ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
194K subscribers
280 photos
1 video
16 files
208 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ሁለት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ማርጋሬት ከእንቅልፏ  ስትነቃ ሃሳብ ውስጥ ገባች፡: ዛሬ ለአባቴ ቁርጡን እነግረዋለሁ  አለች በሆዷ አሜሪካ ሲደርሱ ከእነሱ ጋር
እንደማትኖር ከቤት ወጥታ ቤት ተከራይታ እና ስራ ይዛ ልትኖር እንደሆነ
ትነግራቸዋለች፡፡ መቼም አባቷ ይህን ሲሰሙ ኮረንቲ ይጨብጣሉ፡፡

ማርጋሬት ነገሩን ባሰበችው ቁጥር ፍርሃትና ሃፍረት ይሰማታል አባቷን ለመቃወም ስትነሳ የሚሰማት ይኸው ነው፡፡ አሁን አስራ ዘጠኝ ዓመቴ ነው፡፡ አሁን ልጅ አይደለሁም፡፡ ትናንት ከድንቅ ሰው ጋር ወሲብ
ፈጽሜያለሁ፡፡ ታዲያ ለምንድነው የምፈራው? ስትል ታስባለች፡

ለምን አባቷ ሁልጊዜ እንደ አውሬ በግርግም ውስጥ እንደሚዘጉባት አይገባትም፡ ኤልሳቤትንም እንዲሁ ነበር የሚያደርጓት፡፡ ፔርሱን ግን ለቀቅ አድርገውታል፡፡ ሴት ልጆቻቸውን እንደ ጌጣጌጥ ነው የሚቆጥሯቸው: አንድ
የሆነ ስራ እንስራ ብለው የተነሱ እንደሆን ቁጣቸው ለጉድ ነው፡፡ ለምሳሌ
ዋና እንዋኝ ወይም ብስክሌት እንንዳ ብለው ቢነሱ በቃ አለቀላቸው፡
ልብስ የፈለጉትን ያህል ቢያወጡ ምንም የማይሉትን ያህል መጽሐፍ
እንግዛ ቢሉ ጸጉራቸው ይቆማል፡

ማርጋሬት ይህን ባሰበች ቁጥር ሽንፈቷ አይደለም የሚያሳምማት፡፡አባቷ የእሷን ሀሳብ ውድቅ ለማድረግ የሚያወርዱባት የስድብ ውርጅብኝና
የፌዝ ጋጋታ እንጂ፡

ብዙ ጊዜ አባቷን ለማታለል ሞክራለች፡ የተሳካላት ግን ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው፡፡

ሁልጊዜም ከአባቷ ትዕዛዝ ውጭ የምትፈጽመው በሌሎች እርዳታ
ነው:: ስለወሲብ ያስተማረቻት ዘመዷ ሞኒካ ናት፡፡ ፔርሲ ተኩስ አስተምሯታል፡፡ ሹፌራቸው መኪና መንዳት አስለምዷታል አሁን ደግሞ
ሄሪና ናንሲ ሌኔሃን ነጻነቷን እንድትቀዳጅ ይረዷት ይሆናል።

አሁን ለየት ያለ ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ መኝታዋ ላይ ተጋድማ መላ አካላቷን ደባበሰችው፡፡ ከዚህ ቀደም ጸጉሯ የተንጨፈረረ ቅርጿ ደግሞ የማያምር አድርጋ ትገምት ነበር፡፡ አሁን ግን ገላዋን እየወደደችው
መጥታለች፡ ሄሪ ‹‹ቅርጽሽ ያምራል›› ብሏታል
አይሮፕላኑ ውስጥ የሰዎች ሹክሹክታና የዕቃ ኳኳታ ይሰማታል ተጓዦች ከመኝታቸው እየተነሱ ነው መጋረጃውን ገለጥ አድርጋ ስታይ ዱባው አስተናጋጅ ኒኪ የእናትና የአባቷን መኝታዎች ወደ መቀመጫነት እየቀየረ ነው፡፡ ሄሪ ሙሉ ልብሱን ለብሶ ቁጭ ብሎ በተመስጦ በመስኮት ወደ ውጭ ይመለከታል፡፡
እሱን ስታይ አፈረችና ሳያያት ወዲያው መጋረጃውን ዘጋችው::ከጥቂት ሰዓት በፊት በወሲብ ሲያብዱ ቢቆዩም አሁን ግን ሁኔታው
አሳፈራት።

