የስንኝ ቋጠሮ
1.68K subscribers
17 photos
1 video
1 file
7 links
የዚህ ቻናል ዋና አላማ የተለያዩ ወጣቶች የግጥም ችሎታቸውን የሚዳብሩበት እና የሚያወጡበት ቻናል ነው።
ግጥሞችን ለመላክ @mogea ይጠቀሙ መልሰን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል!!
Download Telegram
#ለሀጥያት_ሙት
ሞትም የት አባቱ ገዳይ ብቻ ሆኖ ዘመን ያስቆጠረ
በ ሃጢአት ስር ሽፋን የሰውን ዘር ሁሉ ሲቀጣ የኖረ
ከዘመናት ሁአላ ከዘመናት በፊት ነባር የነበረ
ሞግዚትነት ሽሮ ነፃነት አብስሮ ሞትንም ያሰረ
ሞትበሞት ተገድሎበመስቀልተቀጥቶ ሰላምከተገኘ
አሸናፊው እሱ ነው ለፅድቅ ለመኖር ሞቶ የተገኘ
@mogea @gitmv
Live stream started
አትሳቅ
 
መክነፌ ሳያንሰኝ በአይኖችህ 👀ውበት
መድከሜ ሳይበቃኝ ውሉን ሳላውቅበት
በፍቅርህ ቀንበር ውስጥ የተያዘ ልቤን 🫀
ላስመልስ ሰታገል የወሰድከው ቀልቤን
         ትቼህ እንዳልተውህ በሀሳቤ 🧠እንዳልፀና
          ስቀህ አታለልከኝ ጥርስህ ይርገፍና😁
በ ማህሌት
Human Hair የሚፈልግ በ ውስጥ መስመር ያናግረኝ 👉 @mogea
ቶሎ ና🏃💨

ቆሜያለው ከደጁ 🏠ናፍቆትን አርግዤ😔
ትመጣለህ👣 የሚል ትንሽ ተስፋን ይዤ
ከብርዱ እንድሸሸግ እቅፍን ናፍቄ
ከጉያዬ ውስጥ ፍቅርን አምቄ
     
   እየጠበኩህ ነው👤
           .
           .
    ብርዱ  ሳይጠናብኝ እባክህ ቶሎ ና
     ብቻዬን እንዳልሆን ስጎዝ በጎዳና
ትመጣልኛለህ ከቅፍህ እንድኖር
ከአለም እርቀን በፍቅር እንድንበር💓
                  አሰብከው አለሜ💑
                          .
                          .
አነስ ባለ ጎጆ በእሳት በሞቀ
በ'ቅፍህ ውስጥ ሆኜ ፍቅርን ባመቀ
ልባችን ታድሞ ከጣፋጩ ዜማ
ከእሳቱ ዳር🔥 ሆነን መውደድን ስንሰማ
              ለማይደገመው ለዚ ጣፋጭ🍯 ጊዜ
              ዝናብ ብርዱን ችለህ ቶሎ ና በጊዜ Be Mahi
Forwarded from Mekdim Admasu
ለምን ቀረሽ
ሳልኖር ካንቺ ጋር፣
ሳላቀው ስሜቱን ሳልኖር በቅፍሽ ውስጥ፣
ሳለየው ጠረንሽን ሳይቀር ልቤ ውስጥ።
ላክሽኝ ተስፋ ሞልተሽ ከማላቀው ሰው ጋር።
ጉንጮቼን ደባብሰሽ አቅፈሽ ስትስሚኝ፣
እንባዬን ጠራርገሽ በስስት ስታይኝ፣
መች ገባኝ እማዬ ቻው እንደምትይኝ፣
እመጣለሁ ልጄ መሸት ሲል ቀኑ ነበር እኮ ያልሽኝ።
ቀኑም መሸት ሲል ጀንበር አዘቅዝቃ ወደ ቤቷ ገባች፣
ተረኛ ጨረቃም በከዋክብት መሀል አሸብርቃ ወጣች።
እኔም ወጣሁ ከቤት መምሸቱን አይቼ፣
ከበራፉ ቆሜ እጠብቅሽ ጀመር እስካይሽ ጓጉቼ፣
አቅፌ ልስምሽ አጆቼን ዘርግቼ።
        ግን ግን ግን
     አልመጣሽም እማ
ለምን እንደቀረሽ ሚነግረኝ አጣሁ፣
የኔንም መጠበቅ ላንቺ የሚነግር ተላላኪም አጣሁ።
ታዲያ ለምን ቀረሽ እመጣለሁ ብለሽ?
ምን እንቅፋት ያዘሽ ልጅሽ እንዳታይሽ።

