FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.7K photos
35 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የካምፕና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

በመከላከያ ጠቅላላ አገልግሎት ዋና ዳይሬክቶሬት የካምፕና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለሰራዊቱ  የቤቶች እደላ፣ የውሃ፣ የመብራት ዝርጋታ የቢሮና መኖሪያ ቤቶች ግንባታና የጥገና ስራ ፍትሃዊ በሆነ አገባብ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አሥታውቋል።

ዳይሬክቶሬቱ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በጎፋ ካምፕ የንፁህ መጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ አጠናቆ አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን የእንጨት፣ ብረታ ብረት ስራ በተቋሙ ለሚገኙ ክፍሎች በመሥራት እያቀረበ እንደሚገኝ  የካምፕና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ሞላ ታምሩ ገልፀዋል።

እንደ ዳይሬክቶሬት በበጀት ዓመቱ አመራርና አባላቱ በመጣመር በርካታ ስራዎችን በጥሩ ውጤት ያከናወኑ ሲሆን ለዚህም በክፍሉ የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ላይ የተሻለ አስተዋፅኦ ለነበራቸው አባላት ሽልማት ተሰጥቷል።

ዘጋቢ ደጀኔ አሳይቶ
ፎቶግራፍ ሳሙኤል መንገሻ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
57👍12🔥4👎1👏1
ምድቡ ለተቋሙ ተልዕኮ በሚመጥን የወትሮ ዝግጁነት  ቁመና ላይ ይገኛል።
  ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በ4ኛው አየር ምድብ የስራ አፈፃፀምና ወትሮ ዝግጁነታቸውን በማስመልከት ከምድቡ የሰራዊቱ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ መሪው የመሪነቱን ሚና በመወጣቱ ምክንያት የምድቡ ሰራዊት የሚገጥሙትን  ፈተናዎች ሁሉ ተቋቁሞ ኃላፊነቱን በጀግንነት  ተወጥቷል ብለዋል።

ሠራዊቱ ሙያውንና አቅሙን ተጠቅሞ ተቋሙን ባገለገለ ቁጥር በተለያዩ አገሮች ተፈላጊነቱ መጨመሩንና በአሁን ወቅትም ራሱን እንዲሁም ቤተሰቡንም ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በቀጣይም የምድቡ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላት በተቋማዊ የለውጥ ሀዲድ ውስጥ ራሳቸውን በማስገባት የውጊያ መሳሪያዎችን በመንከባከብ የሠው ሀይል ግንባታውንም አጠናክረው የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ የዝግጁነት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ዘጋቢ ሙላት ምሕረት ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
36👍6🔥2
ለሁለት ቀናት የቆየው የመከላከያ ሚኒስቴር ተጠሪ ክፍሎች ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም ውይይት ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ሁሉም የሚኒስቴሩ ተጠሪ ክፍሎች ከተሰጣቸው ተግባር እና ሀላፊነት አንፃር ያቀዱትን እቅድ እና አፈፃፀማቸውን እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫ ካስቀመጡ በኋላ በቀረቡት ሪፖርት ላይ ውይይት ተደርጓል።

በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጡት የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የበጀት ዓመቱ ከምንጊዜውም በላይ አበረታች እና ተጨባጭ ለውጦች የታዩበት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል።

የተቋሙ ወታደራዊ ድፕሎማሲ፣ ከቴክኖሎጅ ጋር ያለው ትስስር እና የሰው ሀይል ብቃት ከፍ እያለ መምጣቱን ተናግረዋል። በዲጅታላይዜሽን ስራዎችን በመሥራት ለበላይ አመራር በማቅረብ፣ የውስጥ እና የውጭ ኦዲትን አጠናክሮ በመስራት፣ ብሔራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ፣ የቤት ልማቶችን እና ኢንቨስትመንቶችን በማጠናከር፣ የውጭ ግንኙነትን ጤናማ በማድረግ፣ የኢንዱስትሪዎች አዳዲስ ንቅናቄዎች በመፍጠር እና በመሰል ጉዳዮች በኩል ተስፋ ሰጭ የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በአጠቃላይ የበጀት ዓመቱ እንደተቋም ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገርም ተጨባጭ ለውጦች የተመዘገቡበት የስራ ዘመን ሆኖ ማለፋን ጠቅሰዋል።