ሌሎቹ ሰዎች የት ሄደው ይሆን?› ስትል አሰበች፡፡ ፔርሲና አባቷ ውጭ ወጥተው ይሆናል፡ አባቷ ለወትሮው በጧት ነው የሚነሱት፡ እናቷ
ግን በጧት መነሳት አይሆንላቸውም፡፡ ምናልባትም መታጠቢያ ቤት ይሆናሉ፡ ሚስተር መምበሪም በቦታው የለም፡፡

ማርጋሬት በመስኮት ስትመለከት ነግቷል፡፡ የሰማይ በራሪው አይሮፕላን
አንድ ትንሽ የወደብ ከተማ ዳርቻ ላይ ታስሮ ቆሟል፡ እንደገና መኝታዋ ላይ
ጋደም አለች፡፡ የለሊቱ ሁኔታ በዓይነ ህሊናዋ ድቅን አለ፡፡ የትናንቱ ቀን ድንግልናዋ የተወሰደበት ቀን አድርጋ ነው የቆጠረችው፡፡ ከኢያን  ጋር ስትፈጽም የነበረው ወሲብ ችግር ያልተለየውና ጥድፍ ጥድፍ ያለ ነበር፡
ከእሱ ጋር ወሲብ ከፈጸመች በኋላ ሁልጊዜ በእፍረት ትሸማቀቃለች፡ትናንት ከሄሪ ጋር ያደረገችው ግን አስደስቷታል፡፡ እያንዳንዱ የስውነት ክፍሏ እየተቆጠረና እየተዳበሰ የተፈጸመ ወሲብ ነበር፡፡ ምንም እፍረት ያልነበረበት፡፡ እንደ ሴት ራሷን የቆጠረችበት ወቅት ነበር፡፡ እንዲህ አይነት ወሲብ ከሄሪ ጋር በተደጋጋሚ መፈጸም አለብኝ አለች ለራሷ፡ የትናንት ማታው ትዝታ የወሲብ ፍላጎቷን ቀሰቀሰባትና ሰውነቷን አወራጨች።

ሄሪ የክት ልብሱን ለብሶ መስኮቱ ጋ ተቀምጦ በተመስጦ ሲያይ ሰርቃ
አየችው:፡ የሆነ ነገር እያሰላሰለ መሆኑን መልከ መልካም ፊቱ ነገራት::
ልትስመው ዳዳት፡፡ መጋረጃውን ገለጥ አደረገችና ‹‹እንደምን አደርክ ሄሪ አለችው፡፡

ድንገት የሰማው ድምጽ ሲሰርቅ እንደተያዘ ሰው አስደነገጠውና ደንብሮ
ዞር አለ፡፡ ሲያያት አየችውና ፈገግታ ተለዋወጡ፡፡ እንደ ጅል ለረጅም ጊዜ ሲሳሳቁ ቆዩ፡፡ በኋላም ማርጋሬት አይኗን ሰበረችና ተነሳች።

አስተናጋጁ የእናቷን መቀመጫ ከሚያዘጋጅበት ቀና ብሎ ‹‹ደህና አደርሽ እመቤት ማርጋሬት ቡና ላምጣልሽ?›› አላት፡

‹‹ኒኪ ይቅርብኝ አመሰግናለሁ›› አለችው ሁኔታ እንደ ጭራቅ ለራሷ
አስፈራት፡፡ ጸጉሯ ተንጨፍርሯል፡፡ ልብስም በቅጡ አልለበሰችም፡፡ ሄሪ ግን ጢሙን ተላጭቶና ዘንጦ አዲስ ሳንቲም መስሏል

ብትስመው በወደደች፡፡

ነጠላ ጫማዋን እግሯ ላይ ሰካች፤ ሌሊት ለወሲብ ስትቻኮል ሄሪ አልጋ
ስር እንዴት እንደተወችውና አባቷ ሳያይዋት እንዴት አድርጋ አንስታ አልጋው ውስጥ እንደከተተችው እየታወሳት፡፡

የሌሊት ልብሷን ስትለብስ እርቃኗን ስለነበረች ሄሪ ጡቶቿ ላይ ዓይኑን
ተከለ፡፡ ቢያያትም ምንም አልመሰላትም፡፡ ሄሪ ጡቷን ሲያይ ደስ አላት፡ የሌሊት ልብሷን መቀነት ጠበቅ አደረገችና ጸጉሯን አሻሸች፡፡
ኒክ ስራውን ጨረሰ፡፡ ሄሪን መሳም ስለፈለገች ኒኪ ከዚያ ቦታ ቶሎ እንዲ ሄድላት ፈለገች፡፡ ኒኪ ግን የልቧን ፍላጎት ስላላወቀ መቀመጫውን ላዘጋጅልሽ?›› አላት

