በአሸባሪው የሸኔ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም
በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን በአሞሮ ወረዳ እና በኦሮ ቡልቅ ወረዳ አካባቢ የሽብር ስራውን ለመስራት ሲንቀሳቀስ በነበረው የአሸባሪው ሸኔ ላይ እርምጃ መውሰዱን የባሩድ ክፍለጦር አስታውቋል።
በምዕራብ ዕዝ የዋልታ ኮር ባሩድ ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል ተክኤ ሀይለ የሽብር ቡድኑ የህዝብን ሰላም ለማወክ ሲንቀሳቀስ ከህብረተሰቡ በደረሰን ጥቆማ መሰረት ድንገተኛ እርምጃ በመውሰድ ስምንት የቡድኑ አባላት ሲገደሉ ከአስር በላይ የማሆኑትን ቁስለኛ በማድረግ የያዘውን ስድስት ክላሽና የወገብ ትጥቆችን በቁጥጥር አውለናል ብለዋል። ዘጋቢ ወንድወሰን ፍቃዱ ነው
በተመሳሳይ በማዕከላዊ ዕዝ የአባይ ክፍለ ጦር የሰራዊት አባላት በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳያ ቢላ ወረዳ ሳዋና ሎጵ በተባሉ ቀበሌዎች ሁለቱ ሬጅመንቶች ባደረጉት የጋራ ስምሪት በሽብር ቡድኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረሳቸውን በማዕከላዊ ዕዝ የአባይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አባይነህ አስማማው ተናግረዋል።
በተደረገው ስምሪት በርካቶች ሲደመሰሱ 04 የሽብር ቡድኑ አባላት ተማርከዋል። ብሬን ፣ ስናይፐር ፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች እና በርካታ ተተኳሾች መማረካቸውን የሬጅመንት አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ዮሱፍ ከተማ ገልፀዋል ። ዘገባው የደረጀ ኤልያስ ነው
በተያያዘ በምዕራብ ሸዋ ዞን የ6ኛ ዕዝ ሉሲ ክፍለ ጦር አባላት የጥፋት እጁን በመዘርጋት ሠላምን አልቀበልም ባለው የሸኔ ቡድን ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካቶችን መደምሰስና ተተኳሾች መማረካቸውን የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ወንድሙ ሃብቴ ገልጸዋል።
ክፍለ ጦሩ በግንደ በረት ወረዳ በሼ ቀበሌ ባደረገው ስምሪትና በወሰደው እርምጃ ጅረኛ ወርቁ የተባለውን የሸኔ አመራር ከነ ስድስት ግብረ አበሮቹ ሲደመሰሱ ፣ 11 የቡድኑን አባላትና በርካታ ተተኳሾችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አዛዡ ገልጸዋል። ዘጋቢ ሰይድ አደም ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤58👍18🔥4🏆3👎2
ጤና ይሥጥልን ጥቂት ሥለጤናዎ ኮሌስትሮል እና የስኳር በሽታ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
ኮሌስትሮል ማለት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኝ ቅባት ነው። ሁለት አይነት ኮሌስትሮል አለ
High density lipoprotein(HDL-C) :ጥሩ የሚባለው ሲሆን
Low density Lipoprotein(LDL-C) :አደገኛ የሚባለው ነው
የስኳር በሽታ ጥሩ የሚባለውን ኮሌስትሮል በመቀነስ አደገኛ የሚባለውን ደሞ እንዲጨምር ያደርጋል። በተጨማሪም የስኳር በሽታ የደም ስሮችን ግርግዳ ያበላሻል። የተበላሸው የደም ስር ግድግዳ ላይ ደግሞ መጥፎ የሚባለው ኮሌስትሮል በመጣበቅ የደም ስሮች እንዲጠቡ ብሎም እንዲዘጉ ያደርጋል
በመሆኑም ይሄ ስብ የልብ ደምስርን በመዝጋት ድንገተኛ የሆነ ሞት ሊያስከትል ይችላል ወይም የአንጎል ደም ስርን በመዝጋት ከፍተኛ ችግር ያመጣል። ይሄንን ችግር ለመከላከል ስታቲን (Statins) የተባሉ ኮሊስትሮልን የሚቀንስ መድሃኒት መውሰድ ያስፈልጋል
ስለዚህ በተለይ እድሜያቸው ከ 40 ዓመት በላይ የሆኑ የስኳር ታማሚዎች ተመርምረው አደገኛ የሚባለው ኮሌስትሮል 70 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ስታቲን የተባለውን የቅባት መቀነሻ መድሃኒት መጀመር አለባቸው
እድሜያቸው ከ አርባ በላይ የሆኑ እና ስኳር የሌለባቸው ከሆነ ደሞ አደገኛው የኮሌስትሮል መጠን 70 እና ከዛ በላይ ከሆነ ሌሎች አደገኛ ነገሮች መኖራቸው ከተጣራ በኃላ የቅባት መቀነሻ መድሃኒት ስታቲን እንዲጀምሩ ይደረጋል
ስለዚህ ስኳር ግፊት የልብ ህመም እንዲሁም ስትሮክ ያለባቸው ሰዎች የኮሌስትሮል መጠናቸው ሊለካ ይገባል።

