ጀግና
አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣
አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣
ተነሳ ተቆጣ!፦
ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤
ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣
ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣
ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤
በማለዳው ነቅቶ ፣
የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣
ኦኔ እያ'ነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤
ድል እያደረገ ቢያ'ዝም በጠላት ፣
እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣
መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤
እሱ...
የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣
እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣
ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤
ጀግናው
አብዲሳ አጋ !።
ከሻምበል ዋቅጋሪ
ከ ጅማ
20/08/2014
አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣
አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣
ተነሳ ተቆጣ!፦
ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤
ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣
ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣
ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤
በማለዳው ነቅቶ ፣
የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣
ኦኔ እያ'ነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤
ድል እያደረገ ቢያ'ዝም በጠላት ፣
እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣
መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤
እሱ...
የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣
እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣
ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤
ጀግናው
አብዲሳ አጋ !።
ከሻምበል ዋቅጋሪ
ከ ጅማ
20/08/2014
ለኔ...
የድፍን አፍሪካ ኩራት፤የሀያላን ሀገራት ውርደት
የመላው ዓለም ውዥምብር ፤የጣሊያን ቅስም ስብራት
የጥቁር ህዝቦች መመኪያ፤የአፍሪካ ነጻነት ብስራት
ተንቀው ወድቀው ለታዩ፤የዕሳት ትንታግ አለኝታ
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዋርድያ፤የጥቁር ዘር መከታ...
ሚኒሊክ ዕኮ ሀገር ነው...
ግርማው ከተራራ የገዘፈ፤ወኔው ነጭን የረታ
በድፍረት የደነደነ ፤ልቡ የማይፈታ
ጨካኝ አትለው እምዬ ፤ ልቡ የሴት ቦርቧራ
እኖር ባይ አይደለ ቆራጥ፤ የሚቀበል መከራ
ጀግንነት ዕኮ እዳ አለው ፤ ለፈሪ ግን ቀብድ ነው
ዛሬ ጀግናነኝ የሚል ፤ ለሀገር ጥሎሽ ብድር ነው
ለኔ...
ጀግብናዬ እሱ ነው ፤ ስሙን እንደ ዕሾህ ዓለም የፈራው
ጀግና የጀግና ጀግና፤ሚኒሊክ የኛ ሀገር ነው።
@ s@m! d@n
🇪🇹🇪🇹🙏🙏
የድፍን አፍሪካ ኩራት፤የሀያላን ሀገራት ውርደት
የመላው ዓለም ውዥምብር ፤የጣሊያን ቅስም ስብራት
የጥቁር ህዝቦች መመኪያ፤የአፍሪካ ነጻነት ብስራት
ተንቀው ወድቀው ለታዩ፤የዕሳት ትንታግ አለኝታ
የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዋርድያ፤የጥቁር ዘር መከታ...
ሚኒሊክ ዕኮ ሀገር ነው...
ግርማው ከተራራ የገዘፈ፤ወኔው ነጭን የረታ
በድፍረት የደነደነ ፤ልቡ የማይፈታ
ጨካኝ አትለው እምዬ ፤ ልቡ የሴት ቦርቧራ
እኖር ባይ አይደለ ቆራጥ፤ የሚቀበል መከራ
ጀግንነት ዕኮ እዳ አለው ፤ ለፈሪ ግን ቀብድ ነው
ዛሬ ጀግናነኝ የሚል ፤ ለሀገር ጥሎሽ ብድር ነው
ለኔ...
