DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
✅🔸የዓለማችንን መልክ የቀየሩት 20ዎቹ የምንግዜም ታላላቅ ኢኖቬሽኖች
========================
▫️በሰው ልጆች ረዥም የህይወት ጉዞ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚና እንዲ በቀላሉ የሚገለፅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ሰዎች ወደዚች ምድር ከመጡ አንስቶ አካላዊውን ዓለም ለመግራት የሚያስችሉ የተለያዩ ፈጠራዎችንና የኢኖቬሽን ውጤቶች ያለማቋረጥ ሲተገብሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ መሳሪያዎች አለም አሁን ያላትን መልክ ያጎናፀፏት እና የቀጣዩንም ትውልድ እጣ ፋንታ በበጎም ይሁን በክፉ የመወሰን አቅማቸው በእጅጉ የተጠበቀ ነው፡፡ አለማችን እስካሁን ያየቻቸውን የኢኖቬሽን ውጤቶች ለሰው ልጆች ከሰጡት ግልጋሎት እና በታሪክ ውስጥ ካላቸው የገዘፈ ተጽዕኖ አንፃር የሚከተሉት ኢኖቬሽኖች ከምንግዜም ታላላቆቹ መካከል ይገኙበታል፡፡ በዘመን ቅደም ተከተል እንመልከታቸው፡

▫️1. እሳት (FIRE) - ስለእሳት ስናነሳ ብዙዎች የሚከራከሩበት ጉዳይ ቢኖር እሳት ተፈለሰፈ ከሚባል ይልቅ ተገኝቷል የሚለው ሃሳብ እጅግ ተስማሚ መሆኑን ነው፡፡ ቀደምት የሰው ዘሮች እሳትን እንዴት መፍጠር እና መቆጣጠር እንደሚችሉ ከማወቃቸው በፊት የእሳትን አደጋዎች በየአጋጣሚው ተመልክተው ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የእሳትን ምንነት ከተረዱና የሚሰጣቸውን ጥቅም ካወቁ በኋላ እሳትን እንደ አንድ ትልቅ መገልገያ መጠቀም ጀምረዋል፡፡ አንዳንድ የአርኪዎሎጂ አጥኝዎች እሳት ጥቅም ላይ የዋለው ከ2 ሚሊዮን አመት በፊት ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ 125 ሺ አመታት እንዳስቆጠረ ይገልፃሉ፡፡ ይህ ክርክር ምንም ተባለ ምንም በሰው ልጆች ታሪክ ታላቅ ግኝት የሆነው እሳት ሰዎች ራሳቸውን ከተለያዩ ነገሮች እንዲከላከሉ እና ማብሰል የሚባለውን ትልቅ ክህሎት እንዲረዱ ያስቻል አስገራሚ ግኝት ነው፡፡

▫️2. ተሽከርካሪ ጎማ (WHEEL) - ይህ ፈጠራ የተገኘው በ3500 ዓመተ ዓለም (B.C) በሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን ነበር፡፡ የሜሶፖታሚያ ህዝቦች ይህንን አስገራሚ ፈጠራ የሸክላ ቁሳቁሶችን ለማበጃጀት ሲጠቀሙበት የቆየ ቢሆንም ከሶስትና አራት መቶ አመታት በኋላ ፈጠራው ለሰረገላ ማሽከርከሪያ ጥቅም ላይ ከዋለ በኋላ የመሳሪያው ተፅዕኖ እጅግ እየናኘ ሄዷል፡፡ ተሽከርካሪ ጎማ ለሰው ልጆች የመጓጓዣ እና የንድግ ስርዓት መፈጠር ትልቅ ሚና ያለው ግኝት ነው፡፡

▫️3. ኦፕቲካል ሌንሶች (OPTICAL LENSES) - የሰዎችን የእይታ አቅም ይበልጥ ለመጨመር እንደ ኦፕቲካል ሌንሶች ያሉ አስገራሚ ግኝቶች እጅግ ወሳኝ ነበሩ፡፡ ረዥም የፈጠራ ሂደት የነበራቸው እነዚህ ግኝቶች በጥንቱ የግብፅ እና የሜሶፖታሚያ የስልጣኔ ዘመን እንደበለፀጉ የሚታመን ሲሆን ከግሪክ የተገኙት የብርሃን ንድፈ ሃሳቦች ደግሞ ለግኝቱ እውን መሆን ትልቅ ሚና ነበራቸው፡፡ ኦፕቲካል ሌንሶች እንደቴሊቭዥን፣ ፎቶግራፍ እና ፊልም ያሉ ትልልቅ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎች እንዲፈጠሩ መንገድ የጠረጉም ናቸው፡፡

▫️4. ኮምፓስ (COMPASS) - ይህ እንቅስቃሴን ለመምራት የተዘየደው የቴክኖሎጂ ግኝት የሰው ልጆችን የአሰሳ ጥበብና አቅም ወደ አዲስ ምዕራፍ በመወሰድ ተተኪ የማይገኝለት አስገራሚ ግኝት ነው፡፡ የመጀሪያዎቹ ኮምፓሶች በተፈጥሮ የመግነጢሳዊ ይዘት ባላቸው የማዕድን ቁራጮች ወይም (lodestone) አማካኝነት የተሰሩ ሲሆን፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 300 እና 200 አመተ አለም አካባቢ በቻይና እንደተሰሩም ይነገራል፡፡

▫️5. ወረቀት (PAPER) - በ100 ዓመተ አለም አካባቢ በቻይና የተፈለሰፈው ይህ ግኘት የሰው ልጆችን የፅህፈት እና ሃሳብን የማጋራት ልምድ በእጅጉ የቀየረ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ከዚህ ጊዜ በፊት በግብፅ እና በሜክሲኮ የስልጣኔ ዘመናት የተፈለሰፉት እንደ ፓፒረስና አሜት ያሉ የመፃፊያ ቁሶች ለወረቅት መፈጠር አስተዋፅዖ ቢኖራቸውም በቻይና የነበረው ግኝት ግን አሁን ላለው የወረቀት ቴክሎጂ ትልቅ መሰረት የጣለ ነው፡፡
▫️6. ባሩድ (GUNPOWDER) - ከተለያዩ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ተቀይጦ የሚሰራው ይህ ተቀጣጣይ ፈንጂ በ9ኛው ክፍለ ዘመን በቻይና እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን ለዘመናዊው የጦር ቴክኖሎጂ መስፋፋትም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡ ይህ ግኘት በሰው ልጆች የውጊያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደረ መሆኑም ይነገርለታል፡፡

▫️7. ማተሚያ (PRINTING PRESS) - እንደአውሮፓውያኑ በ1439 በጀርመናዊው ዮሃንስ ጉተንበርግ የተፈጠረው ይህ መሳሪያ ለሰው ልጆች የአዲስ ህይወት መጀመሪያ ዘመን ተደርጎ በብዙዎች ይወሰዳል፡፡ ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ በሰዎች እጅ እየተፃፈ የሚሰራጨውን አድካሚ የፅህፈት ስርዓት በሜካናይዝድ ማሽን በመተካት የእውቀት አድማስ በሰዎች ዘንድ በቀላሉ እንዲሰፋፋ እና የሃይማኖት አስተምህሮዎች በአለም ላይ በፍጥነት እንዲናኙ ያስቻለ አስገራሚ ግኘት ነው፡፡

