ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
233K subscribers
290 photos
1 video
16 files
230 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት (ክፍል 15)
Join @Eyosc1 የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት

#ክፍል 15 - የፍቅር ታሪክ

ከሜሪ ፈለቀ
ትረካ በ ረድኤት ኃይሌ እና አማኑኤል አሻግሬ


-------ይቀጥላል-------                    

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት (ክፍል 16)
Join @ Eyosc1 የቴሌግራም ቻናል
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት

#ክፍል 16 - የፍቅር ታሪክ

ከሜሪ ፈለቀ
ትረካ በ ረድኤት ኃይሌ እና አማኑኤል አሻግሬ


-------ይቀጥላል-------                    

#መልካም ቀን ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት (ክፍል 17)
Join @Eyosc1 የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት እኔ የቀጠልኩት

#የመጨረሻው ክፍል 17 - የፍቅር ታሪክ

ከሜሪ ፈለቀ
ትረካ በ ረድኤት ኃይሌ እና አማኑኤል አሻግሬ


ተፈፀመ              

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
🤔አርቀህ ተመልከት ....... !

ከስህተት ለመታረም መስዋዕትነት መክፈል ይፈልጋል፡፡ ከባድ ስህተት ደግሞ ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል፡፡
እውነትን መቀበል መስዋዕት መክፈል ማለት ነው፡፡

የደን እሳቶች የሞቱ እንጨቶችን ያቃጥላሉ፤ እና በእንጨቶቹ ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮችን ወደ አፈርነት ይለውጣሉ። አንዳንዴ ግን እሳት የዛፉን ግንዶች ከማጥፋትም አልፎ አፈሩን ጥቅም ላይ እንዳይውል የማድረግ አቅም አለው፡፡

የእውነተኞቹ ድምፅ የሚያስተጋባው ጩኸት “የምፈልገው ነገር ሆኗል? አልሆነም! ስለዚህ አላማዬ ወይም አካሄዴ ስህተት ነበር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ የምማረው ነገር አለ፡፡” የሚል ሲሆን፣

ነገሮችን አርቆ ለመረዳት የማይፈልጉ ሰዎች አስተሳሰብ ደግሞ “የምፈልገው ነገር ሆኗል? አልሆነም! ስለዚህ ዓለም ኢ-ፍትሃዊ ነች፤ ሰዎች ቀናተኞች ናቸው፤ እና ለመረዳት የማይችሉ ደደብ ናቸው። የአንድ ነገር ወይም የሌላ ሰው ጥፋት ነው።” የሚል ነው፤

ይህ “እውነት የለሽ” ሰዎች የሚያስተጋቡት ድምጽ ነው፡፡

📗የሕይወት ቀመሮች መጽሐፍ!

#መልካም ቀን ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
💚ለውብ ቅዳሜ

🙏እግዜአብሔርን_ፍሪ
:
:
አምናለው አልክድም እጅጉን ታምሪያለሽ፤
ስሜትን የሚጭር ብዙ ነገር አለሽ።
:
:
ፀዳልሽ ያስፈራል ግርማሽ ነው የንግስት፤
ባይኔ ዞሮ አያውቅም እንዳንቺ አይነት እንስት።
:
:
ግና በኔ መስፈርት፤
በአምላክ ቃል መሰረት፤
ውበትም ሀሰት ነው ደምግባትም ከንቱ፤
ጌታዋን ምትፈራ በፅኑ በብርቱ፤
በፈሪሀ እግዚአብሔር ሰርክ ምትተጋ፤
ከቀይ ዕንቁ በላይ ተመን አላት ዋጋ።
ትመሰገናለች፤
ለባሏም ዘውድ ነች።


ቃሉ ያልገባቸው፤
ቁንጅናሽ ሰልቧቸው፤
ቁመናሽ ተብትቦ፤
ቀልባቸውን ስቦ፤
ማማርሽ ድር ሰርቶ በመልክሽ ተጠልፈው፤
ወንዶች ሲከጅሉሽ አየሁ ተሰልፈው።


እኔስ አይጠፋኝም ...
ውበት ማገር ሆኖት ቁመናም ምሰሶ፤
ተገንብቶ እንደሆን መልክ ተቀይሶ፤
የደበዘዘለት ማማር ከበርቻቻው፤
ዘመም ይላል ጎጆ ይናዳል ጉልቻው።


እናልሽ አንቺ ሴት ...
ለብቻው ሞግቶ እኔን ስላልጣለኝ
የውበትሽ ወጥመድ፤
በርግጥ ካፈቀርሺኝ ከሰው የተለየ
ለኔ ካለሽ መውደድ፤
እንደወይን ፍሬ ከትናንቱ ዛሬ
በስሎ እየጎመራ፤
ፍቅራችን ተባርኮ ለምልሞ እንዲያፈራ፤
እንድሸነፍልሽ እንዶንሽ ከከጀልሽ
እውነተኛ አፍቃሪ፤
መሽቀርቀሩ እንዳለ እግዜአብሔርን ፍሪ።

ሄኖክ_ብርሃኑ

#መልካም ቀን ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
የአንበሳውን አሟሟት ስናስተውል!

ጥያቄ፦ 'ባለግርማው አንበሳ እድሜው ሲገፍ በምን ይሞታል?'

መልስ፦  'በስቃይ'

የቱንም ያህል በእድሜ ቢቆይ  አንበሳ በመጨረሻ ዘመኑ መከራ ይበዛበታል፤ ታላቁ የጫካ ንጉሥ አሟሟቱ የከፋ ነው።

በጥንካሬው ጊዜ የሁሉ የበላይ በምግብ ሰንሰለቱ ጫፍ ላይ የነገሰው፣ ሌሎቹን አሳዶ የሚበላው፣ አንበሣ አሟሟቱ 'በርሀብ' ነው።

የሞተ የማይበላው፣ አድኖ የገደለውን በልቶ ሲጠግብ፣ የተረፈውን ፍርፋሪ ለጅቦች ይተው የነበረው፤ የጫካው ገዥ ግን እድሜው ደርሶ ሲያረጅ ማደን፣ መግደል ወይም መከላከል ይሳነዋል፤ እናም በጅቦች ጥግ ይቆማል፣ ከነርሱ እየተረፈውን ይበላል።

ሞት እስኪወስደው ድረስ በሞገሱ የሚያስፈራ የነበረው 'ማግሳቱ' ቀርቶ የጣር እና የሲቃ ጩኸት ይጮሀል።

በኃይል ጊዜው በክብር ሳያስደፍር ያቆየውን ግዛቱን ትቶ ይንከራተታል።

ይሄው ነው.... 'ህይወት አጭር ናት!'

