Shambel Wakgari:
ፈተና ነው
ክንደ ብርቱዋኑ ሀያል የተባሉ
ሉአላዊ ሀገር ያፈርሳሉ አሉ
ዲሞክራሲ ሚሉት በዳቦ ስማቸው
ቆይቶአል አሉ አለም ካወቃቸው
ድሮ እዛ ያልነው ዛሬ እዚህ ደርሶ
ባይኔ አይቻለሁ ወገን አስለቅሶ
ሀገሬን ቢጎዱዋት አለሙ አብሮ
ውስጥ-ውጩ ባንድት ፍፁም ተተባብሮ
ቢጎሿሽማትም...! አለየሚረዳት ከፀባዖት ሆኖ
ማያልፍ የለም እና ያልፋል ተፈትኖ
ያልፋል። ያልፈሉ!
ብቻ ክብር ለሀገር!
@*** 18
በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ሊሙ ሻይ ከተማ ቀበሌ
ሻምበል ዋቅጋሪ ጃለታ
ፈተና ነው
ክንደ ብርቱዋኑ ሀያል የተባሉ
ሉአላዊ ሀገር ያፈርሳሉ አሉ
ዲሞክራሲ ሚሉት በዳቦ ስማቸው
ቆይቶአል አሉ አለም ካወቃቸው
ድሮ እዛ ያልነው ዛሬ እዚህ ደርሶ
ባይኔ አይቻለሁ ወገን አስለቅሶ
ሀገሬን ቢጎዱዋት አለሙ አብሮ
ውስጥ-ውጩ ባንድት ፍፁም ተተባብሮ
ቢጎሿሽማትም...! አለየሚረዳት ከፀባዖት ሆኖ
ማያልፍ የለም እና ያልፋል ተፈትኖ
ያልፋል። ያልፈሉ!
ብቻ ክብር ለሀገር!
@*** 18
በጅማ ዞን ጎማ ወረዳ ሊሙ ሻይ ከተማ ቀበሌ
ሻምበል ዋቅጋሪ ጃለታ
ሀገሬ ኢትዮጵያ ፣ሞኝ ነሽ ተላላ ፣እንዳለው ገጣሚ፣
እኔም ልወቅስሽ ነው፣ ልብ ብለሽ ስሚ፣
እውነትም ሞኝ ነሽ ፣ሕዝብሽም ሞኝ ነው፣
የሄደው የመጣው ፣እንደልብ ሚነዳው፣
እውነትም ሞኝ ነሽ፣ ሕዝብሽም ሞኝ ነው፣
አምላኩን ረስቶ፣ ንጉስ የሚያመልከው፣
እኔ ግን ልንገርሽ ፣እኔ ግን ልውቀስሽ፣
ፈጣሪን ማስታወስ ፣ፈጣሪን መጥራት ነው፣ ላንቺ የሚበጅሽ፣
እንደ ቀደም ጊዜ ፣ልክ እንደ በፊትሽ
ኢትዮጵያ ታበፅ ፣እሱ ነው ሚያምርብሽ ፣
✍✍ ሮቤል
አድራሻ : ዓለም ገና
እኔም ልወቅስሽ ነው፣ ልብ ብለሽ ስሚ፣
እውነትም ሞኝ ነሽ ፣ሕዝብሽም ሞኝ ነው፣
የሄደው የመጣው ፣እንደልብ ሚነዳው፣
እውነትም ሞኝ ነሽ፣ ሕዝብሽም ሞኝ ነው፣
አምላኩን ረስቶ፣ ንጉስ የሚያመልከው፣
እኔ ግን ልንገርሽ ፣እኔ ግን ልውቀስሽ፣
ፈጣሪን ማስታወስ ፣ፈጣሪን መጥራት ነው፣ ላንቺ የሚበጅሽ፣
እንደ ቀደም ጊዜ ፣ልክ እንደ በፊትሽ
ኢትዮጵያ ታበፅ ፣እሱ ነው ሚያምርብሽ ፣
✍✍ ሮቤል
አድራሻ : ዓለም ገና
ለ ሰው ሞት አነሰው
ያለችው ቀበሮ ምን ተሰምቷት ይሆን?
