FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
39.5K subscribers
30.8K photos
36 videos
9 files
8.52K links
# ቁልፍ እሴቶች
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
Download Telegram
የመከላከያ ማርሽ ባንድ በጅማ ከተማ በመዘዋወር ትርኢት አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

‎ዕዙ ባለፉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎችን እየመከተ የመጣ ሲሆን አፈፃፀሙን ለመመልከት እያካሄደ ባለው ክብረ በዓል የፕሮግራሙ ድምቀት የሆነው ማርሽ ባንዱ በከተማው ንቅናቄ መፍጠር እና ህብረተሰቡ ሰላሙን ለመጠበቅ የበለጠ እንደመዘጋጅ ማድረግ መሆኑን የማዕከላዊ ዕዝ የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ሀላፊ ኮሎኔል ለችሳ መገርሳ አስረድተዋል።

‎ዕዙ ግዳጁን የሚዋጣው ህብረተሰቡን ይዞ በመሆኑ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር በሚል የተገነባበትን ተቋማዊ እሴት ተግባራዊ በማድረግ ነው ያሉት ከፍተኛ መኮንኑ ማዕከላዊ ዕዝ በተሰማራበት አካባቢ ህብረተሰቡ ሰላምን ለመጠበቅና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ግምባር ቀደም ተሰላፊ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ማርሽ ባንዱ በተዘዋወረበት ወቅት የከተማው ነዋሪዎች አብሮ በመንቀሳቀስ ትርዒቱን በማድመቅ እና ደስታቸውን በመግለፅ ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብር ገልፀዋል ።ዘጋቢ መሀመድ አህመድ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2613🔥3🥰2
ዕዙ ሀገር እንደ ሀገር በኩራት እንድትቀጥል ያስቻለ ጠንካራ ዕዝ ነው ።
        ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ዕዝ ዓመታዊ ክብረ በዓሉን እያካሄደ ነው። በዛሬው ዕለት በዋዜማው መርሃ-ግብር በዕዙ አዛዥ የተመራና ከሁሉም የዕዙ ክፍሎች የተውጣጡ የዕዙ የሠራዊት አመራርና አባላት የታደሙበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ከሰሜኑ ውጊያ ጀምሮ የነበረውን የዕዙን በርካታ ጥንካሬዎችና አንዳንድ እጥረቶች ያነሱት የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ ዕዙ ሀገር እንደ ሀገር በኩራት እንድትቀጥል ያስቻለ ዕዝ ነው ብለዋል።

የሠራዊቱና የተቋማችን ልኩ የኢትዮጵያና የህዝቦቿን ሉዓላዊነት ማስጠበቅና የመጨረሻ ምሽግ ሆኖ መዝለቅ ነው ያሉት ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ ማዕከላዊ ዕዝ በሰሜኑ ህግ ማስከበር ዘመቻም ይሁን በምዕራብ ኢትዮጵያ እያካሄደ ባለው የፀረ ሽምቅ ውጊያ የሀገርን ደህንነትና የህዝብን ሠላም ለማረጋገጥ የሠራቸውን አኩሪ ታሪኮች በማንሳት የዚህ ዕዝ አባል መሆን ያኮራል በቀጣይም ታሪካችንን ጠብቀን ማስቀጠል ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ዕዙ በመደበኛ ውጊያ የነበሩት ጥንካሬዎች አሁንም ተጠናክረው ቀጥለዋል ያሉት የዕዙ አዛዥ ሀገር በከፍተኛ ደረጃ የልማትና ዕድገት ማንሰራራት ላይ መሆኗንና ተቋማችን መከላከያም ሁለንተናዊ አቅሙን በእጅጉ እያሳደገ መሆኑን አብራርተው ማዕከላዊ ዕዝ በማንኛውም ሁኔታ ለሚሰጠው ተልዕኮና ግዳጅ በተሟላ አስተማማኝ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

በየደረጃው ያደረግናቸው ስልጠናዎች ለሁለንተናዊ አቅምና ጥንካሬያችን ወሳኝ ሚና ተጫውቷል በማለት  የተናገሩት ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ ከህዝባችን ጋር ተቀናጅተን የሰራናቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።

ዘጋቢ ዮሴፍ ጉርቢያው
ፎቶ ግራፍ ሲሳይ ጉርሜሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
28👍13🔥1
በፈተናዎች የማይበገር ጠንካራ ኃይል ተገንብቷል።
   ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ14 ቀን 2017 ዓ.ም

በፈተናዎች የማይበገር ጠንካራ ሠራዊት መገንባት ተችሏል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት መንግስትና ተቋማችን የሰጡንን ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በላቀ ብቃት በመወጣት የጠላቶቻችንን አንገት አስደፍተናል ብለዋል።

ከዘመኑ ጋር እየዘመነ የሚሄድ፣ስነ-ልቦናዊ ጥንካሬ ያለው ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገሩ ሲል ውድ ህይወቱን የሚከፍል ሁሌም በህገ-መንግስታዊ ዕምነቱ የፀና የመከላከያ ኃይል ተገንብቷል ብለዋል ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ።

እንደተቋም ወታደራዊ ዝግጁነታችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ደረጃ መጠናከሩና በየትኛውም ጊዜና ቦታ ተልዕኮን በጀግንነት መፈፀም የሚያስችል ብቃት መላበሳችን እንዲሁም ከባቢያዊና ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን ተረድቶ የሚዘጋጅና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችል ሁለንተናዊ  አቅም መፍጠራችን ለጠላቶቻችን ራስ ምታት ሆንባቸዋልም ብለዋል።

በጀግኖች መስዋዕትነት ፀንታ የቆየች ሀገር በእኛ ትውልድ አትደፈርም ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ መልማታችን የሚያማቸው፣ ዕድገታችን የሚያሰጋቸው ጠላቶቻችንን መቼም ቢሆን እንደማንታገሳቸው ጠንቅቀው ያውቁታል ሲሉ አንስተዋል።

ዕዙ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር አብረው ሀገር ለማተራመስ የተፍጨረጨሩ የውስጥና የውጪ ጠላቶቻችንን ሴራ አክሸፏል ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ የባንዳነት ተልዕኮን ያነገቡ ቅጥረኞች አከርካሪ ተሰብሯልም ነው ያሉት።

ዕዙ ውስብስብና አስቸጋሪ ግዳጆችን በፅናት ተወጥቷል ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በህገ-መንግስታዊ ዕምነቱ የፀና፤ ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብር የሚዋደቅ ብሎም ለመስዋዕትነት ዝግጁ የሆነ ኃይል የማፍራት ጥረቱን አመራሩ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባው አሳስበው የቀጣናችንን ሠላም በማረጋገጥ የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ያለአንዳች እንቅፋት እናስቀጥላልን ሲሉም ተናግረዋል።  ዘገባው የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍2118🔥1
ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን አሠልጣኝ ሆኑ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ጥሩ ስም ካላቸው እና በድሬዳዋ ወንዶች ቡድን እንዲሁም በኢትዮ- ኤሌክትሪክ ሴቶች ቡድን ወጤታማ ጊዜን ማሳለፍ የቻሉት ኢንስትራክተር እና አሰልጣኝ መሠረት ማኔ የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነዋል።

ባሳለፍነው አመት አምስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የመቻል ሴት እግር ኳስ ቡድን በ2018 የውድድር አመት ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ከዋና አሰልጣኝ ጀምሮ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። ዘጋቢ ገረመው ጨሬ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30👍8