የጉብዝናችን ወራት ያልፍል፣ ሀብት ጠፊ ነው፤ ጉልበት ይነጥፋል፤ የፈካው አካላዊ ውበት እንደ ጀንበር ጊዜውን ጠብቆ ይከስማል፣ በአንድወቅት የበላይ ብንሆን ጊዜው ሲደርስ  ደካሞች እና ለስቃይ የተጋለጠን እንሆናለን፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ አንድ ቀን ሁሉንም ለተረኛ አሳልፈን ሰጥተን እናልፋለን።


 ከሣሙኤል ተክለየሱስ 

#መልካም ቀን ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
💚ድሮ ድሮ ብሶት በወለደው በዘመነ ኢህአዴግ


👉ድሮ ድሮ ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ ለተመረቀ ልጃቸው በሬ አርደው የሚደግሱ ቤተሰቦች ነበሩ

👉ድሮ ድሮ ኑሮ ጥሩ ስለነበረ ህዝቡ ደረጄና ሀብቴ "ሙያሽ ይዘርዘርልሽ" እያሉ ሲዘፍኑ ሆዱን ይዞ ይስቅ ነበር


👉ድሮ ድሮ ወደደብረ ማርቆስ የሚጓዝ አውቶቡስ ውስጥ የታደለ ገመቹን የነቀምት አውቶቡስ ውስጥ የሰማኸኝ በለውን ዘፈን መስማት ኖርማል ነበር


👉ድሮ ድሮ ታመን ጤና ጣቢያ ስንሄድ ከመድኃኒቱ በፊት ወተትና ስጋ መመገብ እንዳትረሱ የሚል ማስጠንቀቂያ ይሰጠን ነበር


👉ድሮ ድሮ አንድ ሱፍ ለመስፋት 30 ሜትር ጨርቅ እንጠቀም ነበር


👉ድሮ ድሮ አዜብ መስፍን የተባሉ የቤት እመቤት ባለቤታቸው በሚከፈላቸው 7500 ብር ወርሃዊ ደመወዝ ድልቅቅ ብለው እንደሚኖሩ ከታይላንድ ጉብኛታቸው በዃላ ነግረውናል


👉ድሮ ድሮ የመንግስት ሰራተኛው በወርሃዊ ቁጠባ ኮንዶሚኒየም ይደርሰው ነበር


👉ድሮ ድሮ አርከበ እቁባይ የተባለ የብዙ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ህይወት የቀየረ ከንቲባ ነበረ


👉ድሮ ድሮ አበበ ተካ የሚባል ዘፋኝ የሆነች ቀሽት ዲያስፖራ አፍቀሮ "አለቅሳለሁ" የሚል ዘፈን አውጥቶ ሲያለቃቅስ ህዝቡ በጣም ስለተሰማው ገንዘብ ተሰብስቦ በአላሙዲን ድጋፍ አሜሪካ ሄዶ ልጅቷን እንዲያገኛት ተደርጓል


👉ድሮ ድሮ ኃይሌ ገብረስላሴ 5 ኪሜ ውድድር ሲያሸንፍ ህዝቡ ከኮተቤ ፒያሳ ድረስ 10 ኪሜ እየሮጠ ደስታውን ይገልፅ ነበር


👉ድሮ ድሮ ሰው ቤት ገብቶ መዘፍዘፊያ የሰረቀ ሌባ ፖሊስና ህብረተሰብ ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ ይወገዝ ነበር


👉ድሮ ድሮ ከሰል ለማያያዝ አንድ ሌትር ጋዝ የሚጠቀሙ እናቶች ነበሩ


👉ድሮ ድሮ ሀገሪቱ ውስጥ ከነበረው ህዝብ መካከል ስጋ በደንብ አያገኝም ተብሎ በፍለጋ የተገኘ አንድ አዛውንት አለቤ ሾው ላይ ቀርቦ ለ3 ዓመት ስጋ በነፃ እንዲወስድ ስሙን የረሳሁት ስጋ ቤት ቃል ገብቶላቸው ነበረ


👉ድሮ ድሮ ተኽላይ ደምቢዶሎ ውስጥ አራርሳ ባህርዳር ላይ ሆቴል ነበራቸው


👉ድሮ ድሮ ባለስልጣናትና አርቲስቶች የእግር ኳስ ግጥሚያ በህዝብ ፊት ያካሂዱ ነበር


👉ድሮ ድሮ "ምግብማ ሞልቷል አምላክ መች ነሳኝ" የሚል ዘፈን ነበር


👉ድሮ ድሮ ምግብ በተትረፈረፈበት ዘመን ከመመገባችን በፊት እጃችንን መታጠብ አንርሳ የሚል ተደጋጋሚ ማስታወቂያ ነበረ


👉ድሮ ድሮ የ4ኛ ክፍል መምህር ካዛንቺስ ተከራይቶ ይኖር ነበር


👉ድሮ ድሮ ማር ሲበዛ ይመራል የሚሉ ማር ያላቸው ወላጆች ነበሩን


👉ድሮ ድሮ የቀበሌያችን ሊቀመንበር ልጆች አብረውን ደጃዝማች ወንድይራድ ት/ቤት ይማሩ ነበር


👉ድሮ ድሮ መክሰስ የሚባል 10 ሰዓት ላይ የሚበላ ምግብ ነበረ😂

#መልካም ቀን ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
❤️የህይወት እስትንፋስ(The kiss of life)

ይህ ምስል የተነሳው በጋዜጠኛ ሮኮ ሞርቢቶ በ1967 ዓ.ም እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር ነው፡፡ ሮኮ ፎቶውን ያነሳው በጃክሰን ቪል ፍሎሬዳ ወደ ስራ እያመራ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ በጊዜው ሁለት የመብራት ሀይል ሰራተኞች የተለመደ ስራቸውን እየሰሩ በነበረበት ጊዜ ፎቶ ማንሳት ፈልጎ ካሜራውን ከቦርሳው እያወጣ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ጩኸት ይሰማል፡፡ ከላይ ሲጠግን የነበረው ራንዳል ጂ ቻምፒዮን በኤሌክትሪክ መብራት ይያዛል፡፡ ከዚያም አብሮት ሲሰራ የነበረው ቶምሰን አንድ መላ ይዘይዳል፡፡ ይህም በእጁ ደረቱን በመምታት(CPR) ቦታው ባይመቸው አፉን በአፉ በማስጠጋት የእርዳታ ሠራተኞች እስኪመጡ ድረስ የስራ ባልደረባውን ይህወት ማዳን ችሏል፡፡ ጋዜጠኛ ሮኮ ሞርቢቶም ሁነቱን በካሜራው ማስቀረት ችሏል፡፡ በዚህ ምስልም 1968 እ.ኤ.አ Pulitzer Prize for Spot News Photography ማሸነፍ ችሏል፡፡ ምስሉም የህይወት እስትንፋስ(The kiss of life) ተብሎ ይጠራል፡፡

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😳ሰው ወደ አምላክነት ሲያድግ (Homo deus)

🤔የሃይማኖት አባቶች ስለ AI ምን እያሉ ይሆን?


የሰው ልጅ የነበረውንሃይማኖት ወደ ቴክኖ-ሃይማኖቶች (techno religious) ይቀይራል! ሞትም ሊቀር የሚችል ቴክኒካዊ ችግር ነው...ይለናል ዮቫል ኖህ ሀራሬ! የዮቫል ኖህ ሃራሬ ሦስቱም መጽሐፎቹ ማለትም ሳፒያንስ ፣ 21 lessons for the 21st century እና homo deus ከምርጥ መጽሐፍቶች ከፊት የሚቀመጡ አንቂ መጻሕፍቶች ናቸው ። ሀራሬ ራሱን እንደ አንድ ልእለ ሰብእ በማሰብ ለመላ የሰው ልጆች በዝግመተ ለውጥ የሚመጣውን ያደገውን ኃያሉን የሰው ዘር ጠባይ እየነገረን ይገኛል። የሰው ልጅን ተስፋና ሥጋቶችንም በምርጥ ትንታኔው እየነገረን ነው።

ይኸ በAI (Artificial intelligence) የሚታገዘው የሰው ዘር አጠቃላይ የኑሮ ዘይቤው ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀየርና የሚያመልከውም ሃይማኖት ቴክኖ-ሰዋዊነት እና ማእከላዊ የመረጃ እምነት እንደሆነ በዝርዝር ይተነትናል ። እውን እሱ እንደሚለው አሁን ላይ ያሉ ሃይማኖቶች ሙሉ ለሙሉ ወደ ተረትነት ይቀየሩ ይሆን ? እርሱን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው።

አስደንጋጩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት(Artificial intelegent) ርቀትና ምጥቀት የማን ፈቃድና ሥራ ነው? ፈጣሪ በዚህ ለእኛ አስደንጋጭ በሆነው የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ላይ ያለው ፈቃድ ምን ይሆን? የሥነ መለኮት ጠበብት ስለ AI ምን ይላሉ? AI (ሰው ሰራሽ አስተውለቶችና ) ልውጥ የሰው ዘረመል በሚፈጥሩት ኅብረታዊ ተአምር ሌላ ዓለምና ሌላ ፍጥረት ሕልው ሊሆን ይችላል። አሁን ላይ በምዕራባውያን እየተተገበረ ያለው የዘረ መል ምህንድስናና የአርቴፌሻል ኢንተሊጀንስ ተአምር ምናልባትም ሀራሬ እንዳለው አሮጌው ሰው (Homo sapience) ሞቶ አዲሱ ሰው Homo deus ሊመጣ ይችላል። የዮቫል ኖህ ሀራሬ መጽሐፍ ሰዎችን በማንቃት ደረጃ ከፍተኛ ጥቅም ቢኖረውም የሃይማኖት ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች አይመከርም!

#እውን ሞት ሊቀር ይችላልን??

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎እውነት ምንድን ነው

በአንድ መንደር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አይነስውሮች ነበሩ። ታዲያ እነዚህ አይነ ስውሮች በአካባቢያቸው ስለሚኖሩ ዝሆኖች ሲነገር ይሰሙ ነበርና ዝሆን ምን አይነት እንደሆነ ለማወቅ ፈልገው በአቅራቢያቸው ወዳሉት ዝሆኖች ይሄዳሉ።
እዚያም እንደደረሱ አንደኛው እግሩን ይነካና ይኸ ምሰሶ ይመስላል አለ። ሁለተኛው ወይኔ ኧረ ገመድ ነው አለ ጭራውን የነካው። ሶስተኛው ኩንቢውን ነክቶ ቧንቧ ነው የሚመስለው አለ። አራተኛው ደግሞ ትልቅ ማራገቢያ ነው አለ ጆሮውን የነካው። አምስተኛው ሆዱን ነክቶ ግንብ ነው የሚመስለው አለ።
አንድ ሰው በአጋጣሚ ሲያልፍ ክርክራቸውን ሰምቶ ምን እንደሆኑ ይጠይቃል? እነሱም ዝሆን ምን እንደሚመስል ለማወቅ እንደፈለጉና የየራሳቸውን ግምት ይነግሩታል። ሰውዬውም ነገሩ ይገባውና እንዲህ አላቸው፦
ሁላችሁም ያላችሁት ትክክል ነው። ምክንያቱም ስትነኩት የነበረው የዝሆኑን ሰውነት ነበርና አላቸው። ከዚያም ሁሉም የአሸናፊነት ስሜት ተሰምቷቸው ክርክራቸውን አቆሙ።
. . . ብዙ ጊዜ እውነት በአንጻራዊነት ከራስ አመለካከት ጋር የተያያዘ በመሆኑ እውነት ያለችው ከእኔ ጋር ብቻ ነው አትበል ከሌሎቹ በኩልም ያለውን እውነታ ተቀበል።የሌሎችን አመለካከት አክብር።

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት
     
@Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ @Eyos18 አድርሱን
   
    📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
💚ለቅዳሜያችኝ📕

የስምንት ዓመቱ ብላቴና ከታናሽ እህቱ ጋር የቀለጠ የገበያ ማዕከል ውስጥ ብቻቸውን ወዲህና ወዲያ በእግራቸው እየተንሸራሸሩ ነበሩ።ብዙ ከተንሸራሸሩ በኋላም ትንሿ እህቱ አንድ ሱቅ መስኮት ላይ ቆም አለች።እህቱ ወደ ኋላ መቅረቷን ያስተዋለው ታላቅየው ወንድሟ ወደ ኋላው መለስ ይልና ምን ወደ ኋላ እንዳስቀራት ተመለከተ።ቀልቧን የሰረቀው ነገር ምን
እንደሆነም ወዲያው ገባው።እህቱ እንዲያ በተመስጦ የምታየው በሱቁ ውስጥ ያለውን የሚሸጥ አሻንጉሊት እንደሆነ ለመረዳት ቅጽበት እንኳ ጊዜ አልወሰደበትም።
ብላቴናው እህቱ አሻንጉሊቱን በርግጠኝነት መፈለጓን መረዳቱን በሚያሳይ መልኩ“ ምን የሆነ የምትፈልጊው ነገር አለ ?”ሲል ጠየቃት።እህትየውም ምን እንደምትፈልግ ዓይኗን ከሱቁ መስኮት ላይ ሳታነሳ በእጇ አሻንጉሊቷን በመጠቆም አሳየችው።ብላቴናውም አሻንጉሊቷን ዐየት አደርጎ እንደ ቁምነገረኛ ታላቅ ወንድም እህቱን በእጇ ይዞ ወደ ሱቁ ይዟት ገባ።ከመደርደሪያው ላይ ፍጹም በሆነ በራስ መተማመን መንፈስ አንሥቶ ለእህቱ አሻንጉሊቱን ሰጣት ። እህትየው ወንድሟን ቀና ብላ ዐየችውና ፈገግ አለች።በጣም መደሰቷን ከፊቷ ላይ ማንበብ ይቻላል።ባለሱቁ ይህ ሁሉ ሲሆን ከመጀመሪያው ጀምሮ በጥንቃቄ እያንዳንዷን ነገር እየተመለከተ ነበር።በዚህ ልጅ ሁኔታ በጣም ተገርሟል።
እህቱ በመደሰቷ የረካው ትንሹ ልጅ ወደ ሱቁ ሒሳብ መክፈያ ሣጥን መጣን ባለሱቁን ኮራ ብሎ “ጋሼ፣ የዚህ አሻንጉሊት ዋጋ ስንት ነው?”ሲል ጠየቀ።ይህ ባለሱቅ እንደ ዕድል ሆኖ ፍጹም ደግ ሰው ነበረና...የነዚህን ወንድምና እህት ፍቅር በማየት ልቡ በርህራሄ ቀለጠ።ረጋ ባለ ድምፀት ቀስ ብሎ ለትንሹ ገራሚ ልጅ “ ስንት መክፈል ትፈልጋለህ ?” ሲል ጠየቀው። ልጁ ምንም ገንዘብ እንዳልያዘ ያው የታወቀ ነው።ግን ከባሕሩ ዳርቻ የለቃቀማቸውን የቀንድ አውጣ ቅርፊቶች በኪሱ ይዞ ነበር።
እህቱ ለወሰደችው አሻንጉሊት ሒሳቡን ለመክፈል ሁሉንም የቀንድ አውጣ ቅርፊት ከኪሱ አወጣና ለባለ ሱቁ ተንጠራርቶ ጠረጴዛው ላይ ዘረገፈለት።ባለሱቁም የእውነት ገንዘብ የተከፈለው ይመስል ቅርፊቶቹን አንድ ባንድ እያነሳ ቆጠራቸው።ቆጥሮ ሲጨርስም ሕፃኑን ልጅ ቀና ብሎ ዐየው፣ ልጁም እንደ መጨነቅ አለና “ ምነው አይበቃም?”ሲል በፍራቻ ጠየቀው።የልጁን ጭንቀት ያስተዋለው ባለሱቅ “ኧረ እንዲያውም…የሰጠኸኝ ከዋጋው በላይ ነው።ስለዚህ ትርፉን እንካ መልሼ ልሃለሁ ያንተ ነው ያዘው” አለው።እንዲህ ብሎ መልሶለት ለራሱ ያስቀረው ዐራት የቀንድ አውጣ ቅርፊት ብቻ ነበር።ብላቴናው በጣም ተደሰተና ከትንሿ እህቱ ጋር አመስግኖ ከሱቁ ወጥቶ ሔደ።ከባለሱቁ ጋር የሚሠራ ሌላ ተቀጣሪ ሠራተኛ ባለሱቁ እየሠራ ያለውን ሥራ እየተከታተለ ነበርና በነገሩ በጣም ተገረመ።
ወደ ባለሱቁ ጠጋ አለና “ አለቃ! ያን የመሰለ ውድ አሻንጉሊት
እንዴት በዐራት የቀንድ አውጣ ቅርፊት ትለውጣለህ ?”ሲል ጠየቀው።ባለሱቁ ፈገግ ብሎ ለሠራተኛው “እንዴት መሰለህ፣ እነዚህ ለኛ የማይረቡ የቀንድ አውጣ ቅርፊቶች ናቸው።
ግን ለዚያ ትንሽዬ ልጅ ከምንም በላይ ውድ ነገር ናቸው።
እና በዚህ ዕድሜው፣ ገንዘብ ምን ማለት እንደሆነ አይገባውም ።ሆኖም ሲያድግ የገንዘብ ትርጉም ምን እንደሆነ ያኔ
ያውቃል።በገንዘብ ሳይሆን በቀንድ አውጣ ቅርፊት አሻንጉሊት እንደገዛ ትዝ ያለው ቀን እኔን ያስበኛል።ይህችም ዓለም በቀና ሰዎች የተሞላች ስለመሆኗ ያስባል።በዚህም ቀና አመለካከት በውስጡ እንዲያጎለብትና ጥሩ ሰው ለመሆን እንዲችል ይበረታታል።”

