FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
40.5K subscribers
31.9K photos
39 videos
9 files
8.86K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል በአርጆ ወረዳ ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል በምስራቅ ወለጋ ዞን አርጆ ወረዳ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የተደረገው ድጋፍ ለተማሪዎች ከ71ሺህ ብር በላይ የሚገመት የመማሪያ ቁሳቁስ ሲሆን ለ110 ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች እንደተበረከተ ተገልጿል።

ድጋፉን ለተማሪዎቹ ያበረከቱት የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ጀንበሬ ማሞ  ሰራዊቱ በግልፅ የተቀመጠ ተልዕኮ ያለውና ለተልዕኮውም እስከ ህይወት መስዕዋትነት እየከፈለ እጅግ አድካሚና ውስብስብ ግዳጆችን እየተዋጣ የሃገርን ሉዓላዊነትና የዜጎችን ሰላም እየጠበቀ ከተልዕኮው ጎን ለጎንም እሴቱን መሰረት ያደረጉ ድጋፍና የበጎ አድራጎት ተግባራትን እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡

ሰራዊቱ ህዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ፣ ተማሪዎች እንዲማሩ፣ ከፍ ሲልም ሃገር እንድትቀጥል ከሚከፍለው መስዕዋትነት በተጨማሪ በየግዳጅ ቀጠናው ህዝባዊነቱን የሚያሳዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን በማንሳት የዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል የተደረገው ድጋፍም የህዝብ ወገንተኝነቱን የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የዲጋ ወረዳ የህዝብ አደረጃጀት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ከፍያለው ቀነዓ በበኩላቸው ሰራዊቱ የሃገርን ሉዓላዊነትና የህዝብን ሰላም ከመጠበቅ ዋና ተልዕኮው ጎን ለጎን የህዝብ አለኝታነቱን የሚያሳይ የህዝብ ልጅ ነው ሲሉ ተናግረዋል። 

ድጋፍ የተደረገላቸው  ተማሪዎችም በሰራዊቱ ስላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ዘገባው የማሰልጠኛ ማዕከሉ  የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ  ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍6🔥1🥰1👏1
የደቡብ ዕዝ ኮር ከምዕራብ ጉጂ እና አጎራባች ዞኖች በጸጥታ ጉዳይ ዙሪያ ምክክር አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም

የደቡብ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል አባዲ ልዑል የምዕራብ ጉጂ ዞን፣ የጌዴኦ፣ የቡርጂ እና የኮሬ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በታደሙበት መድረክ የፀረ-ሠላም ሃይሎችን ዕቅድ በማክሸፍ የዞኖቹን ሠላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ኮሎኔል አባዲ ልዑል የህዝቦችን አንድነት ለማናጋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ የሆነውን የአሸባሪው ሸኔ ርዝራዥ ከህብረተሰባችን ጋር በመቀናጀት ደምስሰን በመንግስት የተጀመሩ ፈጣን የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲሳኩ ሌት እና ቀን መስራት ይገባናል ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ጸጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ሃላፊ  ኮሚሽነር ጸሃዬ ነጋሽ በበኩላቸው የሃገራችን የማንሰራራት ጉዞ የማይጥማቸው ጠላቶቻችንን እና ተላላኪዎቻቸውን ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በላይ በመተባበር ሃገራዊ ራዕያችንን ልናሳካ እንደሚገባ ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ በቀጠናው አስተማማኝ ሠላም ለማረጋገጥ እያከናወነ ያለውን ተከታታይ ዘመቻ በሚገባ በመደገፍ የአሸባሪ ቡድኑን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ዘገባው የኮሩ የሠራዊት ሥነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👍8🔥2🥰1
ከአፍሪካ ህብረት የተውጣጡ ልዑካን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 06 ቀን 2018 ዓ.ም

የጉብኝቱ ዓላማ በቀጣይ በሶማሊያ በሚሰማራው የሀገራችን ሰላም አስከባሪ ሀይል  በቅድመ ስምሪት ዝግጅትና በሠላም ማስከበር ስምሪት ወቅት ከተባበሩት መንግስታት ጋር የሚፈፀም የውል ስምምነቶች/MOU/ እና ሠራዊቱ የሚገለገልበት ቁሳቁስ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ ያለመ ነው፡፡ 

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነህ መንግስቴ፣ ለተባበሩት መንግስታት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ የሰው ኃይል እና ቁሳዊ ሃብት በማዋጣት  ወታደራዊ አስተዋፅኦ እያደረጉ ካሉት ሀገራት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ ገልፀው ፣ ከ2014 ጀምሮ ኢትዮጵያ በሶማሊያ በርካታ ሠራዊት  በማሰማራት ውጤታማ የሠላም ማስከበር ግዳጅ እየተወጣች እንደምትገኝ ገልጸዋል ፡፡

በቀጣይም ወደ አንሶስ /UNSOS/ የሚሰማራው የሰው ኃይልና ሠራዊቱ የሚገለገልበት ቁሳቁስ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በሰላም ማስከበር  ለሚሰማራው ሠራዊት የሚከፈል የሀገር ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የቀን የውሎ አበል፣ ወርሃዊና የካሳ ክፍያ በሚመለከት የጋራ ውይይት ተደርጎ የውል ስምምነት መፈረሙን የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የውል ስምምነት እና ክፍያ ክትትል /COE/ ቡድን መሪ ኮሎኔል መሐመድ ሻፊ ገልፀዋል፡፡

