ፈለገ ጥበብ ሚዲያ felegetbeb media
985 subscribers
8.53K photos
102 videos
110 files
1.25K links
ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ፈለገ ጥበብ ሰንበት ት/ቤት የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ክፍል ሲሆን ይህ ቻናል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሆኑ አስተምህሮቶች በየእለቱ የሚለቀቅበት ቻናል ነው ቻናላችን ስለተቀላቀሉ በእግዚአብሔር ፅኑ ፍቅር እናመሰግናለን ።

#የፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት_የመረጃ_ሚዲያ_እና_ህዝብ_ግንኙነት_ክፍል
#FTM
Download Telegram
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ሲኖዳ ለማይወልዱ መካኖች እጅግ ልዩ ቃልኪዳን ነው የተሰጣቸው፡፡ መቃብራቸውን እየዞሩ እምነታቸውን እየተቀቡ ገድላቸውን እየታሹ የማይወልዱ መካኖች የሉም፡፡ ከሩቅም ሆነው በስማቸው ተስለው እምነታቸውን ተቀብተው የሚወልዱ በጣም ብዙዎች ናቸው፡፡

የጻድቁ ሌላኛው በስማቸው የተሰየመውና እጅግ ተአምረኛው ታቦታቸው ዛሬም አቡነ ሲኖዳ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከአ.አ 180 ኪ.ሜ ርቆ ከጣርማ በር አልፎ ሞላሌ ከተማ ውስጥ ይገኛል፡፡ በሰሜን ሸዋ በሚገኘው በዚህ ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ በዘመናችንም በጣም በርካታ ተአምራት ይደረጋሉ፡፡ ለጻድቁ የተሰጠችውን የስዕለት በግ ጅብ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ገብቶ ሊበላ ሲል ቀንዱን ነክሶ ደርቆ ሞቶ ሲገኝ በጉ ግን ምንም አልሆነም፡፡ አቃቢቷም እንዲሁ ከትልቁ ተራራ ሥር በትልቅ ቅል ውኃ ቀድተው ሲመለሱ ገመዱ ተበጥሶ ቅሉ ከነውኃው ከትልቁ ገደል ገብቶ ድንጋይ ላይ ቢያርፍም ቅሉ ሳይሆን ድንጋዩ ነው የተሰበረው፡፡ የአካባቢው ነዋሪም ‹‹በጉ ጅብ ገደለ፣ ቅሉ ድንጋይ ሰበረ›› እያሉ ጻድቁን ያወድሷቸዋል፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_እና_ግንቦት#ከገድላት_አንደበት#ነገረ_ቅዱሳን_አንስት (መዝገበ ሃይማኖት አፕሊኬሽን))
✝️✝️ ትርጓሜ ✝️ ወሐተታ ✝️✝️

✝️ #ወይን ለማይጠጣ ሕይወቱ ምንድን ነው? ✝️

"" ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ "" (ሲራክ. 34:26)

=>ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወይንን (ጠላ : ቢራ . . .)
¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም::
¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም::

¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው!" አትልም::
¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄ አድርጉ" ትለናለች::

+በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ::

1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም!)

2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ . . . ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው::

+በተለይ "ወይን ያስተፌስሕ ልበ ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው::

+አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን::

¤እኛ ግን የሊቀ ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን : ቅዱስ ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ : በአባቶቻችን ካህናትና ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ : ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (ለምን . . . አንቀላፍተናላ!!!)

=>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!)

+ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለውን) በመቶኛ /በ%/ ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90% ) "ኦርቶዶክሳዊ ነኝ" ባይ ነው::

+ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ : ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል::

✝️ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው??
~ለመሆኑ ቅዱስ መጽሐፍ ጠጪነትን ያበረታታል??
~አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) ✝️

+ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ::

+በመጀመሪያ ግን ብርሃነ ዓለም : ዓዘቅተ ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) ቅዱስ ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:-

1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው (1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና::

2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው::

+ቅዱስ መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው : በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው::

=>ነቢዩ "ወይን ለማይጠጣ ምን ሕይወት አለው?" ይላል::

1.ወይን = (ምስጢረ ሥላሴ)

¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19)

+ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን : ወልድ ጉንደ ወይን : ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል::

2.ወይን = ክርስቶስ (ምሥጢረ ሥጋዌ)

¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ : አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "አነ ውእቱ ጉንደ ወይን = እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1)

+መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ : ወልደ አብ ወልደ ማርያም : ሥግው ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው::

3.ወይን = ድንግል ማርያም (ነገረ ማርያም)

¤ጌታን "ወይን" ካልን ድንግል ማርያምን "ሐረገ ወይን" : "አጸደ ወይን" ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ)

+መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን ወላዲተ አምላክ መሆኗን : ዘለዓለማዊ ድንግልናዋን : ፍጹም ሞገስ ያላት አማላጅ መሆኗን : ቅድስናዋንና ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1)

4.ወይን = ቅዱሳን (ነገረ ቅዱሳን)

¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን "ወአንትሙሂ አዕጹቂሁ =እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5)

+ስለዚህም በቅዱሳን ክብር : አማላጅነት : ፈራጅነትና የጸጋ አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28)

5.ወይን = ሥጋ ወደሙ (ምስጢረ ቁርባን)

¤እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለ ጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1)

+ለዚያም ነው "ወይንኬ አልቦሙ = ወይንኮ የላቸውም" ስትለው : "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ = እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት::

+ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል::
"የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ : ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53)

¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን::

+ቅዱሱ ነቢይ ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው::
¤በወይን በተመሰሉ:-
#በምስጢረ_ሥላሴ
#በምስጢረ_ሥጋዌ
#በነገረ_ማርያምና
#ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ : ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና::

=>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን::

✝️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝️
(06/10/07)

Re. 2014
ለሌሎች አጋሩት
+<< #ወይን_ለማይጠጣ_ሕይወቱ_ምንድን_ነው? >>+

"ምንትኑ ሕይወቱ ለዘኢይሰቲ ወይነ" (ሲራክ. 34:26)

=>#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ወይንን (ጠላ: ቢራ . . .)
¤"አትጠጡ" ብላ አትከለክልም::
¤ግን ደግሞ "ጠጡ" ብላም አታበረታታም::

¤አልኮል መጠጦችን መጠቀም "ኃጢአት ነው" አትልም::
¤ግን ደግሞ " . . . ካያያዝ ይቀደዳል" እንዲሉ አጠቃቀማችን ወደ ኃጢአት ሊወስደን ስለሚችል "ጥንቃቄን አድርጉ" ትለናለች::

+በዘመናችን ከመጠጥ ጋር በተያያዘ (በተለይ ለክርስቲያኖች) 2 ፈተናዎች ይታያሉ::

1.አብዛኛው የቤተ ክርስቲያናችን ምዕመን (በተለይ ወጣቱና ጐልማሳው) አነሰም በዛም ጠጪ እየሆነ ነው:: (ልብ በሉልን "ይሰክራል" አላልኩም)

2.እጅግ በሚያስቀይም መንገድ ለመጠጣት ጥቅሶች ከቅዱስ መጽሐፍ ሲጠቀሱ እየሰማን ነው::

+በተለይ "#ወይን_ያስተፌስሕ_ልበ_ሰብእ" (መዝ. 103:15) ከእኛው አልፎ በዘፈንና በመገናኛ ብዙኃን ማስታወቂያዎች ላይ ሲጠቀስ ስንሰማ አንጀታችን ካላረረ የቁም ሙት ሆነናል ማለት ነው::

+አሕዛብ ከመጽሐፋቸው አንዲት ዘለላ ብትነካ ሃገሪቱን በተቃውሞ እንደሚንጧት እናውቃለን::

¤እኛ ግን #የሊቀ_ሰማዕታት ስም የቢራ ማሻሻጫ ሲሆን: #ቅዱስ_ቃሉ ለአልኮል መጠጥ ሲጠቀስ: #በአባቶቻችን_ካህናትና_ጻድቃን ላይ በፌዘኞች (ኮሜዲያን ነን ባዮች) ሲቀለድ: ማንም ባለጌ በተቀደሰች ሃይማኖታችን ላይ አፉን ሲከፍት ምንም አይመስለንም:: (አንቀላፍተናላ!!!)

