Hakim
53.1K subscribers
24K photos
242 videos
490 files
4.48K links
Ethiopian blend of Medicine, History and Humor.
Download Telegram
የረቲና ካንሰር ምንድን ነዉ?

የረቲና ካንሰር (በእንግሊዝኛዉ አጠራር ‹‹ረቲኖብላስቶማ/Retinoblastoma›› በህጻናትና በልጆች ዓይን ላይ የሚከሰት የካንሰር ዓይነት ሲሆን ካንሰሩ የሚጀምረዉ ከረቲና (የዉስጠኛው ዓይን ክፍል) በመሆኑ የረቲና ካንሰር ተብሎ ይጠራል።

ይህ ካንሰር የሚከሰተዉ በ13ኛዉ የዘረ-መል ግንድ (‹‹ክሮሞዞም››) ላይ በሚገኝ ዘረመል ላይ በሚደርስ ጉዳት ነዉ። ዐሥር ከመቶ (10%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት በቤተሰብ የሚተላለፍ ሲሆን ዘጠና ከመቶ (90%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት በድንገት የሚከሰት ነዉ። ከሚታወቁ የካንሰር አጋላጭ ነገሮች ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ፣ ወዘተ ጋርም ምንም ዓይነት ግንኙነት የለዉም።

የረቲና ካንሰር ችግሩ እንደተከሰተ ብዙም ሳይዘገይ ቢቻል ደግሞ ወዲያዉኑ በምርመራ ታዉቆ ተገቢ ሕክምና ካልተደረገለት ዕይታን ካንሰሩ ወደ ሰዉነት ከተሰራጨ ደግሞ ሕይወትን ያጠፋል።

የረቲና ካንሰር በአንድ ወይንም በሁለት ዓይን ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በብዛት (ዘጠና ከመቶ) እስከ አራት ዓመት የእድሜ ክልል ዉስጥ በሆኑ ልጆች ላይ ይታያል። ሰባ ከመቶ ገደማ (70%) የሚሆነዉ የረቲና ካንሰር በአንድ ዓይን ላይ ብቻ የሚከሰት ሲሆን ሠላሳ ከመቶ (30%) የሚሆነዉ ደግሞ በሁለት ዓይን ላይ ይከሰታል። ዐሥር ከመቶ (10%) የሚሆኑት የረቲና ካንሰር ሕሙማን ደግሞ ከቤተሰቦቻቸዉ ውስጥ አስቀድሞ በዚሁ ካንሰር የተያዘ ሰዉ ይኖራል።

ይህ የረቲና ካንሰር በአደጉ ሀገሮች በሕክምና የመዳን ዕድሉ ከ95 በመቶ በላይ ሲሆን በታዳጊ ሀገሮች ግን የግንዛቤ እጥረት፣ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እና የሕክምና መድኃኒት አቅርቦት ችግር ስላለ ህጻናትና ልጆችን ለሞት በመዳረግ ላይ ነዉ። ይህ ችግር ሲከሰት በአብዛኛዉ የዓይን ብሌንን (‘Pupil’) በከፊል ወይንም በሙሉ የሚሸፍን ነጭ ነጸብራቅ የሚመስል ነገር (‘Leucocoria') ይታያል። በነጭ ነጸብራቅ በከፊል ወይንም በሙሉ የተሸፈነ የዓይን ብሌን የድመት ዓይን ስለሚመስል ወላጆች የልጄ ዓይን እንደ ድመት ዓይን ያበራል (የድመት ዓይን ይመስላል) በማለት ይገልጹታል (ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ የቀረበውን ምስል 16.2.1-2.2 ይመልከቱ) በተጨማሪም ይህ የረቲና ካንሰር ሌሎች ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል (ምስል 16 2.1-2.8 ይመልከቱ)። ዋና ዋና ምልክቶቹም፡-

• የዓይን መንሸዋረር፣
• የዓይን መቅላት፣
• የዓይን ማበጥና ወደ ዉጭ መጎልጎል፣
• የዓይን መጠን ማነስ፣
• የዓይነ መስታወት (‘Cornea’) መተለቅና መዳመን ናቸዉ።

ስለሆነም ወላጆች እነዚህን ምልክቶች ሲያዩ ወዲያዉኑ ሐኪም ሊያማክሩና ካንሰር እንዳልሆነ ሊያረጋግጡ ይገባል። የዚህ ካንሰር እዉቀቱና ልምዱ የሌላቸዉ የጤና ባለሙያዎች ለምልክቶች በቂ ትኩረት ላይሰጡ ስለሚችሉ በተቻለ ዐቅም እነዚህ ምልክቶች ያሉባቸዉን ህጻናትና ልጆች በዓይን ስፔሻሊስት ሐኪም እንዲታዩ ማድረግ ተገቢ ነዉ።

ለረቲና ካንሰር የሚደረጉ ሕክምናዎች ምንድን ናቸዉ?