▫️8. ኤሌክትሪክ (ELECTRICITY) - የኤሌክትሪክ ፈጠራ ብዙ ብሩህ አዕምሮዎች ለሺህና ከዚያ በላይ አመታት አስተዋፅዖ ያደረጉበት እፁብ ድንቅ የሆነ የቴክኖሎጂ ግኝት ነው፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ቤንጃሚን ፍራንክሊን ስለኤሌክትሪክ የነበረውን የአለም መረዳት አንድ እርምጃ ያራመደ የመሪነት አበርክቶት እንደነበረው የሚገለፅ ሲሆን በምርምር ዘርፍ ደረጃ ለመስኩ የሰጠው ሁለንተናዊ ትኩረት የቴክኖሎጂውን እድገት በእጅጉ አፋጥኖታል፡፡ ከዚህ ሂደት በማስከተል በ1879 የቶማስ ኤዲሰን የብርሃን አምፖል መፈጠር የኤሌክትሪክ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ወደሰዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ክስተት ነው፡፡ ይህ የምንግዜም ታላቅ ፈጠራ የሰው ልጆችን የህይወት መንገድ እስከወዲያኘው የቀየረ ግሩም ቴክኖሎጂ ነው፡፡

▫️9. የእንፋሎት ሞተር (STEAM ENGINE) - በስኮትላንዳዊው የፈጠራ ባለሙያ ጀምስ ዋት ከ1763 እስከ 1775 ተሰራ የሚባለው የእንፋሎት ሞተር ሌላኛው ለሰው ልጆች ትልቅ መሰረት የጣለ አስደናቂ የፈጠራ ውጤት ነው፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ግኝት በጊዜው ለነበሩት ባቡሮች፣ መርከቦች እና በጠቅላለው ለኢንዱስትሪው አብዮት ዋና የሃይል ምንጭ በመሆን ተከትሎ ለመጣው የሰው ልጅ አብርሆት ታላቅ ውለታ ያደረገ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️10. የነዳጅ ሞተር (INTERNAL COMBUSTION ENGINE) - በ19ኛው ክፍለዘመን የተዋወቀው ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ በመጀመሪያ በቤልጄሚያዊው ኢንጅነር ኢትየን ሌኖየር (በ1859) የተፈጠረ ሲሆን ከጥቂት አመታት በኋላ በጀርመናዊው ኒኮላስ ኦቶ ይበልጥ ሊሻሻል ችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ፈጠራ የኬሚካል ኢነርጂን ወደ ሜካኒካል ኢነርጂ በመቀየር ቀድሞ የእንፋሎት ሞተር ሲሰጥ የነበረውን ግልጋሎት በተሻለ ሁኔታ በመተካት ለዘመናዊ መኪናዎችና አውሮፕላኖች ማገልገል የቻለ አስገራሚ ፈጠራ ነው፡፡

▫️11. ስልክ (TELEPHONE) - የስኮትላንድ ተወላጁ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል በሰው ልጆች የመገናኛ ጥበብ ውስጥ ትልቅ አብዮት የፈጠረውን የስልክ ቴክኖሎጂ በራሱ ስም ያስመዘገበ ታላቅ የፈጠራ ባለሙያ ቢሆንም ከሱ ቀደምና እሱ በነበረበት ዘመንም ብዙ የፈጠራ ባለሙያዎች ለቴክኖለጂው ማበብ የራሳቸውን አሻራ ጥለዋል፡፡ አሌግዛንደር ግርሃም ቤል አንደአውሮፓውያኑ በ1876 በኤሌክተሪክ ስልክ የመጀመሪያውን ፓትንት ካገኘ በኋላ የሰው ልጆች እርስ በእርስ የመገናኘት ልምድ እስወዲያኛው ተቀይሯል፡፡
▫️12. ክትባት (VACCINATION) - የክትባት ግኘት ለአንዳንዶች አከራካሪ ፈጠራ ቢሆንም ብዙዎች እንደሚገልፁት ከሆነ ግን በአለም ላይ የተከሰቱ በሽታዎችን በማጥፋት እና የሰው
ልጆችን በመታደግ በኩል እስካሁን ከታዩ አስደናቂ ግኝቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡ በአለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው ክትባት እንደአውሮፓውያኑ በ1796 ለፈንጣጣ (smallpox) በሽታ የተሰራው ክትባት ሲሆን ኤድዋርድ ጄነር በተባለ ተመራማሪ የተገኘ ነው፡፡ ከዚህ ክትባት በኋላ በ1885 በፈረንዊው ኬሚስትና ባዮለጂስት ሊዩስ ፓስተር የተሰራው የሬቢስ (rabies) ቫይረስ ክትባት ደግሞ ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂ ትልቅ በር የከፈተ ነበር፡፡

▫️13. መኪና (CARS) - ተሽከርካሪ መኪናዎች የሰዎችን የጉዞ ስርዓት እና ተያይዞ የመጣውን የከተሞች ባህሪ እስከወዲያኛው የቀየረ ግሩም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ተሽከርካሪ መኪናዎች በዘመናዊው ቅርፃቸው በአለም ላይ ብቅ ማለት የጀመሩት በ19ነኛው ክፍለ ዘመን የመጨረሻ አመታት ላይ ሲሆን በዋናነት በጀርመናዊው ካርል ቤንዝ እና ባልደረቦቹ የተከናወኑ ናቸው፡፡ ካርል ቤንዝ እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር በ1885 የመጀመሪያዋን ሞተር ብስክሌት ተግባራዊ ካደረገ በኋላ የመኪና ቴክኖሎጂ በአለም ላይ እየናኘ ሄዷል፡፡

▫️14. አውሮፕላን (AIRPLANE) - በ1903 በአሜሪካውያን ወንድማማቾች ለውጤት የበቃው ይህ አስገራሚ ቴክኖሎጂ የሰው ልጆችን የረዥም ርቀት ጉዞ ፈጣን አማራጭ በመስጠት የትራንስፖረት ኢንዱስትሪን እስከወዲያኛው የቀየረ ነው፡፡ የአውሮፕላን ቴክኖሎጂ የአለም ሰዎችን ይበልጥ እንዲቀራረቡ በማድረግ የባህል፣ የምጣኔ ሃብት እና የእውቀት ልውውጦችን ይበልጥ ያዳበረ ቢሆንም በቴክኖሎጂው የማብሰሪያ ጊዚያት በአለም ላይ ለተከሰተው አለምአቀፍ ጦርነት ሌላ አባባሽ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

▫️15. ፔኒሲሊን (PENICILLIN) - እንደአውሮፓውያኑ በ1928 በስኮትላንዳዊው ሳይንቲስት አሌክዛንደር ፍሌሚንግ የተቀመረው ይህ ግኘት የፋርማሲዩቲካል ዘርፉን አንድ እርምጃ በማራመድ የመጀመሪያውን አንቲባዮቲክ መድሃኒት ለአለም ያስተዋወቀ ነው፡፡ ፔኒሲሊን እጅግ ብዛት ያላቸው ተላላፊ ባክቴሪያዎችን በመከላከል ለረዥም ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለ አንቲባዮቲክ ሲሆን ለዘመናዊው የመድሃኒት ቴክኖሎጂም ፈር ቀዳጅ የሚባል ነው፡፡