💚ውብ ቅዳሜ

#መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📗እንዲ ነው እንግዲ👁

ቢገባንም ባይገባንም _የገባን መስለናል
ሁሉን ተቀብለን_ መኖር ጀምረናል
እንዲ ነውም ሲሉን_ ይሁን ይሁን ብለን
ትልቅ ተመኝተን _ትንሽ ተቀብለን
እውነት የሚመስል_ውሸት መኖር ለመድን።
👁ምን ታደርገዋለህ......
ባዘመመች ጎጆ በተንገዳገደች
እንኳን አንተንና እራሷን በረሳች
መኖር ይሉት ትርጉም ግራው እንደገባ'
ከምድር ከሰማዩ ፍፁም ሳትግባባ
ቀናት ይቆጠራል አመት ይተካካል
ስንቅ አድርገህ ይዘህ ያልፋል የሚልን ቃል!
👁ግን የታለ....
የተስፋ ዳቦህን ዛሬም ትገምጣለህ
ጊዜ ላጎፈረው ታበጣጥራልህ!
በታፈነች ጎጆ ጥላት በወረሳት
ለታይታ ብርሃን ከውጭ ቢያለብሷት
ያጎበጠ አካሏ ቀና አይል በውሸት
ከእግር እስከ እራሷ ወገሻ ካላያት!
እንደው ያልገባትን ገብቶሻል እያሉ
አሳብ ያወርዳሉ አሳብ ይጭናሉ።
እንጂማ አጥግቦ ማን ያሳድርና
ሁሉ ቃል የሚሰጥ በገናለገና።
👁ይኽው ሲሰለቸን
ባይገባንም እንኳ የገባን መስለናል
ሁሉን ተቀብለን መኖር ጀምረናል
ለመተንፈስ ያክል አለው ለማለቱ
የተሰጠን ቦታ ይበቃል መሬቱ ።
እስክንወድቅ ድረስ አፈር እስኪነካን
የገባን መስለናል ቢገባን ባይገባን...

#መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
❤️ከል ጅነት ጣፋጭ ትዝታ
ስለመጽሐፍ አንዲት ጠብታ…

ጊዜው ልክ እንዳ'ሁኑ የክረምት ወቅት ነበር ።(ግን ደስ የሚል ክረምት)

ትዝ ይለኛል ገና የሦስተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ ።
ልክ የዓመቱ የትምህርት ጊዜ ተጠናቅቆ ትምህርት ቤት ሲዘጋ ለዕረፍት ዘመድ ጋ ተላኩ።
(አቤት ያኔ ለዕረፍት ዘመድ ቤት መሄድ እንዴት ብርቅ እንደነበር)

አስታውሳለሁ በቆይታ ጊዜዬ ቤት ውስጥ ካሉት ውብ ነገሮች ሁሉ በላይ ዐይኖቼን ማርከው የሚያስቀሩት የግድግዳውን ግማሽ ጎን በሸፈነው መደርደሪያ ላይ በሥርዓት የተደረደሩት መጻሕፍት ርዕሶች ነበሩ።

ብዙዎቹ አሁንም ርዕሳቸው የትላንት ያህል ትዝ ይለኛል…

"አምሳል " "ዳር እስከ ዳር " "እምባ እና ሳቅ " " ያልተመለሰው ባቡር" "እምዩ " "አንድ ለእናቱ" "ቋሳ" "ጥቁር ደም " " ወንጀለኛው ዳኛ" " የሕልም ዣት" "ፍቅር እስከ መቃብር" " እንደወጣች ቀረች" "ሳባ እና በፍቅር ያበደው " "ሀዲስ" "ከአድማስ ባሻገር" "የተከፋፈለ ልብ" "የተሸጠው ሠይጣን" "የወዲያ ነሽ" "ጉንጉን" "ሰመመን" "የቅናት ዛር" "ሕያው ፍቅር" "ሙሉ ልብስ" "የተወጋ ልብ" "ዶሰኛው" "የወይራ ስር" "ሀኖስ" "ሙሽራው" "ማዕበል" "አልወለድም" "ነገም ሌላ ቀን ነው" "ካፖርቱ " "አስኳል" "የጣ ፈለግ" "የውበት ወጥመድ" "ብርቅርቅታ" "ምንዱባን" "እፎይታ" "ሳቤላ" "ሽማግሌው እና ባህሩ" "እናት" "የናስሮዲን ቀልድ ቀመስ ቁምነገሮች" "ፀጉራማዋ ልጃገረድ" "ፍካት"
እና ሌሎችም…

በር'ግጥ እንዳነብ የተፈቀደልኝ የቀልድ እና የተረት መጽሐፎችን ብቻ ቢሆንም እኔ ግን አሳቻ ሰዓት እየጠበቅኩም ቢሆን እነዛን የማረኩኝን መጻሕፍት አንድ ባ'ንድ አነበብኳቸው።

እንዲሁ የቃላት ላይ ሩጫ ቢሆንብኝም፣ ጭብጣቸውን ባልረዳም፣ ታሪካቸው ባይገባኝም ወደድኳቸው።
ገፀ-ባሕርያቱም እንዳይጠፉ ሆነው በውስጤ ተስለው ቀሩ።

ዓመታት አለፉ…

ለመጽሐፍ ያለኝም ፍቅር ሥር ሰደደ…
ከማንነቴ ተዋሃደ…
ከፍላጎቴ ተዛመደ።

ያኔ ያነበብኳቸውን አብዛኛዎቹን መጽሐፎች በመረዳት እና በማስተዋል ደግሜ አነበብኳቸው፤ እናም ደግሜ ወደድኳቸው።

ጥቂቶቹን ግን ሳላገኛቸው ቀረሁ።
ከጥቂቶቹ አንዱ ደግሞ እስካሁንም ፈጽሞ ልረሳው ያልቻልኩት ሆነ።

ፈለግኩት አስፈለግኩት እሱ ግን የለም።

ይሄ የልጅነት ትዝታዬ ውስጥ ታትሞ የቀረው የኔ ተወዳጅ መጽሐፍ የታላቁ አሜሪካዊ ደራሲ የሲድኒ ሸልደን ድንቅ ስራ የሆነው "የጣ ፈለግ " ነበር።

