያለ የማህበረሰብ ችግር ነው ።አስቸኳይ ህክምና መፈለጉ ህክምናው በግዜ የተገደበ መሆኑን ያሳያል ። አንጎል በግዜ የተገደበ ነው ። ያለ ምግብና መጠጥ የአንጎል ህዋሳት በሒወት ሊቆዩ የሚችሉት ለደቂቃዎችና ለጥቂት ሰዓታት ብቻ ነው ። <ግዜ አንጎል ነው > በሚል መፈክር ነው እስትሮክ የሚታከመው ።

አሁንም እስትሮክ የማይታከም ህመም ፤ የሰይጣን ምት ተደርጎ ይታሰባል ። እስትሮክን ማከምም መከላከልም እንደሚቻል ሳይንስ አረጋግጧል ። ከዚያ በላይ ታክመው የዳኑ የአይን እማኞች በብዙዎቻችን አጠገብ ይገኛሉ ። ያንን ያላደረኩ ከኛ መራቃቸውን እናስታውሳለን ። ችግሩ የግንዛቤ አለፍ ሲልም የአገልግሎት ውስንነት መኖሩ ነው ። ተገቢውን የነቃና የተቀላጠፈ የድንገተኛ ህክምና አሰጣጥ ስረዓት በሁሉም ሆስፒታሎች በመዘርጋት ፤እያንዳንዱን ማህበረሰብ ስለ ህመሙ አስከፊነት እና አስቸኳይነት ግንዛቤ በማስረፅ ተጎጂዎችን በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል እንዲመጡ በማድረግ እስትሮክን በመርፌ በሚሰጥ መድሐኒት ማከም እንደሚቻል እናሳውቅ ።

መድሐኒቱ የሚሰጥበት የግዜ ገደብ አጭር በመሆኑ ተጎጂዎች ቀድመው መድረስ አለባቸው ። እስትሮክ ያለ ምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚከሰት የእጅና እግር መስነፍ ፣ ፊት መጣመም አለያም የመገዳገድና እረፍት የለሽ ትውከት የሚያስከትል ድንገተኛ አካላዊ የአንጎል ችግር ነው ፤ችግሩ የደም ዝውውር መቋረጥ ነው ።

መድሐኒቱ ውድ በመሆኑ በቀላሉ የሚቀመስ አይደለም ። የጥቁር አንበሳ የነርቭ ህክምና ትት ክፍል ባደረገው ጥረት መድሐኒቱን ከለጋሾች በነፃ ለታካሚዎች እያደረሰ ይገኛል ። ምንም እንኳ ከለጋሽ የሚገኝ ልገሳ ቋሚ ይሆናል ባይባልም ለግዜው ግን ብዙዎችን መታደግ አስችሏል ።ቀጣይ ዘላቂ መፍትሔ በሆስፒታሎች በኩል ከሚመለከተው አካል ጋር ተመካክሮ እንዲቀርብ ግንዛቤውን ለመንግስትም ማስረዳት የባለሙያ ሐላፊነት ነው ።

እስከዚያው ሁሉም ሰው እስትሮክ ታማሚን በአፋጥኝ ህክምና ወዳለበት መሔድ እንደሚገባው ይኸን መልእክት ያሰራጭ፤ ያሳውቅ!

References
Jankovic J, Mazziotta JC, Pomeroy SL, Newman NJ, Bradley WG (Walter G. Bradley and Daroff’s neurology in clinical practice, eight's edition P 1393-94.