የረቲና ካንሰር ሕክምና ዋና ዓላማ ሕይወትን ማዳን ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ካንሰር ያለበት ዓይን በቀዶ ሕክምና (በኦፕራስዮን) ተጠርጎ እንዳይወጣና ከተቻለም ጠቃሚ ዕይታ እንዲኖረዉ ማድረግ ነዉ። የሚደረጉ ሕክምናዎች እንደ ካንሰሩ ደረጃና እንደ ጤና ተቋሙ ልምድና አቅርቦት የሚለያይ ቢሆንም ዋና ዋና የሕክምና ዓይነቶች የሚባሉት፡-

1. የ’ሌዘር’ (‘LASER’) ሕክምና
2. በደም ሥር የሚሰጥ የካንሰር መድኃኒት እና
3. የጨረር ሕክምና ናቸዉ።

ካንሰሩ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰና ወደ ሰዉነት የመሰራጨት ዕድሉ ከፍተኛ ሆኖ ሲገኝ ካንሰር ያለበትን ዓይን በቀዶ ሕክምና ጠርጎ ማዉጣት የግድ ይላል። ስለሆነም ዓይኑ በቀዶ ሕክምና ተጠርጎ እንዲወጣ ከተወሰነ ወላጆች (አሳዳጊዎች) ሳይዘገዩ ሊስማሙ ይገባል። ቅድሚያ የሚሰጠዉ ሕይወትን ማዳን ነዉና!! ከዚህ ጋር ተያይዞ ወላጆች የዉሳኔው ክብደት ከሚፈጥረው ጫና አንፃር የሐኪም ምክርን ወደ ጎን በመተው የባሕል መድኃኒት እና ሌሎች ፍቱን ያልሆኑ ነገሮች በሞከር ረጅም ጊዜ ያጠፋሉ:: ካንሰሩ ገፍቶ እና ተሠራጭቶ አጠቃላይ ዓይኑ ቆስሎ እና መርቅዞ ለጊዜያው እፎይታም ቢሆን በቀዶ ሕክምና ዓይኑን ማስወጣት አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጥር ብቻ የመስማማት ሁኔታ ብዙ ጊዜ ይከሰታል:: የረቲና ካንሰርን በባሕላዊ ዘዴ መፈወስ እንደማይቻል አውቆ ተባባሪ መሆን የግድ ይላል::

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ ከአንድ በላይ የሕክምና አይነቶች ለአንድ ታካሚ ይሰጣሉ። ካንሰሩ እስኪጠፋም ተደጋጋሚ ሕክምና ማድረግን ይጠይቃል። ካንሰሩ ከዳነ በኋላም እንደገና ተመልሶ ሊከሰት ስለሚችል ከሕክምና በኋላ ለረጅም ዓመታት (ከአምስት እስከ ዐሥር ዓመት) ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

የረቲና ካንሰር በዘር ሊተላለፍ ይችላልን?

አርባ ከመቶ (40%) የሚሆነዉ የረቲና ካንሰር በዘር ሊተላለፍ ስለሚችል በቤተሰብ ዉሥጥ ችግሩ እንዳለ የሚታወቅ ከሆነ ህጻናትና ልጆች ተገቢ ምርመራና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል። በቤተሰብ ዉሥጥ ችግሩ ያለባቸዉ ሰዎች ልጅ ሲወልዱ የህጻናት ቅድመ ጥንቃቄ ምርመራዉን ከወለዱበት ሳምንት ጀምሮ ሊያደርጉ ይገባል።

በዘር የረቲና ካንሰር ችግር ያለባቸዉ ሰዎች እንዲሁም የረቲና ካንሰር ያለበት ልጅ ያላቸዉና የረቲና ካንሰር ሕክምና አድርገዉ የዳኑ ሰዎች ወደፊት ስሚወልዷቸዉ ህጻናት የካንሰር ተጋላጭነት በአግባቡ መረዳት እንዲችሉ የዘረ-መል ዉርስ የምክር አገልግሎት ሊያገኙ ይገባል። ለግንዛቤ እንዲረዳ ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰንጠረዥ 16.1 የተገለጸዉን የካንሰር መተላለፊያ መንገድና የመያዝ ዕድል መረጃ ይመልከቱ።