የራሱን አዳፋ የራሱን መጥፎ ሃሳብ
በሰው ላይ ለመፍረድ በሰው ለማሳበብ
አብሮት ያለውንም አብሮት እንደሌለ
መካድ መካካዱን
መጥላት መጥላላቱን
ለራሱ አላብሶ ውስጡ እያኖረ
ይሄኔ እኮ እሷ
እኛን ከኛ በላይ አውቃን ኖሮ ይሆናል
እኛም በኛ ቤት ላይ ይሄን ተሳልቀናል
ቀበሮ አለች አሉ ምን አውቃ ለራሷ
ምንም የማታስብ እንስሳ ናት እሷ
አዬ እንስሳ እቴ እኛም ሰው ተባልን
እሷን ኖረን ሆኖ እንደሷ ባወቅን
ሰው ተብሎ መለየት ለማሰቡ ነበር
እኛ ላለማሰብ የማልን ይመስል
ለማያስበው ነው የሚሰጠው ክብር
እንዲህ ያለችውን ቀበሮን ባወኩዋት
እንዴት እንዳወቀች ቀርቤ ባዋያት
ያውም እኮ ያኔ በደናው ጊዜ ነው
እሷ የነበረች
አሁን ብትኖርማ አነሰውም ሳይሆን
ይገባዋል ብላ ገድላ በጨረሰች::
ሰርክ አዲስ
ያለችው ቀበሮ ምን ተሰምቷት ይሆን?
የራሱን አዳፋ የራሱን መጥፎ ሃሳብ
በሰው ላይ ለመፍረድ በሰው ለማሳበብ
አብሮት ያለውንም አብሮት እንደሌለ
መካድ መካካዱን
መጥላት መጥላላቱን
ለራሱ አላብሶ ውስጡ እያኖረ
ይሄኔ እኮ እሷ
እኛን ከኛ በላይ አውቃን ኖሮ ይሆናል
እኛም በኛ ቤት ላይ ይሄን ተሳልቀናል
ቀበሮ አለች አሉ ምን አውቃ ለራሷ
ምንም የማታስብ እንስሳ ናት እሷ
አዬ እንስሳ እቴ እኛም ሰው ተባልን
እሷን ኖረን ሆኖ እንደሷ ባወቅን
ሰው ተብሎ መለየት ለማሰቡ ነበር
እኛ ላለማሰብ የማልን ይመስል
ለማያስበው ነው የሚሰጠው ክብር
እንዲህ ያለችውን ቀበሮን ባወኩዋት
እንዴት እንዳወቀች ቀርቤ ባዋያት
ያውም እኮ ያኔ በደናው ጊዜ ነው
እሷ የነበረች
አሁን ብትኖርማ አነሰውም ሳይሆን
ይገባዋል ብላ ገድላ በጨረሰች::
ሰርክ አዲስ
አፍቃሪ ልብ
አፍቃሪ ልብ ይዤ እንጎራደዳለሁ፣
ማፍቀሬን እያወኩ ብዙውን አያለሁ።
ልቦቼ ትንንሽ ቶሎ ይሰበራሉ፣
ቢተርፉ ቢተርፉ ይሸራረፋሉ።
አፍቃሪ ልብ ይዤ ወዲህ ወዲያ እላለሁ
ወይ ግሩም ማንነት፣
ወይ መርሳት ወይ ማጣት።
ስንቱን አፈቀርኩኝ፣
ልቤ ግን ስንት ነው እያጠያየኩኝ። የመውደድ ማህተቤ መቼም አልበጥስም
ትልቅ ሀይል አለው ይህንን አልክድም።
የወደድኩት ከድቶኝ ብሰቃይ ባነባ ፣
ህይወት ይቀጥላል ይፈስና እንባ።
ስትል እየሰሟት ባሽሙር ሲስቁባት፣
እኔ ብቻ ገባኝ ፍቅርን እንደራባት።
በምድር ቢሞላ የወንድ ጋጋታ
ሴትን ዝቅ የሚያረግ ስሜት የሚነካ
ተወልዶ ያላደገ ስነ ምግባር ተራ፣
ጥበቡን ሲጀምር አምላኩን ያልፈራ
ፍቅርን እያስራበ ሆዷንም ካባባ፣