❤24🔥7👍4
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ሞ
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን በደቡብ ሱዳን የጃንግሌ ስቴት ፕሬዝዳንት ዶክተር ሪክ ጋይ ኮክ ገልፀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራር በዶክተር ጆን ጋራን መታሰቢያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ምረቃ ላይ በተገኙበት ዕለት ነው።
የደቡብ ሱዳን ህዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ከማድረግ አኳያ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሠራዊት በዩናሚስ ተልዕኮ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ሠራዊቱ በተለይ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ከማጠናከር ጋር ተያይዞ በሚሰራቸው ስራዎች በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ማገኘት ችሏል በማለት ገልፀዋል።
የ20ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ በበኩላቸው በቀጠናው በዩናሚስ የተሰጠንን ሰላም የማስከበር ተልዕኮን በብቃት የመወጣት ሂደታችንን አጠናክረን በመቀጠል ወዳጃችን ለሆኑት የደቡብ ሱዳን ህዝብ አለኝታነታችንን በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለንም ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት የሰላም አምባሳደር በመሆኑ ከተልዕኮው ባሻገር የሁለቱን ሃገራት ለዘመናት የቆየውን መልካም ወዳጅነት የሚያጠናክሩ ተግባራትን በስፋት አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት ኮሎኔል ሰጥየ አራጌ ተናግረዋል።
ዘጋቢ አንዋር ሁሴን
ፎቶ ግራፍ መብርሂት ገብረሚካኤል

❤30👏9👍6🔥2
"በመትከል ማንሰራራት" የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሠራዊት አባላት ዘንድ ቀጥሏል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የጦላይ የከፍተኛ ባለሌላ ማዕረግተኛ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አመራሮች አሰልጣኞችና ሰልጣኝ ምልምል ወታደሮች "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
መርሃ-ግብሩን የማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ጡምሲዶ ፊታሞ ችግኝ በመትከል ያስጀመሩ ሲሆን ሠራዊታችን የተሰጠው ተልዕኮ ሀገር መጠበቅ ቢሆንም ሀገራችንን ለማልማት እያሰለጠንን የአረንጓደ አሻራ ፖሊሲ ለማሳካት ችግኝ እየተከልን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል።
እንደሃገር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የሀገራችንን የደን ሽፋን ወደነበረበት ለመመለስ እያሳደገው ይገኛል ያሉት ዋና አዛዡ ችግኝ እየተከልን ያለነው የጎርፍ አደጋና ድርቅ እንዳይከሰት በመከላከል የሀገራችንን የተፈጥሮ ሀብት መንከባከብና አሻራችንን አሳርፈን መጭው ትውልድ የተሳካ ኢትዮጵያዊ ገፅታ ይዞ እንዲያድግ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ዘጋቢ ይትባረክ ፀዳሉ ነው
በተመሳሳይ የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል ግሩፕ እና የመከላከያ ዲያጎኖስቲክስ ማዕከል ማህበረሠብ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
የችግኝ መትከል መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የሆስፒታሉ ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ሸዋዬ ኃይሌ ዛሬ ላይ የምንተክላቸው ችግኞች ነገ በሀገራችን የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ለማሥቻል ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
የሆስፒታሉ የሰራዊት አማራር አባላት እና ሲቪል ሰራተኞች ከቢሾፍቱ የከተማ ልማትና ችግኝ ዘግጅት ቡድን ጋር በመተባበር የችግኝ መትከያ ቦታዎችን በማዘጋጀትና በእቅድ በማውጣት ሁሉንም ያሳተፈ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ማካሄዳቸውን ገልፀዋል።

❤37👍10🔥2
ኮሩ በሸኔ ላይ በወሰደው እርምጃ የቡድኑ አመራርና አባላት ተደመሰሱ።
የኢፊዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
የ6ኛ ዕዝ አንድ ኮር በሰሜን ሽዋ ዞን በደገም ወረዳ ሌሊሴ አሊደሮ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዋጁና ቀርሳ በተባለው ቦታ መሽጎ በማህበረሰቡ ላይ ዘረፋና ጉዳት ሲያደርስ በቆየው አሸባሪ የሸኔ ቡድን ላይ በተወሰደው ጠንካራ እርምጃ በርካታ የሸኔ አመራሮችና አባላት ሲደመሰሱ ተተኳሽና የጦር መሳሪያ መማረክ መቻሉን የኮሩ ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ ተናግረዋል።
ኮሎኔል ጋዲሳ ዲሮ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በቡድን ተደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ማህበረሰቡን በማገት እየገደለና እያስፈራራ ገንዘብና ንብረታቸውን እየቀማ መቆየቱን ገልፀው አሁን ላይ ኮሩ እየወሰደ ባለው ጠንካራ እርምጃ ሸኔ ከጥቅም ወጪ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
በተደረገው ዘመቻ ጃልገዳ ፣ጃል ቃንቄ እና ጃል ኦፍሳ የተባሉትን ጨምሮ በርካታ የቡድኑ አባላት ሲደመሰሱ መሣሪያና ተተኳሾች በቁጥጥር ስር ውሏል።
ዘጋቢ ውበቴ አማረ
ፎቶግራፍ አያልቅበት ገዛሃኝ