ጀግብናዬ እሱ ነው ፤ ስሙን እንደ ዕሾህ ዓለም የፈራው
ጀግና የጀግና ጀግና፤ሚኒሊክ የኛ ሀገር ነው።
@ s@m! d@n
🇪🇹🇪🇹🙏🙏
ውድ ቤተሰቦቻችን ውድድራችን ቀጥሏል 60 ላይክ ቀድሞ ለደረሰ ተወዳዳሪ የምንሸልም ሲሆን የወደዷቸውን ግጥሞች ላይክ ያድርጉ፤ይሳተፉ።
ውድ ቤተሰቦቻችን እንደምን ከረማችሁ፤እንደሚታወቀው የዚህ ቻናል ዋንኛ አላማ የጀማሪ ገጣሚያንን የግጥም ስራዎች በይበልጥ መውጣት እንዲችሉ መርዳት ነውና ገጣሚያን በየትኛውም ሰዓት የግጥም ስራዎቻችሁን @Abebekasu እና @mogea ላይ ብትልኩልን የምንቀበል ይሆናል።
መቼ ትመጣለህ
ፀሀይ ስትዘቀዝቅ ስታዞረው ፊቷን
ጨረቃ ስትስቅ ስናይ ፈገግታዋን
ሲከፋኝ ስታመም ስምህን ሳነሳ
ስላንተ ሳወጋ ፍቅርህን ሳወሳ
አልበላ ሲለኝ ባር ባር ሲለው ሆዴን
ንገረኝ መቼ ነው እማየው አይንህን
ለሊት አልጋዬ ላይ ሆኜ እንቅልፌ ሲጠፋ
መኖር አስጠልቶኝ ልቤ ሲቆርጥ ተስፋ
ስልኬን አነሳ እና ፎቶህን አያለሁ
ትመጣለህ እያልኩ በርበሩን አያለሁ
ከቀጠርከኝ ቦታ ቀድሜ ብደርስም
ቆሜ ብጠብቅም አንተ ግን የለህም
ትመጣለህ አደል አትቀርም ልጠብቅ
ዝናቡ ቢዘንብ ቢወርድብኝ መብረቅ
ነይ ካልከኝ ቦታ ላይ ቆሜ አንተን ስጠብቅ
ጎርፍ ወስዶ ቢጥለኝ ባካል ካንተ ብርቅ
ስቃዩ ቢበዛ ቢከብድም ንፋሱ
ሳትስመኝ አልሞትም ከንፈሬን በስሱ
ባንተ ሳልታቀፍ ህሜን ሳልነግርህ
አትቀርም ልጠብቅ መቼ ትመጣለህ
🤔🤔
@nitsuhti1419
ፀሀይ ስትዘቀዝቅ ስታዞረው ፊቷን
ጨረቃ ስትስቅ ስናይ ፈገግታዋን
ሲከፋኝ ስታመም ስምህን ሳነሳ
ስላንተ ሳወጋ ፍቅርህን ሳወሳ
አልበላ ሲለኝ ባር ባር ሲለው ሆዴን
ንገረኝ መቼ ነው እማየው አይንህን
ለሊት አልጋዬ ላይ ሆኜ እንቅልፌ ሲጠፋ
መኖር አስጠልቶኝ ልቤ ሲቆርጥ ተስፋ
ስልኬን አነሳ እና ፎቶህን አያለሁ
ትመጣለህ እያልኩ በርበሩን አያለሁ
ከቀጠርከኝ ቦታ ቀድሜ ብደርስም
ቆሜ ብጠብቅም አንተ ግን የለህም
ትመጣለህ አደል አትቀርም ልጠብቅ
ዝናቡ ቢዘንብ ቢወርድብኝ መብረቅ
ነይ ካልከኝ ቦታ ላይ ቆሜ አንተን ስጠብቅ
ጎርፍ ወስዶ ቢጥለኝ ባካል ካንተ ብርቅ
ስቃዩ ቢበዛ ቢከብድም ንፋሱ
ሳትስመኝ አልሞትም ከንፈሬን በስሱ
ባንተ ሳልታቀፍ ህሜን ሳልነግርህ
አትቀርም ልጠብቅ መቼ ትመጣለህ
🤔🤔
@nitsuhti1419
ጠብቄህ ነበረ
ግንስ አልወሽህም ጠብቄህ ነበረ
ስታረፍድጊዜ ለዚያ ነው የቀረ።
ዘንጬ ለብሼ
ሽቶ ተነስንሼ።
ደግሞም ....
ፍቅሬ ምነው ቀረህ?
ዛሬ ምን ገጠመህ?
እያልኩ ጠብቄህ ነበረ
አንተ በማርፈድህ ለዚያ ነው የቀረ
በሰኮንድ ልዩነት እያየሁ ሰዓቴን
የስልክ ጥሪዎች ኮብራ
እየመሠሉኝ
ልቤ እስክትወጣ እያስደነገጡኝ።
እውነቴን ልንገርህ? ጠብቄህ ነበረ
ባቡር, ስታረፍድ ጊዜ ልቤ ተሰበረ
ለስራ አረፈድኩ 'ቦስም' ተማረረ።
ወይንሃረግ✍ @gitmv
ግንስ አልወሽህም ጠብቄህ ነበረ
ስታረፍድጊዜ ለዚያ ነው የቀረ።
ዘንጬ ለብሼ
ሽቶ ተነስንሼ።
ደግሞም ....
ፍቅሬ ምነው ቀረህ?
ዛሬ ምን ገጠመህ?
እያልኩ ጠብቄህ ነበረ
አንተ በማርፈድህ ለዚያ ነው የቀረ
በሰኮንድ ልዩነት እያየሁ ሰዓቴን
የስልክ ጥሪዎች ኮብራ
እየመሠሉኝ
ልቤ እስክትወጣ እያስደነገጡኝ።
እውነቴን ልንገርህ? ጠብቄህ ነበረ
ባቡር, ስታረፍድ ጊዜ ልቤ ተሰበረ
ለስራ አረፈድኩ 'ቦስም' ተማረረ።
ወይንሃረግ✍ @gitmv
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
(በእውቀቱ ስዩም)
.
