የስንኝ ቋጠሮ
1.64K subscribers
17 photos
1 video
1 file
7 links
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Download Telegram
*አትምጪ*
አለመምጣትሽን ልቤ ይከጅለዋል
ጠብቄሽ መቅረትሽን ውስጤ ይሽተዋል
የመጣሽ እንደሆን 'መሄድሽ ነው' እያልኩ ሰዓቱን እያየሁ
ከመቅረትሽ ይባስ በሃሳብ እዋኛለሁ
ናፍቆት ያጎበጠው፤ድካም የተጫነው ልብ እና አካሌን
መምጣትሽ አይደለም እቅፍሽም እንዲሁ መዳኛ 'ሚሆነው
በዛው መቅረትሽ ነው ከደዌ 'ሚያርቀው።
Ab
17/11/2014
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች የግጥም ውድድር ሀሙስ ምሽት ለማሰናዳት አስበናል።ስለዚህም ለዛ የሚሆን ግጥም ብትልኩልን እንደምንቀበል ለማሳወቅ እንወዳለን።
1.የግጥሙ ሀሳብ በክረምት ውስጥ ስለሚያልፍ ጊዜ የሚያትቱ ስንኞች ይሆኑ ዘንድ እንሻለን።
👉እስኪ ክረምትን በስንኞቻችሁ ግለፁልን።
ምናልባት "ክረምት እና ናፍቆት"፣"ክረምት እና ልጅነት"፣"ክረምት እና ትዝታ"፣"ክረምት እና ፍቅር" እና መሰል የግጥም ሀሳቦችን የያዙ ስንኞችን @mogea እና @Abebekasu ላይ ላኩልን።
ምሽት ላይ ለሚኖረን የግጥም ውድድር ግጥሞቻችሁን @mogea@Abebekasu ላኩልን።
ክረምቱ ስንኞቻችሁን ይሻል።በክረምት ያላችሁን የትዝታ፣የናፍቆት፣የፍቅር፣የልጅነት ስሜቶቻችሁን አጋሩን።
ሌሎች ወዳጆቻችሁንም ወደ ቻናሉ ጋብዙ።
@gitmv
የቀድሞው ህጋችን እንደተጠበቀ ነው።ቅድሚያ 60 ላይክ ለሚደርስ ተወዳዳሪ የ 25 ብር ካርድ፣ሁለተኛ 15 ብር እንዲሁም ለሶስተኛ 10 ብር ካርድ የምንሸልም ይሆናል።
ውድድሩን ምሽት 3:00 እንጀምራለን።እስከ 2 ሰዓት ድረስ ግጥሞቻችሁን ላኩልን።
@gitmv
ውድድራችንን ለመጀመር የተወሰኑ ደቂቃዎች ይቀሩናል።አሁንም ወዳጆቻችሁን ወደ ቻነሉ መቀላቀል አትርሱ።
@gitmv
አደራ ለቡሄ

ክረምቱ ዝናቡን ያለልክ ሲያፈሰው
በቤቱ ሲታደም ጉብል አዋቂው ሰው
ናና በፉጨትህ ጥራኝ እወጣለሁ
አረማ ጉልጉሎ ወይ እንጨት ለቀማ
በወጣሁኝ ቁጥር ባንተ ከምታማ
አንተ ብቅብለህ ድምፅን አሰማ
አባባ ሳይሰማ እማማም ሳታየኝ
አንዴ ብቅ ብለህ አይንህን አሳየኝ
ይህ ሁሉ ካልሆነ አንዱም ካልተሳካ
ፎቶህን ስደደው አቅፌው ልተኛ
ይሄም ካልሆነልህ ከጠፋህ መፍትሔ
ያው ነሀሴም አይደል እንዳትቀር ለቡሄ
የምትወደውን ሙልሙሉ ስለምሰራ
እንዳትቀርብኝ አንተ ልጅ አደራ
ሆያ ሆየ እያልክ የመጣህልኝ እለት
አይኖቼ ይበራሉ አገኛለሁ ጉልበት
ሽንሽኔን ለብሼ ደር እና አምባሬን አጌጥበታለሁ
ሆያያ ሆየ እያልክ ና እጠብቅሃለሁ
ቡሄ ምክንያቴ ነው እኔ አንተን ለማየት
ሳላይህ እንዳይልፍ እንዳይልቅ ክረምት