❤51👍23🔥1🏆1
የባህር ኃይል አመሰራረት ታሪክ በኢትዮጵያ
የኢፈዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም
በ1948 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሮያል የባህር ኃይል “የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የባህር ኃይል” የሚል ይፋዊ ስም ተሰጥቶት ቋሚ የጦር ሠፈሩን በምፅዋ ወደብ ላይ አቋቋመ።
በ1950 ዓ.ም ላይ ሦስት ተከታታይ ዓመታትን የፈጀው ታላቅ የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ሮያል የባህር ኃይል ከንጉሠ ነገሥቱ የምድር ጦር እና የአየር ኃይል በመቀጠል በኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ሥር በሦስተኛነት ተደመረ።
የኢትዮጵያ ሮያል የባህር ኃይል ታሪክ እንደሚያስረዳው ሲቋቋም ጀምሮ ዋና ግዳጁ የነበረው በቀይ ባህር ጠረፎች ላይ ቁጥጥርና አሰሣ የማድረግ ቋሚ የቅኝት ግዳጅ ሲሆን ዋና ማዘዣውን አዲስ አበባ እና ምፅዋ ላይ በማድረግ፣ በመጀመሪያ በክብር ዘበኛና የምድር ጦር ምክትል ዋና አዛዥ ሥር፣ በመቀጠልም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሆኑት በንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘ-ኢትዮጲያ ዋና የጦር አዛዥነት ሥር እንዲመራ ተደረገ።
የኢትዮጵያ ሮያል የባህር ኃይል በቆይታው ዘመን የናቫል መኮንኖች ማሰልጠኛ ኮሌጅ በአስመራ፣ የዳይቪንግ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በምፅዋ፣ የስፔሻል ኮማንዶ ዩኒት ማሠልጠኛ ኮሌጅ በምፅዋ፣ በአሰብ እና በአስመራ የባህር ኃይል የመገናኛና ጥገና ኮሌጅ በቀይ ባህር ዳህላክ ደሴት ላይ እንዲቋቋሙ ከማድረጉም በላይ በንጉሠ ነገሥቱ መልካም ፈቃድና ጥረት በዓለም ስመ-ጥር በሆኑት የሮያል ኖርዌጂያን የባህር ኃይል ኮሌጅ፣ የብሪትሽ ሮያል ባህር ኃይል ኮሌጅ፣ የጣሊያን ናቫል አካዳሚ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ናቫል አካዳሚ፣ የሶቭየት ናቫል አቪዬሽን፣ እና በሌሎችም ታዋቂ የባህር ኃይል መኮንኖች አካዳሚዎች የኢትዮጵያና የኤርትራ ተወላጆች በከፍተኛ ቁጥር እየተላኩ ትምህርት ቀስመው በአማካሪነት እና በአሠልጣኝነት ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን እንዲያገለግሉ አድርጓል።
በዛ ዘመንም ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀይ ባህር በኩል 1000 ኪ.ሜ የባህር በር የነበራት ሲሆን ከቀጠናውም አልፋ በአለም አቀፍ ደረጃ ገናናቷን ያስመሰከረች ሀገርም ነበረች። ነገር ግን በ1983 ዓ.ም የኢህአዴግ መንግሥት ለውጥ ሲያደርግ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል እንዲፈርስ ተደርጓል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአለማችን ሃያላን ሃገራትን ጨምሮ በርካታ የባህረ ሰላጤው ሃገራት በአፍሪካ ቀንድ (በቀይ ባህርና በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻዎች) የወደብ ግንባታ እና የወታደራዊ ጦር ሰፈር ምስረታ ፉክክር ውስጥ መግባታቸው ይታወቃል።
ሃገራችን ኢትዮጵያ በቀጠናው ያለው የሃገራቱ የጦር ሰፈር ምስረታና የወደብ ግንባታ እሽቅድድም ነገሮችን በጥሞና በመመልከት ለንግድ መርከቦቿ ደህንነት እና በአካባቢው ያለው ፉክክር ወደ ፊት ሊያመጣ የሚችለውን ማንኛውንም ተፅዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም እና የንግድ መርከቦቿን ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መንገድ ለማስጠበቅ በአዋጅ ቁጥር 1100/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ምንም የራሱ የሆነ የባህር በር ባይኖርም የመከላከያ ሃይሎች አካል ሆኖ ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።
የኢትዮጵያ ባህር ሃይል አሁን ላይ ራሱን በሚገባ በሰው ሃይል በመሠረተ ልማት በስልጠና እያደራጀ ጠንካራ እና መሠረት ያለው የሚሠጠውን ተልዕኮ መፈፀም በሚያስችል አግባብ ወደ ፊት መራመድ የቻለ ክፍል እየሆነ ነው።
በምትኩ ዘውዴ

❤67👍12🔥8🏆3