FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የሚጠበቅበትን ተልዕኮ በውጤት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራለ ሹማ አብደታ በከፍሉ አጠቃላይ የግዳጅ አፈፃፀም ብቃትና ውጤት ላይ በመወያየት የነበሩትን ድክመቶች በማስወገድ ጥንካሬዎችን አጎልብቶ ለላቀ የስራ አፈፃፀም መዘጋጀትን አላማ ያደረገ ውይይት ከዕዙ አመራሮች ጋር አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም ዕዙ በበጀት አመቱ ባስቀመጠው ዕቅድ መሰረት ስኬታማና አመርቂ ስራዎችን መስራቱን የገለፁት አዛዡ በተለይ የተላላኪ ባንዳዎች ኢትዮጵን የማተራመስ ስትራቴጂን በመከታተል ከማኮላሽት አኳያ የላቀ ስራ መስራቱን ገልፀዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የቁርጥ ቀን ደራሽ በመሆኑ ሀገሩን ያሻገረ ዕዝ መሆኑን ገልፀው በመሆኑም የታሪካዊ ጠላቶቻችን ተላላኪ ባንዳዎች እጅ በመቁረጥ የህዝቦችን በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የመወሰን መብት እንዲከበር እዙ የሚጠበቅበትን ግዳጅ ውጤታማ በሆነ መንገድ ተወጥቷል ብለዋል፡፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ዕዙ ባደረጋቸው ስምሪቶችም በርካታ የፅንፈኛ አባላት እጅ እንዲሰጡ ተፅዕኖ በመፍጠር በርካቶች እጅ መስጠታቸውን አስታውሰው ክፍሉ በአዲሱ በጀት አመትም የዕዙን የግዳጅ አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እና የሚሰጡትን ሀገራዊ ተልዕኮዎች በጥራት በመፈፀም ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምን በማረጋገጡ ሂደት ውስጥ የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚጫወት አረጋግጠዋል፡፡

ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ ጦርነትን ለማስቀራት ለጦርነት መዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን በማብራራት ዕዙ ከዚህ አኳያ ከአመራር ጀምሮ እስከ ተራ ተዋጊ በርካታ የአቅም ግንባታዎችን ባሳለፍነው ባጀት አመት ውስጥ በመስራት የማድረግ አቅሙን ከፍተኛ ማድረግ ችሏል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከሠራዊቱ ፊት ቆሞ የሚዋጋ ሀይል እንደሌለና የዘራፊነት እንጂ የተላላኪዎች የአሸናፊነት መንፈስ መኮላሸቱን ያብራሩት አዛዡ በቀጣይነት መንደር ለመንደር የሚቀማውን የፅንፈኛ ሀይል የመመንጠሩ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል። ዘጋቢ አብዱራህማን ሀሰን ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
49👍31🕊3🔥2👎1
ዕዙ በበጀት አመቱ ውጤታማ ተግባራት ማከናወን መቻሉ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የ6ኛ ዕዝ በበጀት አመቱ የአሸባሪና የፅንፈኛ ቡድኖችን በመደምሰስ የተሰጠውን ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከናወን መቻሉን የዕዙ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ተናግረዋል። ዋና አዛዡ በዕዙ የተልዕኮ አፈፃፀም ዙሪያ ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ዕዙ በተሰማራባቸው ቀጠናዎች የፅንፈኛና የአሸባሪ ሃይሎች ህዝብን በማሰቃየት ፣በመዝረፍ በአቋራጭ ለመበልፀግ አልመው ያደረጉትን ሙከራ በመቀልበስ ረገድ በበጀት አመቱ የሰራው ስራ ህዝባዊነቱን በተግባር የሚያሳይ ነው ያሉት ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን ይህ ውጤታማ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተዋል።

አሁን ላይ በሁሉም አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንደተፈጠረ ያወሱት ዋና አዛዡ የህዝቡ እና የመስተዳደር አካላት ተሳትፎ የጎላ እንደነበርም አንስተዋል።

የገጠመን ፈተና ውስብስብና የውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ከውስጥ ባንዳዎች ጋር አብረው የሚያደርጉት የሽብር ተግባር መሆኑን የጠቀሱት ጀኔራል መኮንኑ ዕዙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት ሃገርን ከብተና፣ህዝብን ከጭቆና የታደገ የማድረግ ብቃቱን ከትናንት ደማቅ ድሉ የቀሰመ ጀግና ክፍል እንደሆነም አስረድተዋል።

ከህዝብ ጋር ተቀራርበን ያከናወናቸው በርካታ ውይይቶች የጥፋት ቡድኖችን ከማህበረሰቡ ለመነጠል አግዞናል ሲሉ ያስረዱት ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ ጥላሁን የአሸባሪና የፅንፈኛ ቡድኖች ከንቱ ህልም አሁን ላይ በሰራዊታችን ብርቱ ክንድ ከስሟል ፣የጠላት የማድረግ አቅምም ሆነ ሞራል ተዳክሟል ነው ያሉት።

በበጀት አመቱ የነበሩንን ጥንካሬዎች አቅበን በመቀጠል ለበለጠ ድል እና ስኬት መትጋት ፣ከተልዕኳችን ጎን ለጎን በስልጠና መብቃት በልጦ መገኘት የዘወትር ተግባራችን ልናደርገው ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ ደባልቅ አቤ
ፎቶ ግራፍ ሰው መሆን ሃብቱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
18👍17🔥3
ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ የቀጠለ የአያሌ ዘመን ታሪክ ያላት ሃገር ናት
   ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰብረማንያን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ኃይል አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በዩናሚስ ሴክተር ኢስት ግዳጁን እየፈፀመ የሚገኘውን የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃን ጎብኝተዋል።

ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በጉብኝታቸው ወቅትም ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ የቀጠለ የበርካታ አያሌ ዘመን ታሪክ ያላት ሃገር መሆኗን በመጥቀስ በተለይ በአለም ሰላም ማስከበር ሂደት ዘመን ተሻጋሪ ታሪክ እንዳላት እና እሱን ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከአድዋ እስከ ካራ ማራ የዘለቀው የማይደበዝዘው አኩሪ ታሪክ የኢትዮጵያዊያን የጀግንነት ታሪክ ነው። ከዚህም ባለፈ በኮሪያ ምድር የተጀመረው የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር አስተዋፅኦ አሁን ያለው ሠራዊትም  በውጤታማነት እያስቀጠለው መገኘቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

አሁን ላይም በደቡብ ሱዳን የተሰማራችሁ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት የትላንቱን የአያቶቻችሁን የጀግንነት ታሪክ በመድገም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ቀጠና ሆኖ እንዲቀጥል መስራት ይጠበቅባችኋል በማለት አሳስበዋል።

ሌተናል ጀኔራል ሞሃን ሰበረማኒያን በታምቡራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ካምፕ አድዋ በሚል ስያሜ መሰየማቸውን አስታውሰው  በደቡብ ሱዳን ሴክተር ኢስት የሚገኘውን የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃንም ካራማራ በሚል መጠሪያ ስያሜ ሰጥተዋል።

የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ የተሰጠው ስያሜ አባቶቻችን በጀግንነት ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው ጠላትን ድል የነሱበት ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው የነሱን ታሪክ በተጀመረው የአለም ሰላም ማስከበር ስኬታማ የግጃጅ አፈፃፀም አጠናክረን እንድናስቀጥል የሚያነሳሳ ስያሜ ነው ብለዋል።

በወቅቱ የሴክተር ኢስት አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ራዛቅ አህመድ ፣ የመስክ ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ የፎርስ ኮማንደር እና የሴክተር ኢስት ስታፍ አባላት በቀጠናው የሚገኙ የተለያዩ ሃገራት ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዦች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ አንዋር ሁሴን
ፎቶ ግራፍ መብሪሂት ገብረ ሚካኢል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍1918👏10🔥2
በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጤራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ  የነበሩ የፅንፈኛው አባላት ለሠራዊቱ እጅ ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ጤራ ወረዳ አሳግርት ቀበሌ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የጽንፈኛው አባላት ከአንድ ድሽቃ መሳሪያ እና ከነሙሉ ትጥቃቸው ጋር እጃቸውን  ሰጥተዋል።

በሰላማዊ መንገድ እጅ ለሠጡት ለእነዚህ የፅንፈኛ አባላትም የሰሜን ሸዋ ዞን አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ንጉሴ ሞገስ ፅንፈኛው ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ማድረሱን ገልፀው ቡድኑ ከሥህተቱ ሊማር ባለመቻሉ አስተማሪ እርምጃ ሥለተወሰደበት በርካታ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት እጃቸውን ለሠራዊቱ እየሠጡ ይገኛሉ ብለዋል።
  
በመሆኑም በጤራ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፅንፈኞች አንድ ዲሽቃ ፣አራት ብሬን ፣ስናይፐር ፣በርካታ ክላሽ፣ የእጅ ቦምብ እና ተተኳሽ በመያዝ ከ13 አባላት ጋር ለመከላከያ ሠራዊቱ እጅ ሰጥተዋል።

ዘጋቢ ፋሲል ጌትነት
ፎቶግራፍ ጌትነት አበባው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
33👍10👏6🔥2
የምስራቅ ዕዝ አመራሮች በባህርዳር ከተማ በኮሪደር ልማት የተሰሩ ስራዎችን ጎበኙ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሪደር ልማቱ የተሰሩ ስራዎችን በማሥመልከት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ለጎብኝዎች ገለፃ አድርገዋል። አመራሮቹ በጣና ሀይቅ ዳር የተሰሩ መዝናኛ ቦታዎችንና በከተማው የተሰሩ መንገዶችን እንዲሁም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሀመድ ተሰማ መከላከያ ሠራዊት እንደመሆናችን መጠን በጠረፍም ይሁን መሃል ሀገር የተሰሩ ልማቶችን አይተናል፤ ዛሬ ደግሞ በባህርዳር  ከተማ በሚገርም ሁኔታ የለማውን ለባህርዳር ከተማ የሚመጥን የኮሪደር የልማት ሥራ ተመልክተናል ብለዋል።

ባህርዳር ከተማ በሀገሪቱ ካሉ ምቹና ለእይታ ማራኪ ከሆኑ ከተሞች አንዷ መሆኗን ገልፀው ሁላችንም የስራችንን ዉጤት ያየንበት እና ሀገራችን የበለጠ ሰላም ሆና ብትለማ ይበልጥ ማደግ እንደምንችል ያረጋገጥንበት ሥለሆነ ይህ የልማት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስተያዬት ሰጥተዋል።

ዕዙም ህግ የማስከበር ግዳጁን ከመወጣት ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ አረጋግጠዋል፡፡

ከጎብኝዎች መካከል ብርጋዲየር ጄኔራል መለስ መንግስቴ እና ኮሎኔል ፈይሳ አየለ በተመለከቷቸው የልማት ሥራዎች እና ውጤቶች ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው፤ ተስፋ የሚሰጡ ስራዎች ማሳያ ስለሆኑ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
17👍6👏5🔥1