እሺ›› አለች ውስጧ በንዴት እየጨሰ፡፡ ሄሪን ድጋሚ የምትስምበት ጊዜ እንደሰማይ ራቃት፡፡ የመታጠቢያ ዕቃዎቿን የያዘችበትን ቦርሳዋን
አነሳችና ሄሪ በሀዘኔታ እያያት ተነስታ ሄደች፡፡

ሌላው አስተናጋጅ ዴቪ መብል ክፍሉ ውስጥ ምግብ እየደረደረ ነው፡፡
እግረ መንገዷን አንድ የእንጆሪ ፍሬ ሰርቃ አፏ ላይ አደረገች፡ ስትሄድ
ብዙዎቹ መኝታዎች
ወደ መቀመጫነት ተለውጠዋል አንዳንዶቹ
ተሳፋሪዎች ቡና እየጠጡ ነው፡ ሚስተር መምበሪ ከሳይንቲስቱና ከባሮን
ጋቦን ጋር ወሬ ይዟል፡፡

መታጠቢያ ክፍሉ ውስጥ ስትገባ እናቷ መስታወት ፊት ቁጭ ብለው ይዋባሉ፡፡ እሳቸውን ስታይ እፍረት ተሰማት፡ ‹እናቴ ካለችበት አንድ ሁለት ርምጃ ርቀት ላይ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር አደርጋለሁ? አለች በሆዷ፡
ጉንጮቿ በእፍረት በርበሬ መስለዋል፡፡ ‹‹እንዴት አደርሽ እማማ›› አለች

‹‹ምን ሆነሽ ነው ፊትሽ እንደዚህ የቀላው? እንቅልፍ አልተኛሽም እንዴ?›› ሲሉ ጠየቋት፡፡

‹‹ኧረ በደምብ ተኝቻለሁ›› አለች ማርጋሬት፡፡ ‹‹አንዲት ፍሬ እንጆሪ ከጠረጴዛ ላይ አንስቼ ስለበላሁ ነው›› አለችና መጸዳጃ ቤት ጥልቅ አለች ከዚያም መታጠቢያው ላይ ውሃ ሞላችና ፊቷን ታጠበች፡:

ትናንት የለበሰችውን ልብስ ዛሬም በመልበሷ ደስ አላላትም፡፡ የታጠበ
ልብስ ብትለውጥ በወደደች: አንገቷ ስርና ጡቶቿ ውስጥ ሽቶ
አርከፈከፈች፡፡ ሽቶ ለይቶ የሚያውቅ ያየችው ወንድ ሄሪን ብቻ ነው፡፡

ረጅም ጊዜ ፈጅታ ጸጉሯን አበጠረች፡፡ ያላት ውበቷ ጸጉሯ ስለሆነ ለጸጉሯ የማትሆነው የለም፡፡ መልኬን ለማሳመር ስል ማድረግ ያለብኝ ሁሉ
አደርጋለሁ አለች ለራሷ፡ እስካሁን ስለመልኳ ተጨንቃ አታውቅም፡፡ ዛሬ ግን አስተሳሰቧ ተለውጧል፡፡ ገላዬን ልቅም አድርጎ የሚያሳይና ረጅም ታኮ
ጫማ ያስፈልገኛል፡፡ ከገላዬና ከጸጉሬ ከለር ጋር የሚሄድ ልብስ መምረጥ
አለብኝ፡፡› አሁን የለበሰችው ልብስ እንደ ሽክላ ቀይ ነው፡፡ እንዲያው ዝም ብሎ የወረደና ቅርጸ ቢስ መሆኑን በመስታወት አይታ ትከሻውጋ ቀጥ ያለና
ወገቡ ጋ በመቀነት ሸብ የሚደረግ ቢሆን ጥሩ ነበር ስትል ተመኘች።ሜክአፕ ባትቀባባም ያላት መልክ በቂ ነው፡ ጥርሶቿም አያሳጡም፡፡