▫️16. ሮኬቶች (ROCKETS) - ቀደምት የሚባለው የሮኬት ቴክኖሎጂ ሙከራ በቻይና የስልጣኔ ዘመናት እንደነበር የሚወሱ የታሪክ ማዛግብቶች ቢኖሩም አሁን ላይ የሚታወቀው ዘመናዊ የሮኬት ቴክኖሎጂ ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተዋወቀ ነው፡፡ ይህ ግኝት በሰው ልጆች የህዋ ምርምር እና የጠፈር አሰሳ ላይ ትልቅ አበርክቶት የነበረው ፈጠራ ሲሆን በወታደራዊው ዘርፍም የማይናቅ አስተዋፅኦ ያለው ነው፡፡

▫️17. የኒውክለር ማብሊያ (NUCLEAR FISSION) - አተሞችን ይበልጥ ጥቃቅን ወደሆኑ ቅንጣቶች መከፋፈል እና በዚህም ከፍተኛ መጠን ያለው ኢነርጂ የመፍጠር ሂደት የኒውክለር ኃይል ማመንጫዎች እና አቶሚክ ቦምቦች እንዲፈጠሩ አስችሏል፡፡ ይህ አስገራሚ ግኘት በ20ኛው ክፍለ ዘመን በዚህ ዘርፍ ዙሪያ ሲሰሩ በነበሩ ስመጥር የፊዝክስ ሊቃውንት የተከናወነ ቢሆንም የኒውክለር ማብሊያውን በዋናነት በመስራት ረገድ ጀርመናውያኑ ኦቶ ሃን እና ፍሪትዝ ስታስመን አንዲሁም የኦስትሪያ ተወላጅ የሆኑት ሊዝ ማይትነር እና ኦቶ ፍሪሲች በቀዳሚነት ይጠቃሳሉ፡፡

▫️18. ሴሚኮንዳክተሮች (SEMICONDUCTOR) - የአሜሪካ ወይም የአለም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ማዕከል ከሆነችወ ሲልከን ቫሊ ቅጽል ስም ጀርባ የሚገኘው የሴሚኮንዳክተር ግኘት ብዙ ነገሩ ከሲልከን የተሰራ ሲሆን የአፈጣጠር ሁኔታውም በኤሌክትሪክ ዘመን እና እየመጣ በሚገኘው ዲጂታል ዘመን መካከል ላይ ነበር፡፡ የመጀመሪያው የሴሚኮንዳክተር ቁስን የያዘ መሳሪያ እንደአውሮፓውያኑ በ1947 የተዋወቀ ሲሆን በአሜሪካውያኑ ጆን ባርደን እና ዋልተር ብራታን የተሰራ ነው፡፡

▫️19. የግል ኮምፒውተሮች (PERSONAL COMPUTER) - አንደአውሮፓውያኑ በ1970ዎቹ የተፈጠሩት የግል ኮምፒውተሮች የሰው ልጀችን ሁለንተናዊ አቅም በማሳደግ በኩል ተወዳዳሪ አልነበራቸውም፡፡ በ1974 በማይክሮ ኢኒስትሩመንቴሽን እና ቴሌሜትሪ ሲስተም (MITS) የመጀመሪያ የሚባለው የግል ኮምፒውተር ከተዋወቀ በኋላ ቀጥለው የመጡት እንደ አፕል፣ ማይክሮሶፍት እና አይ ቢ ኤም ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎች ዘርፉን እስከወዲያኛው አራቀውታል፡፡

▫️20. በይነ መረብ (INTERNET) - አሁን አሁን የሰው ልጅ እስትንፋስ እስከመሆን የደረሰው ይህ አስገራሚ ግኘት ከ1960ዎቹ ጀምሮ ሙከራዎች ሲደረጉበት የቆየ ቢሆንም አሁን በምናውቀም መልኩ ለሰው ልጆች መድረስ የጀመረው ከ1990ዎቹ ጀምሮ ነው፡፡ በጊዜው አንግሊዛዊው ቲም በርነር-ሊ የመጀመሪያውን የበይነ መረብ መግባቢያ የአለም አቀፍ ድር (WWW) ከቀመረ በኋላ አጠቃላይ የአለም መልክ ሊቀየር ችሏል፡፡ ከዚህ ጊዜ አንስቶ ንግዳችን፣ ፖለቲካችን፣ መዘናኛችን የፈለጋችሁን ስም ስጡት ብቻ ሁለ ነገራችን በኢንተርኔት እና በኢንተርኔት ሁኗል፡፡

ምንጭ፡ Bigthink
✅🔸ሃከሮች 600 ሚሊዮን ዶላር የሚተመን የክሪፕቶከረንሲ ዝርፊያ አካሄዱ
========================
▫️በብሎክቼን ዘርፍ ላይ የተሰማራው ፖሊ ኔትወርክ የተባለው ግዙፍ ድርጅት በሲስተሙ ላይ ባጋጠመ መጠነኛ ተጋላጭነት በመረጃ ጠላፊዎች ወይም ሃከሮች እንደ Ether ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የዲጂታል ገንዘቦችን እንደተዘረፈ አስታወቋል፡፡ ድርጅቱ በቲውተር ገፁ እንደጠቀሰው የተካሄደበት የክሪፕቶከረንሲ ዝርፊያ በመደበኛው ገንዘብ ሲተመን እስካሁን ካጋጠሙ ስርቆቶች ተወዳዳሪ እንደሌለው እና ዝርፊያውም በ10 ሺ የሚቆጠሩ የክሪፕቶ ደንበኞቹን በቀጥታ የሚያጠቃ መሆኑን አንስቷል፡፡
ያልተማከለ የዲጂታል መዝገብ ወይም የ (ledger) አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረው ፖሊ ኔትወርክ በኮንትራት ጥሪዎች ወይም ግንኙነቶች መካከል በተፈጠረ መጠነኛ ተጋላጭነት በመረጃ ጠላፊዎች ሊመዘበር መቻሉን ያወሳው የቢቢሲ ዘገባ በጠቅላላው Ether ከተሰኘው ክሪፕቶከረንሲ 267 ሚሊዮን ዶላር፣ ከ Binance coins 252 ሚሊዮን ዶላር እና USDC ከተባለው ዲጂታል ከረንሲ ደግሞ 85 ሚሊዮን ዶላር ሊዘረፍ መቻሉን ዘግቧል፡፡
ፖሊ ኔትወርክ ዝርፊውን ያካሄዱ የመረጃ ጠላፊዎች በየትኛውም ሀገር ህግ ትልቅ የኢኮኖሚ ወንጀል መፈፀማቸውን ተረድተው መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ስምምነት ከድርጅቱ ጋር እንዲመሰርቱ በቲዊተር መግለጫው አክሏል፡፡ የመረጃው ጠለፋ ኮይንቼክ እና ኤምቲ ጎክስ በተባሉ በቅርብ ጊዜ በተደረጉ የልውውጥ ጥሰቶች ላይ ተንተርሶ የተፈፀመ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት እንዳለም ዘገባው አትቷል፡፡
የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚገለጹት አሁን ላይ ይህን መሰል ከባድ ጥቃት በክሪፕቶከረንሲ ገበያ ላይ የተፈፀመ ቢሆንም ባለፉት ሁለት አመታት ከተፈፀመው ጥቃት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ይህ ክሪፕቶከረንሲ የሳይበር ጥቃት በ2020 1.9 ቢሊዮን ዶላር ውድመት አስከትሎ የነበረ ሲሆን በ2019 ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር ወንጅል የተፈፀመበት ክስተት ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡ ቢቢሲ
✳️ YouTube News ፡ ዩቲዩብ ከሰሞኑ በጣም አስደሳች ዜና ይዞ ብቅ ብሏል። 1000 Subscribers እና 4000 watch hours ሳንሞላ በ Short ቪዲዩ ብቻ ገንዘብ መስራት ተችሏል። 😍

