ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
194K subscribers
280 photos
1 video
16 files
207 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ወግ
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
🎯መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
☎️• 0922788490

📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከመሐል አትላንቲክ ወደ ቦትውድ (ካናዳ)


ዳያና ላቭሴይ ባሏ ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑን መሳፈሩ በእጅጉ አስቆጥቷታል፡ በመጀመሪያ ዱካዋን እግር በእግር ተከታትሎ በመምጣት መሳቂያ መሳለቂያ ስላደረጋት አፍረት ውስጥ ከቷታል፡ ባሏ እቤታችን እንሂድ ቢላትም ሀሳቧን መለወጥ አትፈልግም ከማርክ ጋር ወደ አሜሪካ ለመሄድ የወሰነች ብትሆንም መርቪን ግን የመጨረሻ ውሳኔዋ ነው ብሎ መቀበል አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ በቁርጠኝነቷ ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡እሱም ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤነው ደጋግሞ ስላሳሰባት ውሳኔዋን
በተደጋጋሚ ገልጻለታለች፡፡ በመጨረሻ ግን የአየር ጉዞዋ የሰጣትን ደስታ
ነጥቋታል፡፡

በህይወት አንዴ ብቻ የሚገጥም ከፍቅረኛ ጋር የሚደረግ ጉዞ፡፡

ከሳውዝ ሃምፕተን ሲነሱ የነበረው የነጻነትና የደስታ ስሜት አሁን የለም: መርቪን ከመጣ ወዲህ ምቹው አይሮፕላን፣ ከተለያዩ ተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀሉና እጅ የሚያስቆረጥመው ምግብ ደስታ እየሰጣት አይደለም፡መርቪን ባጋጣሚ ሲያልፍ ያየኛል ብላ ስለፈራች ከማርክ ጋር መላፋት፣መተሻሸትና መሳሳም አልቻለችም፡፡ መርቪን የት እንደተቀመጠ አታውቅም፡፡ካሁን አሁን ይመጣ ይሆን እያለች ትበረግጋለች። ማርክ ካሊፎርኒያ ስለሚጠብቃቸው ኑሮ በተስፋ ሲያወራና ሲቀልድ ቆይቶ ጣውንቱ ከሰማይ
እንደወደቀ ሁሉ ድንገት አይሮፕላኑ ውስጥ ጥልቅ ካለ ወዲህ ግን ቀልቡ
ግፍፍ ብሏል፡ አሁን የተነፈሰ ፊኛ መስሏል፡፡ ዳያና አጠገብ ቁጭ ብሎ
አንድም ቃል ሳያነብ የመጽሔቱን ገጾች ያገላብጣል፡፡ ስሜቱ መጎዳቱን ዳያና አይታለች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ይዟት እንዲጠፋ ከቆረጠች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ነበር፡፡ አሁን ባሏ ስለመጣ ከእሱ ጋር እሄዳለሁ ብላ ሃሳቧን
የማትለውጥ መሆኗን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡
የአየሩ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱ ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል

አይሮፕላኑ ልክ ኮረኮንች ላይ እንደሚሄድ መኪና ይንገጫገጫል፡፡ በየሰዉ
ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል፡፡ ተሳፋሪው ሁሉ የሚያወራው ይህንኑ ነው፡

ዳያና ባሏ የት እንደተቀመጠ ማወቅ ፈለገች፡፡ እግረ መንገዴን ባየው እየተዘዋወረች ብትቃኝም መርቪንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ በመጨረሻ የቀራት ክፍል የሙሽሮቹ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ወምበሮች ያሉ ሲሆን አንዱ ወንበር ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ትኳኳላለች፡፡ ዳያና በሩን ልትዘጋ ስትል አይሮፕላኑ ዘጭ ሲል ሚዛኗን ስታ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም፡፡ እንደምንም ተንገዳግዳ ሄዳ ባዶው ወምበር ላይ ዘፍ አለች።

