የመከላከያ ሪፎርም ውጤት የሆነው ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ መሪዎች መፍለቂያና የውጤታማ ጥናቶች ምንጭ ሆኗል
ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ መከላከያ እየተገበረ በሚገኘው ሪፎርም በአዳዲስ መልክ የተመሠረተና በጥቂት ዓመታት ውስጥም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ተናግረዋል።
በኮሌጁ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ማጠቃለያ ላይ የተገኙት ሚኒስትሯ ኮሌጁ ያዘጋጀውን የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ሚናና ውጤቶቹን የሚገልጽ መጽሃፍንና የኢትዮጵያ መከላከያ ስትራቴጂክ ጥናት ጆርናልን መርቀዋል።
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራሮች መፍለቂ መሆን መቻሉን ያነሱት ሚኒስትሯ በኮሌጁ ሃገራዊ ፖሊሲዎች፣የፖሊሲ ሃሳቦችና መመሪያዎች ተሰንደው የሚወጡበት የልህቀት ማዕከል መሆን መቻሉንም ጠቁመዋል።
በኮሌጁ የሚሰነዱ ወሳኝ ምክረ - ሃሳቦች፣መጽሃፎችና ጆርናሎች በአግባቡ መተግበር እንዲችሉ አበክረን እንሰራለን ያሉት ኢንጅነር አይሻ "በጥናት ላይ የተመሠረቱ የኮሌጁ የዕውቀት መረጃዎች ለዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነት የሚያበቃን ነው" ብለዋል
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ኮሌጁ በተቋሙ የተሰጠውን ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እናም ዓለማቀፋዊ ሁኔታዎችን መረዳት፣መተንተንና ከዚህም ተነስቶ ሰራዊቱን በአግባቡ ማዘጋጀት የሚችል ስትራቴጂክ አመራር የማፍራት ተልዕኮውን በስኬት ስለመወጣቱ ያነሱት ደግሞ የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ ናቸው።
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዲን ኮሎኔል ጥላሁን ደምሴ በበኩላቸው ኮሌጁ ባሳተማቸው ሁለቱ መፅሃፍትና ጆርናሎች ዝግጅት ላይ ሀገሪቱ ያፈራቻቸውን እና በተለያዩ የሙያ መስክ የተሠማሩ ምሁራንን ብሎም የቀድሞ ሰራዊት የላቁ ሞያተኞችን ማሳተፍ መቻሉ ለሀገር ፋይዳ ያላቸው ሀሳቦችን ማግኘት እንዳስቻለውና ይህንንም አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አብራርተዋል።
በዓመቱ የስራ አፈጻጸም ለኮሌጁ ስራ መቃናት መልካም አበርክቶ ለነበራቸው የተለያዩ ሲቪል እና የመከላከያ ተቋማት ምስጋና የተቸረ ሲሆን የላቀ የስራ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ለኮሌጁ ሲቪልና የሠራዊት አባላትም ዕውቅና ተሰጥቷል።
ዘጋቢ አስቻለው ኛኙኬ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

❤35👏7👍6
የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመከላከያ ክፍሎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ፣ በውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት እና በሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ክፍለ ጦር ተካሂዷል።
ሠራዊቱ የተሰጠውን ሃገራዊ ተልእኮ ከማሳካት ጎን ለጎን እንደሃገር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመሳተፍ የሀገራችንን የደን ሽፋን ለማሳደግ የተለያዩ የፍራፍሬና ሃገር በቀል ችግኞችን በመትከል ውብና አረንጓዴ ገጽታን የተላበሰች ሀገር ለመፍጠር እንደሚያስችል በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙ የሰራዊቱ አመራሮችና አባላትና ሲቪል ሰራተኞች ተናግረዋል።
በተያያዘም የሰሜን ምስራቅ ዕዝ የአንድ ክፍለ ጦር ሬጅመንት የሠራዊት አባላት ከዳውንት ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እና ከህዝቡ ጋር በመሆን ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሀገር በቀል ችግኝ ተክለዋል።
የዳውንት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ አያሌው መከላከያ ሠራዊቱ ከህዝብ አብራክ የወጣ መሆኑን ገልፀው፤ ከግዳጅ ጎን ለጎን በተለያዩ የልማትና የበጎ ስራ ላይ በንቃት እየተሳተፉ ስለሆነ ልትመሰገኑ ይገባል ብለዋል። ዘገባው የክፍሎች ነው

