ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
183K subscribers
279 photos
1 video
16 files
201 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
Live stream finished (5 minutes)
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሃምሳ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ለማንኛውም ልድገምልሽ ኤርምያስ እባላለሁ…ለ15 ዓመት ያህል በማንዴላ ሀገር በሆነችው ደቡቡ አፍሪካ ጀሆንስበርግ ኖሬያለሁ… ወደሀገሬ ከተመለስኩ  ሁለት ዓመት ከግማሽ ሆኖኛል፡፡የ20ዓመት አፍላ ፍንዳታ ሆኜ ሄጄ የ35 ዓመት ሙሉ  ደንዳና ወጣት ሆኜ ተመለስኩ….››
‹‹አሀ ዲያስፖራ ነሀ….?››
‹‹አይ ዲያስፖራ ..!!! ‹ጽድቁ ቀርቶብኝ  በቅጡ በኮነነኝ ›ትላለች እናቴ… ለማንኛውም  እወነቱን ንገረኝ ካልሺኝ … በእነዛ ዓመታት ውስጥ በሰው ሀገር ላይ  ስዳክር ..ሞራሌን ከማንቆሻቆሽ…ሰው ሆኜ መፈጠሬን ከመጠየፍ እና ወጣትነቴ ላይ ጢቢ ጢቢ ከመጫወት ውጭ ምንም ያተረፍኩት ነገር አልነበረም…ብዙ ህልም በልቤ ብዙ ምኞት በውስጤ አጭቄ ነበር የተጓዘኩት …እርባነቢስ ሆኜ ባዶ እጄን በሀገሬ ለመሞት ብቻ ብዬ  ነበር የተመለስኩት …ይገርማል አይደል?
ሰው እንዴት ለመሞት ብሎ ከደብቡ አፍሪካ ድረስ ኪሎሜትሮችን አቆርጦ ይመጣል ትይኝ  ይሆናል..….?ለእኔ ግን ትርጉም ነበረው..››
‹‹ንገረኝ እስኪ ትርጉሙን…››ከሳዕታት ትርኪ ሚርኪ ወሬ እና መዛለል በኃላ ድንገት ምርር ወዳለ የህይወት ታሪክ ሀተታ መግባቱ አስደምሟታል አስደስቷታልም…አሁን እየነገራት  ያለውን ታሪክ እሱ ሳይነግራት እንደተለመደው  ወጭ እየጠበቀት ያለውን ንስሯን እንዲረዳት አድርጋ በዝርዝር ማወቅ ትችላለች..ግን አልፈለገችም …እንዲሁ እየጓጓችና ቀጥሎ ምን እንደሚናገር እየገመተች ቀጥታ ከራሱ አንደበት መስማቱ የሆነ የተለየ ስሜት ስለፈጠረባት ደስ ብሏታል…
ቀጠለ ‹‹በህይወቴ እያለሁ የመኖር ምኞቴ ሰልበው በድን አድርገውኝ …ወጣትነቴን ከንቱ አስቀርተውብኝ የመጨረሻውን ክስረት ማክሰራቸው ሳይበቃቸው …ከሞቴም በኃላ ክብር ስጋዬን  ለሀገራቸው ምድር  ልገብር …?አላደርገውም ፡፡ለዘላለም የባዕድ ሀገር አፈር ሆኜ መቅረት  አልፈለኩም  ..ይህ  መልካም አይደለም…ቢያንስ አገሬ እትብቴን በክብር በወርቃማ አፈሯ ውስጥ ቀብራ ከማንነቷ ጋር እንዳወሀደችው ሁሉ ስሞትም በድኔን በክብር ልትቀበለኝ እና ለዘላለም በጉያዋ ልትሸሽገኝ ይገባል..አዎ እንደዛ ነው መሆን ያለበት..በዛ ላይ እናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ማየት እፈልጋለሁ… አያየኋት መሰናበት፤ስሮ በመኖር  እና እሷን መጦር ችዬ ላስደስታት  ባልታደልም… እጇ ላይ ሞቼ አልቅሳ ልትቀብረኝ እና እርሟን ለማውጣት እንድትችል ግን እድሉን ላመቻችላት ይገባል..አዎ ስመጣ እንደዛ ብዬ  እና እንደዛ ወስኜ ነበር …
‹‹ከዛስ….?››
‹‹ከደረስኩ ኋላማ … ቆይ ዛሬ ስል …ቆይ ትንሽ ልሰንብት ስል ..የመኖር ጉጉቴ ቀስ በቀስ ከሞተበት  እያንሰራራ እና እየተቀሰቀሰ መጣ..ምንም አግኝቼ አልነበረም ..ከእናቴ የማገኘው ተንሰፍሳፊ ፍቅር  እና ከጓደኞቼ የማገኘው ማፃናኛ …››
‹‹በጣም አሪፍ ታሪክ ነው ያለህ››
‹‹አዎ መራር የህይወት ገጠመኞች  ለሰሚው ወይም ለፅሀፊው ሳቢ ታሪክ ይወጣቸዋል…››
‹‹ከዛስ እንዴት ሀሳብህምን ሙሉ በሙሉ ልትቀይር ቻልክ….?››
‹‹አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተውኩትም…አሁንም  የመሞት እቅዴ በውስጤ አለ…››
‹‹እሺ እንዴት ልታራዝመው ቻልክ….?››ጥያቄውን አስተካከለችለት፡፡
‹‹እንዴት መሰለሽ….ከዛ ከሰው ሀገር  በገንዘብም በመንፈስም ክስርስር ብዬ የመጣሁ ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ሚስኪን የልጅነት ጓደኞቼ  አዋጥተው አሁን የምጠቀምባትን ላዳ ገዝተው ሰጡኝ..በቃ የመሞት ሀሳቤን አራዘምኩት ..ለራሴ ሁለተኛ እድል ሰጠሁት..ቢያንስ ለጊዜው ሰርቼ ስጋዬን የማኖርበትን  ካገኘሁ አንድ ቀን ምን አልባት ሁለተኛውን የህይወት ምኞቴን በሆነ ተአምር ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል…ብዬ ተስፋ አደረኩና መጨረሻውን እስከማይ ሁለት ዓመት ተኩል በሀገሬ ኖርኩ..ዘና ብዬ ለማንም ለምንም ሳልጨነቅ…ባሳኘኝ ሰዓት እየሰራሁ ሲያሰኘኝ ደግሞ እየተኛው..የእናቴን ሽሮ እየበላሁ ተስፋዬን በመጠበቅ እንሆ አለሁልሽ››
‹‹ምንድነው ተስፋህ..ማለቴ ይሳከልኛል ብለህ የምትጠብቀው….?››
‹‹የልጅነት ፍቅሬን… ..አንድ ቀን ቀና ብላ ታየኛለች የሚል ተስፋ..አንድ ቀን ከቄስ ትምህርት ቤት ጀምሮ እንደማፋቅራት እና ዕድሜዬን ሙሉ በልቤ ተሸክሜያት ስዞር እንደኖርኩ  ተረድታ በእቅፎ ታስገባኛለች ብዬ ተስፋ  በማድረግ..አንድ ቀን እጄ ትገባለች በሚል ተስፋ…..››