ጠቅለል ባለ መልኩ የህጻናትና ልጆች የዓይን ብሌን ነጭ ሆኖ ከታየ የችግሩ መንስኤ የረቲና ካንሰር ሊሆን ስለሚችል ወዲያዉኑ የዓይን ምርምራ ማድረግ የግድ ይላል።

በመጨረሻም ችግሩ ያለባቸዉን ህጻናትና ልጆች ቶሎ በማሳከም ተገቢ ያልሆነ የህጻናትና የልጆች ሞትን ለመቀነስ የድርሻችንን እድንወጣ አደራ ማለት እወዳለሁ።

ምንጭ መጽሐፍ:-“የዓይን ጤናና እንክብካቤ” በፕ/ር የሺጌታ ገላዉ ብርሃኑ (በደራሲው ፈቃድ መረጃው ተደራሽ ይሆን ዘንድ ከመጽሐፉ ገጽ 171-176 በከፊል ተወስዶ የተለጠፈ)

@HakimEthio
"ልጆች እየተጫወቱ የባዕድ ነገር ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?" - ዶ/ር አቤል ግደይ ፤ የህፃናት ሐኪም

ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦ ሲገባ ትንታን ያስከትላል። ይህ የአየር ወደ ሳንባ መግባትን በመከላከል እና ትንፋሽን በመቁረጥ የአተነፋፈስ ስርዓትን በማቆራረጥ ለአዳጋ ያጋልጣል።

ለየት የሚያደርገው የአየር መግባት በመከልከል በአጭር ጊዜ ለሞት ሊያደርስን ስለሚችል ነው። ለምሳሌ፦ አጥንት ፣ ክኒን ፣ ውሃ ፣ ኦቸሎኒ ፍሬ ፣ ስንዴ… ሌሎችን ጠጣር ነገሮች ወደ አየር ቱቦ ሊገቡ እና ትንታን ሊያስከትሉ የሚችሉ ናቸው።

የትንታ ምልክቶች

ልክ ባዕድ ነገሮች ወደ መተንፈሻ አካላት ሲገቡ የሚኖሩ ምልክቶች እነዚህ ናቸው
1. በሃይል ማሳል
2. መናገር አለመቻል
3. ጮክ ያለ ድምፅ
4. መጥቆር
5. ትንፋሽ ማጠር
6. ማላብ
7. ድንጋጤ
8. አንገት ማሳከክ
9. መፍጨርጨር
10. ቀልብን መሳት
11. ማንቀጥቀጥ

ግዜ ከወሰደ
•ተደጋጋሚ ሳል
•ሽታ ያለው ዓክታ
•ክብደት መቀነስ
•ትንፋሽ ማጠርና መድከም

የትንታ የመጀመርያ እርዳታ አሰጣጥ
1. ሁኔታውን መታዘብ
2. መጠየቅ
3. ሰዎች እንዲረዱን መጣራት
4. ጀርባ መምታትና ሆድን መጫን
አንድ ከእናንተ ጋር እየተመገበ የነበረ ሰው ድንገት ትን ቢለው በእነዚህ ከላይ በተዘረዘሩ መንገዶች ማገዝ ይቻላል።

ልጆች እየተጫወቱ ቆይተው ክኒን ውጠው ቢታነቁ ምን እናደርጋለን?

1. ሁኔታን መታዘብ
• ምን እንደዋጡ መታዘብ
• ይህም ህክምና ሂደን ለማስረዳት ይረዳናል
• እርዳታ ሰጪ የአደጋ ምስክር እንደሆነ አስቡ።

2. መጠየቅ
• ምን እንደዋጠ መጠየቅ
ለምሳሌ ፍሬ ፣ ምግብ ፣ ድንጋይ

3. ሰዎች ለእርዳታ መጣራት
• እሪ ብሎ መጮህ እና ሰዎችን እርዳታ መጠየቅ

4. ጀርባ መምታትና ሆድ መጫን
• ሁኔታውን በፍጥነት በመረዳት ወደ እርዳታ መግባት ያስፈልጋል።

ሀ. ጀርባ መምታት
ትልልቅ ሰዎች እንዲያጎነብሱ በማድረግ ከታች ከሚታየው ስዕል አድርገን 5 ግዜ ጀርባቸው መምታት ደጋግመን መተን ተስፈንጥሮ ከወጣ ጥሩ ካልሆነ ወደ ሆድ መጫን መቀጠል።