                                          MW
          @gitmv                          13-07-2015
ቃል ነበረ በሰው የተሰበረ
እንደ አሞራ ገደል የተሸረሸረ
ለሰው የተሰጠ በሰው የተሻረ
ቃል ነበረ!
እንደ ወርቅ የነፃው ከውሃ እኩል የጠራው
ድብልቅልቅ ብሎ
ዛሬ ላይ ቢያጣ ከውሸት ሚያጠራው
ቃሎች?
ክብራን ነበሩ ልክ እንደ እንቁ
ዛሬ ላይ ተገፍተው ተጥለው ቢወድቁ
ዛሬ ላይ!
ሚያነሳቸው አጥተው ቢመስሉ ትቢያውን
ውስጣቸው ንፁ ነው አይመስሉም ጣይውን
ጣይውን ቢመስሉ ከድሮም አይኖሩ
ለኛም አይሰጡን ከላይ ከእግዜሩ

                                 ✍️🏽በሰለሞን
#3_ሰአት_ሙሉ_የ_ቲክቶክ_ተንቀሳቃሽ_ምስል_እያየን_3_ደቂቃ_መፃፍ_ማንበብ_ተራራን_የመግፋት_ያክል__ሚከብደን_ለኛ_ለዘመኑ ወጣቶች አጭር መጣጥፍ መፃፍ ራሱ ድንጋይ ላይ ውሃን እንደማፍሰስ የሚቆጠር ቢሆንም ድሮ ልጆች እያለን አምሳ ሳንቲም ይዘን ዘፈኑን፣ ኮሌክሽኑን፣ እና ሙሉ የ ህንድ ፊልም ከ 3-4 ሰአት የሚያህል ቁጭ ብለን ለማየት የነበረን #ትዕግስት አሁን ስም ብቻ ሆኖ መቅረቱን ሳስብ ይገርመኛል። አሁን ላይ ላለን ወጣቶች አንድ ነገር ላይ ረጅም ሰአት መቆየት የንገፈግፈናል ቤተክርስቲየን ገብተን 20 ደቂቃ ስንቀመጥ የሚያፍሽገን መፅሃፍ ቅዱስን ወይም ሌሎች መፅሃፍትን ለማንበብ ስንቀመጥ ከሶስተኛው ገፅ በሁአላ የሚያቁነጠንጠን ትምህርት ለማጥናት ስንቀመጥ አይናችን ውሃ የሚቋጥረው ነገር ለምን ይሆን? አሁን ላይ በ ሃገራችን ሆነ በ አፍሪካ ብሎም በ አለም ላይ ለተጋረጠብን ድቅድቅ ጨለማ ብርሃን መሆን የምንችለው በ አንድ ነገር ላይ ጥልቅ የሆነ እውቀት እና መረዳት ሲኖረን ለዛ ነገር ፈላጊ(demand) አቅርቦት(supply) እንሆናለን። ለ አንድ ነገር ጥልቅ የሆነ መረዳት ሊኖረን የሚችለው በዛ ነገር ላይ መቆየት ስንችል ብቻ ነው። ስለዚህ እዚህም እዚያም እየረገጥን ወደ ጎን ከምናሰፋ የተወሰነ ቦታ መርጠን ወደ ጥልቅ ብንቆፍር ምንጭ እናገኛለን ተገፍተን የማንወድቅ ስር የሰደድን እንሆናለን። እንታገስ! እንቆይበት! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ። ከታዘብኩት @gitmv
እውነት እየዘቀጠ ስፍራን እያጣ ሀጥዕ እየለመለመ እና ስፍራን እያገኘ በመጣበት በዚህ አለም የህይወት ፍርድ ተገማድሎበት መንገደኛው በሙሉ ብቻውን ቢያወራ እና እብዱን ከ ጤነኛው መለየት ቢያዳግት ተአምር አይደለም ሰው ሁሉ አብዷል! ነገር ግን የሚያስደንቀው ነገር የሰው የእብደት ምክኒያት በሙሉ ምድራዊ መሆኑ ነው! አዳሜው ሄዋኔው በሙሉ ትኩረቱን አፈር ላይ ሰፍቶታል ማበድ ብርቅ ባይሆንም ያበደበት ምክኒያት ግን እብደቱን ልዩ ያደርገዋል! ንጉስ ዳዊት በንግስናው ወራት እርቃኑን ሲዘምር መቼስ ንጉስ ነው ሁሉ በ እጁ ሁሉ በደጁ የሆነለት ሚፈልገውን ነገር ሳይንቀሳቀስ አዞ ማስመጣት የሚችል በኑሮ ቀውስ ነው ጨርቁን የጣለው ብንል ውሃ የማያነሳ ብይን ይሆንብናል።