‹‹ወየው ጉዴ!!›አለኝች በውስጧ፡ በዚህ ቅርብ ጊዜ ውስጥ የምትቀርባቸውና የምትመኛቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት እንዴት ሆኖና  ምንስ በሚሉት አጋጣሚ   እንደዚህ በፍቅር ስክር ያሉና የታወሩ ሆነው እንደሚገኙ ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም...?‹‹ይሄኛውንስ ዛሬ አልምረውም…በፍጽም፡፡››ስትል ፎከረችው፡፡

‹‹ይቅርታ ሙሉ ታሪኩን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ….››

‹‹እየነገርኩሽ እኮ ነው …እየተረተርኩልሽ…..ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አይደል የሚባለው››

‹‹አይ እዚህ አይደለም…እኔ ቤት እንሂድና ተረጋግተን እየጠጣን ታወራልኛለህ….አሁን ሆቴሉም ሊዘጋ መሰለኝ››

‹‹ይቻላል››ይከራከረኛል  ወይም ይቃወመኛል ብላ ነበር የጠበቀችው ..ቀድሟት ተነሳ ..ሂሳብ ከፍላ ተከተለችው …. እየተወለጋገድና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ላደው ድረስ ሄድ ..ሹፌሩ ተቀብሏቸው እቤት ድረስ አደረሳቸውና የለሊቱን ግዳጅ ጨረሶ  ተለያቸው.. 
እሷም ዛሬ ለዛውም ከመሸ ያወቀችውን ባለ ላዳ ይዛው  ወደቤቷ ገባች…..

            ይቀጥላል

#ክፍል 51,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሃምሳ_አንድ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ  አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..

‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››

‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል

‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››

‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ  ነበር ያቆምኩት….?››

‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››

‹‹አዎ….አይገርምሽም …

እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››

‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››

‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..

‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ  አይነት በሽታ ነው፡፡››

‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››

‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ  በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና  የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን   .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››

‹‹ይገርማል!!››

‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር  የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ  ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር  ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››

‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት

‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ   ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር  የተነሳ….››

አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ

‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ  አብሬት በምማርበት  በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ  በስደትም እያለው እንደዛ ነበር  እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ  ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ  ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት  ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት  ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ  ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን   ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ  ሰላምታ  ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን  እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››

‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር  ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ  እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት  ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››

‹‹ምን ተከሰተ….?››

‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ   ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ  አቁሜ እኔም ላዳዬ  ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ  የእብድ ድርጊት መስሎኝ  በርግጌ ተነሳሁና  አንገቴን በመስኮት አስግጌ  ወደ ኃላው ተመለከተኩ…

‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››

‹‹ክፈትልኝ››

‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..

‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ  …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና  ነደሁት

‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት

‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት

-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው  የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››

‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ  ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ  አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም  ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡ 
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና  ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡
‹‹ቤተክርስትያን….? ጭራሽ ቤተክርስትያን…በፍጽም… የደረሰብኝ መከራ  ሁሉ በእግዚያብሄር ትዕዛዝና ፍላጎት  ነው የሆነው..እንዲህ የቀጣኝ እሱ ነው…..ፍፅሞ ወደቤቱ አልሄድም..››ብላ ተንገሸገሸች
ምርጫውን ወደራሷ መለስኩት‹‹እሺ የት ልውሰድሽ…….?››

‹‹-መጠጥ ቤት…››

‹‹አልተከራከርኳትም..ነዳሁት….እስከለሊቱ 5 ሰዓት ብትን እስክትል ድረስ  እስክትጠጣ ጠበቅኳት …ከዛ አዝዬ ማለት ይቻላል አቤቷ አስገብቼያት ደስ ብሎኝም ከፍቶኝም ወደቤቴ ገባሁ….ደስ ያለኝ ከስንት አመት በኃላ ከእሷ ጋር ማውራት፤ከእሷ ጋር ጊዜ ማሳለፍ በመቻሌ ነው…የከፋኝ በዚያ አይነት በእሷ ባልሆነ ሀዘን፤ በእሷ ባልሆነ ምሬት ውስጥ በተዘፈቀችበት ሰአት ስለገኘኋት ነው …..

‹‹ከዛስ እንዴት ሆነ….?››ስትል ጠየቀችው.. በታሪኩ ከመመሰጧ የተነሳ ምሽቱን  ሙሉ ጭኖን  የሚበላት  የነበረው  ክፉ አመሏ ራሱ ቀንሶላት ነበር።

            ይቀጥላል

#ክፍል 52,,እንዲለቀቀ 👍(5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Live stream finished (14 minutes)
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሁለት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ከተለየኋት በኋላ ስለእሷ ማሰብ ላቆም አልቻልኩም ነበር..እንዴት አድርጌ ከዚህ ሀዘን ላወጣት  እችላለሁ….?እንዴት አድርጌ ላግዛት እችላለሁ….? የግድ አባቷ እስኪመጡ መጠበቅ የለብኝም..አባቷ ስል አባቷ ብቻ አይደሉም እናቷም ጭምር.. ጓደኛዋም ጭምር እንደሆኑ መላ ሰፈሩ ያውቃል..ብቻቸውን ነው ያሳደጎት….እድሜ ልኳን ከአባቷ ተለይታ ኖራ አታውቅም..ይሄንን ማንም ያውቃል…ዩኒቨርሲቲ ጎንደር ደርሷት መለያየት ግድ በሆነበት ጊዜ እንኳን  እሷ ከአንተ ተለይቼ መሄድ ስለማልችል ትቼዋለሁ ስትል..አባቷም እውነትሽን ነው አንቺ ትምህርትሽን ከምትተይ እኔ አብሬሽ ሄዳለሁ በማለት…ስራቸውን ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር በመቀየር አብረዋት ዘምተዋል…ይህ ሀገር የሚያውቀው ሀቅ ነው……..አሁን አባቷ ለጉዳይ ወደውጭ ሀገር እንደሄዱ ነግራኛለች….ስጨነቅ አንግቼ  በማግስቱ ያለውን ቀንም በተመሳሳይ መሸበር አሳለፍኩ

