የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብርት ስራ ማህበር የሶስተኛ አመት 7 ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል
👍3❤1
Ethio-Terit SACCOS Official Channel
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብርት ስራ ማህበር የሶስተኛ አመት 7 ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል
የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብርት ስራ ማህበር የሶስተኛ አመት 7 ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል
አዲስ አበባ .6/11/2017 ዓ.ም
በ2017 ዓ.ም በጀት አመት ብዙ አዳድስ አባላት ማፍራት የቻለ ፣ ብዙ ብድር ለአባለቶች መልቀቅ የቻለ፣ ብዙ የእውቅና ሰርተፍኬቶችን ማግኘት የቻለ በፌደራል ደረጃ ተመዝግቦ እውቅና ያገኘ ለብዙ ሰዎች የስራ እድል የፈጠረ ብቃት ባላቸው አመራሮች እየተመራ ያለ ለአባላቶች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ ስድስት ቅርንጫፎችን የከፈተው የኢትዮ ጥሪት ቁጠባና ብድር መሰረታዊ የህብርት ስራ ማህበር በዛሬው ቀን በገላን ኮንዶምኒም በአርቲስት ሀንጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የሶስተኛ አመት 7 ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አካሂዷል
የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ እዝራ ወ/ሰንበት ፕሮግራሙን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱ ሲሆን በፖሮግራሙ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፣የቁጥጥር የኮምቴ ሪፖርት፣የአምስት አመት ስልታዊ እቅድ ፣የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ፣ የተሻሻሉ ህጎች ያቀረቡበትና አወያይቶ ያፀደቀበት ጉባኤ ነበር፡፡
በጉባኤውላይም የማህበሩ መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ እንዳሻው ተገኝ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን እስካሁን ማህበሩ በሃሳብ ፣ በዕውቀት ፤ በጉልበት ፤ በገንዘብ እይገዙ ያሉትን ግለሰቦችን እና ተቋማቶችን እንዱሁም ሊት ተቀን የሚሰሩትን ሰራተኞች ያመሰገኑበት ጉባኤ ነበር፡፡
በተጨማሪም አቶ እንደሻውየማህበሩ የ2016 ዓ.ም እና የ2017 ዓ.ም በጀት አመት እድገት በንጽጽር አቅርበዋል፡፡
የ2017 ዓ ም በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የማህበሩ ምክትል ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሙላቱ በዕደ ሲሆኑ ፤ አቶ ሙላቱ በዕደ ባቀረቡት ሪፖርትም ማህበሩ በ 2017 ዓ.ም በጀት አመት ብዙ አዳድስ አባላትን ማፍራቱን ፣ ለብዙ አባላት ብድር መስጠቱን፣ ብዙ የእውቅና ሰርተፍኬቶችን ማግኘቱን በፌደራል ደረጃ እውቅና ማግኘቱን ለብዙ ሰዎች የስራ እድል መፍጠሩን አቅም ያላቸው አመራሮ ማፍራት መቻሉ፤ ግልፅ እና ለሁሉም በሚገባ መልኩ አቅርበዋል፡፡
የማህበሩ ቁጥጥር ኮምቴ ሪፖርት ያቀረቡልን የኮምቴው ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ከፈለኝ አበበ ሲሆኑ በሪፖርቱ ላይም የ2017 በጄት አመት በወጣው ህገ-ደንብና መመሪያ መሰረት መሰራቱን ገምግመው አቅርበዋል፡፡
የአምስት አመት ስልታዊ እቅድ ያቀረቡት የማህበሩ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ደቨሎፐመንት ዳራክተር የሆኑት ዶ/ር አታክልት ሃይሉ ሲሆኑ በዕቅዱም ማህበሩን በአምስት አመት ውስት ምን ምን ለመስራት እንዳቀደ ስልታዊ በሆነ መልኩ አቅርበዋል፡፡
በጉባኤውም የ 2018 ዓ.ም በጀት አመት ዕቅድ ያቀረቡት የማህበሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አለምፀሐይ ታዙ ሲሆኑ ማህበሩ በአንድ አመት ውስጥ ምን ምን ለመስራት እንዳቀደ ግልጽ በሆነ መልኩ አቅርበዋል፡፡
በተጨማሪም ጉባኤው ላይ የተሻሻሉ ህጎዎች በውይይት የፀደቀ ሲሆን በጉባኤው ላይ የተገኙት የአባላት ተወካዮችና የክብር እንግዶች የማህበሩን እድገትና የስራ አፈፃፀም ሲያደንቁና ወደፊትም ጠንክረው እንዲቀጥሉበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የደቡብ ምስራቅ ገዳ ባንክ ድስትሪክት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወለቡማ ተስፋዬ የማህበሩን የአስራር ስርአትእና የአመራር ብቃት በማድነቅ ገዳ ባንክ ወደፊት ብዙ ስራዎችን ከማህበሩ ጋር እንደሚሰራ ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም ጠቅላላ ጉባኤውን እንድናካሂድ ስፖንሰር ላደረጉልን ተቋሞዎችን፣ ቁጠባቸውን ሳያቆራርጡ የቆጠቡ አባላት፣ ብድርራቸውን ከብድር ውላቸው በፊት አስቀድመው የዘጉ አባላት እና ማህበሩ ራዕዩን እንዲያሳካ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ያሉትን አባላት የእውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል፡፡

👏4❤3👍2
Waldaan Hojii Gamtaa Qusannoo fi Liqii Itiyoo-Xirriit, Yaa'ii Idilee Walii Galaa waggaa 3ffaa marsaa 7ffaa geggeesse