◽️ይሄ ዜና ሞኒታይዝ ላልሆኑ ሰዎች በጣም ትልቅ ዜና ነው። Short ቪዲዮዎችን ብቻ በመልቀቅ ተከፋይ መሆን ይቻላል። እንዴት ለሚለው ጥያቄ❓ዩቲዩብ Short ቪዲዩ ለሚሰሩ ሰዎች ለማበርታቻ በሚል 100 Million Dollar ፈንድ አዘጋጅቷል።

◽️እና Short ቪዲዩ ስትለቁ ብቻ አይደለም የሚከፍላቹህ። በመጀመሪ የምትለቁትን ቪዲዩ ያጣራል ከዛም በስትክክል የምትሰሩ ከሆነ በ Email መልዕክት ይልክላቹሀል።

◽️በመቀጠልም ከ AdSense ጋር አካውንታቹን Connect እንድታደርጉ ይጋብዛቹሀል። ያኔ ነው ገንዘብ መስራት የምትችሉት።‼️ ነገር ግን አዲስ ህግ አለ

◽️የምትለቁት ቪዲዩ ላይ ምንም አይነት Logo ወይም Watermark መኖር የለበትም። ይህንንም ያደርገበት ምክንያት የ TikTok ቪዲዮችን ለማስቀርት ነው። ማለት ዩቲዩብ ላይ እንዳይለቁ ማለት ነው።

◽️የተቀሩት ደሞ የድሮዎቹ ህጎች ናቸው።
ŠMame_Tech
📍በአለማችን ይኖራሉ ብለው የማይገምቷቸው አስገራሚ ድረ ገፆች....

- በአሁኑ ወቅት መጠኑ ይለያይ እንጂ አንዳንዶቻችን በየቀኑ የኢንተርኔት መረቦችን መቃኘታችን የተለመደ ተግባር ሆኗል።

- የምንቃኛቸው ድረ ገፆችም ብዙ ጊዜ የምናውቃቸውን አልያም በጣም ታዋቂዎቹን ነው።

- አንዳንድ ጊዜም በፌስቡክ አማካኝነት ያገኘናቸው መረጃዎች አዳዲስ ድረ ገፆችን ያስተዋውቁናል።

- እነዚህን አዳዲስ ድረ ገፆችም ጠቃሚ ሆነው ስናገኛቸው ለሌላ ጊዜ እንድንጠቀማቸው ቡክማርክ አድረገን እናስቀምጣቸዋለን።

- ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 10 ድረ ገፆች ግን ምናልባትም አይተናቸው የማናውቃቸው እና የተለየ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው.....

1. 10Minutemail.com

- ይህ ድረ ገፅ ለ10 ደቂቃ የሚቆይ የኢሜል አድራሻ ለመክፈት ያስችላል።

- ድረ ገፁ የተላላክናቸውን መልዕክቶች እና የኢሜል አድራሻውን ከ10 ደቂቃዎች በኋላ ሙሉ በሙሉ ያጠፋዋል።

- 10Minutemail.com እንደከፈትነው ምንም ምዝገባ ሳያስፈልገን ራሱ የኢሜል አድራሻ ይሰጠናል።
👇👇👇👇
በተጨማሪም Tempmail ለዚህ ይጠቅመናል አጠራጣሪ ድረገጾች ስንከፍት ኢሜል ሲጠይቁን በዚህ መጠቀም እንችላለን

2. Fake Name Generator

- በጣም አይነአፋር የሆኑ፣ የግል ጉዳያቸው የሚያስጨንቃቸው እና ትክክለኛ ስማቸውን ይፋ ማድረግ የማይፈልጉ ሰዎች በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የሀሰት ስም እና ዝርዝር መረጃዎችን መፍጠር ይችላሉ።

3. Down for Everyone or Just Me

- አንዳንድ ጊዜ ኮምፒውተርዎ የተወሰኑ ድረ ገፆችን አልከፍት ሊልዎት ይችላል።
- እናም በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት እውን ይህ ድረ ገፅ አልከፍት ያለዎት ስለማይሰራ ነው አልያስ ሆን ተብሎ እንዳይከፍቱት ስለተደረገ ነው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላሉ።

4. Date and Time

- በዚህ ድረ ገፅ ደግሞ በቀናት እና አመታት መካከል ያሉ ልዩነቶችን ለማስላት ይጠቅማል።

- ለአብነትም እድሜያችን በቀናት ለማስላት የተወለድንበትን ቀን፣ ወር እና አመት እና የእለቱን ቀን ወር እና አመት በማስገባት በምድር ላይ ለስንት ቀናት ቆይታ እንዳደረግን ማስላት እንችላለን።

- የምናሰላው ቀን በአላትን እና ቅዳሜ እና እሁድን አካቶ አልያም ሳያካትት ስንት እንደሆነም ማወቅ ያስችላል።

5. Web Capture

- የተለያዩ ድረ ገፆችን የፊት ገፅታ ምስል ለማስቀረት እና ወደ JPG/JPEG፣ PNG አልያም PDF ፎርማት ለመቀየር ይህን ድረ ገፅ ይጠቀሙ።

6. Google NCR

- የጎግል ድረ ገፅን (google.com) ስንከፍት ጎግል ወደ የሀገራችን ዶሜን ያስገባናል። ለምሳሌ ጎግልን በኢትዮጵያ ስንከፍት google.com.et ወደሚለው ያሸጋግረናል። ይህም የሚሆነው ጎግል እንደየሀገራቱ የሚከለክለው እና የሚፈቅደው ስላለው ነው።

- እናም ጎግልን ያለምንም የሀገራት ገደብ ለመክፈት google.com/ncr ብለን መፈለግ በቂ ነው።

7. Virustotal

- ከጓደኞቻችን አልያም ከማናውቀው ግለሰብ የሚያጠራጥር ፋይል ከተላከልን እና ከኢንተርነየት በቀጥታ ካወረድነው በዚህ ድረ ገፅ አማካኝነት የተላከልን ፋይል ቫይረስ መያዙን እና አለመያዙን ማወቅ እንችላለን።

- ቪሩስቶታል ነፃ የኢንተርኔት የቫይረስ መመርመሪያ (ስካነር) ነው።

8. IPviking

- በአለም ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ የመረጃ ምንተፋዎች፣ የአይፒ አድራሻዎች፣ የመረጃ ዘራፊዎቹን አድራሻ እና የመሳሰሉ መረጃዎችን http://map.norsecorp.com/#/ በተባለው ድረ ገፅ ላይ መመልከት ይቻላል።