…..ግን……?››

ድንገት ንግሩን አቋረጥኩትና ‹‹አልደከመህም መኝታ ቤት ሄደን አልጋ ላይ አረፍ ብለን የቀረውን ትጨርስልኝ….?››አለችው  

‹‹በቀላሉ  ያልቃል ብለሽ ነው….?››

‹‹እንሞክረው….?››

ደስ እንዳሽ ብሎ ብርጭቆውን ይዞ ተነሳ.. ቀድማው ወደመኝታ ቤት አመራች፤ እየተንጋዳገደ ከኃላ ተከተላት….የእሱና የሰላም የፍቅር ታሪክ ብቻ ሳይሆን የእሷ እና የእሱንም መጨረሻ እንዴት እንደሚጠናቃቅ ማወቅ አጓጓት
///

መኝታ ቤት ገብተው አልጋ ላይ ጎን ለጎን ትራስ በመደገፍ ጋደም ብለው ከተመቻቹ በኃላ ወሬውን ካቆሙበት ቀጠሉ፡፡

‹‹እና እንደነገርኩሽ በእሷ ጉዳይ ስጨነቅ አድሬ ስጨነቅ ውዬ …ከእንደገና መልሼ መጥፎ ለሊት ካሳለፍኩ በኃ
ኋላ ዛሬ ጥዋት ስልኬ ጠራ …አነሳሁት‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ››

‹‹ማን ልበል….?››ስል ጠየቅኩ፡፡

‹‹ትናንት ማታ ያደረስከኝ ልጅ ነኝ..ቁጥርህን ከተውክልኝ ካርድ ላይ አግኝቼው  ነው››አለቺኝ.…

እንደዛ በፍጥነት ትደውልልኛለች ብዬ አላሳብኩም ነበር..ትናንትና ስልክ ቁጥሬን ፅፌ ትቼላት ሰወጣ ለምን አልባቱ ብዬ ነበር..ምን አልባት በዛ ስካር ውስጥ  ሆና የሰጠኋትን ወረቀት ቀዳዳም ቆሻሻ ቅርጫት ውስጥ ልትጥለው ትችላላች የሚልም ግምት ነበርኝ..እና ደወለችልኝ ..ለዛውም ገና በጥዋት4 ሰዓት…እንደደረስኩ መኪናዬን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳሁ…ከፈተችልኝ….

‹‹እሺ ደህና ነሽ ግን….?››
ጥያቄዬን ችላ ብላ ‹‹አሁን እየጠበቅኩህ ነው ና››አለችኝ 

‹‹አቤት….?››አልኳት ይበልጥ እንድታብራራልኝ ፈልጌ 
እሷ እቴ ስልኩን  ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችው

‹‹ይህቺ ልጅ ጤናም የላትም እንዴ . ….?.››አልኩና የላዳዬን ሞተር በማስነሳት ወደቤቷ ተፈተለኩ..እንዴ እሷ ና ብላኝ እንዴት እዘገያለሁ….?፡፡ 

‹‹ታዲያ እቤት ስትሄድ አገኘሀት….?››ኬድሮን ነች የጠየቀችው በእጇ ከያዘችው ብርጭቆ መጠጥ አንዴ እየተጎነጨች
‹‹አዎ ..እንደደረስኩ መኪናዋን ዳር አስይዤ  አቆምኩና ወርጄ የውጩን በራፍ እንኳኳው…እራሷ ከፈተችልኝ….ጉስቁልናዋ እንዳለ ነበር..ስልችት ብሏታል…የሆነ ልቧን ስብብርብረ ያደረገው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ..እንደውም የፍቅር ነገር ይመስለኛል….››

‹‹እሺ ማን ነበረ ስምህ….?›› አለችኝ ግድ የለሽ እና አናዳጅ በሆነ የድምጽ ቅላፄ….አይገርምሽም ዕድሜሽን ሙሉ ያመለክሽው ልጅ… ስንት ቀን እና ሌት የናፈቃሽው እና በትዝታው የተሰቃየሽለት ልጅ -ማን ነበር ስምሽ ሲልሽ…..….?

በውስጥሽ  የሚፈጥረው ስሜት ግማሽ ህልውናሽ  የመደምሰስ አይነት ነው …..እመኚኝ በጣም ነው የሚያመው …እሷ ግን ለእኔ የስሜት መጎዳት ቁብ ሳይኖራት፤.መልሴንም ለመስማት ትግስት አጥታ ወደትዕዛዞ ተሸጋገረች

‹‹ካላስቸገርኩህ የሆነ ቦታ ትወስደኛለህ…….?››

‹‹የፈለግሺው ባታ …ተዘጋጂና ነይ መኪና ውስጥ እጠብቅሻለሁ››ብዬ ወደላዳዬ ፊቴን አዞርኩ‹‹አይ ላዳህን ወደግቢው አስገባት እና አቁማት.. በእኔ መኪና ነው የምንሄደው፤ ከከተማ ወጣ ማለት ነው የፈለግኩት…..››አለቺኝ፡
ግራ ግብት እንዳለኝ ወደኃላዬ ተመለስኩና ላዳዬ ውስጥ ስገባ እሷ ደግሞ የውጩን በራፍ ከፈተችልኝ…ወደ ጊቢ ውሰጥ አስገባኋትና ሚጢጢ ላዳዬን  ግዙፍ የእሷ ላንድኩሩዘር መኪና ጎን አቆምኳትና ሞተሩን አጥፍቼ ወጣሁ… በሩን ዘግቼ ቆምኩ..
‹‹እሷ ወደሳሎን ተመልሳ እየገባች ነበር…ደግሞ የሰውነቷ ቅርፅ ከቁመቷ ጋር ያለው ምጣኔ እንዴት አባቱ ያምር ነበር መሰለሽ…..5 ደቂቃ ሳትቆይ ተመልሳ ወጣችና የሳሎኑን በራፍ መቆለፍ ጀመረች ….በእጇ ካንጠለጠለችው ቦርሳ በስተቀር ምንም  የያዘችውም ሆነ የቀየረችው ነገር አልነበረም… እንደነበረችው ነው ተመልሳ የመጣችው..ዝንጥንጥ ብላ የምትመጣ መስሎኝ ነበር..ግን በለበሰችው ቱታ ሱሪ እና ቲሸረት ነው አሁንም ያለችው..ስሬ እንደደረሰች ከቦርሳዋ ውስጥ ቁልፍ አወጣችና ወረወረችልኝ …በአየር ላይ ቀለብኩና ወደመኪናዋ ተንቀሳቀስኩ…..ሞተሩን እስነስቼ ከግቢሁ ከወጣሁ በኋላ አቁሜ ጠበቅኳት… የውጩውን በራፍ  በመዝጋት እና በመቆለፍ መጣችና ጋቢና  በመግባት ከጎኔ ትቀመጣለች ብዬ ስጠብቅ  የኃላውን በራፍ ከፍታ ገባች……››

