የስንኝ ቋጠሮ
1.64K subscribers
17 photos
1 video
1 file
7 links
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Download Telegram
ከ አራት ስንኝ ያልበለጠ ግጥም በማንኛውም ርዕስ ፅፋችሁ ላኩልኝ @gitmv ግጥም ለመላክ @mogea ሌሎቹ ህግጋት እንደተጠበቁ ናቸው እስከ ሶስት ሰአት ድረስ ላኩ
ደቂቃዎች ቀርተውታል ልክ ሶስት ሰአት እንደሞላው ውድድሩን እንጀምራለን!! ጓደኞቻችሁን ወደቻናሉ ጋብዟቸው!! ስልሳ ላይክ ቀድሞ የሞላ የካርድ ሽልማት አለው!! @gitmv
ቀንን የጠበቀ
ጊዜውን ያወቀ
ድንገት ሲፈነዳ
ቆስቋሹን እንዳለ ይዞት ገደል ገባ
ቢያብሱት አይደርቅም ብሶት ያዘለ እንባ።
ዮኒ @gitmv
ኣታን @yonatoz
#ሺህ _አመት_ይንገሱ
ትንሽ አይከብድም ወይ
መቶ አመት ኖሮ ሺህ አመት መንገስ፣
ታምቡር የሚበጥሱ ጩኸቶችን
መሰረታዊ ጥያቄዎችን አጎንብሶ አለመመለስ፣
ለእናት እንባ ለህፃን ምኞት
ቶሎ አለመድረስ። @gitmv
🖊መኮንን ዮሴፍ(ባቢ)🖊
የፈጠርከው ፍጡር ~ከሰይጣን ሰይጥኖ
ልጆችህን ሲገለን ~ህግጋትክን ተቃርኖ
ስለምን ዝምአልከው~ ስንቴስ እንቀጣ
ውረድና ፍረድ !!
አልያ ህግክን ሻርልን ~እራሳችን እንድንቀጣ!!
@gitmv

#bluefish
ስሚኝ
እወድሽ ነበረ ፍቅሬ ባይገባሽም፣
የኔ መዉደድ ላንቺ እውነት ባይመሰልሽም
አይንሽ እንባ ሲያዝል ሆድሽ ባር ባር ሲለው፣
እኔም ከፍቶኝ ነበር እውነቱ ይሄ ነው።
@gitmv
ምህረት
26/10/2014
*የፎረሸ ስሜት*
ወይ ቀረሁ ብለሽኝ መሄጃ አላበጀሁ
ወይ መጥተሽ አግኜሽ ናፍቆቴን አልሸኘሁ
እንዲሁ
ትመጭ ይሆን እያልኩ በር በር እንዳየሁ
በምኞት ጥላ ስር በቀቢፀ ተስፋ ስንት ዘመን ቆየሁ።
Ab
ያኔ
ያኔ ያልታሰበው ሲፈጠር በሂወቴ፣
ከባዱ ፈተና ሲጫን በጫንቃዬ፣
የማያልፍ ይመስል ተዛብቶ መንገዴ፣
ክፋትን ያስመኘኝ ደካማው ጉድለቴ፣
ምናለ አይቶት ቢሆን የዛሬ እኔነቴን።
@gitmv
አዲስአለም
#ሴትሆይ
ስከተልሽ ኖርኩኝ ካስጠጋሽኝ ብዬ
የልቤን ስነግርሽ ሳልደብቅ ሚስጥሬ

