FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.8K photos
36 videos
9 files
8.51K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመከላከያ ክፍሎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ፣ በውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት እና በሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ክፍለ ጦር ተካሂዷል። 

ሠራዊቱ የተሰጠውን ሃገራዊ ተልእኮ ከማሳካት ጎን ለጎን እንደሃገር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የሀገራችንን የደን ሽፋን ለማሳደግ የተለያዩ የፍራፍሬና ሃገር በቀል ችግኞችን በመትከል ውብና አረንጓዴ ገጽታን የተላበሰች ሀገር ለመፍጠር እንደሚያስችል በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ተናግረዋል።
 
በተያያዘም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ክፍለ ጦር   ሬጅመንት የሠራዊት አባላት ከዳውንት ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና ከህዝቡ ጋር በመሆን ከዘጠኝ ሚሊዮን  በላይ ሀገር በቀል ችግኝ ተክለዋል።

የዳውንት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ አያሌው መከላከያ ሠራዊቱ ከህዝብ አብራክ የወጣ መሆኑን ገልፀው፤  ከግዳጅ ጎን ለጎን በተለያዩ የልማትና የበጎ ስራ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ስለሆነ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል። ዘገባው የክፍሎች ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2015
የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ከሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዬ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በምዕራብ ጎጃም የዞንና የወረዳ አመራሮች ከምዕራብ ዕዝ የኮር አመራሮች ጋር በዞኑ ስላለው ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ ዙሪያ በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አሥቀምጠዋል።

በምዕራብ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዘዘው መኮነን ሠላሙን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ሠራዊቱ እያደረገ ያለውን ትግል የሲቪል አመራሩና ህብረተሰቡ እስከመጨረሻው ከጎኑ መቆምና መደገፍ እንደሚገባው ገልፀዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ እድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በዞኑ ቀጠና አጠቃላይ ስላለው የሠላም ሁኔታ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳሳወቁት ክልሉን ለማፍረስ እየሰራ ያለው ፅንፈኛ ቡድን እያስከተለ ያለውን የጥፋት ተግባራት ለማጥፋት የዞኑ ስራ አመራርና የፀጥታ አካላት ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ቅንጁነት በመፍጠር አሁንም ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

ዘጋቢ አብዲ ሁሴን
ፎቶ ግራፍ አብዲ ሁሴን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27👍15
የማዕከላዊ ዕዝ ክብረ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

ማዕከላዊ ዕዝ የ5 ዓመታት የተልዕኮና ግዳጅ አፈፃፀሙን የሚያይበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በጅማ ከተማ በተለያዩ ክንውኖች መካሄዱን ቀጥሏል።

በክብረ በዓሉ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ፣ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይን ጨምሮ የመከላከያና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጀነራል መኮንኖች የጅማ ዞንና የከተማው አሥተዳደሮች እንዲሁም ማህበረሰቡና የዕዙ የሠራዊት አባላት ሲገኙ የሰልፍ ትርኢትና የፎቶ አውደ ርዕይ እንዲሁም በርካታ ሁነቶች ተከናውነዋል።

በዕዙ አመራሮችና በመከላከያ ማርች ባንድ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የዕለቱ የክብር እንግዳ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃነ ጁላ ዕዙ ባለፉት ዓመታት በርካታ ግዳጆችን በአስተማማኝ ብቃትና በላቀ ድል ማጠናቀቁን ገልፀው ከአመራር እስከ አባል ይህን ላከናዎነው የዕዙ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጂማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር ማዕከላዊ ዕዝ በቀጠናው ሠላም እንዲሰፍን ሁለንተናዊ መስዋዕትነት በመክፈል ከህዝብና መስተዳድር ጋር ቅንጅት ፈጥሮ አስተማማኝ ሠላም እንዲሠፍን ሌት ተቀን እየተጋ ያለ የሃገር መከታ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ጅማሮውን ያደረገው መርሃ ግብሩ ከቀትር በኋላ በፓናል ውይይት መካሄዱን ቀጥሏል። ዘገባው የዕዙ ስነ-ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
22👍17👏1
በፅንፈኛው ቡድን ታግተው የነበሩ የመስኖ ፕሮጀክት ሰራተኞች ከታገቱበት ተለቀቁ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ የአድዋ ክፍለጦር  ግለሰቦቹ በፅንፈኛው ከታገቱበት ጊዜ ጀምሮ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጥምር በመስራትና በአካባቢው ሰራዊቱን በማሰማራት ከታገቱ ከሶስት ቀናት በኋላ ማስለቀቅ ተችሏል።