ለ. ሂልማች ማኑቨር / ሆድ መጫን
ጀርባ ደጋግመን 5 ግዜ ከመታን በኃላ ቀጥለን ሆድን መጫን ያስፈልጋል። ይህ መቆም በሚችሉ ሰዎች ጀርባ ከመምታት በኃላ የምንፈፅመው ይህ ባዕድ ነገር መውጣት አለመውጣቱን ማየትና ካልወጣ እንዲወጣ እየመላለስክ መሞከር ወሳኝ ነው።

ትንታ በማይቆሙ ህፃናት

ልክ ባዕድ ነገር ሲገባባቸው ቁልቁል ደፍተን ጀርባቸውን 5 ግዜ በመምታት ከዛም ደረታቸውን እየደጋገምን ሌላ ጉዳት በማያስከትል መልኩ መጫንና መጠፍጠፍ ይጠበቅብናል።

5. ህክምና መሄድ
አንድ ባዕድ ነገር ወደ አየር ቱቦው የገባበት ሰው ወደ ህክምና መሄድ አለበት። ሳንባ ቁስለት እንዳይፈጥርበት ሃኪም ሊያየው ይገባል።

የመጀመርያ እርዳታ የመጨረሻ አይደለም!

@HakimEthio
የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) እና የባሕል ሕክምናው መዘዙ

(ከታች የቀረቡት ሁለት ታሪኮች በእውነታኛ ገጠመኞች የተመሠረቱ ሲሆን 'አቶ አበበ' እና 'አቶ ከበደ' የሚሉት ስሞች እውነተኛ የታካሚዎች ስም አለመሆኑን እንገልጻለን)

አቶ አበበ የ60 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ የ5 ልጆች አባት ናቸው፡፡ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኪንታሮት (Hemorrhoid) በሽታ ታመው ከነገ ዛሬ ይሻለኛል ሲሉ ቢቆዩም ሕመሙ ግን እየተባባሰባቸው መምጣት ጀመረ፡፡ ሕመሙ ሲብስባቸው ጎረቤታቸውን በማማከር ወደ ባሕል መድኃኒት ቤት ያመራሉ፡፡

ባለመድሃኒቱም የሚቀባ የባሕል መድሃኒት ይሰጣቸውና እንደሚያድናቸው አረጋግጦላቸው ይሸኛቸዋል፡፡ አቶ አበበ የተሰጣቸውን መድኃኒት እንደተባሉት መቀባት ይጀምራሉ፡፡ በሦሥተኛው ቀን ኪንታሮቱ ይፈነዳና መግል ማውጣት ጀመረ፡፡ በአራተኛው ቀን አቶ አበበ ራሳቸውን ይስታሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ልጆቻቸው ተደናግጠው ወደ ሆስፒታል ያመጧቸዋል፡፡

ሆስፒታል ሲደርሱ የአቶ አበበ የልብ ምት በጣም ይፈጥናል፡፡ የደም ግፊታቸው በጣም ወርዷል፡፡ በድንገተኛ ክፍል ያሉ የጤና ባለሙያዎች በመረባረብ በመርፌ መድሐኒቶችን ፣ ግልኮስ፣ ፈሳሻ ንጥረ ነገርና የተለያዩ ምርመራዎችን ቢያደርጉላቸውም ቁስሉ ኢንፌክሽን ፈጥሮ በደም ውስጥ ስለተሰራጨ የደም ግፊታቸው ሊስተካከል አልቻለም፡፡ ከዚህም የተነሳ አቶ አበበ ጽኑ ሕሙማን ክፍል በአስቸኳይ እንዲገቡ ተደርጎ የተለያዩ የሕክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሕይወታቸውን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

ሌላኛው ታካሚ አቶ ከበደ ናቸው፡፡ እድሜያቸው 58 ሲሆን የባሕርዳር ኗሪ ናቸው፡፡ ከ5 ዓመት በፊት ጀምሮ የኪንታሮት ሕመም (Hemorrhoid) ጀምሯቸው በየጊዜው እየተባባሰቸው ይሄዳል፡፡

ከዚህም የተነሳ አንድ ታዋቂ የባሕል ሕክምና አዋቂ ጋር ይሄዳሉ፡፡ ባለመድኃኒቱም ከመረመራቸው በኋላ በመርፌ የሚወጋ መድኃኒት አዘዘላቸውና ያበጠው ኪንታሮት ላይ መድኃኒቱን በመርፌ ይሰጣቸዋል፡፡ ከዚያም እንደሚድን ነግሯቸው ይሰነባበታሉ፡፡