‹‹ተረፍሽ?›› ስትል ጠየቀች ሴትየዋ፡፡

‹‹አዎ፣ አመሰግናለሁ›› አለች ዳያና ‹‹አይሮፕላን እንዲህ ሲሆን አልወድም››

‹‹እኔም አልወድም፡ ከዚህ በኋላ ጉዟችን የከፋ እንደሚሆን አንድ ሰው
ነግሮኛል፡ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል›› አለች፡፡

የአይሮፕላኑ ውዝዋዜ ጋብ ሲል ዳያና ጸጉሯን ማበጠር ጀመረች።

‹‹ሚስስ ላቭሴይ ነሽ አይደለም?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አዎ ዳያና በይኝ››
‹‹እኔ ናንሲ ሌኔሃን እባላለሁ:: ፎየንስ ላይ ነው የተሳፈርኩት”
ከሊቨርፑል ካንቺ. . . ከሚስተር ላቭሴይ ጋር ነው የመጣሁት››
‹‹ኦ!›› ዳያና ይህን ስትሰማ ፊቷ በእፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ‹‹ጓደኛ እንዳገኘ አላወቅሁም ነበር›› አለች በምጸት፡፡

‹‹ይህን አይሮፕላን ለመሳፈር ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ለመሄድ ፈልጌ
ሊቨርፑል ላይ መውጫ አጥቼ ስጨነቅ ባለቤትሽን አየር ማረፊያ ላይ
አገኘሁትና እንዲወስደኝ ለመንኩት››

‹‹እንኳን ቀናሽ›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹የእሱ መምጣት እኔን እፍረት ውስጥ
ከቶኛል፡፡››

‹‹ማፈር የለብሽም፡፡ ሁለት ወንዶችን በፍቅር ማጥመድሽ ደስ የሚል
ነገር ነው፡፡ እኔ አንድ እንኳን ፍቅረኛ የለኝም፡፡››

ዳያና ናንሲን በመስታወት አየቻት፡፡ ሴትየዋ ቆንጆ ባትባልም የደስ ደስ አላት፡ ጸጉረ ጥቁር ስትሆን ከሰውነቷ ጋር የሚሄድ ልብስ ለብሳለች።
ስትታይ በራሷ የምትተማመን ትመስላለች፡ መርቪን ሊፍት ቢሰጥሽ
አያስገርምም፡ እሱ እንዳንቺ ያለች ሴት ነው የሚፈልገው አለች ዳያና በሆዷ፡፡
‹‹እንዴት ነው ያሳየሽ ባህሪ ጥሩ ነበር?›› ስትል ጠየቀቻት ናንሲን፡፡
‹‹ብዙም ጥሩ አልነበረም›› አለች በቅሬታ ፈገግታ፡
‹‹አዝናለሁ፡ ይህ ባህሪው ነው የሚያስጠቃው›› አለችና ሊፒስቲኳን ጨረገች

‹‹ሆኖም በችግሬ ጊዜ ስለደረሰልኝ ባለውለታዬ ነው›› አለችና ናንሲ
ተናፈጠች፡ ናንሲ ቀለበት ማሰሯን ዳያና አጤነች፡፡ ‹‹ትህትና ባይኖረውም
ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ ራትም ጋብዞኛል፡ ጨዋታ ያውቃል፡፡ የሴት ልጅን
ልብ የሚሰርቅ ቁመናና መልክ አለው›› አለች፡፡

ጥሩ ሰው ቢሆንም….... አለች ዳያና ‹‹ሰው ይንቃል፡፡ ትዕግስትም የሚባል ነገር ፈጽሞ አልፈጠረበትም፡፡››
ናንሲ ጥቁር ጥቅጥቅ ያለውን ጸጉሯን ታበጥራለች ሽበቷን ለመደበቅ ቀለም ትቀባ ይሆን?› አለች ዳያና በሆዷ።

አንቺን መልሶ በእጁ ለማስገባት ሲል የሚደርስበትን መከራ ለመቀበል ቆርጧል››

‹‹አይደለም ክብሩ ስለተነካ ነው›› አለች ዳያና ‹‹ሌላ ወንድ ስለወሰደኝ ነው ያንጨረጨረው፡፡ ተጋፊ ስለመጣበት ነው ተከትሎኝ የመጣው፡ ጥዬው
እህቴ ቤት ሄጄ ቢሆን ኖሮ እኔን ለመፈለግ እግሩን አያነሳም ነበር››

