FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.4K subscribers
30.6K photos
33 videos
9 files
8.48K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ዕዙ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ ላይ መሆኑን አሥታወቀ።
               
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ምስራቅ ዕዝ በስራ አፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡና የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ከፍተኛ መኮንኖች እና መስመራዊ መኮንኖች ማዕረግ አልብሷል።

ዕዙ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም በማረጋገጥ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት በመወጣት የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ፣ ካሉበት ሃላፊነት አንፃር አንድ ደረጃ ከፍ ማለት ለሚገባቸው የስታፍ አመራሮች የተፈቀደላቸውን ማዕረግ ለብሰዋል።

የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ አገልግሎት ድጋፍ ሜጄር ጄኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ፣ ማዕረግ ሲጨምር የበለጠ ሃላፊነትና ተጠያቂነት የሚጨምር መሆኑን ጠቁመው የቀጣይ ተልዕኳችሁን በላቀ ሁኔታ ለመወጣት ራሳችሁን የምታዘጋጁበት የአመራር ብቃታችሁን ፣ ልምዳችሁንና ክህሎታችሁን የምታሳድጉበት በመሆኑ በተቋሙ ከፍተኛ እምነት ተጥሎባችሁ የተሰጣችሁ እድገት መሆኑን ልትረዱ ይገባል ብለዋል። ዘጋቢ አወል መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
31👍15🔥1
ብቃት ያላቸው ተተኪ የሠራዊት አባላትን ማፍራታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን።
     ሌተናል ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በእውቀታቸው እንዲሁም በዲስፕሊናቸው ብቁ የሆኑ ተተኪ የስታፍ አባላትን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የደቡብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሰለሞን ኢተፋ ተናግረዋል።

የደቡብ ዕዝ ስታፍ እየሰራ ያለው ስራ በጣም ትልቅ እንደሆነ እና እታች ላሉ ስታፍ እንዲሁም ተዋጊ ለሆኑ ክፍሎች አንቀሳቃሽ ሞተር መሆኑን ብሎም ትልቁን ድርሻ የሚይዝ እንደሆነ አንስተዋል።

በሀገሪቱ በርካታ ቀጠናዎችን ሸፍኖ ግዳጁን እየተወጣ የሚገኝ ዕዝ መሆኑ ያነሱት ጀኔራል መኮንኑ የስታፍ ክፍሉም ከኋላ ደጀን ሆኖ ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባው እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱን በመግለፅ ታዛዥ ብሎም ቅን በመሆን ተዋጊውን ኃይል መደገፍ እንደሚገባውም አሳስበዋል።

በተለያዩ መመዘኛዎች በመለካት ብቁ ተተኪ አባላቶችን በማፍራት ተሞክሮ ያለው ዕዝ መሆኑን የገለፁት አዛዡ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ ብሎም ጥሩ የስራ አፈፃፀም ለነበራቸው አባላት ማዕረግ አልብሰዋል::

ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን
ፎቶግራፍ አብረሀም ወርቁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👏18👍8🔥1
የትራንስፖርት መምሪያ ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ክፍል ነው።
ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል የሠራዊታችንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት ለማረጋገጥ በሎጀስቲክስ ስር ያሉ ሁሉም ክፍሎች በቅንጅት የሚሠሩ ቢሆንም ትራንስፖርት መምሪያ ለየት ባለ የተዘጋጀውን ሁሉንም አቅርቦት ለሠራዊታችን በተፈላጊው ጊዜና ቦታ ኃላፊነት ወስዶ ተደራሽ በማድረግ እየፈፀመ ያለው ግዳጅ የሚያኮራ ነው ብለዋል።

የትራንስፖርት መምሪያ የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ለሁሉም የሰራዊት ክፍሎች እንዲደርስ እንዲሁም ዝግጁነታችንን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ክፍል መሆኑንም አንስተዋል።

በተቋማችን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሎጀስቲክስ እየተተገበሩ ያሉት የልማት ስራዎች አካል የሆነውን የትራንስፖርት ማዕከል ጽዱ፣ ውብና ለስራ የተመቸ በማድረጋቸው ጀኔራል መኮንኑ ምስጋና አቅርበው፤ በመምሪያው ውስጥ ያለው አሃዳዊ ፍቅር እና አንድነት የሚያኮራ እንደሆነ ገልጸዋል።

የትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊ ኮሎኔል ፍቃዱ ታደሠ በበኩላቸዉ ተቋማችን አስተማማኝ የሞቢሊቲ  አቅም መገንባቱን ተናግረው፤ መምሪያው የትኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ባለፈው በጀት አመት በሎጀስቲክስ ማዕከላት ግቢ ውስጥ ወጪ ቆጣቢና ዘመናዊ አሰራርን በመከተል ትርጉም ያለው የልማት ስራ መስራት መቻሉንም አንስተዋል።

በዕለቱ በግዳጅ አፈጻጸማቸው የላቀ ዉጤት ላስመዘገቡ የመምሪያው አባላት የምስጋና እና የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሂዷል።

ዘጋቢ ዳዊት ብርሃኑ
ፎቶ ግራፍ በድሩ መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38🔥4👍2
የተቋሙን ውጤታማ የለውጥ ጉዞ  በሳይበር ዘርፉም ለመድገም ተዘጋጅተናል።
  የሳይበር  ዋና ዳይሬክቶሬት አመራሮች 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክትሬት በበጀት ዓመቱ ላከናወናቸው ውጤታማ ተግባራት የዕውቅናና የምስጋና ዝግጅት አካሄዷል።

በዕለቱም ዕውቅናና ሽልማት ከተሰጣቸው  መካከል    የሳይበር ኦፕሬሽን ዳይሬክተር ኮሎኔል ሀገር አስቻለ ፣ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን የሀገርና የተቋሙን የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ቁመና እየተገነባ  እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በቀጣይም ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን በማከል የተጀመሩ  ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅና በሳይበር ዘርፉ የተመዘገቡ ድሎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

የሳይበር ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ኮሎኔል እስማኤል አብደላ በበኩላቸው በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ስራዎችን በውጤታማነት በማከናወናቸው ለዕውቅና መብቃታቸውን ጠቁመው፣  በተለይም በሰው ሀይል ግንባታ፣ በሳይበር የስጋት ትንተና፣ በሳይበር እሴትና በፈጠራ ላይ በማተኮር የተሰሩት ስራዎች አበረታች ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2018 የበጀት ዓመት የተሻለ የስራ ዕቅድ በማውጣትና ለመፈፀም የሚያስችል ሁለንተናዊ አቅም መገንባቱንም ገልፀዋል።

የሳይበር አካላዊ ደህንነት ቡድን መሪ ተወካይ ሻለቃ ሀብታሙ ደሳለኝ፣ በራስ ተነሳሽነት ሶፍትዌር በማበልፀግና የተቋሙን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የደህንነት ሶፍትዌር በራስ አቅም መስራታቸውንና የተቋሙን የለውጥ ጉዞ ለማገዝ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

በዓመቱ ብቁና ዲሲፒሊን ወጣት የሳይበር ባለሙያዎችን ለማብቃት በርካታ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን የገለፁት በዋና ዳይሬክትሬቱ የሳይበር ደህንነት ስልጠና ክትትል ኤክስፐርት ሻምበል ሲሳይ ዴሬሳ ፣ ስራዎችን በዕውቀትና በዲሲፕሊን የሚሰሩ ባለሙያዎችን የማፍራትና የራስን አቅም የማሳደግ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍12🔥3
የምዕራብ ዕዝ የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አመራርና አባላቱ ማዕረግ አልብሷል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ለተሿሚዎች ማዕረግ ያለበሱት የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት የማዕረግ ሹመቱ አመራሩን ለተሻለ የግዳጅ አፈፃፀም የሚያነሳሳና ተጨማሪ ሃላፊነት የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

ዕዙ በአመቱ በርካታ ውጤታማ ስራዎች ማከናወኑን ገልፀው በዚህ ሂደትም የሃምሌ ወር ማዕረግ ተሿሚዎች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዋል።

የምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አመራርና አባላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈተነችበት ጊዜ ፈተናዋን በድል እንድትወጣ ያደረገ ጀግና ሠራዊት በመሆኑ ይህን አኩሪ ድል ለመድገም ተሿሚዎች ከፍተኛ ሃላፊነት አለባችሁ ብለዋል።

ሌተናል ጄኔራል መሰለ መሰረት ግዳጃችን ሰፊና ውስብስብ ቢሆንም ሀገራችን የኛን ጥንካሬ የምትፈልግበት ጊዜ በመሆኑ ህዝባዊ አለኝታነታችንን በተግባር በማሳየት የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ማዕረግ ተሿሚዎች ድርብ ሀላፊነት እንደተሰጣቸው በማሰብ በቀጣይ ለተሻለ ውጤት ጠንክረው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ዘጋቢ ፍፁም ከተማ
ፎቶ ግራፍ  ሽመልስ እሸቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
40🔥6👍3🥰1