ዛሬም ትጮሀለች ፍቅርን ተርባ።
ምህረት ወርቁ
5/8/2013
አፍቃሪ ልብ ይዤ እንጎራደዳለሁ፣
ማፍቀሬን እያወኩ ብዙውን አያለሁ።
ልቦቼ ትንንሽ ቶሎ ይሰበራሉ፣
ቢተርፉ ቢተርፉ ይሸራረፋሉ።
አፍቃሪ ልብ ይዤ ወዲህ ወዲያ እላለሁ
ወይ ግሩም ማንነት፣
ወይ መርሳት ወይ ማጣት።
ስንቱን አፈቀርኩኝ፣
ልቤ ግን ስንት ነው እያጠያየኩኝ። የመውደድ ማህተቤ መቼም አልበጥስም
ትልቅ ሀይል አለው ይህንን አልክድም።
የወደድኩት ከድቶኝ ብሰቃይ ባነባ ፣
ህይወት ይቀጥላል ይፈስና እንባ።
ስትል እየሰሟት ባሽሙር ሲስቁባት፣
እኔ ብቻ ገባኝ ፍቅርን እንደራባት።
በምድር ቢሞላ የወንድ ጋጋታ
ሴትን ዝቅ የሚያረግ ስሜት የሚነካ
ተወልዶ ያላደገ ስነ ምግባር ተራ፣
ጥበቡን ሲጀምር አምላኩን ያልፈራ
ፍቅርን እያስራበ ሆዷንም ካባባ፣
ዛሬም ትጮሀለች ፍቅርን ተርባ።
ምህረት ወርቁ
5/8/2013
ሀገሬ አርቧ ነው !
ተነሺ እናት ዓለም
ይብቃ ያንቺ ህማም
ትንሣኤሽ ይሰማ
ድል ንሺ ጠላትን ውጪና ከማማ
ሀገሬ አርቧ ነው !
ብዙ ንፁህ ነፍሶች ደም የሚሸትበት
እንደ አንድዬ ያ'ብ ልጅ
ምንም ያላጠፋ ህዝብ ሚቀጣበት
ስቅለት ላይ ላለችው
ይሁዶች ለከዱአት
ዕጣ ተጣጥለው ለሚቀራመቷት
ፈራጅ እንደ አይሁዶች ሞልተው ለሚፈስዋት
ሀገሬ አርቧ ነው!
ኤሎሄ ኤሎሄ ብላ እንዳጠራው
ያልተዋትን አምላክ ምን ብላ ትክሰሰው
ወንድም ለከዳነው
ወገን ላቆሰልነው
ራስ ለወደድነው
ዘር ጎጥ ለወረሰን
ገንዘብ ለሚገዛን
ለየቱ ተማፅና የትኛውን ትተው
ለስቅለት ያበቃት ሁሉ ሕማሟ ነው
አባት ሆይ ታረቀን
መከፈል መገረፍ መገደሉ ይብቃን
የእናት ኢትዮጵያን እንይ ትንሣኤዋን
አሜን !!
ሰርክ አዲስ
@gitmv
ተነሺ እናት ዓለም
ይብቃ ያንቺ ህማም
ትንሣኤሽ ይሰማ
ድል ንሺ ጠላትን ውጪና ከማማ
ሀገሬ አርቧ ነው !
ብዙ ንፁህ ነፍሶች ደም የሚሸትበት
እንደ አንድዬ ያ'ብ ልጅ
ምንም ያላጠፋ ህዝብ ሚቀጣበት
ስቅለት ላይ ላለችው
ይሁዶች ለከዱአት
ዕጣ ተጣጥለው ለሚቀራመቷት
ፈራጅ እንደ አይሁዶች ሞልተው ለሚፈስዋት
ሀገሬ አርቧ ነው!
ኤሎሄ ኤሎሄ ብላ እንዳጠራው
ያልተዋትን አምላክ ምን ብላ ትክሰሰው
ወንድም ለከዳነው
ወገን ላቆሰልነው
ራስ ለወደድነው
ዘር ጎጥ ለወረሰን
ገንዘብ ለሚገዛን
ለየቱ ተማፅና የትኛውን ትተው
ለስቅለት ያበቃት ሁሉ ሕማሟ ነው
አባት ሆይ ታረቀን
መከፈል መገረፍ መገደሉ ይብቃን
የእናት ኢትዮጵያን እንይ ትንሣኤዋን
አሜን !!
