በፅንፈኛው ቡድን ታግተው የነበሩ የመስኖ ፕሮጀክት ሰራተኞች ከታገቱበት ተለቀቁ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የምዕራብ ዕዝ የአድዋ ክፍለጦር ግለሰቦቹ በፅንፈኛው ከታገቱበት ጊዜ ጀምሮ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጥምር በመስራትና በአካባቢው ሰራዊቱን በማሰማራት ከታገቱ ከሶስት ቀናት በኋላ ማስለቀቅ ተችሏል።
የአድዋ ክፍለጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል አንተነህ ደጀኔ የሰላምና የዕድገት እንቅፋት የሆነው የፅንፈኛ ቡድን በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ በእንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ላይ ለአካባቢው የመስኖ ስራ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን አምስት የፕሮጀክት ሰራተኞች አግቶ ገንዘብ በመጠየቅ ሽብር የፈጠረ ቢሆንም በአካባቢው መከላከያ ሰራዊቱን በማሰማራትና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋርም በመመካከር ታጋቾቹን ካሉበት ቦታ ማስለቀቅ ተችሏል ብለዋል።
የሰራዊቱን ምት መቋቆቋም የተሳነው ይህ ዘራፊ ቡድን ንፁሃንን በማገት የማሰቃየት ተግባሩን የጀመረ ቢሆንም የሰላምን አማራጭ እንዲጠቀም የማድረግ ስራን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ሌተናል ኮሎኔል አንተነህ ደጀኔ።
ከታገቱት መካከል የፕሮጀክቱ ማናጀር የሆኑት አቶ እንዳለ አለምነህ የፅንፈኛው ቡድን አስተባባሪ የሆነው መልካሙ ጣሰው እየተባለ የሚጠራው ግለሰብ እንድትለቀቁ ከፈለጋችሁ ሶስት ሚሊዮን ብር አምጡ ያለበለዚያ እርምጃ ይወሰድባችኋል ካለ በኋላ በአካባቢው መከላከያ ሠራዊቱ እየንቀሳቀሰ መሆኑን ሲሰሙ እኛን ወደ ሀገር ሽማግሌዎች ሂዱ ብለው ለቀውናል ሲል ተናግሯል።
ዘጋቢ እሴት ደመቀ
ፎቶግራፍ ወንድወሰን ፍቃዱ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
❤38👍13
የናይጀሪያ ከፍተኛ መኮንኖች ለትምህርታዊ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ መከላከያ መጥተዋል፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
በአፍሪካ ደረጃ ጠንካራ ወታደራዊ የሎጅስቲክስ አመራሮችን በማፍራት ከሚታወቀው የናይጀሪያ ሎጂስቲክስ ኮሌጅ የመጡት ከፍተኛ መኮንኖች በየዓመቱ ለሚያደርጉት ዓለማቀፋዊ እና ወታደራዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን መርጠው መምጣታቸው ታውቋል፡፡
ወታደራዊ ልዑኩ ኢትዮጵያን መርጠው በመምጣታቸው የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ የኢትዮጵያን መከላከያን የላቀ የተልዕኮ አፈፃፀም እና ጦርነት የሚሸከም ሎጀስቲክስ በማደራጀት መምራት አንፃር ያለው ልምድ ከፍተኛ በመሆኑ ለተጠቃሹ ተቋማዊ ትምህርታዊ ጉብኝት ኢትዮጵያን መምረጣችሁ ብልህ መሆናችሁን የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እና ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ ወታደራዊ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ናይጀሪያ እና ኢትዮጵያ የቆየ ወታደራዊ ግንኙነት እንዳላቸው የተናገሩት ሜጀር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ ሀገራቱ በመከባበርና በመተባበር ላይ የተመሰረተ የጋራ ጥቅም መሰረት ያደረገ ግንኙት እንዳላቸው እና ጉብኝቱም ሰላም እና ፀጥታን እንዲሁም ወታደራዊ ልህቀትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
የልዑኩ መሪ ሜጀር ጀኔራል ኢቱክ ዋይስዶም ቤንጃሚን ኢትዮጵያን በተለይም የኢትዮጵያን መከላከያ ሚኒስቴር ሊጎበኙ በመምጣታቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀው በቆይታቸውም ወቅት የተለያዩ ተቋማትን እንዲጎበኙ ሁኔታዎች ተመቻችቶላቸዋል።
ጄኔራል መኮንኑ ኢትዮጵያን መርጠው መምጣታቸው ትክክል መሆኑን ገልፀው ከኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጋር በሰላም ማስከበር እና በሌሎችም ግዳጆች የነበራቸው ግንኙነት ጠንካራ መሆኑንና ለወዳጆቻቸው ፍቅር እና ክብር መስጠት የሚወዱ የተሰጣቸውን ግዳጅ በስኬታማነት የማጠናቀቅ የዓላማ ፅናት ያላቸው ጀግኖች ስለመሆናቸው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ጉብኝቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል የሎጅስቲክስ አቅምን ለማሳደግ እና የጋራ ወታደራዊ እቅምን ለመገንባት ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶግራፍ ድምሩ ህሩይ