‹‹ምነው እዚህ አይሻልሽም….?›› ልላት ነበር ..ግን አንደበቴን ማላቀቅ አልቻልኩም…በእስፖኪዬ ወደኃላ ተመለከትኳት ….ግማሽ እሷነቷ ሞቶ ግማሽ እሷነቷ ብቻ በህይወት እና በሞት መካከል ያለ ይመስላል..ልክ እኔ  ለመሞት ወደሀገሬ ልግባ ብዬ በወሰንኩበት በዛ ጭለማ ጊዜ የነበርኩበትን ሁኔታ አስታወሰችኝ ….

‹‹ሰላም ወዴት ነው የምንሄደው..….?››ብዬ ጠየቅኳት

‹‹አቤት›› አለችኝ እንደመባነን ብላ
‹‹ወዴት ልንዳው ነው ያልኩሽ….?››

‹‹ወደ ፈለከው…. ግን ከከተማ ውጭ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይሁን እንጂ ወደየትም ይሁን …..››
‹‹እሺ››
‹‹ግን ስሜን መቼ ነው የነገርኩህ….….?ሰላም ብለህ የጠራህኝ መሰለኝ….?››

‹‹ነግረሺኝ አይደለም…››

‹‹እና እንዴት  አወቅከው…..….?››

‹‹አውቄውም አይደለም…ሰላም ማለት ለእድሜ ልኬ ያፈቀርኳት..አሁንም ድረስ የማፈቅራት ከህጻንነቴ ጀምሮ የማውቃት ፤መቼም ልረሳት የማልችላት  ልጅ ስም ነው…እና ያው ፍቅሯ ጅል አደርርጎኛል መሰለኝ ብዙ ሴቶችን ሰላም ብዬ መጥራት እወዳለሁ…››አልኳት….ሽሙጤ ሳይገባት….ፈገግ አለችና‹‹ ይገርማል እንደአጋጣሚ የእኔም ስም ሰላም ነው››አለችኝ 

‹‹አውቃለሁ››

‹‹ማለት›….?›››መልሶ  ግር ብሏት

‹‹በመልክም በጣም ትመሳሰላላችሁ ልልሽ ፈልጌ ነው››
ዝም አለች….በጦር ኃይሎች አድርገን በ18 ማዞሪያ ታጥፈን በአንቦ መስመር አሸዋ ሜዳን አቆርጠን ወደቡራዬ ተጓዝን…እሷ እውነትም እንዳለችው ወደየትም ብነዳው ግድ ያላት አትመስልም ነበር..አይኗን በመኪናው መስታወት ወደውጭ ልካ በየመንገዱ ዳር ያለውን ትዕይንት ምታይ ትመስላለች ….ግን አታይም እሳቤዋም እይታዋም ከውስጧ ጋር እንደሆነ ያስታውቃል…ብራዩንም አለፍን ፣እኔም አላቆምኩም እሷም አቁም አላለችኝ…ግን ጊንጪ ልንደርስ ኪሎ ሜትሮች ሲቀረን  የሆነ ለጥ ያለ ሜዳ ጋር ስንደርስ…..‹‹ይቅርታ ማን ነበር ስምህ...….?››ስትል ከሳዕታት ዝምታ በኃላ አብሻቂ ጥያቄ ለሁለተኛ ጊዜ ጠየቀችኝ….
‹‹ኤርሚየስ››
‹‹ኤርሚያስ …እዚህ ጋር ታቆምልኝ..….?››
ዳር ያዝኩና አቆምኩላት…ወረደችና የመኪናዋን የኃላ ኮፈን ከፍታ ምንጣፍ በማውጣት አንድ ጠርሙስ ያልተከፈተ ውስኪ በመያዝ ከመኪናው እርቃ ወደአንድ ዘርፋፋ ቅርንጫፍ ወደተሸከመ ዛፍ ሄደችና ጥላው ባለበት አቅጣጫ ምንጣፍን አንጥፋ እንደቡዲስት መለኩሴ እግሮቾን አነባብራ  በመቀመጥ የጠርሙሱን ክዳኑን ተታግላ ከፈተችና አንዴ በመጎንጨት ወደ ፅሞናዋ ተመለሰች…..
እኔን  ልክ እንደ ግኡዙ  መኪናዋ ነበር የቆጠረችኝ… እስከመፈጠሬም እረስታኛለች…20 ለሚሆኑ ደቂቃዎች  ከመኪናው ሳልወርድ የተለያዩ ኤፍ. ኤም ጣቢያዎችን እየቀያየርኩ ሳረብሻት ለመቆየት ሞከርኩ… ከዛ በላይ ግን አልቻልኩም… መኪናውን ከፍቼ ወጣሁና በዝግታ እርምጃ ወደእሷ በመሄድ አንድ ሜትር ከእሷ ርቄ ከፊትለፊቷ  ሳር የለበሰ ሜዳ ላይ ቁጭ አልኩ……በሁለት ጉንጮቾ እንባዋ ያለምንም ድምጽ ትረጫዋለች….ደነገጥኩ…. ምን እንደምላትም ሊገለፅልኝ አልቻለም፡፡
‹-በህይወትህ መሞት ፈልገህ ግን ደግሞ እንዴት መሞት እንዳለብህ ግራ ገብቶህ ያውቃል….?፡፡››ስትል ጠየቀችኝ 

‹‹ብዙ ጊዜ አዎ…….?››መለስኩላት

‹‹እና እንዴት አደረግክ….?››

‹‹ቆይ ዛሬ…ቆይ ነገ…በገመድ ተንጠልጥዬ ብሞት ይሻላል ወይስ መድሀኒት ልጋት……….?ከፎቅ ላይ እራሴን ልፈጥፍጥ ወይስ የሚበር መኪና ውስጥ እራሴን ወርውሬ ይጨፍልቀኝ….? ብዬ ሳማርጥ በአንዱ መወሰን አቅቶኝ ስዋልል ቆይና ሁለት የምወዳቸው ሰዎች ወደአዕምሮዬ ሲመጡ ደግሞ እስኪ ቢያንስ ለእነሱ ስል  ብዬ  እታገሳለሁ..ከዛ ቀስ በቀስ ያ ስሜት ይጠፋል ወይም ይደበዝዛል…ቢያንስ ለጊዜውም ቢሆን ››
‹‹ለሁለት ሰዎች ስትል….?››


