FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.8K photos
36 videos
9 files
8.52K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ሆኑ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጥሩ ስም ካላቸው እና በድሬዳዋ ወንዶች ቡድን እንዲሁም በኢትዮ- ኤሌክትሪክ ሴቶች ቡድን ወጤታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻሉት ኢንስትራክተር እና አሰልጣኝ መሠረት ማኔ የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነዋል።

ባሳለፍነው አመት አምስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን በ2018 የውድድር አመት ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ከዋና አሰልጣኝ ጀምሮ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍8
ሠራዊቱ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚሞከርን ትንኮሳ መመከት በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል-        
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት ከየትኛውም አቅጣጫ የሚሞከርን ትንኮሳ መመከት በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ  የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

የማእከላዊ እዝ "በጠንካራ መሰረት ላይ ለላቀ ድል እንተጋለን" በሚል መሪ ሃሳብ ሲያካሂድ የቆየውን የተለያዩ ክንውኖች ማጠቃለያ መርሃ ግብር በጅማ አካሂዷል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ ሠራዊቱ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚሞከርን ትንኮሳ ለመመከት በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዋና ተልእኮ አገሩን መጠበቅ እና ሉዓላዊነትን ማስከበር በመሆኑ ለዚህም ሁል ጊዜ ዝግጁነቱ ተጠናክሮ  መቀጠሉን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያዊያን የጀግንነትና የአይበገሬነት ስነ-ልቦና ያለን ህዝቦች መሆናችንን ዓለም የሚያቀው እና ታሪክ የሚመሰክረው ሀቅ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ወደፊትም ሰራዊቱ ኢትዮጵያን ለማጽናት፤ እና ክብሯን ጠብቆ ለማቆየት ዛሬም እንደትናንቱ በአስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል። ማእከላዊ እዝም በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ሰላምን ከማስከበር ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክት መቆየቱን አስታውሰው እዙ አሁንም ዝግጁነቱን እያጠናከረ መሄድ አለበት ብለዋል።

አሁንም በየአካባቢው ታጥቀው የአገርን ሰላም እያወኩ የሚገኙ አካላት ወደ ሰላም መመለስ እንዳለባቸው ያሳሰቡት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ፥ ሰላም ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም አክለዋል።

የማእከላዊ እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፔሬሽናል ሜጀር ጀነራል አብድሮ ከድር፥ እዙ ስምሪት በሚያደርግበት ስፍራ ሁሉ በጀግንነት ተልእኮውን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በወለጋና አካባቢው የነበሩትን የጸጥታ ችግሮች ከአካባቢው ህዝብ ጋር በመቀናጀት ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልጸዋል።

እዙ የአካባቢውን ሰላም በማስከበር ረገድ ግዳጅን በላቀ ሁኔታ በመወጣት የተሳካ ስራ መስራቱን የበለጠ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

የእዙ አባላት ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በማህበራዊ አገልግሎት በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸው፥ በእዙ የተዘጋጁት የተለያዩ ኩነቶች ሰላምን እና ለህብረተሰቡ ህዝባዊ አብሮነትን ለማሳየት ታልሞ የተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢዜአ እንደዘገበው በመርሃ ግብሩ የማእከላዊ እዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና ሲቪል አመራሮች እንዲሁም የጅማ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
32👍16
የመከላከያ ሪፎርም ውጤት የሆነው ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ መሪዎች መፍለቂያና የውጤታማ ጥናቶች ምንጭ ሆኗል
‎   ኢንጂነር አይሻ መሃመድ

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ መከላከያ እየተገበረ በሚገኘው ሪፎርም በአዳዲስ መልክ የተመሠረተና በጥቂት ዓመታት ውስጥም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ተናግረዋል።

‎በኮሌጁ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ሚኒስትሯ ኮሌጁ ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ሚናና ውጤቶቹን የሚገልጽ መጽሃፍንና የኢትዮጵያ መከላከያ ስትራቴጂክ ጥናት ጆርናልን መርቀዋል።

‎የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራሮች መፍለቂ መሆን መቻሉን ያነሱት ሚኒስትሯ በኮሌጁ ሃገራዊ ፖሊሲዎች፣የፖሊሲ ሃሳቦችና መመሪያዎች ተሰንደው የሚወጡበት የልህቀት ማዕከል መሆን መቻሉንም ጠቁመዋል።

‎በኮሌጁ የሚሰነዱ ወሳኝ ምክረ - ሃሳቦች፣መጽሃፎችና ጆርናሎች በአግባቡ መተግበር እንዲችሉ አበክረን እንሰራለን ያሉት ኢንጅነር አይሻ "በጥናት ላይ የተመሠረቱ የኮሌጁ የዕውቀት መረጃዎች ለዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያበቃን ነው" ብለዋል

‎በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ኮሌጁ በተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እናም ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን መረዳት፣መተንተንና ከዚህም ተነስቶ ሰራዊቱን በአግባቡ ማዘጋጀት የሚችል ስትራቴጂክ አመራር የማፍራት ተልዕኮውን በስኬት ስለመወጣቱ ያነሱት ደግሞ የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ናቸው።

‎የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዲን ኮሎኔል ጥላሁን ደምሴ በበኩላቸው ኮሌጁ ባሳተማቸው ሁለቱ መፅሃፍትና ጆርናሎች ዝግጅት ላይ ሀገሪቱ ያፈራቻቸውን እና በተለያዩ የሙያ መስክ የተሠማሩ ምሁራንን ብሎም የቀድሞ ሰራዊት የላቁ ሞያተኞችን ማሳተፍ መቻሉ ለሀገር ፋይዳ ያላቸው ሀሳቦችን ማግኘት እንዳስቻለውና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አብራርተዋል።

‎በዓመቱ የስራ አፈጻጸም ለኮሌጁ ስራ መቃናት መልካም አበርክቶ ለነበራቸው የተለያዩ ሲቪል እና የመከላከያ ተቋማት ምስጋና የተቸረ ሲሆን የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ለኮሌጁ ሲቪልና የሠራዊት አባላትም ዕውቅና ተሰጥቷል።

‎ዘጋቢ አስቻለው ኛኙኬ
‎ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
35👏7👍6