እመጣለሁ

ወንዙን ተራራው ባህሩን አልፌ
ለፍቅራችን ስል ውዴ ተንሰፍስፌ
እኔም ናፍቀሽኛል አይንሽን አያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ
አባታሽ ሳያዩኝ ወንድምሽ ሳይገለኝ
ላንቺ የምነግርሽ አንድ መልክት አለኝ
ግን አሁን አይሆንም ያኔ እነግሻለሁ
የኔ አለም ጠብቂኝ ሆ ብየ እመጣለሁ
የጌቶች ጌታየን ፍቃድ ጠይቂያለሁ
ገና ሳትነግሪኝ መንገድ ጀምሪያለሁ
ሆያሆየ ብየ እመጣልሻለሁ



.... @nitsuti1419
ቀጠሮ በክረምት
ጠዋት ተነስቼ ጀመርኩኝ ዝግጅት
አንድ ቀጠሮ አለኝ መቅረት ማልችልበት
የቀጠሮ ሰዓት ደርሶ እስካገኘው
ጠረኑን አሽትቼ ቀርቤ እስካቅፈው
የልጅነት ፍቅሬን አይኑን እስከማየው
እንዴት እንደ ጓጓው ትርታዬ ያወራል
እጅ እግሬ ታስሮ ውስጤ ግን ቸኩሏል
ንፁ አየር ፍለጋ መስኮቴን ከፍቼ
ሰማዩን አየሁት ሽቅብ በአይኖቼ
መብረቁ ያስፈራል ሰማዩም ጠቋቁሯል
ልክ እንደኔ ስሜት አንዳች ነገር አዝሏል
ሰዓቴን አይቼ ዘጋሁት መስኮቴን
ከቤቴ ልወጣ ጀመርኩ እርምጃዬን
ያጥቁሩ ሰማይ ደመናን ያዘለው
በእኔው ሰዓት ላይ ዝናቡን ለቀቀው
ያሁሉ ህልምና የሁሉ ዝግጅት
የልጅነት ፍቅሬን የማየቱ ጉጉት
በጓርፉ አለፈ አይ ቀጠሮ በክረምት
Noa
አንቺ ጋር ስመጣ
""""""""""""""""""""""""""""""

ዣንጥላም አልሻም.....
ዝናቡን አልፈራ፣ ከቶም አይበግረኝ
ፍቅርሽ አይደለም ወይ...
ከዝናቡ በላይ፣ የሚያረሰርሰኝ።

/ ልጅ_ወርቅነህ..✍️✍️ /


ጆይን/join/
👇👇👇👇
@lij_werkneh_gitm
@lij_werkneh_gitm
የብሄ ብርሃን ለኛም በራልን×፪
እያልክ ብሄ በሉ የደብረ ታቦርን ተአምር ስታውጅ
በድምፅክ ብለ'ይ መሆንክን የኔ ወዳጅ
ስትል ብሰማ ክፈት በለው በሩን
እንኳን አደረሳቹ ልትል እንኳን አደረሰክ ብዬ ከፈትኩልህ ልቤን
ለኔም መጥተሃልና ሆነህልኝ ብርሃን
ጅራፋን ስታጮህ ፡ እዚ ቤቶች እያልክ ሰፈር ስታካልል
ፍቅርህን ልታደርስ እኔም ቤት ደርሰሃል

እዚ ማዶ አንድ አብሽ እዛም ማዶ አንድ አብሽ
የዚህ ቤት ጌታ ወርቅ ለባሽ .......................... እያልክ
የቤቶቼን ጌታ አንተ ስታሞግስ  ..........እኔን እያማለልክ
በስርቆሽ ጨዋታ በአይን ተግባቦት
በብሄ ሙልሙል በሆያ ሆዬ ዜማ
የፍቅርህን ድርሳን ከልቤ ብታደርስ ልቤን ልታሸፍት
አባዬ እማዬ እህት ወንድሞቼ
መላው ሳይገባቸው ፍቅርን ተቋደስን
ሆያ ሆዬ ብለውን

ሆይሼ ሆይሼ
ልምጣ ወይ ተመልሼ
በአመት አንድ ቀን ብቅ ብትልልን
ተመኘሁ ሁልጊዜ ብሄ አንዲሆን
ተመላልሰክ አንድትመጣ ሆያ ሆዬ እያልክ
ከልቤ ሙዳይ ከቤቴ ደጃፍ እንዳይክ

እንድትመርቅ
አመት አውደአመትን
የብሄ ብርሃንን
የኔና ያንተን  ፍቅርን
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ተጻፈ በ
            ፡ Metadel_Amel

መልካም ብሄ ;)
በክረምት............