.
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።።
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
።።።።።።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
@gitmv
(በእውቀቱ ስዩም)
.
.
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት፣
እንደ አክሱም ድንጋይ እንደሮሃ አለት፣
የጊዜ ሞገድ ያልነቀነቀኝ፣
የመከራ ዶፍ ያላደቀቀኝ፣
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ፣
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።
ከዋርካ ባጥር ከዕምቧይ ተልቄ፣
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ፣
ከምድረበዳ ጅረት አፍልቄ፣
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።።
ልክ እንደቻይናው የትም ሳልረባ፣
እንደ እንግሊዙ ሳልሰራ ደባ፣
እንደ አሜሪካው በቁም ሳልሰባ፣
በመጠን ኑሬ አፈር 'ምገባ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ፣
ራስምታቴን በዳማከሴ፣
ነቅዬ 'ምጥል፣
አገር በነገር የማብጠለጥል፣
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ኢትዮጵያዊ ነኝ!
።።።።።
እንደመሃረብ ቤቴን በኪሴ፣
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ፣
ይዤ የምዞር ከቦታ ቦታ፣
በዘብ በኬላ የማልገታ፣
ኢትዮጵያዊ ነኝ!!!!
።።።።።።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።
@gitmv
የካድኩት ልጅ አለኝ
ወልጄ 'ማላቀው አሱም የማያቀኝ።
ግሩም ድንቅ ፍጡር
ከሱ በላይ ላሳር።
አይኖቹ ከዋክብት ጠይም አሳ
መሳይ
እኔን እናቱን ሲሆን አይኑ ዞሮ 'ማያይ
ምጡቅ አንጎል አለው
አለም ያደነቀው
ግንሳ.... ብልሀት ጎደለው።
አንጀቱ እንስፍስፍ
ማየት የማይችል ግፍ።
ግንሳ ለናቱ....
አይራራ አንደበቱ።
እናትህ ትቃጠል እናትህ እንዲ
ትሁን
እናትህ..... እናትህ.....የስድብ
ውርጂብኝ።
የካድኩት ልጅ አለኝ
እሱም የማያቀኝ
ስድብ የሚያረገኝ
አስር ጣት እያለው...
ሁለቱን ሦስቱን ካልቆረጥኩ
የሚለኝ።
ወልጄ 'ማላቀው አሱም የማያቀኝ።
ግሩም ድንቅ ፍጡር
ከሱ በላይ ላሳር።
አይኖቹ ከዋክብት ጠይም አሳ
መሳይ
እኔን እናቱን ሲሆን አይኑ ዞሮ 'ማያይ
ምጡቅ አንጎል አለው
አለም ያደነቀው
ግንሳ.... ብልሀት ጎደለው።
አንጀቱ እንስፍስፍ
ማየት የማይችል ግፍ።
ግንሳ ለናቱ....
አይራራ አንደበቱ።
እናትህ ትቃጠል እናትህ እንዲ
ትሁን
እናትህ..... እናትህ.....የስድብ
ውርጂብኝ።
የካድኩት ልጅ አለኝ
እሱም የማያቀኝ
ስድብ የሚያረገኝ
አስር ጣት እያለው...
ሁለቱን ሦስቱን ካልቆረጥኩ
የሚለኝ።
ጥንትስ ያለወትሮ ብዙ አመት
አርግዤ
ሰው ሆኖ ሰው ላይሆን ጭንቅ
ምጥ ተይዤ
ጉዴ ሳይሰማ መስከረም
አልጠባም
መቼ አደለኝና አቅፌ ለመሳም።
በሆዴ ውስጥ ያለው ያረገዝኩት
🤰ልጄ
ልምሻ የመሰለኝ ስዳብሰው በጄ።
አሁን ከኔ ወጥቶ
ምን ሊረባ ከቶ🤔
ግዴለም, ባይወለድ ይቅር
ተወልዶ ላይረባ ኖሮ ላይጠነክር
ደሞ .... አባት የሌለው ልጅ
ኧረ ለማን ሊበጅ!?