            ይቀጥላል

#ክፍል 53,,እንዲለቀቀ 👍(5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ



‹‹አዎ…እናቴ እና ሰላም ያልኩሽ የማፈቅራት ልጅ ትዝ ሲሉኝ››
-‹‹በዛ ሰዓት ላይ ሁለቱም ባይኖሩ ኖሮ…..መቼም እንዳማታገኛቸው እርግጠኛ ሆነህ ቢሆን ኖሮስ….?››ዘግናኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ

‹‹እኔ እንጃ…እንዳልሞት የሚያደርገኝ ምንም ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም››ስል በታማኝነት መለስኩላት፡፡

‹‹ለምን….?››ጠየቀችኝ
‹‹ሁለቱ መላ አለሜ ናቸው…እነዚህ የነገርኩሽ ሁለቱ ሴቶች እና ሌላው ዓለም እኔንም ጨምሮ በሌላ ሚዛን ቢሆን ሚዛን ሚደፉት እነሱ ናቸው…..ስለዚህ እነሱ  የሌሉበት  ዓለም ምን ይረባኛል…››

‹‹አየህ ትክክል ብለሀል..እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ አንተ አንደገለጽከው ነው…እስከአሁን እራሱ ለምን እንደቆየሁ አላውቅም…….?››ብላ የሆነ አዲስ ነገር እንደተገለጽላት ተመራማሪ  ፈገግ ብላ ከተቀመጠችበት  ተነሳች ‹‹ እንሂድ ›› ብላ ጠርሙሷን ይዛ ምንጣፉን ባለበት ጥለ መራመድ ጀመረች…

-‹‹እንዴ ወዴት….? ››

‹‹ወደቤት ….ወደቤት መልሰኝ››

ደነገጥኩ…. ሳላስበው የማይሆን ነገር እንደተናገርኩ ገባኝ…ገደል አፋፍ ላይ ያለን ሰው ከኃላ መግፋት አይነት የቀሺም ሰው ተግባር ነው የሰራሁት..

‹‹ምንጣፉስ..››

ግዴለሽ በሆነ የድምፅ ቃና‹‹ከፈለከው ያዘው›› አለችኝ፡፡ጠቅለል ጠቅለል አደረኩና ወስጄ ኮፈን ውስጥ ከተትኩት፡፡ከዛ ወደመኪናው ገባሁና ወደኃላ አዙሬ የመልስ ጉዞ ….ብራዩ እንደደረስን የሆነ ነገር ማድረግና አሁን ካለችበት ስሜት እንድትዘናጋ ማድረግ እንዳለብኝ   ወሰንኩ…

‹‹..በጣም አመመኝ..››አልኳት …ቀና ብላ አየችኝና ምንም ሳትናገር መልሳ ወደ ሃሳቧ ተመለሰች…..መኪናዋን ወደዳር አውጥቼ አቆምኩ

‹‹ምነው….?››ኮስተር ብላ

‹‹ሆዴን ቆረጠኝ ››

‹‹ማለት….?››

‹‹እኔ እንጃ እራበኝ መሰለኝ..ከነጋ ምንም አልቀመስኩም… ለዛ ይሆናል..ረሀብ ደግሞ አልችልም››

‹‹እና ምን ይሻላል ….?››አለች እንደመበሳጨት ብላ

‹‹በቃ እኔ ሳልበላ መንዳት አልችልም….››

‹‹እሺ ጥሩ  ቁልፉን ስጠኝ…. እኔ ጊዜ ማባከን አልፈልግም …አንተ ብላና በትራንስፖርት ና››የሚል ሀሳብ አቀረበች

‹‹ለምን የሚሆን ጊዜ ነው ማባካን የማትፈልጊው….?››ስል ጠየቅኳት፡፡

‹‹እቤት ተመልሼ በፍጥነት ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ››

‹‹እሺ ነይ…አልኩና ቁልፉን ነቅዬ ከመኪናው ወረድኩ.. እሷም ካለችበተ የኋላ ወንበር ወርዳ ወደጋቢናው ስታመራ ፈጠን ብዬ ሁሉንም በር ጠረቀምኩትና ቁልፍን እያንቀጫጨልኩ   በአካባቢው ወደአለ ሆቴል ጉዞ ጀመርኩ

‹‹ምን እያደረክ ነው….?››

‹‹ምሳ በልቼ እቤትሽ አደርስሻለሁ..አንቺ ስለጠጣሽ መንዳት አትችይም…››

‹‹ምኑ ነህ..….?አሁን ለአንድ ቀን ባትበላ አትሞት…ደግሞ ብትሞትስ ከመኖር ምን ሲገኝ…››

‹‹ግድ የለም.. ልብላና አብሬሽ እሞታለሁ››

‹‹መቀለድህ  ነው..….?››ተከተለችኝና ከፊት ለፊቴ ወንበር ስባ ተቀመጠች…ምግብ አዘዝኩ እስኪመጣ ወሬ ጀመርን 
‹‹በነገራችን ላይ አባትሽን በቅርብ አይቼው አላውቅም..?››

‹‹የለም››

‹‹የት ሄዱ….?››

‹‹ወደ ውጭ ሄዷል››

‹‹አሀ …ለዛ ነዋ እንዲህ ዓለም ድብልቅልቅ ያለችብሽ….?››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ….?››

‹‹በአባትሽ እና በአንቺ መካከል ያለውን ግንኙነት እና ቀረቤታ እኮ ሙሉ ሰፈሩ ነው የሚያውቀው.. እንኳን እኔ ቀርቶ የዛሬ አመት እዛ ሰፍር የገባ ሰው ሳይቀር ያውቃል…››

‹‹አንዴ አንተም እኛ ሰፈር በቅርብ የገባህ መስሎኝ….  ባልሳሳት ሁለት  አመት ..ከዛ ይበልጥሀል..?››

‹‹የእውነትሽን ነው..አታውቂኝም….?›› በእድሜዬ  ከደነገጥኩት በበለጠ መጠን ደንግጬና ተሸማቅቄ ጠየኳት

‹‹ማለት አንተ ታውቀኛለህ እንዴ….?››

……የምመልሰው ነገር ሲጠፋኝ  ሳቅኩ

‹‹የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ እንዴ…››

‹‹አይ ታውቀኛለህ ስትይ ገርሞኝ ነው….ራስህን ታውቃለህ ወይ ብለሽ ብትጠይቂኝ ይሻላል..ግንባርሽ ላይ ያለውን ስንጥቅ ጠባሳ ምን እንደሆነ ልንገርሽ…….?››

‹‹እንዴት ልትነግረኝ ትችላለህ..….?