ናንሲ ሳቀችና ‹‹እንዳነጋገርሽ አንቺን ለማስመለስ ተስፋ ያለው
አይመስልም›› አለች፡፡

‹‹ምንም ተስፋ የለውም›› አለች ዳያና፡፡ ዳያና ድንገት ስሜቷ ስለተረበሸ ከናንሲ ጋር ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ ሜክአፕና ማበጠሪያዋን ቦርሳዋ ውስጥ ከታታ ለናንሲ ያላት ጥላቻ እንዳይታወቅባት የውሽት ፈገግታ አሳየቻትና ‹‹ወደ ቦታዬ ልሂድ›› ብላ ተነሳች፡፡

‹‹መልካም ዕድል!››

ከሴቶች መዋቢያ ክፍል ስትወጣ ሉሉ ቤልንና ልዕልት ላቪኒያ የመዋቢያ ዕቃዎቻቸውን ያጨቁበትን ቦርሳዎቻቸውን አንጠልጥለው ገቡ፡፡
ወደ ቦታዋ ስትመለስ አስተናጋጁ ዴቭ መቀመጫቸውን ወደ ታጣፊ አልጋ ሲቀይር አየች፡፡ ዳያና አንድ ተራ ሶፋ እንዴት ወደ ተደራራቢ አልጋ ሊቀየር
እንደሚችል ገርሟታል። ዴቭ ከወምበሩ ስር አንሶላና ብርድ ልብስ አወጣና
አነጠፈ፡፡

ተደራራቢ አልጋዎቹ ምቹ ቢሆኑም ከሰው እይታ ውጭ ባለመሆናቸው
ዴቭ መጋረጃ አመጣና ጋረዳቸው፡ ከዚያም በአልጋዎቹ ጎን ትንሽ ታጣፊ
መሰላል አያያዘባቸው፡፡ ዴቭ ይህን የሰራው በሚያስደንቅ ቅልጥፍና ነው፡፡

ዴቭ ወደ ዳያናና ማርክ ዞሮ ፈገግታ ሳይለየው መኝታችሁ እንዲዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ ንገሩኝና አዘጋጅላችኋለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹ተደራራቢ አልጋዎቹ ውስጥ ሲተኙ ሰዎች አይታፈኑም?››
‹‹እያንዳንዱ አልጋ የራሱ አየር ማስገቢያ አለው›› ሲል መለሰ ‹ቀና ብለሽ ብታዪ ያንቺ አልጋ አየር ማስገቢያ አለው፡›› ዳያና ቀና ስትል መስቀያና መዝጊያና መክፈቻ ያለው በብረት ፍርግርግ የተሰራ አየር ማስገቢያ አየች:: "ከዚህ በተጨማሪ›› ሲል ቀጠለ ዴቭ ‹‹የራስሽ መስኮት፣ መብራት፣ የልብስ መስቀያና የመፀሐፍ ማስቀመጫ አለሽ።ከዚህ በተረፈ የምትፈልጊው ነገር
እንዲመጣልሽ ስትፈልጊረመ ይህን ቁልፍ ብትጫኚው ከተፍ እልልሻለሁ›› አላት።
​​📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ክፍል_ሰላሳ_አንድ