በሀገራችን ቋንቋ የተተረጎሙትን የሲድኒ ሸልደንን በርካታ ድንቅ ድንቅ ሥራዎች አንብቤ ተደንቂያለሁ። ተደምሚያለሁ። ተደስቻለሁ።

መቼም "ፍቅር ሞገደኛው" 'ከፃዕረ ሞት ጋር ትንቅንቅ" "በሬ ካራጁ" "ፍዳ" "የፍርድ ቀን ዘመቻ" "ሕልምሽን ንገሪኝ" "ታዳኟ ልዕልት" " መዘዝ" "ከእሳት የወጣች ነፍስ" "ማለዳ፣ ቀትር እና ምሽት" የምረሳቸው አይደሉም።

ለዚህኛዉ ያለኝ ፍቅር ግን የተለየ ነበር።

ታዲያ ይሄን የኔ ተዓምረኛ መጽሐፍ ባለፉት ቀናቶች የአሮጌ መጽሐፎች ማደሻ እና መሸጫ ቦታዎች (ስንቴ ሄጄ እንዳጣሁትኮ) በተዳሰሱበት በአንድ የቲቪ ፕሮግራም ላይ አይቼው እንቅልፍ አጥቼ አደርኩ።

ሲነጋ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ።
ከደስታዬ ብዛት እጄን ባፌ ላይ ጫንኩ።

ገና በማለዳ ይሄን ለኔ ልዩ የሆነውን መጽሐፍ ለኔ ልዩ ከሆነ ሰው ስጦታ ሆኖ ተሰጠኝ።
(ለምን የፈለገ ብር አይሆንም ሄጄ እገዛዋለሁ ስል ነበር ያደርኩት)

ደሞ ታድዬ የመጀመሪያው እትም ነው።
በጣም ይገርማል ያኔ የመሸጫ ዋጋው 9.00 የኢት. ብር ብቻ ነበር።
ለካ "መጽሐፎች ከሚተመንላቸው ዋጋ በላይ ናቸው፤ የምንከፍለው ለሀሳቡ ሳይሆን ለወረቀቱ ብቻ ነው" የሚባለው እውነት ነው።

ወዲያው የመጀመሪያውን ገጽ ገልጬ አየሁት። እራሱ ነው፤ "ጃይሜ ማይሮ"
የዋና ገጸ-ባሕርዩን ስም አልረሳሁትም ነበር።

ይኸው ሳምንት አለፈኝ፤ ያልቅብኛል ብዬ መጀመር ፈርቻለሁ።
(አንዴ ከጀመርኩት ሳልጨርሰው አላስቀምጠውማ)

እስኪ እናንተም በልጅነታችሁ አንብባችሁ ስለወደዳችሁትና ስለማትረሱት፤ ወይ ደግሞ እንደኔ ልታነቡ ፈልጋችሁ ስላጣችሁት መጽሐፍ አጫውቱኝ።
(ርዕሳቸውን ንገሩኝ)


#መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
#ራስን መቆጣጠር---

በጥበበኞች ዓይን ከኃይለኛ ዝሆን ጋር የሚፋለም ሰው ጀግና አይባልም።እንደ እውነቱ ከሆነ ጀግና ማለት በተናደደ ጊዜ ራሱን የሚቆጣጠርና ክፉ የማይናገር ሰው ነው።
ሰዎችን መጠየቅ ምንም ጉዳት የለውም።ጉዳት የሚኖረው ሰዎች ሰልችተው በቃ እስኪሉ መመላለስ ነው።ራስክን መቆጣጠር የቻልክ እንደሆነ ከሌሎች ወቀሳ አይደርስብህም።

#መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
😎አንተ ማለት ሁለት ሰው ነህ!(You are double standard)


የዘመኑ ሰው ማንነቱ በቀላሉ አይታወቅም፡፡ እከሌ እንደዚህ ነው ብሎ ደፍሮ መናገር አይቻልም፡፡ ደፍሮ የሚናገርም ካለ አላዋቂ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አንደኛ ሰው ማንነቱን በሙላት አይገልጥም፡፡ ሁለተኛ አንዳንድ ሰው እሱነቱን ለሌላው ሲያሳይ እውነተኛ ማንነቱን ሊደብቅ ይችላል፡፡ ሶስተኛ የሰው ልጅ ሁልጊዜ በለውጥ መንገድ በመሆኑና በየጊዜው ሃሳቡን ስለሚለዋወጥ እንዲህ ነህ ተብሎ አይደመደምም፡፡ ብዙ ሰው ቅቡን እንጂ ወርቁን እሱነቱን ለሰው አያሳይም፡፡ አብዛኛው ከሰው ጋር ለመመሳሰል ሲል የሚጠላውን ያደንቃል፤ የሚወደውን ያወግዛል፡፡ ብዙ ሰው የሚወደውንና የሚፈልገውን ነገር አያደርግም፡፡ ውሥጡ የሚመኘውን በተግባር የሚገልጥ በጣም ኢምንት ነው፡፡ ራሱን የሚመስል ሳይሆን ከሌላው ጋር ለመመሳሰል የሚታገል ሰው ነው የሚበዛው፡፡ አዎ ቅዱስ ጳውሎስ፡- ‹‹የምወደውን አላደርገውም፡ የማልወደውን ግን አደርገዋለው፡፡›› እንዳለው ነው፡፡

ስለሰው የምታስበውን፣ ስለዓለም የተረዳኸውን፣ ስለራስህ የደረስክበትን መግለጥ ከተቸገርክ፣ መኖር በምትፈልገው መንገድና ውስጥህ በተቀበለው እውነት ሕይወትህን ለመምራት የአዕምሮ አቅም ካጣህ ከራስህ ጋር ተለያይተሃል ማለት ነው፡፡ ፊትህና ውስጥህ የማይገናኝ፤ ተግባርህና ቃልህ ለየቅል ከሆነ ከአንተነትህ በብዙ ማይል ርቀሃል ማለት ነው፡፡ የሚሰማህን ስሜት ካዳፈንክ፣ ውስጥህ የሚተራመሰውን እውነት ከደበቅክ አንተነትህ ጭምብል ለብሷል ማለት ነው፡፡ ለሰው የምታሳየው ማንነትህ ቅብ ከሆነ ፎርሸሃል ማለት ነው፡፡ ሰው ደስ እንዲለው ብለህ በማያስደስትህና ፈገግታ በማያጭረው ሁሉ ከገለፈጥክ በውሸት ሳቅ የተሸፈነ ማንነት ነው ይዘህ የምትዞረው ማለት ነው፡፡ ለማትወደው ልማድ ባሪያ ከሆንክ ትክክለኛው አንተነትህን አስረኸው ነው የምትንቀሳቀሰው ማለት ነው፡፡ ሕሊናህን ጥለህ፤ ልባዊ ምኞትህን ደፍጥጠህ፣ ውስጥህን አፍነህ፣ ሀቅህን ረግጠህ፣ እውነትህን ክደህ የምትኖር ከሆነ ቀይ እያበራህ ነው፡፡ በቃ አንተ ማለት ሁለት ሰው ነህ፡፡ አንዱ ውስጥህ፣ ህሊናህ፣ ልብህ፣ ነፍስህ የሚያውቀው፤ ሌላው ለሌሎች የምታሳየው ፌኩ አንተነትህ ነው፡፡ እናም ያንተ ትክክለኛ ማንነት ሰው የሚያውቀው አይደለም፡፡ እውነተኛው አንተ ማለት ለሌላ ሰው ያልገለጥከውንና የደበቅከውን ነህ!!