ስለዚህ እዛው ሁን ልጄ አትወለድ
ቆመህ ላትራመድ።
በማህፀን ሳለ ስመኘው የኖርኩት
የማልወልደው ልጄን ስነ-ፅሑፍ
አልኩት።
ወይንሃረግ
አርግዤ
ሰው ሆኖ ሰው ላይሆን ጭንቅ
ምጥ ተይዤ
ጉዴ ሳይሰማ መስከረም
አልጠባም
መቼ አደለኝና አቅፌ ለመሳም።
በሆዴ ውስጥ ያለው ያረገዝኩት
🤰ልጄ
ልምሻ የመሰለኝ ስዳብሰው በጄ።
አሁን ከኔ ወጥቶ
ምን ሊረባ ከቶ🤔
ግዴለም, ባይወለድ ይቅር
ተወልዶ ላይረባ ኖሮ ላይጠነክር
ደሞ .... አባት የሌለው ልጅ
ኧረ ለማን ሊበጅ!?
ስለዚህ እዛው ሁን ልጄ አትወለድ
ቆመህ ላትራመድ።
በማህፀን ሳለ ስመኘው የኖርኩት
የማልወልደው ልጄን ስነ-ፅሑፍ
አልኩት።
ወይንሃረግ
የባከነ ሌሊት!!!!
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
(በእውቀቱ ስዩም)
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው
(በእውቀቱ ስዩም)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትፀንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው፥ ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው::
መጣ፥ መጣ ፥ መጣ ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ፥ ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እጣርሁ ነው ::
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደ ብስል ሾላ ፍሬ ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
አዲስ ሰማይ ይነቃል፥
እንኳንስ የግርሽ ኮቴ ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ።
(የማለዳ ድባብ)
(በእውቀቱ ስዩም)
በጣራው ላይ ሲረማመድ፥ የዝናቡ ልዝብ ኮቴ
መጋረጃው ሲውለበለብ፥ ሰንደቅ ሆኖ ለመስኮቴ
ዋርካው በቅጠል ጽዋ
ውሀ ሲያቁር ከሕዋ
የምድርን ጉሮሮ ሊያርስ
መሬት ፍጥረትን ስትፀንስ
በዚህ ሁሉ ጸጋ መሀል፥ ያንቺን መሄድ ስተምነው
ኢምንት ነው፥ ምንም ነው
ልረሳሽ እየጣርሁ ነው::
መጣ፥ መጣ ፥ መጣ ፥ የዝናቡ ኮቴ አየለ
ክረምት የፍጥረት መሲሕ፥ በቀጠሮው ከተፍ አለ
ስሱ የጉም አይነርግብ፥ ውብ ገጽሽን ሸፋፈነው
የርጥብ አፈር ፥ ርጥብ ሽታ፥ ውብ ሽቶሽን አዳፈነው
ልረሳሽ እጣርሁ ነው ::
የዝናቡ ኮቴ ይደምቃል
እንደ ብስል ሾላ ፍሬ ፥ አሮጌው ሰማይ ይወድቃል
አዲስ ሰማይ ይነቃል፥
እንኳንስ የግርሽ ኮቴ ፥ ጎዳናሽም ታጥቦ ያልቃል
ልረሳሽ እየጣርኩ ነው ።
(የማለዳ ድባብ)
ጀግና
አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣
አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣
ተነሳ ተቆጣ!፦
ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤
ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣
ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣
ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤
በማለዳው ነቅቶ ፣
የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣
ኦኔ እያ'ነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤
ድል እያደረገ ቢያ'ዝም በጠላት ፣
እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣
መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤
እሱ...
የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣
እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣
ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤
ጀግናው
አብዲሳ አጋ !።
ከሻምበል ዋቅጋሪ
ከ ጅማ
20/08/201
አንጀቷን ቢወጋ በሆድ ኑሮ ባን'ዳ ፣
አብሮ ከጠላት የእናት ቤት ሲከዳ ፣
ተነሳ ተቆጣ!፦
ልክ ግብሩን ሊያሳይ ነቅቶ በማለዳ ፤
ነጆ ያበቀለው እትብተ ወለጋ ፣
ምሎ ለኪዳኗ ጎህ ሲገፍ ሲውጋጋ ፣
ተነሳ ማለዳ ጠላቷን ፍለጋ ፤
በማለዳው ነቅቶ ፣
የጠላቱን ዱካ ካለበት አሽትቶ ፣
ኦኔ እያ'ነሳሳ በአጀብ በቀረርቶ ፤
ድል እያደረገ ቢያ'ዝም በጠላት ፣
እኛን ምሰል ቢሉት ቢሰጡት ዜግነት ፣
መሞት የመረጠ ክዶ ለባርነት ፤
እሱ...
የማይደራደር ከቶ ባገር ጉዳይ ፣
እትዮጵያን ከፍ አርጎ በሮም አደባባይ ፣
ከፎቅ ያመለጠ በእራፊ ትልታይ ፤
ጀግናው
አብዲሳ አጋ !።
ከሻምበል ዋቅጋሪ
ከ ጅማ
20/08/201