9. Hackertyper

- ይህን ድረ ገፅ ከፍተን የተለያዩ ፊደላትን እና ቁጥሮችን ስንጫን መረጃ ዘራፊዎች የሚጠቀሙበትን አይነት ገፅ ይከፍትልናል።

- በዚህም ጓደኞቻችን እና ወዳጆቻችን የተለያዩ ድርጅቶችን መረጃዎችን እየሰረቅን ለማስመሰልና ለመሸወድ እንችላለን።

10. Password Generator

- ጠንካራ እና በቀላሉ ብሬክ የማይደረግ የይለፍ ቃል ለፌስቡክ ለኢሜል ለሌሎች ፓስወርድ ለሚጠይቁ በሙሉ ጠንካራ የይለፍ ቃል (ፓስወርድ) ለመመስረት ይረዳናል።
✅ብዙ ሚሊዮኖችን የዘረፉት ሃከሮች መለሱ
========================
🔸በሳለፍነው ሳምንት የመረጃ መንታፊዎች ወይም ሃከሮች በዲጂታል ገንዘብ ታሪክ በአንድ ጊዜ የተፈጸመ እና እጅግ ግዙፍ የተባለዉን 600 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚተመን ክሪፕቶከረንሲ መዝረፋቸዉ ሲነገር ነበር። ይህ ከበድ ያለ የሳይበር ጥቃት በብሎክቼን ዘርፍ ላይ በተሰማራውና ፖሊ ኔትወርክ በተባለው ግዙፍ ድርጅት ያጋጠመ ሲሆን፤ በሲስተሙ ላይ ባጋጠመ መጠነኛ ተጋላጭነት በሺዎች የሚቆጠሩ የዲጂታል ገንዘቦች የተዘረፈበት ክስተት ነው፡፡

🔸ከደረሰው የሳይበር ጥቃት በኋላ ድርጅቱ በቲውተር ገፁ እንደጠቀሰው የተካሄደበት የክሪፕቶከረንሲ ዝርፊያ በመደበኛው ገንዘብ ሲተመን እስካሁን ካጋጠሙ ስርቆቶች ተወዳዳሪ እንደሌለው እና ዝርፊያውም በ10 ሺ የሚቆጠሩ የክሪፕቶ ደንበኞቹን በቀጥታ የሚያጠቃ መሆኑን አንስቷል፡፡ ደርጅቱ አክሎም ዝርፊውን ያካሄዱ የመረጃ ጠላፊዎች በየትኛውም ሀገር ህግ ትልቅ የኢኮኖሚ ወንጀል መፈፀማቸውን ተረድተው መፍትሄ ሊያመጣ የሚችል ስምምነት ከድርጅቱ ጋር እንዲመሰርቱ በቲዊተር መግለጫው አስታውቋ ነበር፡፡

🔸አሁን ላይ ይህን የሳይበር ጥቃት ያካሄዱ ሰዎች የዘረፉትን 600 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው የዲጂታል ገንዘብ ምንም አይነት ድርድር ሳያደርጉ ለድርጅቱ መመለሳቸው ታውቋል፡፡ Mr. White Hat በሚል ስም የተጠቀሱት የሳይበር ጥቃት አድራሾች እንዲህ ያሉ የደህንነት ጉድለቶችን ለማስተማር እና የግንዛቤ ስራ ለመስራት የሚንቀሳቀሱ ethical hacker መሆናቸውም ተነግሯል፡፡

🔸የብሎክቼን ፎረንሲክ ምርመራ ላይ የሚሰራው ቼንአናሊስስ እንደጠቀሰው እስካሁን ከተፈፀሙት የሳይበር ጥቃቶች ከባድ በሆነው በዚህ ጥቃት ላይ የተሳተፉ ሀከሮች የሰረቁትን ገንዘብ ለመውሰድ ምንም አላማ እንዳልነበራቸው እና የድርጅቱን የብሎክቼን ስርዓት ለመፈተሽና ከፍተቱን ለመለየት ያደረጉት ሙከራ መሆኑን አንስቷል፡፡ የፖሊ ኔትወርክ ኩባንያ በብሎክቼን ሲስተሙ ላይ የነበረውን የደህንነት ተጋላጭነት ለጠቆሙት ለእነዚህ ሰላማዊ የመረጃ ጠላፊዎች የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ቢያቀርብም ጥቃቱን ያደረሱት ሃከሮች ምንም አይነት ገንዘብ መቀበል እንደማይፈልጉ ቼንአናሊስስ አስታውቀዋል፡፡

🔸በብሎክቼን ያልተማከለ የዲጂታል መዝገብ ስርዓት እንዳንዱ ግብይቶች በይፋ የሚታወቁ በመሆናቸው ማንነቱ ያልታወቀ የመረጃ ጠላፊ የወሰደውን ገንዘብ በቀላሉ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚቸገር መሆኑን እነዚሁ የብሎክቼን ፎረንሲክ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ CNN
ምርጥ የተባሉ ቶረንትን ሳንጠቀም በቀጥታ አውርደን ወይም እዛው ላይ [Movies/Tv-Series/Tv-show] መመልከት የሚያስችሉን ሳይቶች

https://fmovies.to
https://www.viki.com
https://ww3.123movies.la
https://www.primewire.ag
https://tubitv.com
https://flixtor.to
https://ww.123movies.la
https://Vudu.com
https://yesmovies.ag
https://Peacocktv.com
https://Tinyzonetv.to
https://afdah.info
https://europixhd.io/
https://www.crackle.com/
https://ww1.1movies.is/
https://www.hoopladigital.com/
https://www.putlockers.cr
http://vumoo.to
https://123movies.net
✅ ይህ ብዙዎች የሚያወሩለት የቲክቶክ ዓለሙ ኮከብ ማን ነው?

ይህ የቲክቶክ የዓለም ፈርጥ እንደ ሌሎች ቢጤዎቹ በቲክቶክ ላይ ሲደንስ አይታይም። እንደውም ለዳንስ አካሉ እሺ ብሎ የሚታዘዝለት አይመስልም።

አይዘፍንም፤ ቃለ ተውኔት ጽፎ በመተወን ሌሎችን ቀልብ ለመሳብም አይጥርም።

የሌሎችን ድምጽና ትወና ለማስመሰል ደፋ ቀና ሲል አይታይም።

ዝም ብሎ የሰው ልጅን ውስብስብ ተግባራት ይተቻል፤ እንደ ዘበት።

በመላው ዓለም ካሉ የቲክቶክ ከዋክብት ሁሉ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው መካከል ሁለተኛው ነው።

100 ሚሊዮን ተከታዮች አሉት። ይህ ቁጥር ግን በአውሮፓ ብቻ ከታየ ቀዳሚ ያደርገዋል።

በቲክቶክ ላይ የሚለጥፋቸው ቪዲዮዎች ቀላል እና አጭር ናቸው።

የእርሱ ትችቶች በንግግር የተደገፉ አይደሉም፤ በቀላል ድርጊት የታጀቡ አንጂ።

ውስብስብ በሆነ መንገድ ቀላል ነገርን የሚከውኑ ሰዎችን ቪዲዮ በማሳየት፣ እርሱ ያንኑ ተግባር ቀላልና ግልፅ በሆነ መልኩ ያሳየዋል።

ከዚያን እጁን በማወናጨፍ እና አንገቱን በመነቅነቅ ያበቃል።
BBC AMAHARIC
✅ ኢትዮ ቴሌኮም በአጠቃላይ ጥቅል አገልግሎት ላይ የ20 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

✅ጥቅል ሳይገዙ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞችም ከ20 እስከ 30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ማድረጉንም ገልጧል።

✅ከሶስት እስከ አስር ደቂቃ የድምጽ አገልግሎት ለሚጠቀሙ ደንበኞች ከመደበኛው ታሪፍ የ20 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ትናንት የተናገሩት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ከአስር ደቂቃ በላይ ለሚጠቀሙ ደንበኞች ደግሞ የ30 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ተደርጓል ብለዋል።
(ኢዜአ)

✅ብዙ ጊዜ ፓኬጅ ለመግዛት please try Again እያለ ሲያማርረን የነበረው *999# በሚገርም ፍጥነት እየሰራ ይገኛል!🔥

✅Ethiotelecom ይህንን USSD Server በአሪፍ ሁኔታ Optimized አርጎታል!
እናመሰግናለን👍

👍 ሞክሩት
©️Elatech
በ2014 የ5ጂ ሞባይል ቴክኖሎጂ ሙከራ እንደሚደረግ ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ!

