FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የዋና መምሪያው አመራር እና አባላት ጉብኝት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ስር የሚገኙ የኮሌጆችና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮችና አባላት ብሄራዊ ቤተ መንግሥትን እና የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ አመራሮች እንዳሉት በቅድሚያ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊጎበኘው የሚገባው ይህን  የኢትዮጵያን እምቅ ታሪክ ለመላው ህዝባችን ለጉብኝት መፈቀዱ ትክክለኛ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።

ወታደራዊ ስልጠና ሳይወስዱ ለአገራቸው ክብርና ነፃነት በአንድነት ቆመው ያስረከቡንን ሀገር አሁን ያለነው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአባቶቻችንን የታሪክ ሀደራ ተቀብለን በኢትዮጵያ የሚቃጡ የውስጥም ይሁን የውጭ ጥቃቶችን በመመከት ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ በትጋት እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ አባቱ ወልደማሪያም
ፎቶግራፍ ምትክ ንጉሴ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
34👍8🔥3
ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፣ ምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ውጤት ማስመዝገቡን አረጋገጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ምስራቅ ዕዝ የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተናገሩት ፣ ዕዙ በበጀት ዓመቱ በተሰማራባቸው በጎጃም ፣በደቡብ ጎንደር እና በምስራቁ የሐገራችን ክፍል ያደረጋቸው ስምሪቶች ውጤታማ ነበሩ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አሁን ላይ የአባቶቻችንን አልሸነፍም ባይነት የወረሰ ፣በአደረጃጀትም ሆነ በትጥቅ ኢትዮጵያን የሚመጥን ሠራዊት መገንባቱን የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ምስራቅ ዕዝ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች በሀገራችን ካለው ሁኔታ አንፃር ቁልፍ ሚና መወጣቱንና የድል ባለቤት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሀገራችንን በዘር፣ በሀይማኖት ፣ በጎሳ እና ሌሎችንም ምክንያት እየፈጠሩ እርስ በእርስ ለማተራመስ የሚያደርጉትን ጥረት ቢቀጥሉም የብዙ ህዝብ ባለቤት ኢትዮጵያ ግን አሁንም ትልቅ ሀገር ሆና በጀግኖች ልጆቿ ትቀጥላለች ብለዋል።

እናንተም የሀገራችንን ህልውና ለማስቀጠል የዚህ ትውልድ ታሪክ ባለቤት በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባችኋል ሲሉም አክለዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ አመራሮች የመንደር ወሬ ሳይበግራችሁ የአሸናፊነት ስነ-ልቦናችሁን በማስቀጠል በሀላፊነትና በተጠያቂነት መንፈስ እዝና ቁጥጥራችሁን አጠናክራችሁ በመቀጠል ግዳጃችሁን መወጣት ይገባችኋል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ለዕዙ የሠራዊት አመራሮች መልካም የስራ ዘመንን ተመኝተዋል፡፡

በዚሁ ውይይት ላይ የምስራቅ ዕዝ  ከክፍለጦር አዛዦች በላይ፣ የዕዝ ስታፍ መምሪያ ሀላፊዎች እና ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶግራፍ ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37👍15🔥4
ቆራጥና ግዳጁን በጀግነት የሚፈፅም መሪና ሠራዊት ማፍራት ተችሏል።
     ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ደቡብ ዕዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሽባሪውን የሸኔ ቡድን በመደምሰስ ማህበረሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ማስቻሉን የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገልፀዋል።

የዕዙ ሠራዊት በተሰማሩባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች በከፈለው መስዋዕትነት ታላላቅ የመንግስት የልማት ስራዎች በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወኑና ለውጤት እየበቁ ነው ሲሉም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።

ፕሮፌሽናል ሠራዊት ለመገንባት በርካታ ስራ መሰራቱንና በሃይማኖት እንዲሁም በብሄር አስተሳሰብ ያልተያዘ ብሎም አንድ የሆነ ኢትዮጵያዊ አመለካከት ያለው ጠንካራ ሠራዊት ተፈጥሯል ሲሉም ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል።

ሠራዊቱ የሀገሪቱ የመጨረሻ ምሽግ እና ሀገሪቱን ከተለያዩ የጥፋት ቡድኖች የታደገ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ይህንን ጥንካሬ አስጠብቆ መቆየት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን
ፎቶግራፍ አሸናፊ ስዩም

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2520🔥4
የምስራቅ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን ችግኝ ተከሉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ችግኞችን እንተክላለን፣ ህግ እናስከብራለን ፣ የሃገራችንን ሰላም እኛ ተሰውተን እናረጋግጣለን። የሚለውን መሠረታዊ ሃሳብ በመያዝ የምስራቅ ዕዝ አመራሮች ከባህርዳር ከተማ አሥተዳደር ጋር በመሆን ችግኝ ተክለዋል። 

በአማራ ክልል መዲና በችግኝ ተከላው መርሀ ግብር ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ እና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የገጠርና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ፣ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጓሹ እንዳላማው እንዲሁም ሌሎች የባህርዳር ከተማ የመስተዳድር አካላት በመገኘት ችግኝ ተክለዋል፡፡