‹‹ከሚስተር ቫንዴርፖስት ጋር ለመጫወት ልትሄጂ ነው አይደለም?››
አሉ እናት፡፡
📕ተአምረተ_ኬድሮን

#ክፍል_አርባ_ሁለት

#ተከታታይ ልቦለድ

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

የጊቢዋ አጸድ ውስጥ ባለ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ የወፎችን ዝማሬ እና የዛፎችን ሽውሽውታ እየታዘበች በሀሳብ እየናወዘች ነው፡፡ያው በህይወቷ አዲስ ክስተት ተከስቷል … አንድ ሰው ላይ ለቀናቶች ሀሳቧ እንደተጣበቀ ነው….ያ ባሪያ ልጅ ልቧን ቅልጥ ሀሰቧን ውስውስ ነው ያደረገባት፡፡ሰሚራ ከምትባለው ፍቀረኛው ጋር ያለውን ታሪክ እና የፍቅር ትስሰር  ሙሉውን ታሪክ ለመጨረስ እራሱ አቅም አነሳት...ስለሱ ከማሰብ የሚያሰንፋት መስሎ እየተሰማት ነው….‹‹ለማንኛውም እስቲ  ታሪኩን ልጨርስ›› ብላ ተቀመጠች …ግን ታሪኩን ለመጨረስ  ንስሯ ያስፈልጋታል..እንደምታየው ደግሞ አሁን ጊቢ ውስጥ  ንስሯ አይታያትም …ብዙም ሳያስጠብቃት ከሄደበት ተመልሶ መጣ 
ቀጥታ ወደዛ ወደተለከፈችበት ታሪክ አመራች …አእምሯዋን ከንስሯ አዕምሮ ጋር በተለመደው መንገድ አቆራኘችው..አዎ አገኘዋቸው…ከከተማ እንውጣ ብለው ላንጋኖ ነው የሄድት …በሀይቁ ዳር በታነፀ ላውንጅ  የተዘጋ መኝታ ክፍል ውስጥ ናቸው፡፡
ህይወት ልክ እንደካርታ ጫወታ ነች…ይበወዝና ተጫዋች ለሆኑት  ኗዋሪዎቾ የሚታደል ዕጣ ፋንታ በሚሉት ምናባዊ ሀዲድ  የምትሸረብ…አጋጣሚ በተባለ የህይወት ሰንሰለታማ  ጉዞ ላይ በትክክለኛው ቦታ በትክክለኛው ጊዜ አንዱ ካንዱ በመገጣጠም መላተም እና በሌላ ገጽ ላይ  በሰከንድ ሽርፍራፊ ሰከንድ መዘግየት ተፈጥሮ ተፈላልጎም ሳይገናኙ  መተላለፍን በውስጧ የያዘች….
በጣርነው መጠን ማናገኝባት…ባመረትነው መጠን ማንሰበስብባት…በተመኘነው መንገድ ማንጓዝበት..እንደሎተሪ ዕጣ ብዙዎቻችን የምንከስርባት…የተወሰነው በማስተዛዘኛ የምንፅናናባት..ጥቂቶች ደግሞ እንደው ጠብታ  ላባቸውን በአልማዝ ተመንዝሮ እጃቸው ላይ የሚቀመጥላቸው …ውጥናቸውን አለም ጠቅላላ ተረባርቦ ከግብ የሚያደርስልቸው ከእርጥብ እድል ጋር የተፈጠሩ…ንግግራቸውን በደቂቃ አለም የሚያደምጥላቸው…እነሱ ለተከዙት አለም ተንሰቅስቆ የሚያለቅስላቸው …እንዲሁ መርቆ የፈጠራቸው አሉ፡፡ … እና ህይወት የካርታ ጫወታ ነች…የጫወታውን ህግ ግን ተፈጥሮዊ ብቻ አይደለም..ሰው ሰራሽም ጭምር ነው … 
ይሄንን ሀሳብ ያሰበችው ሰሚራ ነች ..ፍቅረኛዋ  መላኩ ደረት ላይ ጋደም ብላ እያሰላሰለች የምትገኘው፡፡እንዴት እንዲህ ልሆን ቻልኩ....?እንዴት ከበሽተኛዬ ጋር ፍቅር ውስጥ ገባሁ…...?አጋጣሚው ነው ወደዛ የገፋኝ ወይስ እራሴ ነኝ ፈቅጄ እና አስቤ ወደዚህ ደረቱ ላይ ወደተጋደምኩት ልጅ ልብ ውስጥ የገባሁት…...?
‹‹ምን እያሰብሽ ነው..?››ድንገት በጠየቃት ጥያቄ ለውስጥ ጥያቄዋ መልስ ሳታገኝ  አቋረጠችው፡፡
‹‹መቼ ጥለህኝ እንደምትሄድ እያሰብኩ ነው››አለችው…ለምን እንደዛ እንዳለችው ለራሷም አልተገለጸላትም… ..ምክንያም እያሰበች ያለችው ያንን እንዳልሆነ እሷና እግዚያብሄር ያውቃሉ….ሳታስብ ከንፈሯ ላይ የመጣላት ድንገታዊ መልስ የእውነት ስጋቷ አይደለም ማለት ግን አይቻልም…
‹‹የት ነው ጥዬሽ የምሄደው..?››
‹‹ወደኑሮህ ነዋ››
‹‹ኑሮ ማለት እኮ  የህይወት ደስታሽ የሚመረትበት ቦታ ነው….ማንም ሰው በህይወቱ የሚባክነው ያንን ቦታ ፍለጋ ነው…የደስታው ምንጭ የሚፈልቅበትን ጥግ ለማግኘት …የሰው ልጅ ስኬትም የሚለካው በዚህ ነው…እና እኔ እድለኛ ነኝ .ብዙም ሳለፋ በተዐምራዊ አጋጣሚ አንቺን አግኝቼያለሁ….እንዳገኘውሽ ያወቅኩት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ በቃ ስትስቂ ልቤ ትቀልጣለች…ትንፋሽሽን ወደውስጤ ስስበው በሰውነቴ ውስጥ በስብሰው  ያበቃላቸው ሴሎቼ እንኳን መልሰው ህይወት ሲዘሩ ራሱ ይታወቀኛል…..ከጎኔ መኖርሽን ሳይ ዓለም ጠቅላላ ተሰብስባ ከእጄ የገባች ይመስለኝና ልቤ በኩራት አብጣ ልትፈነዳ ትደርሳለች..እና ከአንቺ ተለይቼ መሄድ ማለት ወደባዶነት ሸለቆ ተወርውሮ መከስከስ ማለት እንደሆነ ሚጠፋኝ ይመስልሻል …...?አሁን ባለሁበት ሁኔታ ከንቺ ውጭ ኑሮ ማለት ሲም ካርድ የሌለው ባዶ የሞባይል ቀፎ መሆን ማለት ነው…..››