ክብርሽን ጠብቂ አክብሬ ባነግስሽ
ጉራ አናትሽ ላይ እናም አልገባአለኝ ሀሳብሽ

ሴትሆይ ስሚኝ አንዴ ከቀልብሽ ሁኚና
ጅል ሆኜ እንዳይመስልሽ ስልልሽ ጎምበስ ቀና
ለፍቅር ብዬ ነው እድሌ እስኪቃና
@gitmv
@samueltsegaye
መለየት ነው ቆርጦ
መሄድ ነው እርቆ
ምንድን ነው የሙጥኝ
ከሰው ሰው ተጣብቆ
@gutmv
ባንተጊዜ
ሀገሬ እንዲህ ናት...
ሀገሬ እርጉዝ ናት ሀገሬ ነፍሰጡር፡
ሀገሬ ድርስ ናት የመውለጃ ቀኗን ስትጠብቅ የምትኖር፡
ሀገሬ በካር ናት፡
ምጥ ላይ ያለች እንስት፡
በወለደች ጊዜ የወለደችውን ወንድ ልጇን ጥላ፡
የእንግዴ ልጇን 'ምታሳድግ አዝላ።
@gitmv
እኔ እወድሻለሁ
ክረምቱም ተተካ በጋውም አለፈ
ከቤትሽ አመጣኝ ፍቅር እያከነፈ
እትቱ በርዶኛል ጋቢ ደርቢልኝ
ከሌለ ግድ የለም በእቅፍሽ አሙቂኝ
እኔም መጥቻለሁ አብረን እንድንሆን
ክረምቱ ሲወጣ እንለያያለን @gitmv
ከመሰለን!
ለሆድ ኑሮ ማለፍ ፣ ለመብላት መባላት
ከሆነ ትግላችን ፤
መሴይጠን ከነበር ፣ ከሰው ተራ መውጣት
አውሬነታችን፤
ምነው ባናወራ ስለ ገነት አንባ፤
ምነው ባናወርድ ከቶ ያሀዘን እንባ።
@Gitmv
26/10/2014 ከሻንበል ዋቅጋሪ ጅማ
የሀገሬ እንግልት ልፋቷና አሳሯ
ምነው እንደ አንዲት ሴት
ዘጠኝ ብቻ ቢሆን የእርግዝና ወሯ
ደሟ ሳይፈስባት ምጧ ሳይበረታ
ከጥበበኛ ሰው
አዋልዳት ነበር በፍቅር በደስታ።
@gitmv
በአክሊሉ
ሆነ ሰበር ዜና
ፈጣሪ ፈልጎት : ዛፉማ ሲፈጠር
ሰው ሊጠቀምበት : ለግልጋሎት ነበር
የሰውን ሞት ረሳን : ዛሬ ያ ቀረና
ዛፍን መትከልና መቁረጥ : ሆነ ሰበር ዜና
@gitimv
አመሏን አውቃለሁ ሰው አልምዳ አታውቅም
ተረተረት እጂ ሀሳብ ህልም የላትም
ስለወደፊቷ ትንሽ ብትረዳ፣
ተስፋ ቢኖራትም
አላሚዋን ጥላ ህልመኛዋን ጥላ ፣
የትም አትሄድም @gitmv
@hashuya
ልብህ ነው
እግርማ ታዛዢ ነዉ..ከላከዉ ሚደርስዉ
እግርህን ላሰርዉ.....ልብህን ጠይቀዉ
እንዳደርስ ላርገህ...... ተራራውን መስሎ
ሳትይዝ ያሳጣህ........ በፍራት ጠቅልሎ
le comment @Amen122119 @gitmv
*የማይድን...*
ምን ብንታገል ከሆድ የማናወጣው
በጊዜ ሂደት እንርሳው ብንል የማንረሳው
ስንት ህመም አለን
ሰርክ የሚያደማን
'እህህ' ብለን የማይወጣልን
በሚመሽ እድሜ የማይመሽልን
እልፍ ህመም አለን
ከቀን እስከሌት ከዘመን ዘመን
ከጉያችን ስር 'ሚበረታብን።
Ab
07/11/2014
የጥቅምት መስክ ነኝ !!
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን: ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት : እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ : መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት: አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ : ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ: አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል: ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ : አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው: ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም: እኔው ነኝ የማውቀው::
(ተከፍተው የተከፉ ለማይመስሉ)
ሆያ ሆዬ

ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ሆያ ሆዬ ስንል ያኔ በልጅነት፡፡
የሙልሙሉ ዳቦ የኩበቱ ሽታ፣
መቼም አይረሳም የቡሄ ትዝታ፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ ስንደዶ፣
የዚ ቤት ጌታ ጥርሰ በረዶ፣
"እንለው ነበረ"
ጥርሱ ግን ወላልቆ ቢሆንም ባዶ፡፡
ድቅን አለ ፊቴ ሳስበው በድንገት፣
ጆሮዬን ተሠማው የጅራፉ ጩኸት፣
ተሠማኝ ሙቀቱ የችቦውም እሳት፡፡
ሆያ ሆዬ ሆ ሆያ ሆዬ፣
ሙልሙሊቷን ስጡኝ እባኮ ጌታዬ፡
እዛ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
እዚ ማዶ ሆ አንድ እረኛ፣
የዚ ቤት ጌታ የኢትዮጵያ አርበኛ፣
" እንለው ነበረ"
ለራሱም ቢያስፈልግ ጠባቂ ዘበኛ፡፡
ዳቦውም ይበላል ችቦው ይለኮሳል፣
ሆያ ሆዬ ተብሎ ቡሄ ይከበራል፡፡
እጅጉን ደነቀኝ ገረመኝ ሳስበው፣
ሆያ ሆዬ ማለት ራሡ ጥበብ ነው፡፡

©Afe.Z.eth @gitmv