በበጀት ዓመቱ የ5ጂ ሞባይል ቴክኖሎጂ ሙከራ እንደሚደረግ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የኢትዮ ቴሌኮም የ3 ዓመት ስትራቴጂና የ2014 በጀት ዓመት እቅድን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ስትራቴጂክ እቅዱ ሲዘጋጅ የድርጅቱን ተወዳዳሪነት እና አስተማማኝ ዕድገት ለማረጋገጥ በሚያስችለ መልኩ እንደተዘጋጀ ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል።በበጀት ዓመቱ የ4ጂ ኤል ሲ እና የ4ጂ ኤል ቲ አድቫንስድ የማስፋፊያ ሥራዎች በክልሎች ዋና ዋና ከተማዎች እንደሚከናወን ነው የገለጹት።

በበጀት ዓመቱ 3.8 ሚሊዮን ተጨማሪ ደንበኞችን ለማስተናገድ የሚያስችል የሞባይል ኔትዎርክ አቅም ለመገንባት እቅድ እንደተያዘም ተገልጿል። የአገልግሎት ጥራትን፣ ተደራሽነትን አና የደንበኞች ተሞክሮን ለማሻሻል የሚያስችል የኔትዎርክ እና ሲስተም አቅም ማሳደጊያ ፕሮጀክቶች እንደሚካሄዱም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ 70 ቢሊየን ብር ለማግኘት አቅዶ እየሠራ እንደሆነ አስታውቋል።

Via EBC
#Android_Vs_iPhone

🚨 #Android ከ #iphone የተሻለ ነው ሊያስብሉት የሚችሉት ጥቂቶቹ ፊቸሮች

🚨በአነስተኛ ዋጋ #Android ማግፕት ይቻላል። #iPhone ግን ዝቅተፕኛ ማግኘት የምትችሉት 399$ ነውን

🚨#Android የተሻለ Refresh Rate ሲኖረው፤ ከሱም በተጨማሪ Screen to body Ratio የተሻለ አለው።

🚨ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ UI ሲኖረው በተጨማሪም እንደፈለጋችሁ Customize ማድረግ ትችላላችሁ።

Nurutech
✅ ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን ሊተካ የሚችል የማህበራዊ ትስስር ገጽ ስራ ላይ ልታውል ነው
በኢትዮጵያ ውስጥ የለሙ የተግባቦት (የኮሙዩኒኬሽን) ፕላትፎርሞች አሁን ላይ ወደ ሙከራ መግባታቸውን የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል።

✅ፌስቡክና ትዊተር ኢትዮጵያዊ የሆነ እውነት የያዙና ተጽእኖ የሚፈጥሩ መልእክቶች ካሉ በአስቸኳይ እንዲጠፉ እያደረጉ ነው ብለዋል።
@dani_apps
⚠️ማስጠንቀቂያ !

❌ በአሁኑ ሰዓት ብዙ ሰዎች እንዲሁም የቻናላችን አባላት 999 ላይ ነፃ ጥቅል አገኘን ብለው unlimited monthly pacage ( ያልተገደበ ወርሃዊ ጥቅል ) እየገዙ ነው ቴሌ እስከአሁን ስለዚ ነገር ያሳወቀው ጉዳይ የለም! ሲመስለኝ ሰሞኑን 999 ኝን optimize እያደረጉት ነበር በዛ መሃል የተፈጠረ Bug ይመስለኛል እናም ልላችሁ የምፈልገው ነገር ነፃ አገኘን ብላችሁ በቀጣይ የማትወጡበት እዳ ውስጥ እንዳትገቡ ነው ( ብራችሁን ቀጣይ ቀን በ Negative ሊቆጥርባችሁ ይችላል 😟 ) 🔥የኛ ያለሆነ ነገርም አይጠቅመንም ስለዚህ ሁሉንም ነገር በራሳችሁ ሀላፊነት አድርጉ ወደ ፊት ለሚመጣባችሁ ችግር😊
‼️ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም‼️

✳️ ሰላም 🙏 ዛሬ ብዙ ሰዎች እያወሩት ስላለው እና አብዛኞቻቹ ስለጠየቃቹኝ ስለ ቴሌ ነፃ ፓኬጅ አገልግሎት አንዳንድ ነገሮች ልበላችሁ።

◽️ይሄንን ፁሁፍ እስከፃፍኩበት ሰዓት ድርስ በነፃ ፓኬጅ መግዛት ትችላላችሁ። አንዳንድ ሰዎች ቴሌ የሳይበር ጥቃት ደርሶበታል የሚል ወሬ እያወሩ ነው።

◽️እውነት ይሁን አይሁን በእርግጠኝነት ለመናገር ይከብዳል። ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች ያጠራጠራሉ።

1. ፓኬጅ በነፃ መስራቱ ነው። እርግጥ ነው ይሄ ምንም የሚያሳምን ነገር የለውም ልትሉ ትችላላችሁ። ወደ ሁለተኛው እንሂድ

2. ሲማቹህ ላይ ምንም ብር ሳይኖር ወደ ሌላ ሰው ስትደውሉ የደወላቹት ስልክ ይነሳል አስተውሉ ስልካቹህ ላይ ምንም ብር ሳይኖር ማለት ነው። እና ይነሳል ግን ምንም ድምፅ የለውም ሁኔታው ግራ የሚያጋባ ነው።

3. ቴሌ እንኳን ቅናሽ ቢያደርግ እንጀዚህ ሙሉ ለሙሉ Free አያርገውም። ምክንያቱም ያከስርዋል። ብቻ የሳይበር ጥቃት ቴሌ ላይ ስለመድርሱ በትክክል የሚገልፅ መርጃ ስላልወጣ እርግጠኛ መሆን አይቻልም። በዚህ ጎዳይ ቴሌ እስካሁን ምንም ያለው ነገር የለም።

‼️አንድ ጓደኛዬ እንደዚ ዳታ በነፃ ነው ሲባል ሰምቶ ማታውን ሞከርው እናም ሰራለት። በጣም ብዙ ሰዓት እንደፈለገ ተጠቀመ። ጥዋቱን ግን ስልኩን ከፍቶ ሲያየው - 423 ብር ተደርገበት

‼️እና ወደ 994 ደውሎ ሁኔታውኝ አስርዳቸው እነሱም ማታውን የተጠቀመውን እያወራረዱ እንደሆነ ነው የነገሩት። ይሀው ልጁ አሁን ሲሙን ልጣለው ወይስ ምን ብሎ ሀሳብ ውስጥ ገብቷል 😂

◽️እና በአጭሩ ምን ልላቹህ ፈልጌ ነው ይሄ ነፃ ፓኬጅ የተባለው ነገር ይሰራል ነገር ግን ሲስተሙ በስትክክል መስራት ሲጀምር ልክ እንደ ልጁ በተጠቀማቹት ልክ ያወራርዳሉ ማለት ነው።
​​✳️ ሞባይላችንን ተጠቅምን ቢሮ፣ ሱቅ ወይንም እቤት ውስጥ ያለን ኮምፒወተራችንን መንካት ሳያስፈልግ፣ ካለንበት ስፍራ እንዴት መቆጣጠር እንችላለን?