አንድ ተማሪ ወደአንድ ጠቢብ ሰው ሄዶ እንዲህ ብሎ ጠየቀ፡-

‹‹ሰው ሁሉ እኩል ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ ታላቅና የተከበረ ሰው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ለምን ትንሽና የሚናቅ ሆነ?›› ጠቢቡም፡- ‹‹ታላቅነትን የሚከተሉ ታላቅ ይሆናሉ፡፡ ትንሽነትን የሚከተሉ ትንሽ ይሆናሉ በማለት መለሰ፡፡ ጠያቂውም የዋዛ አልነበረም፡፡ ‹‹አንዱ ታናሽነትን ሌላው ታላቅነትን እንዴት መረጡ?›› በማለት ጥያቄውን አስከተለ፡፡ ጥበበኛውም፡- ‹‹በማሰብና ባለማሰብ ነው!›› በማለት አጭር መልስ ሰጠ፡፡

አዎ ታናሽነትም ሆነ ታላቅነት የማሰብና ያለማሰብ ውጤት ነው፡፡ራስን መሆን ማለትም በማሰብ ሃይል ተጠቅሞ ሃሳብና ቃል፤ ቃልና ተግባር አንድ እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው፡፡ ጥሩም ይሁን መጥፎ ስሜት ሲሰማህ በስርዓት መግለጽ ከቻልክ ከራስህ ጋር አትለያይም፡፡ ሕሊናህን የማያሳቅቅ ተግባር ስትፈፅም፤ ስጋህና ነፍስህ ሲዋሃድ፣ መንፈስህና አካልህ ሲቆራኝ፤ ከራስህ ጋር ግጭት ስታቆም፤ በፈቃድህ ስትኖር፣ በገዛ ሃሳብህ ስትመላለስ፤ ለሰው ብለህ ራስህን ሳትጥል ከተመላለስክ ያን ጊዜ ራስህን ነህ ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ አንተ ያንተ ሳትሆን የማንም ትሆናለህ፡፡

በጥንታዊዋ ሮማ ታሪክ አንድ የሚታወቅ ባህልና ወግ ነበር፡፡ ይሄ ባህል ፍልስፍናዊ ይዘት አለው፡፡ አስተሳሰቡ በላቲኑ ቃል ‹‹Memento Mori›› ሲባል በእንግሊዘኛው ደግሞ ‹‹Remember you will die›› የሚል ነበር፡፡ በጥንታዊቷ ሮማ ባህል አንድ የጦር ጄኔራል ድልን ሲቀዳጅ ወታደሮቹ እና ባሪያዎቹ ከኋላው እየተከተሉ ሟች መሆኑን እንዲያስታውስ የሚያደርግ ስርዓት ነበራቸው፡፡ በዚህ ባህል ወታደሮቹ ጄኔራሉን ከኋላው ከብበው እየተከተሉት በጆሮው ያንሾካሽካሉ፡፡ ሹክሹክታውም ‹‹አስታውስ ትሞታለህ!›› የሚል ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ጄኔራሉ የትኛውም ጣፋጭ ድል ልክ እንደሕይወት ጊዜያዊ መሆኑን እንዲያስታውስ ያደርገዋል፡፡ መሞትን ማስታወስ አኗኗርን መልካም ያደርጋልና፡፡

ወዳጄ ሆይ... ጭምብልህን አውልቀህ ተገለጥ! ውስጥህን አትጨቁነው፡፡ መንፈስህን አትደብቀው፡፡ ድሪቶህን ገፍፈህ ራስህን ሁን፡፡ አጉል ልማድህን ርታው፡፡ እውነትህን ኑርበት! ልብህን አድምጠው፡፡ ነፍስህን አውራው፡፡፡ ልክ እንደጥንታውያኑ ሮማ ወታደሮች ‹‹ራስህን ካልሆንክ የውሸት ኑሮ ትገፋለህ›› የሚል አስታዋሽ ያስፈልግህል፡፡ በሞት የሚጠናቀቀው ህይወትህ ትርጉም ሳይኖረው እንዳያልቅ የተሸፈነውን አንተነትህን፤ የደበቅከውን እውነተኛው ማንነትህን እንድትገልጥ አንተ አንተን አይደለህም የሚል ቀስቃሽ አላርም ፍጠር፡፡ እስከመቼ ጃል!? ሞትህ ላይቀር የውሸት መኖር አይደብርህም?

Are you not bored living behind a mask?

አዎ እውነተኛው አንተ ማለት ለሌላ ሰው ያልገለጥከውንና የደበቅከውን ነህ!!

ቸር መገለጥ!

ኢትዮጵያና ኢትጵያዊነት ለዘላለም ይኑሩ!

_
እሸ
ቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
እሁድ ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.


#መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለውብ ቀን

ከዛ በላይ ናችሁ!

ማንም ምንም ይበላችሁ እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ፣ ማንም ሰራችሁን ያጣጥል ስራችሁ ግን ከማንም ስራ በላይ ነው፣ ማንም በኑሯችሁ ይፈር ኑሯችሁ ግን ከማንም ኑሮ በላይ ነው፣ ማንም ከፊታችሁ ቆሞ እንደማትችሉ ይንገራችሁ አቅማችሁ ግን ከንግግሩ በላይ ነው። ከውጪ የሚመጣው ጫና ይቅርና በውስጣችሁ እንኳን የሚመላለሰው የገዛ ሃሳባችሁ ከእናንተ በላይ አይደለም። እራሳችሁን በጥራት የምትመለከቱባት የግል መነፅር አላችሁ፣ ለእራሳችሁ የምትሰጡት ቦታ አላችሁ። ውድድራችሁ ከሰዎች ንግግር ወይም ከውስጥ ጩሀታችሁ ጋር ሳይሆን ለእራሳችሁ ከሰጣችሁት ቦታ ጋር እንደሆነ አስተውሉ። ብለሃትንና ጥበብን ትምህርት ቤት ገብታችሁ አትማሩም። እውቀትን ታወሩት ይሆናል ጥበብና ብለሃት ግን በየቀኑ የምትኖሯቸው ናቸው። ጥበበኞች የማይጠቅማቸውን ንግግር አይሰሙም፣ ብልሆች ከጩሀት በላይ በሳል ንግግር ይገዛቸዋል። በየጊዜው ይማራሉ፣ እራሳቸውን በእውቀት መሰረት ላይ ያንፃሉ፣ መንፈሳቸው ጠንካራ ነው፣ ልብና አዕምሯቸው ቅርብ ለቅርብ ናቸው፣ ስለራሳቸው ሚዛናዊ ሀሳብን በማሰብ ይታወቃሉ፣ በእራሳቸው ያምናሉ ከእራሳቸው ጋር ስለሚያወሩት እያንዳንዱ ነገር በሚገባ ይጠነቀቃሉ።