=>ወደ ጉዳዬ ልመለስና የወይንን ነገር እንጨዋወት:: "የትውልዱ ክፋቱ ኃጢአት መሥራቱ አይደለም:: ይልቁኑ ኃጢአቱን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስመሰሉ እንጂ" ብለውኛል የኔታ ክንፈ ገብርኤል:: (በቀኝ ያቁማቸውና!!!)

+ዛሬ በሃገሪቱ የሚገኘውን ጠጪ (ካልጠጣ የሚሞት የሚመስለው) በመቶኛ/በ% ቢሰላ አብዛኛው (ምናልባት እስከ 90 % ) ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ባይ ነው::

+ታዲያ ይህ ጥራዝ ነጣቂ ትውልድ ለምን ስትሉት "ዳዊት እንዲህ አለ: ሐዋርያው ቅ/ዻውሎስ እንዲህ አከለ . . ." ይላል::

<< ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱ ስለ ወይን መጠጣት የሚናገሩ ቃላት ትርጉም እንደሚባለው ነው??
#ለመሆኑ_ቅዱስ_መጽሐፍ_ጠጪነትን_ያበረታታል??
አምላካችን እግዚአብሔርስ ወደዚህች ምድር ያመጣን ለዚሁ ግብር ነው?? (ሎቱ ስብሐት!!!) >>

+ቅዱስ ቃሉን ለገዛ ፈቃድ መተርጐም ፍጹም ኃጢአት ነው:: (2ዼጥ. 1:20) ስለዚህም "ወይን" የሚሉ ቃላት ምንድን ናቸው? ወደሚለው እንመለስ::

+በመጀመሪያ ግን #ብርሃነ_ዓለም: #ዓዘቅተ_ጥበብ (የጥበብ ምንጭ) #ቅዱስ_ዻውሎስ ለደቀ መዝሙሩ #ቅ/ጢሞቴዎስ ስለ ምን "ውሃ ብቻ አትጠጣ:: ጥቂት ወይን ጨምር" አለው ቢሉ:-

1.ወይን በዘመኑ ለሆድ በሽተኞች ፍቱን መድኃኒት ስለ ነበር ነው:: (ቃሉም የሚለው ስለ ሆድህ ህመም ነው(1ጢሞ. 5:23)) ቅዱሱ ከገድል የተነሳ ሆዱ ፍጹም ሕመምተኛ ነበርና::

2.ወይን መጠጣት በልኩ (ጥቂት) የሆነ እንደሆን አካልን ያለመልማል:: ልቡናን ያረጋጋል:: ግን በጊዜው: በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ነው::

+#ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ ግን "ወይን" ተደጋግሞ የተጠቀሰባቸው በርካታ መንፈሳዊ ምስጢራት አሉ:: እነዚህን መነሻ ርዕስ ባደረግነው: በቃለ ሲራክ ተመርኩዘን እንመልከታቸው::

=>ነቢዩ "#ወይን_ለማይጠጣ_ምን_ሕይወት_አለው?" ይላል::

1.ወይን=(#ምስጢረ_ሥላሴ)

¤"ምስጢረ ሥላሴን ላላመነ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ይለናል:: የእግዚአብሔርን አንድነት: ሦስትነት ሳያምኑ ዘለዓለማዊ ሕይወት የለምና:: (ዮሐ. 1:12, 3:17, ማቴ. 28:19)

+ምስጢረ ሥላሴ በወይን መመሰሉን #አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው "አብ ጉንደ ወይን: ወልድ ጉንደ ወይን ወመንፈስ ቅዱስ ጉንደ ወይን . . ." ሲል ነግሮናል::