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋ

ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ  ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ  አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ  ወደ ዋና ጋንዳው አመራች ..ሰውነቷን  ጭፍግግ ስላለት  ዘና ማለት  ነው የፈለገችው….በዋና ሰውነቷን ማፍታታት……
የዋና ገንዳው አካባቢ እንደደረሰች ዘላ ውሀ ውስጥ ገብታ መንቦጫረቅ አልፈለገችም…የመዋኛ ገንዳውን ዙሪያ ከበው ወደ ተዘረጉ ዘመናዊ ወንበሮች ሄደችና ..ባዳውን ከሆነ አንድ ወንበር ላይ ዘና ብላ በመቀመጥ የሚዋኙትን ታዳሚዎች እያየችና  እየታዘበች መዝናናቷን ቀጠለች…..
…..አበሻም ፈረንጆችም…. ሴቶችም ወንዶችም… ህፃናትም፤ ወጣትና አሮጊቶችም በስብጥር  ሲዋኙ እና ሲንቦጫረቁ ይታያሉ….
ስሜቷ አንቀልቅሎ ወደ እዚህ ስፍራ ያመጣት ለምን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀላትም .. …?…..  ድንገት ግን ሳታስብ አንድ ወጣት ዕድሜው በግምት በ25 30 ዓመት መካከል የሚገኝ  ወንድ ላይ አይኗ አረፈ…ያምራል… በጣም ነው የሚያምረው..፡፡ ከደረቱ በላይ ያለው የሰውነት ቅርጽ ውጥርጥር ያለ እና ሚማርክ ነው…ፀጉሩ በውሀው አቅም ተሸንፎ በሚመስል ሁኔታ ዝልፍልፍ ብሎ ግንባሩ ላይ ተዘናፍሏል፡፡አይኖቹ ከጨረቃ የተዋሳቸው ይመስላሉ…ኪሊማንጀሮ ተራራ ጫፍ ላይ ያገኘችውን አንድሪውን አስታወሳት፡፡.
እሷ ደግሞ ካለ ችግሯ ወይም ድክመት ሊባልም ይችላል   ስድስት ወር ወይም አመት ምንም ወንድ ሳያምራት ወይም ከምንም አይነት ወንድ ጋር ሳትነካካ ትቆይና ድንገት በሰከንድ ውስጥ በእይታዋ ውስጥ የሆነ ወንድ ገብቶ ቀልቧን ከሰረቀት በቃ..ስግብግብ ነው የምትለው..፡፡በዛኑ ቀን ወይም ከተቻለም በዛኑ ደቂቃ ማግኘትና አምሮቷን መወጣት አለባት….(ያው የእሷ ፍቅር ከአንድ ጊዜ የወሲብ ፍላጎት አያልፍም ..ከዛ በላይ ፈልጋ አታውቅም ..ለእሷ በፍቅር መነሁለል እና . ወንድን እየተከተሉ መዞር ወይም ወንድ አፈቀርኩሽ እያለ ለሀጩን እያዝረበረበ በዙሪያዋ እንዲሽከረከርባት በፍፅም አትፈቅድም….)
.የእሷ ችግር ጊዜያዊ ነው ..ጊዜያዊም ብቻ ሳይሆን ቅፅበታዊም ጭምር ነው….በፈለገች ጊዜ ማግኘት አለባት… .ካለበለዛ እራሷን ሁሉ መቆጣጠር ስለሚያቅታት ጥፋት ታጠፋለች....የማይሰራ ስራ ትሰራለች…የወሲብ ጠኔም በቀላሉ አዙሮ እና አጥወልውሎ ሊደፋት ሁሉ ይችላል….እና አሁንም ይሄ ሻንቂላ ወንዳ ወንድ ወጣት እፊቷ ያለው ሰማያዊ መዋኛ  ገንዳ ውስጥ ጥበባዊ በሆነ ስልት እንደ ዓሳ ነባሪ ብቅ ጥልቅ በማለት እየዋኘ ቀልቧን ስልብልብ አድርጎታል..
‹‹ተይ ይቅርብሽ››እራሷን ለመገሰፅ ሞከረች…እራሷን መገደብ እንደማይሳካላት ግን ከልምድ ታውቃለች… …..ከለበሰችው የዋና ልብስ ስር እግሯ እና እግሯ መካከል ያሳክከት ጀመረ.. እጣቷን ወደ ጭኗ መካከል በመስደድ የሚበላትን አካባቢ አከክ…አከ…ክ አድርጋ ተንፈስ ለማለት አሰበችና   ዙሪያዋን በሰዎች መከበቧን  ሳታስተውል መልሳ ተወችው....ከተቀመጠችበት መቀመጫ ተነሳችና ወደዋናው ገንዳ ቀረበች…ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ነው…ድንገት በትይዩ አቅጣጫ በሰማዩ ላይ በሶስት መቶ ሜትር  ርቀት ….   ንስራ ሲያንጃብብ ተመለከተችና
‹‹…ወይ ከመቼው ተከትሎኝ መጣ….ግን እንኳን መጣህ.››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…. እሱን በአቅራቢያዋ በማየቷ ደስ አላት..አዎ ይሄ ቀልቧ ያረፈበትን ወጣት ከተቻለ አሁን ለመክሰስ..ካልሆነም ለእራት ለማድረስ የእሱ እርዳታ ያስፈልጋታል….ስለደካማ ጎኑ በእነዛ ሰርሳሪ አይኖቹ  በማየት  ካልነገረራትና በምን ሁኔታ ብትቀርበው የሀሳቧ ሊሳካ እንደሚችል መረጃውን ካላቀበላት ባሰበችው ፍጥነት ሊሰካላት አይችልም ፡፡