አዎ! እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ! ሳትኖሩ ከሚወራባችሁ፣ በጆሯችሁ ከሰማችሁት፣ አዕምሯችሁ ደጋግሞ ከሚነግራችሁ አሉታዊ ማንነት በላይ ናችሁ። ህይወታችሁ በመዳፋችሁ ነች። የትኛውንም ወደ አዕምሯችሁ የሚገባውን አሉታዊ ሀሳብ የማገድ መብት አላችሁ፣ የትኛውንም በአዕምሯችሁ ውስጥ የሚመላለሰውን መጥፎ ሀሳብ ጠራርጎ የማውጣት አቅሙ አላችሁ። የሰዎችን ሀሳብ በማሳደድ አትጠመዱ፣ ስለሚወራባችሁ ነገር ብዙ አትጨነቁ። "ሰዎች ስለእኔ ምን አሉ ሳይሆን እኔ ስለእራሴ ምን እላለሁ?" ብላችሁ ጠይቁ። በማንኛውም ሰዓት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እራሳችሁን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ በየትኛውም ሰዓት ያልጠበቃችሁት ስፍራ ልትገኙ ትችላላችሁ። ይህም ሁኔታ የህይወታችሁ አንድ አካል እንጂ የህይወታችሁ መጨረሻ እንዳልሆነ አስተውሉ። ሁሉም ነገር በፍጥነት ይቀየራል፣ የትኛውም ከባድ ስሜት እንደ ንፋስ ያልፋል። በተፈጥሮ የደስታችን ጊዜ አጭር የመከራችን ወቅት ግን ረጅም እንደሆነ ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ልዩነቱን ያመጣው አስተሳሰባችን እንጂ በእርግጥም የጊዜው ርዝመት ተለያይቶ አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ከየትኞቹም ከባድ ሁኔታዎችህ በላይ ስለመሆንህ አትጠራጠር። የሚሆነው ይሆናል፣ የሚቀረው ይቀራል፣ የምትባለውን ትባላለህ፣ የሚሰጥህ ስም ይሰጥሃል በስተመጨረሻ ግን ህይወት በእራሷ አቅጣጫ ስትቀጥል ትመለከታለህ። አንተ ተስፋ ቆርጠህ ካልቆምክ ምንም የሚቆም የህይወት ፍሰት የለም። ብዙዎች ሰዎችን ሰምተው ባሉበት ቆመው ቀርተዋል፣ ብዙዎች ለራሳቸው በሰጡት መጥፎ ስም ምክንያት ህይወታቸውን ፈተና አድርገውታል። የምትሰማውም ሆነ የምታየው ነገር ሁሉ እውነት እንደሆነ መቀበል አቁም። እውነት የእምነት ቅጂ ነው። ጉዳዩ የሚያወራው ወይም የሚያሳይህ ሰው ሳይሆን የእራስህ አቀባበል ነው። ሀሳብ ሰውን ይገነባል፣ ሀሳብ ሰውን ያፈራርሳል። ማንም የማይገባበት የግል ዓለም እንዳለህ እወቅ። ያንተ ዓለም ያንተ ብቻ ነው። ከማንም ዓለም አያንስም ከማንም ዓለም አይበልጥም። በልብህ ያኖርከውን ያንኑ እምነት በገሃድ አውጥቶ ያሳይሃል። የግል ዓለምህን ጠብቅ። የማንም ሀሳብ ገብቶ እንዳይረብሸው ተጠንቀቅለት። በህይወት አጋጣሚ ከተገኘህበት ሁኔታ የተሻለ ስፍራ እንደምታደርሰው ቃል ግባለት።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለውብ ቀናችን

👍ከዚህ ይበልጣል!

አንዳንድ ሃሳቦች ሃሳብ ብቻ ናቸው፤ አንዳንዶችም ቅዠት ሊሆኑ ይችላሉ። ደጋግመህ ታስበዋለህ ነገር ግን ልታደርገው አትሞክርም፤ ደጋግሞ ይታይሃል፣ ይመጣብሃል ነገር ግን በእውን ልታየው አልቻልክም። ጀርባህ ብዙ ታሪክ፣ ኋላህ ብዙ እንቆቅልሽ፣ ብዙ ሸክም ይኖራል። በምንም ተዓምር በእንቆቅልሽ ማንነት፣ ባልተፈታ ታሪክ ታጅበህ ወደፊት መጓዝ፣ ሃሳብህን መኖር፣ እቅድህን መፈፀም፣ ህልምህን መኖር ሊቀልህ አይችልም። ምንም እንኳን መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ሁሉም ሰው በህይወት አጋጣሚ በህመም ውስጥ ያልፋል፤ በስቃይ ይፈተናል፤ በግል አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃል፤ ደፋ ቀና ይላል፣ ይታገላል። የተደላደለ ህይወት ለማግኘት ብዙ ርቀት መጓዝ ይኖርበታል፤ ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ይጠበቅበታል፤ መወጣት የማይፈልገውን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃላፊነትህ ቢልቅም፣ ተጠያቂነትህ ቢበዛም፣ ችግሮችህ ቢወሳሰቡም ህይወትህ ግን ከዚህ ይበልጣል፤ መቆየትህ ከዚህ ሁሉ ይልቃል። የሚሆኑ የማይመስሉ ታሪኮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ አጣብቂኞቹ ሊደራረቡ ይችላሉ፣ ፍላጎትና አሁናዊው አቅምህ ሊለያዩ ይችላሉ፣ ምኞትህና የጀመርከው መንገድም ሊራራቁ ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ መሃልም ቢሆን መዳረሻህ አንድና አንድ ነው፤ በአዎንታዊነት ዘርፍ ከፍ ማለት፤ ጠቃሚ፣ ችግር ፈቺና አንተ የመጣህበት ከባድ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎችን ማብቃት፣ መደገፍና አቅጣጫውን መጠቆም። የሆነው ቢሆንም የሚበልጠው ላይ ማተኮር ይኖርብሃል፤ እውነታውን ተቀብሎ መቆም ሳይሆን ወደፊት መጓዝ፣ መሰናክሎችን ተሻግሮ የተሻለውን ህይወት መፍጠር ይጠበቅብሃል።

አዎ! በጊዜ ብዛት የተገለጡ፣ ጊዜ ወዳንተ ያመጣቸው ጉዳዮች ፈቺው ጊዜያቸው ነው፤ የሚያቀላቸው እራሱ አምጪው አምላክ ነው። ፅናትህ እስከ ጥግ ሲሆን እንቆቅልሾችህ ይፈታሉ፤ ትዕግስትህ ሲበዛ የላቀውን ብለሃት ትጎናፀፋለህ። በደረሰብህ ጉዳይ ፈጥነህ ብይን አትስጥ፤ እራስህ ላይ ለመፍረድ፣ ማንነትህን ለመተቸት፣ መንገድህን ለማንቋሸሽ አትቸኩል። ሁሉም ሰው የተመረጠለት መንገድ በእርሱ በመራጩ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና እንከን አልባ ነው። ሁኔታህን መቃወም፣ ገጠመኞችህን መተቸት፣ በመጣህበት መንገድ ማፈር ከአምላክህ መቃረን፣ ፈጣሪህን መተቸትና በስራው ማፈር እንደሆነ እወቅ። መሰራት ባለብህ መንገድ ትሰራለህ፤ ብቁ መሆን በሚገባህ አቅጣጫ ብቁ ትሆናለህ። ዋናው ስቃይና ውድቀትህ ሳይሆን ዳግም መነሳትና የፈለክበት ስፍራ መድረስህ ነው።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🌍የዚህ ዓለም እውነታዎች!