የአድዋ ክፍለጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አንተነህ ደጀኔ የሰላምና የዕድገት እንቅፋት የሆነው የፅንፈኛ ቡድን በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ በእንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ላይ ለአካባቢው የመስኖ ስራ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን አምስት የፕሮጀክት ሰራተኞች አግቶ ገንዘብ በመጠየቅ ሽብር የፈጠረ ቢሆንም በአካባቢው መከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋርም በመመካከር  ታጋቾቹን ካሉበት ቦታ ማስለቀቅ ተችሏል ብለዋል።

የሰራዊቱን ምት መቋቆቋም የተሳነው ይህ ዘራፊ ቡድን ንፁሃንን በማገት የማሰቃየት ተግባሩን የጀመረ ቢሆንም  የሰላምን አማራጭ እንዲጠቀም የማድረግ ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ሌተናል ኮሎኔል አንተነህ ደጀኔ።

ከታገቱት መካከል የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ እንዳለ አለምነህ የፅንፈኛው ቡድን አስተባባሪ የሆነው መልካሙ ጣሰው እየተባለ የሚጠራው ግለሰብ እንድትለቀቁ ከፈለጋችሁ ሶስት ሚሊዮን ብር አምጡ ያለበለዚያ እርምጃ ይወሰድባችኋል ካለ በኋላ በአካባቢው መከላከያ ሠራዊቱ እየንቀሳቀሰ መሆኑን ሲሰሙ እኛን ወደ ሀገር ሽማግሌዎች ሂዱ ብለው ለቀውናል ሲል ተናግሯል።

ዘጋቢ እሴት ደመቀ
ፎቶግራፍ ወንድወሰን ፍቃዱ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38👍13
የናይጀሪያ ከፍተኛ መኮንኖች ለትምህርታዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መከላከያ መጥተዋል፡፡  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በአፍሪካ ደረጃ ጠንካራ ወታደራዊ የሎጅስቲክስ አመራሮችን በማፍራት ከሚታወቀው የናይጀሪያ ሎጂስቲክስ ኮሌጅ የመጡት ከፍተኛ መኮንኖች በየዓመቱ ለሚያደርጉት ዓለማቀፋዊ እና ወታደራዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን መርጠው መምጣታቸው ታውቋል፡፡
 
ወታደራዊ ልዑኩ ኢትዮጵያን መርጠው በመምጣታቸው የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ የኢትዮጵያን መከላከያን የላቀ የተልዕኮ አፈፃፀም እና ጦርነት የሚሸከም ሎጀስቲክስ በማደራጀት መምራት አንፃር  ያለው ልምድ ከፍተኛ በመሆኑ ለተጠቃሹ ተቋማዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን መምረጣችሁ ብልህ መሆናችሁን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ ወታደራዊ  የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ 

ናይጀሪያ እና ኢትዮጵያ የቆየ ወታደራዊ ግንኙነት እንዳላቸው የተናገሩት ሜጀር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ ሀገራቱ በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ ግንኙት እንዳላቸው እና ጉብኝቱም ሰላም እና ፀጥታን እንዲሁም ወታደራዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የልዑኩ መሪ ሜጀር ጀኔራል ኢቱክ ዋይስዶም ቤንጃሚን ኢትዮጵያን በተለይም የኢትዮጵያን መከላከያ ሚኒስቴር ሊጎበኙ በመምጣታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው በቆይታቸውም ወቅት የተለያዩ ተቋማትን እንዲጎበኙ ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸዋል።

ጄኔራል መኮንኑ ኢትዮጵያን መርጠው መምጣታቸው ትክክል መሆኑን ገልፀው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በሰላም ማስከበር እና በሌሎችም ግዳጆች የነበራቸው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑንና ለወዳጆቻቸው ፍቅር እና ክብር መስጠት የሚወዱ የተሰጣቸውን ግዳጅ በስኬታማነት የማጠናቀቅ የዓላማ ፅናት ያላቸው ጀግኖች ስለመሆናቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ 

ጉብኝቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሎጅስቲክስ አቅምን ለማሳደግ እና የጋራ ወታደራዊ እቅምን ለመገንባት ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ድምሩ ህሩይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
38👍15🔥9