YouTube
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
# የመከላከያ ሠራዊት ቁልፍ እሴቶች፡-
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
1, ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ጥቅም፣
2, ምንጊዜም የተሟላ ስብዕና፣
3, ያልተሸራረፈ ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
4, በማንኛውም ግዳጅ ወይም ተግባር የላቀ ውጤት።
👍20❤15
የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ከሠራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዬ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
በምዕራብ ጎጃም የዞንና የወረዳ አመራሮች ከምዕራብ ዕዝ የኮር አመራሮች ጋር በዞኑ ስላለው ወቅታዊ የሠላምና ፀጥታ ዙሪያ በመወያየት የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አሥቀምጠዋል።
በምዕራብ ዕዝ የኮር ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል አዘዘው መኮነን ሠላሙን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ሠራዊቱ እያደረገ ያለውን ትግል የሲቪል አመራሩና ህብረተሰቡ እስከመጨረሻው ከጎኑ መቆምና መደገፍ እንደሚገባው ገልፀዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ እድሜአለም አንተነህ በበኩላቸው በዞኑ ቀጠና አጠቃላይ ስላለው የሠላም ሁኔታ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳሳወቁት ክልሉን ለማፍረስ እየሰራ ያለው ፅንፈኛ ቡድን እያስከተለ ያለውን የጥፋት ተግባራት ለማጥፋት የዞኑ ስራ አመራርና የፀጥታ አካላት ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጋር ቅንጁነት በመፍጠር አሁንም ያላሰለሰ ጥረት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
ዘጋቢ አብዲ ሁሴን
ፎቶ ግራፍ አብዲ ሁሴን

❤27👍15
የማዕከላዊ ዕዝ ክብረ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ማዕከላዊ ዕዝ የ5 ዓመታት የተልዕኮና ግዳጅ አፈፃፀሙን የሚያይበት ዓመታዊ ክብረ በዓል በጅማ ከተማ በተለያዩ ክንውኖች መካሄዱን ቀጥሏል።
በክብረ በዓሉ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ጀነራል ጌታቸው ጉዲና ፣ የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይን ጨምሮ የመከላከያና የዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጀነራል መኮንኖች የጅማ ዞንና የከተማው አሥተዳደሮች እንዲሁም ማህበረሰቡና የዕዙ የሠራዊት አባላት ሲገኙ የሰልፍ ትርኢትና የፎቶ አውደ ርዕይ እንዲሁም በርካታ ሁነቶች ተከናውነዋል።
በዕዙ አመራሮችና በመከላከያ ማርች ባንድ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የዕለቱ የክብር እንግዳ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃነ ጁላ ዕዙ ባለፉት ዓመታት በርካታ ግዳጆችን በአስተማማኝ ብቃትና በላቀ ድል ማጠናቀቁን ገልፀው ከአመራር እስከ አባል ይህን ላከናዎነው የዕዙ ሠራዊት ምስጋና አቅርበዋል።
በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የጂማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሃ ቀመር ማዕከላዊ ዕዝ በቀጠናው ሠላም እንዲሰፍን ሁለንተናዊ መስዋዕትነት በመክፈል ከህዝብና መስተዳድር ጋር ቅንጅት ፈጥሮ አስተማማኝ ሠላም እንዲሠፍን ሌት ተቀን እየተጋ ያለ የሃገር መከታ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲዬም ጅማሮውን ያደረገው መርሃ ግብሩ ከቀትር በኋላ በፓናል ውይይት መካሄዱን ቀጥሏል። ዘገባው የዕዙ ስነ-ልቦና ግንባታ ነው

❤22👍17👏1