እሱ እኮ እፃን ሆኜ የሆነ ነገር ነው››

‹‹አዎ ቄስ ትምህርት ቤት አባ ገብረክርስቶስ ጋር ስንማር ድብብቆሽ በምንጫወትበት ጊዜ ልትደበቂ ስትሮጪ  አደናቅፎች ወድቀሽ ብረት ግንባርሽን ሰንጥቆሽ አይደል…?››

አይኖቾ ፈጠጡ ‹‹እንዴ !!!አዎ ትክክል ነህ ..ማነህ አንተ….?..››

‹‹ኤርሚያስ››

‹‹ኤርሚያስ ..ኤርሚያስ እንዴ ኤርሚያስ ካሳ እንዳትሆን……….?››የሆነ የቆየ ህልም የማስታወስ ያህል ተደንቃ

‹‹አዎ ነኝ››

‹‹ታዲያ በጣም እኮ ነው የተቀያየርከው…አረጀህ… በጣም…ደግሞ ከሀገር  ወጥተህ አልነበር…..….?››

‹‹ኦዋ ሁለት  ዓመት አለፈኝ  ተመልሼ   ከመጣሁ..››

‹‹እና ይሄን ሁሉ ጊዜ   ሳታናግረኝ…….?››

‹‹እኔ እንጃ እንደመጣው ጥሩ ስሜት ላይ ስላልነበርኩ ላናግርሽ ጉልበቱ አልነበረኝም….››

‹‹ትክክል አልሰራህም…ጓደኛች ነበርን አይደል….….?.››መገረሟ ሳይገታ የታዘዘው ምግብ መጣ..እሷ ለምግቡ  ደንታም ሳይሰጣት ብላክ ሌብል ታመጣልኝ አለችው አስተናጋጁን….

‹‹አይቻልም..››አልኳት ቆፈጠን ብዬ
‹‹ለምን…….?ዝም በለውና አምጣልኝ ››አምጣላት …ግን ከበላሽ ነው የምትጠጪው..

‹‹አረ ባክህ ››

‹‹እውነቴን ነው››

‹‹እሺ ..››አለች.. እየቆነጠረች ከምግቡ ለመቅመስ ሞከረች እኔ እየለመንኩም እያስገደድኩም አንድ ሶስት ደህና ጉርሻ አጎረስኳት…
ከዛ መጠጧን ጀመረች ‹‹….ይገርማል  ..ዱርዬ ነበርክ እኮ …አሁን የተለየ እና የተረጋጋ ሰው ሆነሀል››

‹‹ምን ታደርጊዋለሽ ህይወት ትገራሻለች… ኑሮ ይሞርድሻል…መከራ ያስተካክልሻል ወይም ያበላሽሻል፡፡››

‹‹ለምን አንተም አትጠጣም….?››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን መኪናውን ማን ይነዳል…….?››

‹‹ግድ የለም ..የሆነ መላ እንፈልጋለን..….?››ልክ ቅድም ላንቺ ታዝዤ አብሬሽ መጠጣት እንደጀመርኩ ..ለእሷም ተስማምቼ አዘዝኩ …የልጅነት ነገር ምንም ሳይነሳ የቀረ ትውስታ የለም..ከማስበው በላይ ስለልጅነታችን ታስታውሳለች…ያ ደግሞ ደስታ ፈጠረብኝ….እሷም ከነበረችበት ስሜት በሆነ ጠብታ ቢሆንም የመረጋጋት ሁኔታ  ታየባት
ተመልሰን ቅድም ለቀነው ወደወጣነው ቤት የሄድን
 
‹‹እየተቆነጠረ የሚመጣው ውስኪ ሊያረካን ስላልቻለ..ሙሉውን አዘዝን…››

ኬድሮን ቆይ ቆይ ..››ብላ አስቋመችው 

‹‹ምነው ደከመሽ..እንተኛ?››

‹‹አይ አንዴ ሽንቴን….›› አለችና ከመኝታዋ ወርዳ ወደሽንት ቤት ሳይሆን ወደሳሎን ሄደች….ይህቺ ታሪኳ ለሊቱን ሙሉ የተነገረላት  ፍቅረኛው የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እየተሰማት ነው ..አዎ ስሜቷ እየነገራት ነው….ለዚህ ነው ወደሳሎን የሄደችው …ንስሯን ፈልጋ..‹‹አይ የኔ ነገር ..››አለች . የዚህ ባለ ላዳ ታሪክ ንስሯንም እንድትዘናጋ ስላደረጋት እራሷን ታዘበች…ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት እንዳለ ተኝቷል….አስነሳችው….‹‹ ‹‹አብሮኝ ያለው ልጅ ፍቅረኛ..ማለቴ የሚወዳት ልጅ ችግር ላይ ትመስለኛለች..አሁኑኑ ሄደህ ያለችበትን ሁኔታ አጣራልኝና  ና…አሁኑኑ……ትንሽ ከዘገየን የሚረፍድብን ይመስለኛ…››
ነቃ ለማለት እዲረዳው  ክንፉን አርገፈገፈ …..የሳሎኑን በር ከፈተችለት… ከሶፋው ላይ ተንሳፎ ጭንቅላቷ ላይ አረፈ…ክንፉን እያማታ ከጭንቅላቷ ላይ ተነስቶ በሩን አልፎ ጭለማ ውስጥ ሰመጠ…..
ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና  ወደአልጋው ሳይሆን  ወደ  ሻወር ቤት ገባች …

ሻወር ቤት ገብታ ሽንቷን ብቻ ሸንታ አልወጣችም..የሻወሩን ውሀ ከፈተችና ልብሷን አወላልቃ ገባችበት….አዎ በሆነ መንገድ መረጋጋት ፈልጋለች……. ‹‹ምንድነው ያጣሁት ነገር…….?.ከሁለት የተለያዩ  ፍጥሮች መፈጠሬ ስለፍቅር ያለኝን ስሜት አበላሽቶብኛል እንዴ….….?ለምንድነው እኔስ መላኩ  ሰሚራን ባፈቀረበት መጠን ላፈቅር  ማልችለው..….?ለምንድነው ይሄ አልጋዬ ላይ ሆኖ የሚጠብቀኝ ኤርምያስ ሰላምን ባፈቀራት መጠን በዚህ የህይወቴ ረጂም ጊዜ ሁሉ ቢያንስ ለአንድ ጊዜ እንኳን  ማፍቀር ያልቻልኩት….….?››በአዕምሮዋ እያተረማመሱ ያሉ ጥያቄዎች ነበሩ….