ሰርክ አዲስ
@gitmv
እንዲህ ነው ያገኛት
እንዲህ ነው ያገኛት
ኖሮ በራሱ ቤት የኛን ሊያይ ሲመጣ
አዝኖ በስራችን ሲወረድ በቁጣ
እንዲህ ነው ያገኛት
እሱ የሰራትን አለም እኛ አበላሽተናት
በሀጢያት ውቂያኖስ በዛ ሰፊ ባህር
ጥላቻ እና ቅናት ገዝፎብን ከፍቅር
ሴት ከሴት ተጋብተው ትዕዛዙን ተላልፈው
ቃየሎች ተነስተው አቤሎችን ገድለው
እንዲህ ነው ያገኛት
ድብልቅልቋ ወጦ ምድር ተሸበራ
የሰዉ ህይወት ቀሎ ሁሉም ሆኖ ተራ
ፈጣሪ መኖሩን ሁሉ ሰው ዘንግቶ
ከነፍስ ደስታ ይልቅ ለስጋው አድልቶ
መፅም መፀለዩ ተለውጦ አየህው
በስካር በዝሙት ብታይ ተጨማልቀው
እንዲህ ነው ያገኛት
መሬቷ ረጥባ የሠው ደም ሞልቶባት
ህዝብ በህዝብ ላይ ይነሳል እንዳለው
ትንቢቱ ሲፈፀም ጊዜው ደርሶ ባለው
እንዲህ ነው ያገኛት
ወደ ምድር ወረዶ ባልታሰበው እለት
✍✍ራኬብ✍✍
እንዲህ ነው ያገኛት
ኖሮ በራሱ ቤት የኛን ሊያይ ሲመጣ
አዝኖ በስራችን ሲወረድ በቁጣ
እንዲህ ነው ያገኛት
እሱ የሰራትን አለም እኛ አበላሽተናት
በሀጢያት ውቂያኖስ በዛ ሰፊ ባህር
ጥላቻ እና ቅናት ገዝፎብን ከፍቅር
ሴት ከሴት ተጋብተው ትዕዛዙን ተላልፈው
ቃየሎች ተነስተው አቤሎችን ገድለው
እንዲህ ነው ያገኛት
ድብልቅልቋ ወጦ ምድር ተሸበራ
የሰዉ ህይወት ቀሎ ሁሉም ሆኖ ተራ
ፈጣሪ መኖሩን ሁሉ ሰው ዘንግቶ
ከነፍስ ደስታ ይልቅ ለስጋው አድልቶ
መፅም መፀለዩ ተለውጦ አየህው
በስካር በዝሙት ብታይ ተጨማልቀው
እንዲህ ነው ያገኛት
መሬቷ ረጥባ የሠው ደም ሞልቶባት
ህዝብ በህዝብ ላይ ይነሳል እንዳለው
ትንቢቱ ሲፈፀም ጊዜው ደርሶ ባለው
እንዲህ ነው ያገኛት
ወደ ምድር ወረዶ ባልታሰበው እለት
✍✍ራኬብ✍✍
ሰላም ውድ "የስንኝ ቋጠሮ" ቻናል ቤተሰቦቻችን በዚህ ሳምንት እንደከዚህ ቀደም ሁሉ አርብ እለት የግጥም ውድድር ይኖረናል።
የግጥሙም ሀሳብ "በሀገራችን ታሪክ የሀገር ባለውለታ ጀግና ነው ለምትሉት ግለሰብ ስንኝ መቋጠር"
በተጠቀሰው ሀሳብ ብቻ የግጥም ስራችሁን @Abebekasu እና @mogea
ላይ ከነገ ሀሙስ ማለዳ ጀምሮ ውድድሩ እስከሚካሄድበት አርብ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ እንድትልኩልን እንሻለን።
ማሳሰቢያ
1.በተጠቀሰው የግጥም ሀሳብ ብቻ እንዲሆን የምትልኩልን ግጥም
2.ከ 12 ስንኝ ያልበለጠ ግጥም
👉እንደሁልግዜው ሌሎች ወዳጆቻችሁንም ወደ ቻናላችን መጋበዝ አትረሱ።
የግጥሙም ሀሳብ "በሀገራችን ታሪክ የሀገር ባለውለታ ጀግና ነው ለምትሉት ግለሰብ ስንኝ መቋጠር"
በተጠቀሰው ሀሳብ ብቻ የግጥም ስራችሁን @Abebekasu እና @mogea