ውሾች እና ድመቶች አልጋ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድን ድሆች ግን የግቢያችን ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ አንፈቅድም፡፡

የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ጸልይ፤ ጤናማ አካሄድ አይደለምና፡፡

የውሻ ቡችላ በዋጋ እየተሸጠ ሰውን ግን በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን እወቀው፡፡

ስለብርቅዬ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ። በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ሕጻናት ግን ቃል አይናገሩም፡፡

ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል)። የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስና ሲጎሳቆል ያስተዋለ የለም፡፡

የወደቁ የታዋቂ ሰዎች ሐውልቶች መልሶ ለመትከል ገንዘብ ይሰበሰባል፤ በየጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ሕጻናት ግን ምንም አይባልም፡፡

በዚች ምድር ሚሊዮኖች ቤት ሳይኖራቸው በሚልዮን ብሮች እስር ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል። ስለሰው ልጆች ስነ ምግባር መመረዝ ግን ማንም ምንም አይልም፡፡
ሰዎች ሆይ! ... ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ትያትረኛ ማንነታችን ፈጥነን እንውጣ ፡፡

☞ ሰዎች ሆይ! ... የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ..።

‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎
🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ምሽት💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
#ሰውና_ተፈጥሮው_እንዲህ_ይልሃል

ሰዎች የቱንም ያህል ልክ ባልሆነ መንገድ ቢያስተናግዱህ ችግር የለውም። መቼም ቢሆን ወደ እነሱ ደረጃ እንዳትወርድ። ረጋ በል፤ ጠንክር እና ትተሃቸው ሂድ!

አንተ እኮ ልዩ ነህ!

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ

የሮበርት ግሪን ምርጥ መጽሐፍት👇

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ
#የኃያልነት_ሕጎች 3ተኛ ዕትም

ሌሎች የሮበርት ግሪን በእንግሊዝኛ የታተሙ👇

#The_Laws_of_Human_Nature
#The_Daily_Laws
#The_33_strategies_of_WAR

ሁሉንም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል።

🎀

እነዚህ #የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ እና #ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍን፦

#ጄዚ
#ካንዬ_ዌስት
#ፊደል_ካስትሮ
#ጆርዳን_ፒተርሰን
#ባራክ_ኦባማ
#ኤለን_መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ኃያል ግለሰቦች ለስኬታቸው እንደምክንያት የሚጠቅሷቸው ናቸው። እናም አንተም ያቀድከውና ያሰብከው የስኬት መዳረሻ ላይ ለመውጣት እነዚህን መጽሐፍት እንደ መሰላል እንድትጠቀምባቸው አቅርበንልሃል፡፡

 LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍ትንሽ አትሁኑ!

ሌሎችን ለመተቸት ጊዜ እስክታጡ ድረስ ራሳችሁን በማሻሻል ተጠመዱ፣ ራሳችሁን በማብቃት ቢዚ ሁኑ። ትልቁ ስራ የሰውን ድክመትና ክፍተት ማውጣት ሳይሆን የራስን አውቆና ተረድቶ እርሱን ማሻሻል መሆኑን እንዳትረሱ። ትቺት የዓለምን ህዝብ እኩል የሚያደርግ በጣም ቀላሉ ስራ ነው፣ በምትኩ ራስን ማሻሻል የዓለምን ህዝብ የሚለይ ትልቁና ዋንኛው ስራ ነው። ማንም ልዩነት ፈጣሪ ሰው ልዩነቱን የፈጠረው ለዓመታት ሰውን ተችቶ፣ በሰው ስራ ተሳልቆ ወይም ሰው ላይ አተኩሮ አይደለም። ይልቅ ራሱን አውቆ፣ ማንነቱን ተረድቶ፣ አቅሙን ተገንዝቦ፣ ያለማቋረጥ ራሱ ላይ ሰርቶ፣ በየቀኑ ራሱን እያስተማረና ራሱን እየፈተነ ነው። ራሳችሁ ላይ ማተኮራችሁን ስትቀጥሉ የሰዎችን ድክመትና ክፍተት የመመልከት እድላችሁ እያነሰ ይመጣል። ጊዜያችሁ እጅግ በጣም ውድ ነው። ከቻላችሁ በገንዘባችሁ ግዙት፣ ሌላ ሰው ማድረግ የሚችለው ጉዳይ ካለ እርሱን ለሰው አሸጋግራችሁ ጊዜያችሁን ለተሻለ ነገር ነፃ አድርጉት።

አዎ! ትናንሽ ነገር እያደረጋችሁ ትንሽ አትሁኑ፣ በአሳፋሪ ተግባር ተሳትፋችሁ በራሳችሁ አትፈሩ። ሰዎች ላይ ያለማቋረጥ የነቀፋ ቃላትን መሰንዘር እውቀት ወይም ስልጣኔ አይደለም። ሁሌም ቢሆን ቁጭ ብሎ ማውራት የትናንሽ ሰዎች ባህሪ ነው፣ የሰው ስራን ሁሉ መናቅ የተናቁ ሰዎች ስራ ነው። አትዘናጉ፣ አይናችሁ ውጪ ውጪውን ሲል ማሻሻልና ማስተካከል የሚችለውን የገዛ ማንነቱን ይዘነጋል፣ ራሱን ይረሳል፣ የት ቆሞ ማንን እንደሚተች ማስተዋል ይሳነዋል። ራስን ማወቅን የሚያክል ትልቅ ምድራዊ ጥበብ የለም። ራሱን የሚያውቅ ሰው ከሁሉም በላይ ፈጣሪውን ይፈራል፣ ራሱን ለእርሱ ትዕዛዝና አስተምህሮ ያስገዛል፣ ቃሉን ያከብራል፣ በሰዎች አይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ከመመልከቱ በፊት የራሱ አይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ያስተውላል፣ ግዞቱ ያልሆነው ውጪ ላይ ከማተኮር ግዞቱና ርስቱ በሆነው ራሱ ላይ ያተኩራል። ከአምላክና ከእናንተ በቀር እናንተን የሚያውቅ ሰው የለም። ማንም ስለእናንተ እንዲነግራችሁ አትጠብቁ። ምንም ዙሪያ ጥምጥም መሔድ ወይም ሰውን ማስጨነቅ አያስፈልግም የራስ ግንዛቤያችሁ ምንጭ እናንተ ብቻ ናችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ዝግጁ ካልሆንክ አንዳች ከውጭ መጥቶ የሚቀይርህ ነገር የለም። ዛሬም እንደ ትናንቱ ዋናው የህይወት አጀንዳህ ሰዎች ከሆኑ ከምታስበው በላይ ለውድቀት እየቀረብክ እንደሆነ አስተውል። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የራሳቸውን ውድቀት በሰዎች ለመሸፈን ይሞክራሉ፣ ሰዎችን በናቁና በተቹ ቁጥር ንፁና ከእነርሱ የተሻሉ ሰዎች እንደሆኑ ያስባሉ። ነገር ግን የትኛውም ከሌላው ሊሻል የሚችለው በወሬ ሳይሆን በስራና በስራ ብቻ ነው። ችሎታው ማውራትና መተቸት ቢቻ የሚመስለው ሰው ስራውን ከመስራቱ ውጪ ትቺቱ የሰውን ስሜት እንደሚጎዳና ህልሙን ሊያደናቅፍበት እንደሚችል አያስብም። ብዙ አውቃለሁ፣ ነገሮችን ተረድቼያለሁ፣ ራሴንም አውቃለሁ ካልክ አፍህን ዝጋ፣ ስለሌሎች አይደለም ስለራስህ እንኳን ከልክ በላይ አታውራ። የምር አዋቂ ከሆንክ ስሜትህን ግዛ፣ ራስህ ላይ ሰልጥን፣ ሰዎችን መተቸት አቅቶህ ሳይሆን ጊዜውን እስክታጣ ድረስ በግል ጉዳዮችህ ተጠመድ፣ ትልቁን ጥበብህንም ገልጠህ ለዓለም አሳይ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