በክረምት በብርዱ፥ በናፍቆት ረመጥ፤
በሞኝ አበስብስ ውስጥ፥ ሞኝ ልቤ ሲሰምጥ፤
ከንፋስ ሽውታ፥ከመብረቅ ብልጭታ፤
በሀሣብ ትመጫለሽ፥ እንደ ድንገት ለአፍታ።
በአል እስኪመጣ፥ ዘመን ተቀይሮ፤
በአጥር እስክንዘል፥በጀርባ በጓሮ፤
ደግሞ እስክንጠራ፥ ት/ቤት ቢሮ ፤
እንዴት አድርጎሻል፥በክረምቱ ኑሮ፤
ትዝ አላለሽም ወይ፥የመምህሩ እሮሮ፤
እኔ.............….........
ባይኖረኝም ፍቅር፥ለትምህርቱ ከቶ፤
ቀኑን እጠብቃለሁ፥እስኪነጋ መሽቶ፤
በጋው እስኪመጣ፥ክረምቱን ረቶ፤
እንችን እስኪያሳየኝ፥አምላኬ ራርቶ።

ተፃፈ በ አቅሌስያ ፋንታሁን (@eyulka@akli03)
ክረምት እና ናፍቆት

በክረምት መግቢያ እፈልግሻለሁ
ምን ባስከፋሽ እንኳን ይቅርታን እሻለሁ
እዚህ ያለሁበት ክረምቱ ይረዝማል
ቆፈኑ ብርቱ ነው አንድ ሆኖ ይከብዳል
እዚህ ያለሁበት ውርጩ አያላውስም
ለብቻ ተሁኖ እርምጃ አይሰምርም
እዚህ ያለሁበት ዝናቡ ያይላል
ከንጋት እስከ-ሌት እዬዬን ያቀልጣል
እዚህ ያለሁበት አንቺን መሳይ የታል
እቅፍን አሙቆ ሀሴት መች ያድላል
እዚህ ያለሁበት አንቺስ የታል ያለሽ
በበጋ እኝደራቅሺኝ እንደሸሺኝ ነሽ
እዚህ ያለሁበት ትዝታሽ ብቻ ነው ውል ሲል ሚታየኝ
ከክረምት አብሮ ቆፈናም ያረገኝ
እዚህ ያለሁበት መች እንደሆን እንጃ መጥተሽ ያገኘሁሽ
ትውስታዬን ሁሉ ከክረምቱ ጋራ አጥቦት የረሳሁሽ

በክረምት...

በክረምት ፍቅራችን ጠሃይን ይሆናል
ሙቀት ተጓናፅፎ ከብርሃን ይፈካል
በክረምት ፍቅራችን ከቁር ይዛመዳል
በጠፈጠፍ መሃል ውብ ሙቀት ይወልዳል
በክረምት ፍቅራችን እርጥበት ያረግፋል
ግግር በረዶንም አቅልጦ ያከስማል
በክረምት ለዛሽ እጅግ ይጥመኛል
ከበጋ ከማውቀው እጅግ ያድግብኛል
በክረምት
ተፈጥሮሽ ውበቱ ተአምር ሲያሰኝ
ከቁሩ ገላግሎ ለፀደይ ሲያቆየኝ
ሳልጠግበው ያልፈኛል
አዲስ አመት ከቶ መምጫው እስኪደርስ እንደሁለመናሽ ሀምሌ ይናፍቀኛል።

እናም...