ወደፊት የሚታቀዱት እቅዶችም የሚቆጠሩ እና በውጤት የሚለኩ ሊሆኑ እንደሚገባ የስራ መመሪያ አስተላልፈዋል። የተቋሙን ታሪካዊ ዳራ ማስቀጠል የሚችል ወቅቱን እና ጥራቱን የጠበቀ የእቅድ እና ሪፖርት አሰራር ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባም አመላክተዋል።

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍16🔥3
ምስራቅ ዕዝ በበጀት ዓመቱ የያዛቸውን ግቦች ማሳካቱን አስታወቀ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ዕዙ ለሶስት ቀናት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም በመወያዬት ጥንካሬዎችን አጎልብቶ ለማስቀጠልና የነበሩ እጥረቶችን ለይቶ በማስተካከል ቀጣይ በተሻለ አፈፃፀም ተልዕኮውን በተሟላ ለማሳካት የጋራ መግባባት ፈጥሯል፡፡ 

የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት ፣ ምስራቅ ዕዝ በበጀት ዓመቱ የተሰጠውን ተልዕኮና የተቋሙን መሪ ዕቅድ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በውጤታማነት ፈጽሟል፡፡

በአማራ ክልል በጎጃምና ደቡብ ጎንደር ዞን ከተደረቡልን የተቋማችን ክፍሎችና በቀጠናው ካለ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመቀናጀት የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለማረጋጋት በፀረ ሽምቅ ስምሪት ግዳጅ አፈፃፀም በቀጠናው አንፃራዊ ሰላም ለማምጣት ውጤታማ ስራዎች ተከናወነዋል፡፡

ሌተናል ጀነራል መሐመድ እንዳሉት ፣ በፀረ ሽምቅ ስምሪት በቀጠናው ታጥቆ የሚንቀሳቀሰውን የፅንፈኛ ቡድን በወሳኝ መልኩ በመደምሰስ ፣ የሚንቀሳቀስበትን ዋና ዋና ቋጠሮ በማጥፋት ፣ የመረጃና ሎጀስቲክስ ሴሉን በመያዝ ከሰራዊታችን ጋር ፊት ለፊት ቆሞ እንዳይዋጋ የማሽመድመድ ግዳጆች ተፈጽመዋል፡፡

በአመቱ የተደረጉ የፀረ-ሽምቅ ኦፕሬሽኖች በወሳኝ መልኩ ውጤት በማስገኘታቸው በክልሉ የመንግስት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ቦርደር በመከላከል ፣ የአልሸባብን እንቅስቃሴ በመከታተል ፣ በውጭ ሶማሊያ ለሰላም አስከባሪ ኃይል ድጋፍ ሰጭ ሆኖ ግዳጁን በመፈፀም ፣ በምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ የኦነግ ሸኔ እንቅስቃሴ ተከታትሎ በቀጠናው ካሉ የጸጥታ ሀይሎች ጋር ተቀናጅቶ በመደምሰስ እና የአካባቢውን ሰላም የማረጋገጥ ግዳጅ በውጤታማነት መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡

የዕዝ ስታፍ በግንባር የሠራዊቱን ግዳጅ በመደገፍ ፣ ደጀን የሚገኘው ደግሞ ከመደበኛ ሥራ በተጨማሪ የእጀባና የተለያዩ ብሔራዊና ሃይማኖታዊ በዓላት ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከበሩ የጥበቃ እና ስምሪት ተግባራትን በማከናወን ተልዕኮውን በብቃት ተወጥቷል ነው ያሉት፡፡

የአመራር ስራችንን የተቋሙን አሰራርና መመሪያ ማዕከል አድርገን በየወቅቱ የሚመጡትን ግዳጆች ውጤታማ በሆነ መልኩ በመምራት ፣ የራሱንና የሚመራውን አባል ስነ-ልቦና በመገንባት ፣ ግልፀኝነት ፈጥሮ አሀዱን አደራጅቶ ግዳጁን በጀግንነት እንዲፈፅም በማስቻል የታዩት መልካም ጅምሮች በቀጣዩ የበጀት አትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

በዚሁ የግዳጅ አፈፃፀም ውይይት ላይ ፣ ከክፍለጦር አዛዦች በላይ ፣ የዕዝ ስታፍ መምሪያ ሀላፊዎች እና ከፍተኛ መኮንኖች ተገኝተዋል።  ዘገባው የምስራቅ ዕዝ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
41👍12🔥3