❤38👍15🔥9
የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እና የሠራዊት አባላት በምስራቅ ሸዋ ዞን በሎሜ ወረዳ ችግኝ ተከሉ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በምስራቅ ሸዋ ዞን በለሚ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ- ግብር ተካሂዷል።
የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ዛሬ በአፈር ላይ የተከልነው ችግኝ ነገ የተስፋ ሀውልት ሆኖ ለጥላነት እና ለምግብነት ይውላል ብለን እናምናለን፤ ነገ የተሻለ እንደሆነ የሚያመላክት የአረንጓዴ አሻራ ፊርማችንም ይሆናል ብለዋል።
ዛሬ አፈር በነካው እጃችን የምንተክለው ችግኝ ነገ ለማንሰራራት እና ለመታደስ መሆኑን እርግጠኛ የምንሆነው ዛሬ የተከልናቸው ችግኞች ነገ ሺህ ቅርንጫፎች ሆነው ለጥላና ለፍሬ እንደሚበቁ ጥርጥር ስሌለለን ነው ያሉት ሚኒስትሯ ጥላ የሚሰጥ ዛፍ የሚተክለውን አይረሳም እንደሚባለው ዛሬ በዚህ የተገኘነው ሁሉ ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገር አሻራ እያስቀመጥን መሆኑን ለአፍታም መዘንጋት የለብንም ብለዋል።
በመትከል ማንሰራራት የዘንድሮው አረንጓደ አሻራ መሪ ቃል መሆኑን ጠቅሰው ለውጥ የሚመጣው እጅን አጣጥፎ በመቀመጥ ሳይሆን ጠንክሮ በመስራት እንደሆነ አመላክተዋል። ይህ ለውጥ እውን ይሆን ዘንድም እንደመከላከያ ከ18 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል የተያዘውን እቅድ ለመፈፀም በርትተው እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ
ፎቶ ግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

❤21👏14👍13
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ አመራርና አባላት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናወኑ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ "በመትከል ማንሰራራት" የሚለውን ሀገራዊ መሪ ሀሳብ መሰረት በማድረግ የዕዙ ዋና አዛዥ ፤ምክትል አዛዥ እንዲሁም የኮር እና ክፍለጦር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት "የሰራዊቱ መሪ ቃል በሆነው ከካምፓችን ወደ ህዝባችን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።
መርሃ-ግብሩን የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ችግኝ በመትከል ያስጀመሩ ሲሆን ሠራዊታችን የተሰጠውን ተልዕኮ እያስቀጠለ እንደሚገኝ በመግለፅ ዛሬ የምንተክላቸው ችግኞች ነገ በሀገራችን የተስተካከለ የአየር ንብረት እንዲኖር ከማሥቻልም በተጨማሪ ለምግብነት የሚያገለግሉ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለመትከል በመዘጋጀት ጭምር እንደሆነ ገልፀዋል። ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን ነው።

❤30👏9👍5