ላይ ከነገ ሀሙስ ማለዳ ጀምሮ ውድድሩ እስከሚካሄድበት አርብ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ እንድትልኩልን እንሻለን።
ማሳሰቢያ
1.በተጠቀሰው የግጥም ሀሳብ ብቻ እንዲሆን የምትልኩልን ግጥም
2.ከ 12 ስንኝ ያልበለጠ ግጥም
👉እንደሁልግዜው ሌሎች ወዳጆቻችሁንም ወደ ቻናላችን መጋበዝ አትረሱ።
ውድ ቤተሰቦቻችን ግጥሞቻችሁን ነገ ምሽት 3 ሰዓት ድረስ እየተቀበልን እንቆይና ወደ ውድድሩ እናመራለን። ከዚህ በፊት የነበሩት ህጎች ቀጣይነት ያላቸው ሲሆን ቀድሞ 60 ላይክ የደረሰ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሲሆን ሁለተኛ እና ሶስተኛ 60 ላይክ የሚደርሱም ተወዳዳሪዎች በቅደም ተከተል የሚሸለሙ ይሆናል።አሁንም ከላይ በጠቀስነው ሀሳብ የግጥም ስራችሁን @Abebekasu እና @mogea ላይ ላኩልን።
ምሽት ላይ ለሚኖረን የግጥም ውድድር አሁንም ግጥሞቻችሁን እየተቀበልን እንገኛለን።
ማን ነው ጀግናችሁ?ስንኝ እስኪ ቋጥሩለት፤እንዲሁም ላኩልን።
ማን ነው ጀግናችሁ?ስንኝ እስኪ ቋጥሩለት፤እንዲሁም ላኩልን።
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ውድድራችንን ለማካሄድ አንድ ሰዓት ገደማ ይቀረናል።አሁንም ግጥሞችን መቀበል ስለምንችል @Abebekasu እና @mogea ላኩልን።
ማነው ጀግና የሀገርህ?
ከሁሉ በላይ ክብር የሚሰጥህ
እስኪ ንገረኝ ወገኔ ማን ይሆን ጀግናህ?
በህይወት እንድትኖር ጊዜ፣ ጉልበቱን ደግሞም ገንዘቡን የከሰከሰልህ
ሀገርህም እንዳትፈርስ ነፍሱን የገበረልህ
በፈጠረህ ንገረኝ ማን ይሆን ጀግናህ?
እኔ ግን እላለሁ ጀግናዬ ገበሬ
አርሶ በጉልበቱ ማዕድ ያቀረበላት ለሀገሬ
አርብቶም ያበላን ተዋግቶ ከአውሬ
ደግሜ ደግሜ እኔ ግን አላለሁ ጀግናዬ ገበሬ
ዋጋው ያልታየለት
በቃ እሱ ነው ጀግናዬ ለሀገሩ የሞተላት
ዳር ድንበሩአንም ያስከበረላት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።✍B. T
ከሁሉ በላይ ክብር የሚሰጥህ
እስኪ ንገረኝ ወገኔ ማን ይሆን ጀግናህ?
በህይወት እንድትኖር ጊዜ፣ ጉልበቱን ደግሞም ገንዘቡን የከሰከሰልህ
ሀገርህም እንዳትፈርስ ነፍሱን የገበረልህ
በፈጠረህ ንገረኝ ማን ይሆን ጀግናህ?
እኔ ግን እላለሁ ጀግናዬ ገበሬ
አርሶ በጉልበቱ ማዕድ ያቀረበላት ለሀገሬ
አርብቶም ያበላን ተዋግቶ ከአውሬ
ደግሜ ደግሜ እኔ ግን አላለሁ ጀግናዬ ገበሬ
ዋጋው ያልታየለት
በቃ እሱ ነው ጀግናዬ ለሀገሩ የሞተላት
ዳር ድንበሩአንም ያስከበረላት
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።✍B. T