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ እንደተናገሩት ፣በመንግስታችን ለተከታታይ 7 ዓመታት ኢትዮጵያን አረንጓዴ ለማድረግ በርካታ ችግኞች ተተክለው ፀድቀዋል። የአየር ንብረቷንም ለውጠዋል። ዘንድሮም የተጀመረው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በተቋማችንም 18 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል ከካምፓችን ወደ ህዝባችን በሚል መሪ ቃል ተጀምሯል።

ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ፣ በዛሬው ቀን ለዕዛችን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ችግኝ እንድንተክል በሁሉም የግዳጅ ቀጠናችን የተሰጠን በመሆኑ ዛሬ በይፋ ስንጀምር  እንደ ዕዝ "ችግኞችን እንተክላለን፣ ህግ እናስከብራለን ፣ የሃገራችንን ሰላም እኛ ተሰውተን እናረጋግጣለን ።" በሚል መሪ ሃሳብ መሆኑን ገልፀው ፣ ክልሉ የጀመረውን የልማት ስራዎች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያከናውን አመላክተዋል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የገጠርና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በበኩላቸው፣የሀገር ኩራት የሆነው ጀግናው የሀገር  መከላከያ ሠራዊታችን በተለይም የምስራቅ ዕዝ በክልሉ በሚገኙ ከተሞችና ገጠሮች ሠራዊቱ ባለበት ሁሉ ከህዝባችን ጎን ሆኖ ሠላማችንን ከመጠበቅ ባሻገር የልማቱ ፈር ቀዳጅ አሻራውን በማስቀመጡ በክልሉና በግብርና ቢሮ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ፣ዕዙ በአውደ ውጊያ የሚያደርገውን ተጋድሎና ድል አድራጊነት ፣ በአረንጓዴ አሻራውም አካል በመሆን በከተማችን ስለመጣችሁና የልማታችንም የሰላማችንም ዋልታና ማገር በመሆናችሁ ሁልጊዜም እናከብራችኋለን ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ
ፎቶ ግራፍ ማሩፍ ደስታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27🔥6👍5
መቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ኢንስትራክተር መሠረት ማኔን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ የሾመው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን የአንድ ነባር ተጫዋች ውል ሲያራዝም አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን  ማስፈረም ችሏል።

የመጀመሪያ ፈራሚ የሆነችው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮ ኤሌክትሪክ ምርጥ ብቃቷን እያሳየች የቆየችው እና በሁለቱም መስመር መጫወት የምትችለው እፀገነት ቡዛየሁ ለመቻል ፈርማለች።

ሁለተኛ ያለፈውን አመት በሊጉ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቤት ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለችው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿ ትንቢት ሳሙኤል ለመቻል ፊርማዋን አኑራለች።

ሶስተኛ ፈራሚ የመሀል ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቿ እና ያለፈውን አመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቆይታ የነበራት ድርሻኤ መንዛ አዲሷ የመቻል ተጫዋች ሆናለች።

አራተኛ ፈራሚ ያለፈውን አመት በሀዋሳ ቤት ምርጥ ጊዜ ማሳለፍ የቻለችው እና ሀዋሳ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ ካስቻሉት ወሳኝ ተጫዋቾች መካከል አንዷ የሆነችው ግብ ጠባቂዋ ቤቴልሄም ዮሃንስ  የመቻል ተጫዋች በመሆን ፈርማለች።

ያለፉትን አራት አመታት በመቻል ቤት የቆየችው 11 ቁጥር ለባሿ እና የመሃል ተጫዋቿ ገነት ሀይሉ በመቻል ቤት ለመቆየት ተስማምታለች። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37🔥10👍3👎1
የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን አቅም የሌላትና ደካማ ሀገር ለማድረግ ከመስራት አይቆጠቡም
   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በየአቅጣጫው ነፍጥ እያነሱ ህዝባችንን ሰላም የሚነሱና ልማት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥ ፅንፈኞች፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን እንዳናለማና ጠንካራ ኢትዮጵያ እንዳትኖር የሚፈልጉ የውጭ ጠላቶቻችን ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ባንዳ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በየጊዜው በሚፈጠሩ ሀገር ወዳድ አርበኞቿ ፀንታ የቆመች ናት ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የአርበኞቻችንን ያክል ቁጥር ባይኖራቸውም የውስጥ ባንዳም ያልተለያት ሀገርም ናት ብለዋል።

አሁንም አገርን ለመበታተን እየተፍጨረጨሩ ያሉ የውጭ ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ባንዳዎችን በመደምሰስ የሀገርን አንድነት ያስቀጠለው ሠራዊታችን የዚህ ዘመን አርበኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የውጭ ጠላቶቻችን ምንጊዜም የማይተኙልን በመሆናቸው፣ ሠራዊታችንን ጠንካራ፣ አስተማማኝና ግዳጁን በብቃት መፈፀም የሚችል አድርገን ገንብተነዋል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚህ ሠራዊት ሀገርም እኔም እንኮራለን፣ እናንተም ክብር ይገባችኋል ብለዋል። ዘገባው የደቡብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግነኙነት ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
45🔥9