ደስታዋ ግን ሀሳቡን አስባ ሳትጨርስ ነው ከውስጧ በኖ የጠፋው….የንስሯን እርዳታ መጠቀም አትችልም…ምክንያቱም ይሄ ሰው ምን አልባት የማይሆን ታሪክ ካለው..ወይም አደጋኛ ሰው ከሆነ ንስሯ  የሆነ ተአምር ፈጥሮ ከእሱ ጋር በምንም አይነት ተአምር እንዳትገናኝ ያደርጋታል..በምኞቷ መካከል ጣልቃ ይገባና ያጨናግፍባታል…ያ እንዲሆን ደግሞ አትፈልግም...ስለዚህ እዚህ ታሪክ ውስጥ ንስሯን አታሳትፈውም፡፡እንደዛ ወሰነች፡፡

..እንዳዛ ከሆነ ደግሞ እየበላት ያለውን በገዛ ጣቶቾ  ስታክ ማደራ ነው…ፈርዶባት ደግሞ በአንዱ የተቀሰቀውን ስሜቷ  በሌላ ወንድ አካክሳ ልታበርደው  አትችልም…ይሄ የእሷ የሆነ ልዩ ባህሪ ነው……
ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በራሷ መወጣት አለባት….."ንስሯን ምንም እርዳታ አልጠይቀውም….እሱ በሚዋኝበት አካባቢ እስትራቴጂካል ቦታ መርጣ   ገንዳው ዳር ተቀመጠችና እግራን ብቻ ውሀ ውስጥ በማስገባት ልክ መዋኘት እንደሚፈልግ … ግን ዋና ስለማይችል መግባቱን እንደፈራ ሰው በመምሰል ማንቦጫረቅ እና በእጇ እየጨለፈች በውሀው መጫወት  ጀመረች….
አዎ  ልጁ እየዋኘ ወደስሯ ተጠጋ…ተመልሶ ሄደ ..ሶስት አራቴ በሰሯ ተመላለሰ…በአምስተኛው በአጠገቧ ሲያልፍና በጣም ሲጠጋት…

‹‹ታድለህ ››አለችው

‹‹ምን አልሺኝ…?››

‹‹ እንደ ዓሳ ነው የምትዋኘው…ታስቀናለህ…!!!  ››  

‹‹አመሰግናለሁ…››ብሏት ዋናውን ሊቀጥል ካለ በኃላ መልሶ ወደ እሷ  በመዞር..‹‹ለምን አትገቢም…? ››ሲል ጠየቀት

‹‹መግባት እፈልጋለሁ ..ግን ዋና አልችልም፤ ብሰምጥስ…?››

‹‹አይዞሽ እኔ እጠብቅሻለው ግቢ››

‹‹ኸረ ተው ይቅርብኝ››ተግደረደረች

‹‹ግቢ. በእኔ ተማመኚ››

የምትፈልገው  ሀሳብ ስለሆነ ቀሰ ብላ ገባችና ልክ እንደጀማሪ ዋናተኛ ተንደፋደፈች..በቅርቧ ስለነበረ ቶሎ ብሎ ከስር ገባና  ሰቅስቆ በክንዶቹ
መሀል አድርጎ ወደ ላይ አወጣት …
  
    ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 32,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