📕ተአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሰውዬው አሁን ያለበት ቦታ ከዚህ እሷ ካለችበት ብዙም በማይርቅ ሌላ ሆቴል ውስጥ ነው..ግን እየጠጣ አይደለም..ቤርጎ ውስጥ ሆኖ ነው የሚታያት፡፡ደግሞ ብቻውን አይደለም..አንድ ቅንጥስጥስ ያለች ለጋ ወጣት ክንዱ ላይ ተዘርራ በፀጉር የተሸፈነ ጥቁር ደረቱን እየዳበሰችለት ነው…..እሱ ከወገቡ በታች ቢጃማ ሱሪ አድርጓል… ልጅቱ ግን በፓንት ብቻ ነች…ደግሞ የሰውነታቸው ቀለም ልዩነት ..እሷ ብጭጭ ያለች ክልስ የምትመስል ሴት ነች….ደግሞ ስዕል የመሰለ ውበት ያለት..
‹‹ይህቺን ይዘህ ነው ለካ በእኔ ላይ የጎረርክብኝ?››ስትል አሰበች....እና ይበልጥ የፉክክር መንፈሷ ተነቃቃ…
‹‹የእኔ ፍቅር አሁንም እንደተበሳጨህ ነው?››ልጅቷ ነች የጠየቀችው
‹‹በጣም እኮ የምታናድድ ሴት ነች..አንተን በዛሬው ቀን ካላወጣሁ እራሴን አጣፋለሁ ትለኛለች?››
(አሁንም ስለእሷ እያወራ መሆኑን ስታውቅ ውስጧ ሞቀ..የሚበላት አካባቢም ጨመረ)
‹‹ታዲያ ጤነኛ ነች ትላለህ?››
‹‹ጤነኛማ አይደለችም››
‹‹ታዲያ ንቀህ ተዋታ..ለምን አትረሳትም .... ?መቼስ አሁን እኔ እቅፍ ውስጥ ነህ…መጠጡም እዚሁ ክፍላችን አለ.. እራቱም እዚሁ ነው የሚመጣልን..እኔን የመሰለች ዘበኛ አለህ እንዴት ብላ ከየት ታገኝሀለች..ነው ወይስ እንደፎከረችው እራሷን ታጠፋለች ብለህ ሰጋህ?››
‹‹ፍግም ትበላ››
‹‹ተው ተው እደዛማ አይባልም…አሁን ለሚሰማህ ሰው አሪፍ ጨካኝ አትመስልም…ሁል ጊዜ እኮ አንደበትህ እና ሆድህ አይገናኝም……….››
‹‹እና እንዴት ነው የሚባለው?››
‹‹አይ ያን ያህል ከወደደችህማ እራሷን ከምታጠፋ አንዴ ብትቸገርላት?››
ገፍትሮ ከደረቱ ላይ አስፈነጠራት ..
እየሳቀች ‹‹አትበሳጭ.. ቀልዴን እኮ ነው›› አለችው ወደአስለቀቃት ቦታ እየተመለሰች
‹‹እንዲህ አይት ቀልድ አይመቸኝም ..ካንቺ ውጭ የሌላ ሴት ገላ ከማቀፍ እኔም እራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…››
‹‹በቃ የእኔ ጀግና›› ብላ ወደ ደረቱ ተመለሰችና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት… ገለበጣትና እላዬ ላይ ተከመረባት…መሳሙን ሳያቆም በአንድ እጁ የለበሰውን ቢጃማ ከሰውናቱ መዥርጦ አወለቀ..
በንስራ ታግዛ እያየችው ያለው ገበናቸው የወሲብ ረሀቧን ከምትቆጣጠረው በላይ እንዲሆንባት አደረገው ፡፡
እሷ ልትተኛው የፈለገችው ወንድ ከዕጮኛው ጋር በወሲብ ዳንኪራ እየጨፈረ ነው…እናም ደግሞ በራሱ ታማኝነት እንዴት ተመፃዳቂ እንደሆነ ከንግግሩ ለሁለተኛ ጊዜ መስማቷ የቅድሞውን ብስጭቷን በእጥፍ እንዲጨምር አደረገው…
ሂሳቧን ከፈለችና መቀመጫዋን ለቃ ወደመኪናዋ አመራች ..መኪናዋን አስነሳችና ሰውዬዋ ወዳረፈበት ሆቴል ነዳችው… ንስሯም በሰማዩ ላይ ጭለማውን ሰማይ እየሰነጠቀ ከላይ እየተከተላት ነው፡፡
ንስሯ‹‹ፍቅራቸውን እና መተማመናቸውን አየሽ አይደል…?ተይው በቃ….››የሚል መልዕክት አስተላለፈላት
‹‹አልተውም.. የማታግዘኝ ከሆነ በራሴ እወጣዋለሁ….››መለሰችለት ለንስሯ
‹‹በራስሽማ የበለጠ ጥፋት ታጠፊያለሽ››
‹‹እንግዲያው ዝም ብለህ በቀላሉ ያሰብኩትን እንደሳካ አግዘኛ››
ንስሩ የመስማማት ምልክት አሳያት ..