2.ወይን=#ክርስቶስ (#ምሥጢረ ሥጋዌ)

¤በወልድ (ክርስቶስ) ያላመነ የዘለዓለም ሕይወት የለውም:: (ዮሐ. 3:36) ስለዚህ ነገር ጌታችን ራሱን የወይን ግንድ: አባቱን ተካይ አድርጐ ሲጠራ እንሰማዋለን:: "#አነ_ውእቱ_ጉንደ_ወይን=እኔ የወይን ግንድ ነኝ" እንዲል:: (ዮሐ. 15:1)

+መዳን የሚቻለውም መድኅን ክርስቶስን "#አምላክ_ወልደ_አምላክ: #ወልደ_አብ_ወልደ_ማርያም: #ሥግው_ቃል" ብሎ ማመን ሲቻል ነው::

3.ወይን=#ድንግል_ማርያም (#ነገረ_ማርያም)

¤ጌታን ወይን ካልን ድንግል ማርያምን #ሐረገ_ወይን: #አጸደ_ወይን ልንላት ግድ ይለናል:: (እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ)

+መዳንን የሚሻ ሁሉ እመቤታችን ማርያምን #ወላዲተ_አምላክ መሆኗን: #ዘለዓለማዊ_ድንግልናዋን: ፍጹም ሞገስ ያላት #አማላጅ መሆኗን: #ቅድስናዋንና #ክብሯን ሊያምን ግድ ይለዋል:: (መዝ. 44:9, 86:5, ኢሳ. 1:9, 7:14, ሕዝ. 44:1)

4.ወይን=#ቅዱሳን (#ነገረ_ቅዱሳን)

¤መድኃኒታችን ክርስቶስ ራሱን የወይን ግንድ ብሎ አልቀረም:: ወዳጆቹን #ወአንትሙሂ_አዕጹቂሁ=እናንተ የወይኑ ቅርንጫፎች ናችሁ" ይላቸዋል:: (ዮሐ. 15:5)

+ስለዚህም በቅዱሳን #ክብር: #አማላጅነት: #ፈራጅነትና #የጸጋ_አማልክትነት ልናምን ግድ ይለናል:: (ዘጸ. 7:1, መዝ. 81:1, ማቴ19:28)

5.ወይን=#ሥጋ_ወደሙ (#ምስጢረ_ቁርባን)

¤#እመቤታችን በቃና ዘገሊላ ቸር ልጇን የጠየቀችው ስለጊዜአዊው መጠጥ ቢመስልም ምስጢሩ ግን ለዘለዓለማዊው መጠጥ (ክቡር ደሙ) ነው:: (ዮሐ. 2:1)

+ለዚያም "#ወይንኬ_አልቦሙ=ወይንኮ የላቸውም" ስትለው: "ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ=እናቴ ሆይ! በቀራንዮ አንባ ሥጋና ደሜን የምሰጥበት ጊዜየ ገና ነው" ሲል የመለሰላት::

+ወንጌል ደግሞ እንዲህ ይላል::
"የክርስቶስን ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም::" (ዮሐ. 6:53)

¤የወይን ትርጉም ይቀጥላል . . . ለእኛ ግን እዚህ ላይ ይብቃን::

+ቅዱሱ #ነቢይ_ሲራክ "ወይን ለማይጠጣ ሰው ምን ሕይወት አለው?" ሲል በአንክሮ የጠየቀው ስለዚህ ነው::
¤በወይን በተመሰሉ #በሥላሴ: #በምስጢረ_ሥጋዌ: #በነገረ_ማርያምና #ነገረ_ቅዱሳን ሳያምኑ: ከወይኑ ግንድ ክርስቶስ ጐን በፈሰሰ #ማየ_ገቦ ሳይጠመቁና #ከቁርባኑ ሳይሳተፉ ሕይወት የለምና::

=>ቸር አምላከ ቅዱሳን የምናስተውልበትን አዕምሮ አይንሳን::

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>