◽️ ድርጅት ኖሯችሁ ባጋጣሚ እሩቅ ቦታ ቢሆኑና ሂሳብ ለመዝጋት (Zreport) በሞባይሎ ትዛዝ ማውጣት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

◽️ ኮምፒውተሮት አዲስ አበባ ሆኖ እርሶ ሆነ ለመዝናናት ውጭ ሃገር ከሆነ ያሉት፣ ያሉበት ሆነው ማን በኮምፒውተሮት ምን እየተጠቀመ እንደሆነ በደንብ መከታተል እንደሚችሉስ ያውቃሉ?

◽️ ለስራም ባሉበት ሆነው ኮምፒውተሮ ላይ የሆነ ነገር ቢበላሽ የኮምፒውተር ባለሞያው መምጣይ ሳያስፈልገው ካለበት ሆኖ ችግሩን እንዲፈታስ?

◽️ ምን እሱ ብቻ ባሉበት ሆነው ሙዚቃ መቀየር ፣ሰራተኛ በስንት ሰአት እንደገባ፣ጌም ማን እየተጫወተ እነደሆነ፣ በቀን ምን ያህል እንደተሰራ ፣ልጆቾት ምን አይነት ፊልም እያዩ እንደሆነ በተጨማሪም እቤትዎ ትንሽ ካሜራ ካሎት የትም ሆነው ማን እንደገባደረገ ነው የሚለውን መከታተልስ?

🔺መልሳችሁ አዎ ከሆነ ምኞቶን የምታሳካ አሪፍ ዘዴ ይዘንላችኅል።

◽️ በመጀመሪያ ለዚህ ስራ የሚጠቅመን በሞባይላችን እና ኮምፒውተር ላይ የምንጭነው ቲም ቪወር (Team Viewer) የተባለ ሶፍትዌር ዳውንሎድ ማድረግ አለብን። ለ ኮምፒዩተራቹ ከዚህ በይነ መረብ ታገኙታላቹ።

◽️ ሶፍትዌሮቹን ዳውንሎድ ካደረግን በኅላ በፕሮግራሙ ያጫጫን step መሰረት በኮምፒተራችን እና ስልካችን ላይ እንጭናለን። ይህን ስናደርግ ፕሮግራሙ በራሱ መለያ ወይንም መገናኛ ኮድ እና መግቢያ ፓስዎርድ ይሰጠናል።

◽️ ፓስዎርድ በራሱ ጊዜ ኮምፒውተራችንን ስንከፍት ስለሚቀያየር ለሁልጊዜ የሚሆን የራሳችንን ፓስዎርድ Team Viewer ፓስወርድ Setting ውስጥ በመግባት "Setup Unattended Access" የሚለውን ምርጫ ነክተን የራሳችንን እንሰጠዋለን።

◽️በመቀጠል ስልካችን ላይ የጫነውን ፕሮግራም ከፍተን ቅድም ኮምፒውተራችን ላይ የሰጠንን ID እናስገባና connect እንልዋልን። በዚ ጊዜ ፓስዎርድ ስለሚጠይቅ ኮምፒውተሩ ላይ የፈጠርነውን ፓስዎርድ በማስገባት በቀላሉ መቆጣጠር እና መጠቀም እንጅምራለን ማለት ነው።

◽️ ይህ ዘዴ በምንኛው ግዜ የኢንተርኔት አገልግሎት በኮምፒውተሩም በሞባይላችንም ላይ ሊኖረን ይገባል።

◽️ የፈጠርነውን ፓስዎርድ እና ID ለስራ ካልሆነ ለሌላ ሰው ማሳየት የለብንም ምክንያቱም ሌሎች ሰዎች በፈለጉት ጊዜ ገብተው ችግር ሊፈጥሩብን ይችላሉ።
#FactCheck

ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ እንደተደረገ የሚጠቁም መልዕክት ደርሶናል፣ በርካቶች ደግሞ አንድ ኮድን በመጠቀም በነፃ የኢንተርኔት ፓኬጅ ማግኘት እንደቻሉ ሲፅፉ ተመልክተናል።

በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ የድርጅቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩን አናግሯል። የሰጡን መረጃ በዚህ መልኩ ይቀርባል:

"ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ አልተደረገም። ስራችን ሳይቋረጥ አዳዲስ አገልግሎቶች ላይ ማስተካከያ (configuration) እያረግን ነው። በዚህ ምክንያት ጥቂት ደንበኞቻችን አንዳንድ አገልግሎቶችን [በነፃ] ሊወስዱ/ሊያገኙ ችለዋል። ሁኔታውን እኛም አውቀነው እየሰራንበት ነው፣ በቁጥጥራችን ስር ነው" ብለዋል።

ድርጅቱ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው መረጃ በመጪው 2014 ዓ.ም ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የሆኑ አዳዲስ አሰራሮችን እተገብራለሁ ብሏል። ከዚህም አንዱ ደንበኞች ፓኬጅ ሲጠቀሙ የ20 በመቶ ቅናሽ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በአዲስ አመት ደግሞ ለአንድ ወር የሚቆይ አደይ አበባ የተሰኘ የሞባይል ፓኬጅ አገልገሎት 44 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት ስራ ላይ ይውላል ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት 70 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት እንዲሁም የደንበኞቹን ቁጥር 64 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን ኢዜአ አስነብቧል።
👍1
​​✳️ የዘመናዊ ኮምፒዉተር አፈጣጠርና እድገት አጭር ታሪክ

◽️ 1950ዎቹ - በ "ቫኪዩም ቲዩብ" ብቻ ይሰሩ የነበሩት ኮምፒዉተሮች መጠናቸዉ የአንድ ቤት መጠን እስኪያክል ድረስ እጅግ ግዙፍ የነበሩ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ እጅግ ቀርፍፍ ነበሩ። በወቅቱ እነዚህን ኮምፒዉተሮች በብቸኝነት ይጠቀምባቸዉ የነበረዉ የአሜሪካ ሚሊቴሪ ተቋም ሲሆን ዋጋቸዉም ውድ ነበር።

◽️1960ዎቹ - በትራንዚስተሮች መፈጠር የተነሳ ቀርፍፍዉን የ"ቫኪዩም ቲዩብን" አሰራርን በመቀየር የኮምፒዉተሮች የአካል መጠን መቀነስ ሲቻል ብቃታቸዉንም ማሻሻል ተቻለ። በዚህ ወቅት ነበር ሜይንፍሬም (mainframe) የተባሉ ፈጣንና ወድ ኮምፒዉተሮች ተፈጥረዉ ከማሊቴሪና የመንግስት ተቋም አልፎ ለግል ድርጅቶች ጥቅም መዋል የጀመሩት።

◽️1970ዎቹ - በመቶዎች የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮችን ያካተተ ኢንቴግሬትድ ሰርኪዩት "Intergrated Circute Board" አንድ ክፍልን ሊሞላ የሚችል መጠን ያለዉን የሜይንፍሬም ኮምፒዉተር አሳንሶ በጠረጴዛ ላይ የሚቀመጥ ኮምፒዉተር "Desktop" እንዲፈጠር አስቻለ።