ጨርቅ መጣል የ እብደት መገለጫ መሆኑ አያከራክርም ሆኖም የዳዊት ጨርቅ መጣል ግን መንሰኤው ከላይ ነው። ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛው ሰው የሆነ % አብዷል ኑሮ በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ሁላችንም ማበዳችን አይቀርም። የኔ ጥያቄ ግን ማበዳችን ካልቀረ ለምን እብደትን አንቀድመውም? የሚል ነው! ለዳዊት የአቻ ነገስታቶች ስጋት ሳይበግረው የሚስቱ ማፈር ሳይበግረው አንድ አንድ ትኩረቱን የሳበ አምላክ ነበረው! ከ አምላኩ አንፃር ሌሎች ጉዳዮች በሙሉ ቀለሉበት ዘመን ሲከፋ ነገር ሲቀያየር ሁኔውታዎች ሲለወጡ የማይናጋ መሰረት እንዲኖረን ትኩረታችንን እርሱ ብቻ ይውሰደው ተባረኩ! ወንድማችሁ ሞገስ ነኝ! @gitmv
መች እረሳሀለው አልወጣህ ከልቤ
ለሰከንድ ለአፍታ አልራክም ከሀሳቤ🧠
ለብቻዬ ስነድናፍቆት አይሎብኝ🙍‍♀️
አታየኝም 👀አባ ፍቅርህ አጓሳቁሎኝ🔗🖇
  በእውነት አልተመቸኝአልደላውም ጎኔን
ችላ አትበለኝ ባክህ አታሳንስ ፍቅሬን
     እኔ ሰበበኛ ሀዘን የማያጣኝ😭
  ፍቅርህ አስከንፎ ካንተ ደጅ አመጣኝ🚶‍♀️🚶‍♀️
    ተው ይቅርብኝ ተዋብሽ አትበለኝ🥀
ከጎኔ ከሌለህ ምንም አያምርብኝ
ባይሆን ስትመጣ አንተ እቅፍ ስታደርገኝ🤗
የነጠፈው ወዜ ዳግም ተመልሶ የዛኔ ያስውበኝ👩
  ያንን ቀን ወደድኩት አንተን ያጋመደኝ💏💑
ደስ የሚል ስቃይ😌 በላዬ ሾመኝ 😊
ደሞም ናፈኩት የተስፋውን ቀን
አብረን ምንውለው ማንም ሳያሳቀን👫
ለተራበው ልቤ ባክህ ቶሎ ናለት🚶‍♂️
መኖር አቅቶታል ትዝታህ አዳክሞት🙇‍♀️
ወይ አላገኘውህ ወይ ትቼ አልተውኩ
እማኝ በሌለበት ልቤን ላንተ ተውኩ 😌😌
            ገጣሚ   @gitmv                           ማህሌት
ሀሳቤም አመሌም አንድ ሆኖ ሳለ
ከትዝታ አይተርፍም ፍቅርን ያስተዋለ
የልቤ ደጃፉ መች ተዘግቶ አደረ
እንዳያጣው እያልኩኝ መልሶ ካልቀረ
ስንቱን አያለሁ አንተ እየመሰልከኝ
ስላንተ እያለሙ መኖር አይታክተኝ
ህይወት እንዳለበት በትዝታ መሀል
ልቤ ታገስ እንጂ ለምን ይከብሀል
      መንገዱ ቢያርቀው ትዝታ ያመጣዋል
    የመለየቱን ቀን ኧረ ማን ያውቀዋል
     መችስ ትዝታ እንደ ሰአት ያልፋል
      እስከሞት ድረስ በልብ ውስጥ ይኖራል
@gitmv
Job Title: Photo Editor (Freelance)
Location: Remote

Project Description:
- Moed Pictures is looking for a talented freelance Photo Editor to handle soft copy photo editing for ongoing projects. We're seeking someone with a strong eye for detail and style.

Responsibilities:
- Edit and retouch digital photos
- Ensure consistent visual quality
- Meet project deadlines

Requirements:
- 2+ years of photo editing experience
- Proficiency in Adobe Photoshop/Lightroom
- Solid portfolio
- Reliable and self-motivated

How to Apply:
- Message your portfolio to @mogea on Telegram

Deadline: May 17, 2025