ከትከት ብላ ሳቀች..ኪ…ኪ..ኪ…እንዴ ‹‹ነገሩን ሁሉ እኮ ስነጽሁፋዊ አደረከው…ከእኔ ከመገናኘትህ በፊት ነጋዴ ነበርኩ ብለሀኝ አልነበር እንዴ..?››

‹‹አዎ በጣም ጎበዝ ነጋዴ ነበርኩ…ምን ተፈጠረ..?››

‹‹አይ ንግግርህ የደራሲ እንጂ የነጋዴ አልመሰለኝ አለኛ…..››

‹‹አታውቂም እንዴ..? ፍቅር እና ችግር ያፈላስፋሉ እኮ….!!!››

‹‹አይ ጥሩ….ለማንኛውም የቀልድህንም ቢሆን በሰማሁት ነገር ደስ ብሎኛል….ምነው በተናገረው መጠን ሊያፈቅረኝ በቻለም ብዬ ተመኝቼያለሁ››

ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ አነሳትና እሱም ከተጋደመበት ቀና ብሎ ተቀመጠ… ወደእሷ ዞሮ አይን ዓይኗን እያየ‹‹አላመንሺኝም እንዴ ..? የምሬን ነው የተናገርኩት….በጣም ነው ያፈቀርኩሽ ..ወደፊት ማግባት የምፈልገው አንቺን ነው….የልጆቼ እናት ላደርግሽም እፈልጋለሁ….. ››
አንገቷን ወደእሱ ዘንበል አድርጋ እጆቾን በመዘርጋት ተጠመጠመችበት ..‹‹በጣም ነው የማፈቅርህ አንተን ስላገኘው እድለኛ ነኝ››
…..
‹‹እሺ አሁን ወጣ ብለን  ቢች ዳር ዘና እንበል…..››አላት በሀሳቡ ተስማማችና ተያይዘው ወጡ…
ላንጋኖ ሀይቅ ላይ ያረፈችው የማታዋ ጀንበር ልዩ ህብረቀለም እየረጨች ስትታይ ለአካባቢው ልዩ ውበት አልብሳዋለች…. ቢች ዳር ኳስ የሚጫወቱ አሉ..ሀይቅ ውስጥ ገብተው የሚዋኙን የሚንቦጫረቁም ጥቂት አይደሉም…… በአካባቢው ደስታ ተመርቶ የሚታደል ወይንም ከንፋሱ ጋር ተቀላቅሎ አየሩን እየሞላው በስፍራው ያለው ሰው ሁሉ እየማገው የሚፈግና የሚደሰት ይመስላል፡፡

‹‹ትዋኚያለሽ …..?››

‹‹አረ ይቅርብኝ …ዝምብለን እዚህ ሳሩ ላይ ቁጭ እንበልና  በማየት እንደሰት..ባይሆን ቆይቶ ከነሸጠኝ አብረን እንገባለን›› አለችውና ቁጭ አለች ..ተከትሎት ከጎኗ ቁጭ አለ…….

ይቀጥላል

#ክፍል 43,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