ሀገራችን ወደ ሠላም ማስከበር ግዳጅ ከምታሰማራው የሰው ኃይል እና መገልገያ ቁሳቁሶች ማግኘት ያለባትን ገቢ በተገባው ውል መሰረት እየተገኘ መሆኑን አንስተዋል።

የልዑካን ቡድን ዳይሬክተር ቪክቶሪያ ፖዚ በበኩላቸው  ለቀጣይ ወደ ግዳጅ ለሚሰማሩ ሠራዊት እና መገልገያ ቁሳቁሶችን አስፈላጊውን ዶክሜንቶችን በመሟላት አሰራሩን የተከተለ ወቅቱን የጠበቀ ክፍያ እንዲፈፀም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡ ዘጋቢ ተፈራ ጥላዬ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍3626👏4🥰3🔥1🏆1
ኢትዮጵያ በማንኛውም ቦታ ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት የሚችል የድል ሠራዊት አላት።
ብርጋዲየር ጀነራል ሺሽር ብሃራድዋጅ

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም

‎በዩናሚስ ደቡብ ሱዳን የሴክተር ሳውዝ አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሺሽር ብሃራድዋጅ የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ጎብኝተዋል።

‎በጉብኝታቸው ወቅት፤ ኢትዮጵያ በማንኛውም ቦታና ሁኔታ ውስጥ አልፎ ድል የሚያደርግና ሰላምን በሰላማዊ መንገድ ማምጣት የሚችል የድል ሠራዊት ያላት ሃገር  ስለመሆኗ በተለያዩ ሃገራት ለረዥም ጊዜ የቆየው የአለም ሰላም ማስከበር ታሪኳ ይመሰክራል ብለዋል።

ብርጋዲየር ጀነራል ሺሽር ብሃራድዋጅ፤ ‎የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ካሉት ዋነኛ አላማው ውስጥ ዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነትን ማስጠበቅ ተቀዳሚ ኃላፊነቱ ሲሆን ይህን ተገንዝቦ የሚሰራ የሰላም አስከባሪ ሠራዊት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ውጤት ማምጣት የሚችል መሆኑን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

‎አሁን ላይ ከሌሎች የሰላም አስከባሪ ሻለቆች ጋር በቅንጅት መስራት በመቻሉ በደቡብ ሱዳን የተሻለ ሰላም እየተፈጠረ መምጣቱን የተናገሩት ጀነራል አዛዡ ይህንን ውጤት ለማስቀጠል የግዳጅ አፈፃፀም መተግበሪያ ደንቡን አውቆ መንቀሳቀስና መፈፀም ትልቅ ዋጋ አለው ብለዋል።

‎ከግጭት በኋላ የሚመጡ የሰላም ሂደቶችን ተከታትሎ በመገንባት እና እንደ ወታደር በራስ በመተማመን በተባበሩት መንግስታት ህጋዊነት ያላቸውን እርምጃዎች በመውሰድ አካባቢውን በኢኮኖሚያዊ እና በማህበራዊ ሁኔታ ጨምሮ በብዙ መልኩ መለወጥ እየቻለ ያለ የሰላም አስከባሪ ሃይል መሆኑንም አንስተዋል።

‎አሁን ላይ በቀጠናው የሰላም ስጋትና ለጥቃት ሰለባ የሚሆኑ ቦታዎችን አጥንቶ በመለየት ማረጋገጥ እና ለመወሰን መዘጋጀት ትኩረትን የሚሻ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት እየታየ ያለውን የሰላም ውጤት ለማስቀጠል በይበልጥ እየሰራን እንገኛለን ያሉት ደግሞ የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ ናቸው።

ዘጋቢ አንዋር ሁሴን
‎ፎቶ ግራፍ መብርሂት ገብረሚካኢል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25👍2🔥2
ክፍለጦሮች በፅንፈኛው ቡድን ላይ አሥፈላጊውን እርምጃ ወስደዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ እና አከባቢው የህዝብን ሰላም  ሲያውክ የነበረው እና ለዘረፋ የተሠማራው ፅንፈኛ ቡድን በቀጠናው በሚገኘው ክፍለጦር እርምጃ የተወሰደበት ሲሆን የተማረኩ ፅንፈኞች እና ትጥቅና መሳሪያ ሥለመኖሩም የክፍለጦሩ አዛዥ ገልፀዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎችም ለሠራዊቱ ያላቸውን ቅርበት እና ድጋፍ በተለያዬ መንገድ የገለፁ ሲሆን ለህዝቡ ፀር የሆነውን ፅንፈኛ ቡድን ከሠራዊቱ እና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን እንደሚታገሉት ተናግረዋል። ዘገባው የክፍለጦሩ ነው

በተመሳሳይ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ የሚገኘው ክፍለጦር 42 ፅንፈኞችን ሲደመስስ 21 በማቁሰል የጦር ሜዳ መናፅርን ጨምሮ መሣሪያ እና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
22🔥2👍1