ወደ ቤት ከሄዱ በኋላ ኪንታሮቱ እብጠቱ እየጨመረ ይሄድና በሳምንቱ ይፈነዳል፡፡ ከዛም ተመልሰው ሲሄዱ ባለመድኃኒቱ እየቆየ እንደሚድንላቸው ነግሮ ይሸኛቸዋል፡፡ ይሁንና ቁስሉ ከመዳን ይልቅ እየሰፋ፣ መግል እያመንጨና እየተባባሰ ይሄዳል፡፡ የዚህን ጊዜ ቁስሉን በጨውና በውሃ እያጠቡ በቤት ይቆያሉ፡፡ ቁስሉ እየሰፋ በመሄዱ ከጥቂት ወራት በኋላ አቶ ከበደ ሰገራ መቆጣጠር ያቅታቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ዳይፐር መጠቀም ይጀምራሉ፡፡

ከዚህም በኋላ ወደ ሆስፒታል ሲሄዱ የሕመሙ ደረጃ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ አቶ ከበደ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተልከው በተደረገላቸው ምርመራ የፊንጢጣ መቆጣጠሪያ ጡንቻዎቹ ሙሉ በሙሉ በመጎዳታቸው በሆዳቸው በኩል የሰገራ መውጫ (Permanent colostomy) እንዲሠራላቸው ተወሰነ፡፡

ከነዚህና መሰል ብዙ ታሪኮች እንደምንረዳው ለኪንታሮት ተብለው ከትልልቅ ከተማ እስከ ገጠር የሚሰራጩ የባሕል መድኃኒቶች በኅብረተሰቡ ላይ ምን ያህል ጉዳት እያስከተሉ እንደሆነ ነው፡፡

የባሕል ሕክምና በአግባቡ ትኩረት ተሰጥቶት ከዘመናዊ ሕክምና ጋር ቢዛመድ ለማኅበረሰባችን አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል ቢታመንም የዕለት ተዕለት ገጠመኞቻች ይህ ዓይነቱ የኪንታሮት የባሕል ሕክምና ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለመናገር ያስደፍረናል፡፡

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids) ምንድነው?

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)፦በፊንጢጣ ላይ የሚገኙ ደም መላሽ የደም ስሮች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ሲሆን በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም ከ45 - 65 ዓመት ባሉት ሰዎች ላይ በብዛት ይከሰታል

የኪንታሮት በሽታ በዋናነት በሁለት (types) ይከፈላል
፩. ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids)፦ በውጨኛው የፊንጢጣ ክፍል ላይ የከሰት ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመምም (Pain) ያስከትላል፡፡

፪. ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids)፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ሕመም አይኖረውም
ይህ የኪንታሮት ዓይነት 4 ደረጃዎች (grades) አሉት።

አንደኛ ደረጃ (Grade-1) ይህ ደረጃ በፊንጢጣ ግድግዳ ላይ እብጠት ሲኖር ነው፡፡ እብጠቱ በዋናነት በስተ ግራ፣ በፊት ለፊትና በስተኋለኛው የፊንጢጣ ግድግዳ ላይ ይከሰታል፡፡

ሁለተኛ ደረጃ (Grade-2) በዚህ ጊዜ የእብጠቱ መጠን ጨምሮ ለሽንት ሲቀመጡ በሚኖር ማማጥ እባጩ ወደውጪ ሲወጣና በራሱ ጊዜ ወደውስጥ ሲመለስ ነው፡፡

ሦሥተኛ ደረጃ (Grade-3) - በዚህ ጊዜ እባጩ ለሽንት ሲቀመጡ ወደውጪ ይወጣና በራሱ ስለማይመለስ የግድ በእጅ መመለስ ሲፈልግ ነው፡፡

አራተኛ ደረጃ (Grade-4) በዚህ ጊዜ እባጩ ላይመለስ በፊንጢጣ ይወጣና ይቀራል፡፡

አጋላጭ ሁኔታዎች (risk factors)

የሆድ ድርቀት -አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸው ምግቦችን ማዘውተር (ፓስታ፣ ማኮሮኒ፣ ነጭ ዳቦ...) እና በቂ ውሃ አለመጠጣት
እርግዝና
የትልቁ አንጀት ካንሰር
ሽንት ቤት ተቀምጦ ለረጅም ጊዜ ማማጥ
ረጅም ጊዜ የቆዬ ተቅማጥ (chronic diarrhea)
ዕድሜ መጨመር