ዶር መስፍን በኃይሉ ፤ ጥቁር አንበሳ

@HakimEthio
fendo-15-1408090.pdf
563.6 KB
Investigating factors influencing overweight and obesity amongadult households in Ethiopia: a multilevel ordered analysis of 2016 EDHS data

Alemayehu Deressa , Dawit Firdisa*, Abdi Birhanu, Adera Debella, Mulugeta Gamachu, Addis Eyeberu, Deribe Bekele Dechasa, Usmael Jibro, Bikila Balis, Moti Tolera', Lemma Demissie Regassa and Ibsa Mussa

https://doi.org/10.3389/fendo.2024.1408090

To send your papers use @HakimAds

@HakimEthio
Prof. Engida Abebe, an Ethiopian consultant General Surgeon as well as Renal Transplant & Endocrine and Breast Surgery Surgeon, has become a Fellow of the American College of Surgeons (FACS)

The letters FACS (Fellow, American College of Surgeons) after a surgeon’s name mean that the surgeon’s education and training, professional qualifications, surgical competence, and ethical conduct have passed a rigorous evaluation, and have been found to be consistent with the high standards established and demanded by the College.

@HakimEthio
Message of condolences

It is with profound sadness that we learned of the tragic passing of Dr. Tibebu Alene who was a graduate of Debre Tabor University and was currently a second year General Surgery resident.

Dr. Tibebu was a dedicated and talented young physician, known for his discipline & commitment to his patients.

His untimely passing is a profound loss to his family, friends, colleagues, and the entire medical community.

Dr. Tibebu is survived by his 2 kids and pregnant wife to support them use the below account number

1000250306397
Lemlem Tesfa Tadesse (His wife)

Our heartfelt condolences go out to his families, friends and all who knew and loved him.

May his soul rest in eternal peace!

@HakimEthio
በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (Total Hip Replacement ) ተጀመረ!

ለሁለት ታካሚዎቸ የተሳካ  የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ማድረግ ተችሏል።

በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (Total Hip Replacement) በንዑስ ስፔሻሊስት (Sub specialist) የተጀመረ ሲሆን የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት እና የቀዶ ህክምና ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር አብዶ ዳመስ በግራ  ዳሌ የመበስበስ (osteonecrosis) ችግር ተጠቂ ለሆነ የ45 ዓመት እድሜ ያለው ታካሚ ሶስት ሰዓት  የፈጀ ስኬታማ ውስብስብ ቀዶ ህክምና ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

ከ6 ወር በፊት በግራ ዳሌ አንገት ስብራት ተጠቂ የሆነች የ50 ዓመት እድሜ ያላት ታካሚም እንዲሁ ሁለት ሰዓት የፈጀ ስኬታማ ቀዶ ህክምና እንደተደረገላት ዶ/ር አብዶ አክለዋል።

ታካሚዎቹ ከህክምና በኋላም በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት ዳይሬክተሩ በቀዶ ህክምናው ለተሳተፉ የህክምና ባለሙያዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

በሆስፒታሉ የአጥንት ህክምና ክፍል ላለፉት ዘጠኝ አመታት ከቀላል የአጥንት ህክምና  ጀምሮ፣ ከአደጋ ጋር የተያያዙ የአጥንት ስብራቶች፣ ውልቃቶች እንዲሁም ከፍተኛ እና ውስብስብ ልዩ ልዩ የአጥንት ቀዶ ህክምናዎች እየተሰጡ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህም ለተመሳሳይ ህክምና የሚደረግ ሪፈራልን በማስቀረት ህብረተሰቡን ከአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ከመታደግ አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የሚገልጹት ዶ/ር አብዶ የህክምና ክፍሉ እንደ ሲ-አርም እና አርትሮስኮፕ (C-ARM, Arthroscope) ያሉ አዳዲስ የህክምና መሳሪያዎችንና ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂ ማሽኖችን በማስገባት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም አስታውሰዋል።

ማህበረሰቡም ይህንን አውቆ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።

Youtube: http://www.youtube.com/@Hakim207?sub_confirmation=1

@HakimEthio
Dr. Wuletaw Chanie, an Ethiopian consultant General Surgeon as well as Hepatopancreatobiliary (HPB) Surgeon, has become a Fellow of the American College of Surgeons (FACS)

The letters FACS (Fellow, American College of Surgeons) after a surgeon’s name mean that the surgeon’s education and training, professional qualifications, surgical competence, and ethical conduct have passed a rigorous evaluation, and have been found to be consistent with the high standards established and demanded by the College.

@HakimEthio