ውሃው ከላይ እየተወረወረ ሰውነቷ ላይ እያረፈ ነው..ዝም ብላ ቆማ በሀሳብ ውስጥ እየነሆለለች ነው….አሁን እነሱ ታሪካቸውን ለማንም ሰው ቢናገሩ ሰሚው ሰው ውስጡ በሀዘን ይተረማመሳል..እንባ አውጥቶም ሊያለቅስ እና  በዛም  መጠን ሊያዝንላቸው ይችላል…እሷ ግን ቀናችባቸው እንጂ ልታዝንላቸው አልቻለችም …ለምን በዚህ መጠን የማፍቀር ስሜት ከውስጧ መብቀል አቃተው…….?እንዴት ሰው በህይወት ዘመኑ ቢያንስ አንዴ በፍቅር ፍላፃ ልብ አይሰነጣጠቅም….?እንዴት በእድሜው አንዴ እንኳን በፍቅር እቅፍ አጥቶና ምቾት ነስቶት ሲነፈርቅ አይታይም…….?ለፍቅር መሸነፍ እኮ ድክመት አይደለም ሰዋዊነት እንጂ…..እሷ የወሲብ ረሀብ ያንን ተከትሎ የጭን መብላት አባዜ ብቻ ነው የሚያሰቃያት….ሙላት ያለው የፍቅር   ስሜት ሳታጣጥም ይህችን ምድር ልትለቅ አራት ቀን ቀራት ..!!!አራት ቀን ብቻ…

ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 54,,እንዲለቀቀ 👍(15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Today's Combo...🚫
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_አራት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››
ሳቋ አመለጣት ..ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች……

‹‹ይሄውልህ…››ብላ የውስጧን ልትግረው ስትጀምር ባለ ላዳው ማለት ኤርሚያስ ሆዬ ከመኝታ ቤት ውልቅልቁ የወጣውን ሰውነቱን እየጎተተ ሳሎን ደረሰና ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አንዴ እሱን አንዴ እሷን እያየ  ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ሲዋልል እሷንም ንግግሯን እንድታቆርጥ አደረገት ….

     ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 55,,እንዲለቀቀ 👍(15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Today's Combo...🚫
Today's Combo...🚫
😎ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_አምስት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን  አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ

‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››

ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››

‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››

ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ

ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት  ጥያቄ  ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና  ሳይጠይቃት መለሰችለት….

‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››

‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት

‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን  አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››

‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ  ነበር የቀራት….. 

እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች   ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው

‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡

‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››

‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን  ለቆ ወጣ……

‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች

….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን  የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና  ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////

ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ  ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን  እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››

‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ›› 

‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››

‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››

‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››

‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››

‹‹ወዴት....?››

‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››

‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››

ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››

‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››

‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ  ሰውና በ20  ደቂቃ  ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው

‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››

‹‹እራስህንማ  እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››

‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት  ኮስተር ብሎ

‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››

‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ  ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ  ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››

‹‹ከዛ ምን…..?››

‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››

‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››

‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››

‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ  በመግባት  እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ  ጉብ አለ….

ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..

‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›

‹‹የማታው ንስር አይደል..?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ምን ይሰራል  እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››

‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››

‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት  

‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››

‹‹እኔና ንስሬ››

ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››

‹‹የምሬን ነው…›

‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን  ማወቅ አልቻልኩም››
‹‹እኔ ግን  አውቄያለሁ››
ሱሪውን ለብሶ ከላይ እራቃኑን እንደሆነ አጠገቡ ያለ ወንበር ላይ ቁጭ አለ‹‹እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…..?እንኳን የእሷን  ታሪክ ይቅርና እኔን  ካወቅሽ እራሱ 24 ሰኣት አልሞላውም››
‹‹የፈለኩትን ነገር ማወቅ እችላለሁ…ንስሬ ከረዳኝ የፈለኩትን ነገር….››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እሺ ጥቂት ደቅቃ ታገሰኝ ››አልኩና ወዲየው ትኩረቴን ወደንሰሬ በመመለስ ከአዕመሮው ጋር ተቆራኘው…..ለሶስት ደቆቃ ከቆየሁ በኃላ

‹‹እሺ ስማኝ …እንድታምነኝ አንተ ብቻ የምታውቀውን የራስህን ሚስጥር ነግራሀለው….ደቡብ አፍሪካ ለ2 ወር ታስረህ ነበር….ከሶስት ሴቶችና ከእንድ ተካልኝ ከሚባል ልጅ ጋር በደባልነት አንድ  ቤት ውስጥ ትኖሩ ነበር…ከሶስቱ ሴቶች  መካከል  ሁለቱን ሴቶች ታወጣቸው ነበር…..››

‹‹በቃ በቃ…..››

‹‹ያው እንድታምን ብዬ ነው…..››
‹‹አመንኩ እኮ …አደገኛ ጠንቆይ ነሽ….ምክንቱም ይሄንን ታሪኬን ለማንም ተናግሬ አላውቅም ..በተለይ የሁለቱ ሴቶችን ጋር ያለኝን ግንኝነት››

‹‹ምክንያቱም መንታ እህትአማቾች ስለሆኑ ትክክለኛ ስራ እንዳልሰራህ ስለሚሰማህ እና ፀፀት ስላለብህ..››ብላ ጨመረችለት፡፡

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…ግን አሁን ሰላም ምንድነው ችግሯ..ከፍቅረኛዋ ጋር ተጣልታ ነው…..?››

‹‹ፍቅረኛ የላትም….ማለቴ በፊት  ነበራት… ከተለያዩ ግን  አመት አልፏቸዋል…እረስታዋለች››

ፈገግ አለ‹‹ይሄንን በመስማቴ ደስ አለኝ….እሺ ሌላ ታዲያ ምን ሆና ነው…..? ስራ ተበላሽቶባት ነው..?››
‹‹ያለችበትን ችግር ምትገምተው አይደለም..››