ምልክቶች (clinical features)

ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደማቅ ቀይ ደም
በፊንጢጣ አካባቢ ማሳከክ
ከፊንጢጣ የወጣ ሥጋ መሳይ እባጭ
በፊንጢጣ አካባቢ የህመም ስሜት መኖር

የኪንታሮት መዘዞቹ (complications)
ኪንታሮቱ ውስጥ የደም መርጋት (thrombosis)ና ከፍተኛ ሕመም
ወጥቶ አለመመለስ (irreducible)ና መበስበስ (Necrosis)
መመርቀዝ (infection)ና መግል መቋጠር
ያልተለመደ የሰውነት ክፍተት (fistula)
የሰውነት መሰንጠቅ (fissure)
ሰገራን አለመቆጣጠር (Incontinence)
የተለመደ ባይሆንም የደም ማነስ ሊያስከትል ይችላል፡፡

ኪንታሮት እንዴት ይታከማል?

በመጀመሪያ ሕመሙ ያለበት ሰው እንደማንኛውም ሕመም ወደ ሐኪም ቤት ሄዶ ለመታከም ፍርሃትን/ሐፍረትን ማሰወገድ ይጠበቅበታል፡፡

፩. በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን (አትክልትና ፍራፍሬ..) መመገብ
፪. ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድ
፫. ለብ ባለ ውሃ ጨው ጨምሮ 20- 30 ደቂቃ በቀን ሁለቴ ወይም ሦሥቴ መዘፍዘፍ (በበረዶም ሊሆን ይችላል)
፬. ሁሌም ከተፀዳዱ በኃላ በንጹሕ ውሃ መታጠብ
፭. ሻካራ የመፀዳጃ ወረቀቶችን አለመጠቀም
፮. የሰገራ ማለስለሻ መድኃኒት
፯. የሚቀቡ የሕመም ማስታገሻ መድኃኒት መጠቀም

አብዛኛውን ጊዜ ከላይ በተጠቀሰው መንገድ ብቻ ሕመሙ ሊሻሻልና ሊጠፋ ይችላል፡፡በእነዚህ ሕክምናዎች ካልተስተካከለ
ቀለል ያለ ቀዶ ሕክምና ሊያስፈልግ ይችላል፡፡

መከላከያ መንገዶች

በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ፣ ፈሳሽ በበቂ ሁኔታ መውሰድና የሆድ ድርቀትን ማስወገድ
ሰገራ በሚመጣ ጊዜ ጊዜውን ሳያሳልፉ ወደ ሽንት ቤት መሄድ
መፀዳጃ ቤት ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ
ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶችን ሲያዩ ወደ ሕክምና ተቋም መሔድና ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ዶ/ር ዮሐንስ ክፍሌ ፤ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና ሬዚደንት

@HakimEthio
THE FIRST WOMAN CARDIAC SURGEON: Dr Nina Starr Braunwald

On March 11, 1960, thirty-two-year-old New York doctor Nina Starr Braunwald (1928-1992), a pupil of the cardiologist Charles Hufnagel (1916-1989), was assisted by another famous heart surgeon, Dr. Starr BraunWald from New York.

Andrew Morrow performed the world’s first successful mitral valve replacement on a forty-four-year-old patient with severe mitral failure at the National Institutes of Health (NIH) Surgical Clinic in Bethesda, Maryland. The patient died four months after the surgery, probably due to a fatal arrhythmia.

Dr. Starr Braunwald performed the surgery after testing the valve on 24 dogs. The implanted valve prosthesis, called “Braunwald-Morrow”, was fitted by the doctor herself and was made of polyurethane flaps that served as the valve blades and Teflon tapes that served as tendon cords.

She later developed the “Braunwald-Cutter” valve, a mechanical valve covered in synthetic fabric, which was successfully planted in thousands of patients throughout the 1960s and 1970s.

Working with Kenneth Moser at UCSD, Nina Starr Braunwald played a fundamental role in the development of thromboendoarterectomy, a surgical treatment for chronic thromboembolic pulmonary hypertension (CTEPH)

@HakimEthio
Clinical_characteristics,_treatment_patterns,_and_outcomes_of_hospitalized.pdf
1.5 MB
Clinical characteristics, treatment patterns, and outcomes of hospitalized patients with acute heart failure in central Ethiopia: a retrospective observational study

Gashaw Solela & Yimer Seid

https://bmccardiovascdisord.biomedcentral.com/articles/10.1186/s12872-024-03905-z