በክረምት አትቀሪ በውርጩ መባቻ
ከብርዱ መግቢያ ላይ ግንቦት መከተቻ
ሀምሌ ላይ አልጣሽ ክረምት ከመበርቻው
ልክ እንደ በፊቱ ልክ እንደ ካችአምናው።
Ab
የትኛውን ግጥም ይበልጥ ወደዳችሁት?ላይክ በማድረግ እንዲሁም ሌሎች ወዳጆቻችሁን ወደ ቻነሉ በመቀላቀል ተሳተፉ።በቅድሚያ 60 ላይክ ለሚደርስ ተወዳዳሪ ሽልማታችን እንደተጠበቀ ነው።
@gitmv
የንጉስ ዝምታ
ከ እልፍ ማስፈራራት ከ ሺ ድምፆች መሃል
በገዢዎች ቁጣ  ከአንበሶች መጣል
ያሰጋ ይሆናል ያርድም ይሆናል
ሃያላን  ሲያብሩ
ተማክረው ሲያሴሩ
ቁጣቸው ድምፃቸው ልብን ያሸብራል
ግና ከድምፀቱ  ከ ቁጣውም በላይ
ከ አንበሶች ግሳት ዝምታው ግን ሲታይ
ነፍስን ያስጨንቃል ከተማን ያውካል
ሃገርን ያምሳል ትጥቅ እንኳን ያስፈታል
የነገስታት ንጉስ ዝም ሲል ያስፈራል
@gitmv @mogea
ውድ አባሎቻችን ረጅም ጊዜ እንደጠፋን እናውቃለን ይቅርታ ይደረግልን እንጠይቃለን። ስለዚህ ታላቁን የግጥም ውድድር ልንጀምር ስላሰብን "ነገ" ምሽት የግጥም ውድድር ይኑር የምትሉ…
ሰላም ውድ የ ስንኝ ቋጠሮ አባሎች እንዴት ቆያችሁ? ዛሬ ማታ ድንቅ የግጥም ውድድር ይኖረናል
ስለሆነም ከታች ያሉ መስፈርቶችን በመከተል እንድትወዳደሩ አሳስባለው!!
👉"አዲስ አመትን በተመለከተ"
👉 ከስምንት እስከ አስር ስንኝ
👉 60 like ቀድሞ የሞላ 25 birr Card ይሸለማል
👉ቀጥሎ ሁለተኛ የወጣ 15 birr Card
👉 ሶስተኛ ላይ 60 like የደረሰ 10 birr Card ይሸለማል
ከ ከአሁን ጀምሮ ግጥሞቻችሁን @abebekasu እና @mogea ላይ ላኩልን
እስከ ምሽት 3:00 ድረስ ግጥሞቻችሁን ላኩልን ልክ ሶስት ሰአት እንደሞላ ግጥም መቀበል እናቆማለን ስለዚህ ተሳተፉ
ግጥም ለመላክ 👉 @mogea @abebekasu ይጠቀሙ!!
የግጥም ችሎታችሁንም አሳድጉ በተጨማሪ ተወዳድራችሁ አሸንፉ ተሸለሙ !! በስንኝ ቋጠሮ ብቻ!
አንድ ሰአት ከ ሃያ ደቂቃ ይቀራል
ሊጀምር ነው
ቼም የማይረሳን-የዓለማት ጌታ
ጆቹ ነንና-ማይተወን ቀን ማታ
ለፈው እድሜ ላይ-ሌላ ዓመት ጨምሮ
ንም ብንበድለው-በይቅርታ ምሮ
.
.
ዲሱ ዓመት ላይ-ሰናይ ያድርግልን
ግሪ ላለው ማስተርስ-ትንሽ ላለው ትልቅ-አብዝቶ ይስጥልን
ጋት ችግሮችን-ከኢትዮጵያ ምድር-ፈፅሞ ያጥፋልን
.
.
ምና ያየነውን- ችግራቱን ሁሉ
ልካም ይተካቸው-ይረሱ ይጣሉ
ህትና በርክቶ-ሃዘን እንዲጠፋ-እስኪ አሜን በሉ
2015🌼🌼🌼
ሮቤል
":እናት ሀገሬ :"

ጣጣሽ ይተካ
እንቁ ልበሺ
ማልቀሱ ይብቃሽ
ፍቅርን አንግሺ
ጨለማዉ ይንጋ
እንደ ዘመኑ
ትንሳኤዉ ይምጣ
የደስታሽ ቀኑ
ጣጣሽ ይወገድ
እንቁ ለጣጣሽ እንበል ልጆችሽ
ጦቢያ ሀገሬ
ይንጋ ለሊትሽ
ደምሽ ይታጠብ
ዉስጥሽ ይደሰት እንደ አበቦችሽ
ይፍካ ይደሰት
መላዉ አካልሽ
ዉስጥሽ ይታደስ
እንደ ዘመንሽ
© @tamiru_mosisa
---አላቆም መመኜት---

አመት በመጣ ቁጥር
አላቆም መመኜት፣
ሰላም ሁኚ ብዬ
መፃፌን በድምቀት፣
ሰላምሽን ባላቀው
ግና አውቀዋለው በእኔ የብዕር ወረቀት፣
መች ትቼ ማጠኔም ከአመት እስከ እለት፣

ምንም ባላውቅበት ቀለም ስርአቱን፣
ዝም ብዬ እፅፍለው የነገ ሰላምሽን ፣
የምመኚልሽን
ከምዕናቤ ምድር የሰነድኩልሽን፣

መመኜት ላላቆም
ዘመን በተለመ ቁጥር፣
እውነቴ ነሽና የብዕሬ ሰንበር፣
ሰላም እስክትሆኚ ፤
ሰላም የለውም የኔብዕር ሀገር ፣
#Eyual