‹‹እሺ ንገሪኛ..? ››

‹‹አባቷ ሞቶባት  ነው..››

መጀመሪያ ተደናግጦ ከተቀመጠበት ተነሳ..ከዛ መልሶ ቁጭ አለ..ለደቂቃ ተከዘ

‹‹እስከአሁን ያልሺው ሁሉ ትክክል ነው..ይሄ ግን የማይመስል ነው..አልነገርኩሽም እንዴ አንድ ሰፈር እኮ ነው የምንኖረው ..ዕድራችንም አንድ ነው….ቢያንስ እኔ ባልሰማ እናቴ ሰምታ ትነግረኝ ነበር..በዛ ላይ   እሷን የሀዘን ልብስ ለብሳ አያት ነበር ….››
‹‹አባቷ እንዲቀበሩባት ስለማትፈልግ ..መኝታ ቤቷ ውስጥ እንዳይበሰብሱ በማድረግ  ድብቃቸዋለች››

‹‹እንዴ!!!! ታዲያ ዝም ትያለሽ እንዴ....?እራሷን ብታጠፋስ....?ይሄንን ሁሉ ቀን የአባቷን እሬሳ ታቅፋ ለብቻዋ ስታድር ጄኒ ቢያጠናግራስ .. ..?እንዴ በቃ ብታብድስ…..?››ይሄን ሁሉ ሚናገረው በጥድፊያ ልብሱን እየለበሰና በተመሳሳይ ጊዜ ወደውጭ እየተንደረደረ ነው….እሷም ከኃላው  ኩስ ኩስ እያለች   ሚለውን ታዳምጣለች…

‹‹እውነት ከሆነ በጣም ነው የማዝንብሽ…..እንዳወቅሽ ልትነግሪኝ ይገባ ነበር…አንድም ሰከንድ ማባከን አልነበረብሽም ..አባቷን እንዴት እንደነፍሷ እንደምትወዳቸው ብታውቂ እንደዚህ ቸልተኛ አትሆኚም ነበር….››ወቀሳውን ሳያቆርጥ ከግቢው ወጥቶ በእግሩ ሊነካ ሲል…

‹‹ና በመኪና ላድርስህ….››ስትለው በደመነፍስ ተከተላትና ማጉረምረሙን ሳያቆርጥ  መኪና ውስጥ ገባ….ሞተሩን እስነስታ መንዳት ጀመረች..ፀጉሩን ይነጫል ….ጨንቅላቱን ይቀጠቅጣል..ከንፈሩን ይነክሳል
‹‹እንዲህ ከሆንክማ እንዴት ልንረዳት እንችላልን....?››አለችውት የእሱም ከቁጥጥር ውጭ መሆን አሳስቧት

‹‹እንዴት ልሁን ታዲያ …..?ሳለምዬ የአባቷን ሬሳ ታቅፋ አምስት ቀን ብቻዋን ባዶ ዝግ ቤት ውስጥ አድራለች እያልሺኝ እኮ ነው…››

‹‹እኮ አሁን ካለችበት ሁኔታ ይልቅ ወደፊት የሚከሰተው ነገር ይበልጥ ይጎዳታል… ስለዚህ እንዴት ልንረዳ እንደምንችል ለማሰብ ያንተ መረጋጋት ያስፈልጋል እያልኩህ ነው››

‹‹እሺ ንጂው…በእግዚያብሄር ፍጠኚ …ደግሞ ንስርሽ ከኃላ እየተከተለን ነው››

‹‹አዎ እሱ በጣም ያግዘናል…››

‹‹በፈጠረሽ …ምንም ነገር እንድትሆንብኝ እልፈልግም›››

‹‹አይዞህ…. ምንም አትሆንብህም…››

ከ25 ደቂቃ በኃላ ሳሪስ ደረሱ ..መኪናውን አቁመው ወደበራፍ  በመከተታል ተንደርደረው ደረሱ... ንስሯ ቀድሞ ግቢው ውስጥ ገባ..መጥሪያውን ተጫኑ..ደጋግመው  ተጫኑ…. እጃችን እስኪዝል በየተራ አንኳኩ ..ከውስጥ ከፋች ሊመጣ አልቻለም..

‹‹ትግስቴ አልቆል…  የግንቡን አጥር ዘለዬ  ልገባ ነው….››አላት በጭንቀት 

‹‹ግንቡ ላይ የተሰካውን የጠርሙስ ስብርባሪ እንዴት አድርገህ ታልፈዋለህ..?››

‹‹የራሱ ጉዳይ…የቆራረጠኝን ያህል ይቁረጠኝ… ››

‹‹ቆይ የተሻለ ዘዴ አለኝ ››አለችው
‹‹ምንድነው....?››

ንስሯን ጠራችው … ከገባበት ግቢ እየተመዝገዘገ መጣና  የፈለገችውን ሳትነግረው በመረዳት የለበሰችውን ልብስ አንገቷ አካባቢ በመንቁሯ ይዞ እያሽከረከረ ወደአየር ላይ ይዞት በመውጣት አጥሩን አሻግሮ ጊቤው ውስጥ ወለል ላይ አሳረፈት…  ከውስጥ የተቀረቀረውን በራፍ  ከፈተችለት…ኤርምያስ ተንደርድሮ ገባ..

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው....?ምንድነሽ አንቺ..?›› እያለ ገፍትሯት ወደሳሎን ሮጠ… ሊያንኳኳ ሲሞክር ብርግድ ብሎ ተከፈተለት..ተከትላው ገባች..ወደየት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት ሲደነጋገር ቀደመችውና ወደመኝታ ቤቱ አመራች..ምክንያቱም ቅድም ንስሯ በምናብ  እቤቱን በደንብ ስላስቃኛት ስለነበር  ታውቀዋለች..፡፡

መኝታ ቤት ሲገቡ …ሰላም ወለል ላይ ተዘርራ ግንባሯን ግዙፉ ፍሪጅ ላይ እስደግፋ በአንድ  እጇ የመጠጥ ጠርሙስ ጨብጣ በሌላ እጇ  የተለኮሰ ሲጋራ  ወደ ከንፈሯ በመላክ ወደውስጥ እየመጠጠች  ጭሱን  ወደውጭ እያትጎለጎለች  ትታያለች  …ከጎኖ 10 ሜትር የሚሆን የተጠቀለለ ሰማያዊ ሲባጎ ገመድ ይታያል….. ኤርምያስ ከእሷ ቀድሞ እሷንም ተራምዶ ወደፍሪጁ ሄደና ውስጡ ያለውን አየ…….

ወደኬድሮን በመዞር  ‹‹…እውነትሽን ነው…..››በማለት ከወገቡ ሽብርክ ብሎ ሰላም ጎን ወላሉ ላይ ተዘረፈጠ..እሷ በቃ ትንኝም በአካባቢዋ ያለ አልመሰላትም.. ፍጽም ደንዝዛለች…ጭርሱኑ ጠፍታለች…..


     ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 56,,እንዲለቀቀ 👍(20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