አሁን ሆቴል ደረሰችና መኪናዋን ቦታ አስይዛ አቆመችና ሞተሩን አጠፋች ….በቀጣይ ምታደርገውን ነገር ግን ገና አላወቀችውም .. መኪናዋ ውስጥ ሆና ትኩረቷን ስብስባ እና ከንስሯ እይታ ጋር እይታዋን በማጣመር ልክ ለስለላ በድብቅ እንደተቀበረ ካሜራ ክፍላቸውን ወደመቃኘቱ ተመሰች
አሁን ፍቅረኛሞቹ ስራቸውን ጨርሰው ሻወር ቤት ግብተዋል…እየታጠቡ ነው ፡፡በመታጠባቸው ውስጥ መተሸሻት ..በመተሻሸታቸው ውስጥ ከወሲባዊ እርካታ በኃላ ያለ ድሪያ አይነት ማሽካካት ይታይባቸዋል….. ታጥበው ከጨረሱ በኃላ ሁለቱም ፎጣ አገልድመው ሻወሩን ለቀው በመውጣት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ….እሱ ተንጠራራና ፊት ለፊታቸው ካለው ጠራጴዛ የወይን ጠርሙሱን በማንሳት የጎደለውን የወይን ብረጭቆ በመሙላት አንስቶ ሰጣት ..ለራሱም አነሳና ተጎነጨ ….እሷ ግን ጠቀም አድርጋ ተጎነጨችና አፏን ወደእሱ አሞጠሞጠች …ከፈተላት.. በጉንጮቾ ያቆረችውን ወይን በከፈተላት ጉንጩ ውስጥ ገለበጠችለት››ይሄንን ስታይ የሆነ ምቾቷ እየቀነሰ መጣ….ያልተለመደ አይነት ሆነባት፡፡
‹‹አሁን ሰርጋችን ቀን መቼ እናድርገው?››እሱ ነው አይን አይኗን በስስት እያያት የጠየቀው፡፡
‹‹እኔ እንጃ››
‹‹በእኔ በኩል በጣም በቅርብ መሆን አለበት ባይ ነኝ››
‹‹ቅርብ ስትል? ››
‹‹በሚቀጥለው ወር ውስጥ››
‹‹እርግጠኛ ነህ….?እኔ ግን ያለችንን ጊዜ እንደዚሁ በፍቅር ብናሳልፋት ይሻል ይመስለኛል፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ ስንት ወር ያወራንበትን ነገር ከእንደገና ወደኃላ ትመልሺዋለሽ ..አድሮ ቃሪያማ አትሁኚ››ኮስተር ብሎ መለሰላት
‹‹የእኔ ፍቀር ላንተው እኮ አስቤ ነው…ከዚህ ጋብቻ መሳቀቅ ብቻ ነው የሚተርፍህ ››
ያንን ጥቁር ፊቱን ይበልጥ አጨልሞ ‹‹ግድ የለም ለእኔ አታስቢ..አንቺ ባለችሽ ጊዜ ቶሎ ቶሎ መኖር መቻል አለብሽ ፡፡.ድል ባለ ሰርግ ማግባት …ልጅ ወልዶ ማቀፍና ማጥባት ላንቺ የሚገቡሽ ነገሮች ናቸው››አላት
‹‹ትቀልዳለህ…..ከዚህ በፊትም ነግሬሀለው …ዛሬም እንደግምልሀለው የማላሳድገውን ልጅ በፍጽም አልወልድም››
‹‹እንግዲህ ነግሬሻለሁ…
ካልወለድሽልኝ አንቺ ጥለሺኝ ስትሄጂ የምጽናናበት ነገር ስለሌለ ያው ከሸኘሁሽ በኃላ እራሴን በማጥፋት እንደምከተልሽ እና በምትቀበሪበት ጉድጓድ አብሬሽ እንደምቀበር አትጠራጠሪ››
‹‹ለምን ታስጨንቀኛለህ?››
‹‹እያስጨነቅኩሽ አይደለም…በትክክል የማደርገውን እየነገርኩሽ ነው…አንቺ ስለመሞትሽ ማሰብን እርሺውና በየቀኑ ማድረግ የምንችለውን እናድርግ.. እንጋባ… ውለጂልኝ..ከዛ በኃላ ያለውን ነገር ለእግዜር እንተወው ..ምን ይታወቃል የሆነ ተአምር ተፈጥሮ በሀኪም ከተቆረጠው የመሞቻ ቀንሽ በፊት ፈውስ የሚሆን መድሀኒት ይገኝ ይሆናል››
ኬድሮን በምሰማው ነገር እየደነዘዘች ነው።
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 34,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