◽️1980ዎቹ - በሚሊዮን የሚቆጠሩ ትራንዚስተሮች እጅግ በጣም ትኝሽ መጠን ባለዉ የኮምፒዉተር ቺፕ ዉስጥ ህያዉ መሆን የኮምፒዉተር በጣም አንሶ በአንዲት ቦርሳ ዉስጥ የሚገባና ከድርጅት አልፎ ለግል ጥቅም መዋል የሚችልበት "Personal Computer (PC)" ዘመን ተወለደ። ኮምፒዉተሮች ጠረጴዛ ላይ ከመቀመጥ አልፈዉ ጭን ላይ የሚቀመጡበትን መጠን ይዘዉ "laptop" በሚል ስያሜ ብቅ አለ።

◽️ 1990ዎቹ - የኢንተርኔት መወለድ ኮምፒዉተሮች እርስ በእርሳቸዉ እና በሌላ ቦታ ከሚገኝ ከፍተኛ አቅምና የመረጃ ብዛት ያለዉ የኮምፒዉተር ስብስብ "data center" ጋር ተገናኝተዉ ከዚህ ቀደም በራሳቸዉ አቅም ብቻ ከሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የላቀ ጥቅምን በፍጥነት መስጠት እንዲችሉ አደረገ።

◽️ 2000 - ለእጃችን መዳፍ እንኳን የማይሞሉ፣ ነገር ግን ብቃታቸዉ ከአንድ መጠኑ ከፍ ካለና ምርጥ ከሚባል ኮምፒዉተር ያልተናነሰ ተግባር ማከናወን የሚችሉ እንደ ረቀቀ ስልክ (Smartphone) ያሉ ተንቀሳቃሽ ቁሶች ላይ ዋሉ። ከስልኮችም አልፈዉ ታብሌቶቻችን፣ ሰዓቶቻችን፣ የቤት ቁሶቻችን፣ መኪናዎቻችን እና ልብሶቻችን ሳይቀሩ የኮምፒዉቲንግ ብቃት እየተካተተላቸዉ ይገኛል።

◽️ ከዚህም በተጨማሪ ይህ ዘመን አብሮን ባለ ኮምፒዉተር ላይ ብቻ ከመደገፍ ይልቅ እንደ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ (Cloud computing) እና የመሴሰሉት የተራቀቁ በኢንተርኔት ተገናኝተዉ መሰራት የሚችሉ እና ከእኛ ርቀዉ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተበታትነዉ በሚገኙ እጆግ ፈጣን ኮምፒዉተሮች አማካኝነት በርካታ ተግባር ማከናወን ተቻለ።

◽️ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ማለት የኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች ሶፍትዌርኝ፣ ሃርድዌርን፣ መረጃን አና የተለያዩ ዲጂታል አሠራሮችን በራሳቸዉ ኮምፒዉተር ላይ ከመጫን ይልቅ ካሉበት ሰርቨሮች በኢንተርኔት አማካኝነት በየትኛዉም ጊዜና ቦታ ልክ መቦራትና ዉሃ ቤታችን ድረስ እንደሚመጣዉ ከአገለግሎት ሰጪዎች ላይ በሚፈልጉት መጠን መጠቀም የሚያስችል አሠራር ነዉ።

◽️ የኮምፒዉተር እድገትና ፍጥነት አሁንም ሩጫዉን ቀጥሏል። ከላይ የተጠቀሰዉን አስደናቂ የኮምፒዉተር የለዉጥ እድገት ህያዉ ያደረገልን የMoore's Law ወደ ፍጻሜ እየመጣ ያለ ይመስላል። ምክንያቱም የትራንዚስተሮች እጅግ አናሳ በሆነ መጠንና በጣም በተጠቀጠቀ ሁኔታ በአነስተኛ ቦታ ላይ እንዲያርፉ የሚደረግበት የቺፕ አሠራር የመጨረሻ ገደቡና ጥጉ ላይ እየደረሰ ስለመጣ ነዉ። አንድን ትራንዚስተር ምንም ያህል እናሳንሰዉ ብንል ከአቶሚክ መጠን በታች ልናደርገዉ አንችልም።

◽️ ይህ ሂደት ወደ ፍጻሜዉ እየተቃረበ የመምጣቱን ባለሞያዎች፣ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች እና አምራቾችም ይስማሙበታል። የትንቢቱ ባለቤት ጎርደን ሙር እራሱ በ2015 ዓ.ም. በሰጠዉ ቃለ ምልልስ ከ50 ዓመታት በፊት የተነበየዉ Moore's Law ማክተማያዉ እየተቃረበ እንደመጣ ጠቁሟል።

◽️ ኮምፒዉተር እስከዛሬ በዚህ አይነት የረቀቀ የእድገት ሂደት ዉስጥ ካለፈ፣ "ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?" የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮ ይመጣል።

🔺"ታድያ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል?"

◽️ የወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች በጨረር፣ በኳንተም የፊዚክስ ህግ እና በሰዉነታችን ዉስጥ በሚገኙ በዲኤንኤ አማካኝነት የሚሰሩ ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም በማንኛዉም ቁስ ላይ ተለጥፈዉ የሚገኙ፣ ወይም ደግሞ የራሳችን ኮምፒዉተር ሳያስፈልገን በሌላ ቦታ ተቀምጠዉ በኢንተርኔት አማካኝነት ያላቸዉን አቅም ሙሉ በሙሉ ከፈለግነዉ ቦታ ሆነን መጠቀም የምንችልባቸዉ አይነቶችም ሊሆኑ ይችላሉ።

◽️ የፋይበር ኦፕቲክስ "Finer-optic" ወይንም በጨረር አማካኝነት መረጃን ከአንድ ኮምፒዉተር ወደ ሌላዉ በፈጣን ሁኔታ በማስተላለፉ አሰራር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። በፋይበር ኦፕቲክስ የሚተላለፉ መረጃዎች በኤሌትሪክ ሽቦ ዉስጥ ከሚተላለፉት ፍጥነታቸዉ በእጅጉ የተሻለ ሲሆን፣ በተጨማሪም እንደ ኤሌክትሮማግኔቲክ ያሉ የተለያዩ ጣልቃ ገብ ግብዓቶች አሠራሩን አያደናቅፉትም።

◽️ ይህ ከተቻለ የኮምፒዉተሮችን የዉስጥ የመረጃ አቀማመር አቅም እጅጉን እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል። ምንም እንኳን ተመራማሪዎች በዚህ ዙርያ ተስፋ ሰጪ የሙከራ ስራዎች ቢያከናዉኑም መጠኑ ያነሰና በብዛት ተመርቶ በኮምፒዉተሮች ዉስጥ ሊገጠም የሚችልን በጨረር የሚሠሩ ቺፕ ህያዉ ለማድረግ ሙሉ ስኬትን እስከአሁን አላገኙም።

◽️ በጨረር አማካኝነት የሚሰሩ ኮምፒዉተሮችን ለመፍጠር በሚደረገዉ ምርምር የኢትዮጵያዉ ዶክተር ሰለሞን አስፍ እጅ አለበት። ዶክተር ሰለሞን የበርካታ ፈጠራ ስራዎች ባለቤት ሲሆን በዋናነት የሚታወቅበት የፈጠራ ስራዉ በተለመደዉ አሠራር በኤሌትሪክ ከሚሰሩ ትራንዚስተሮች ይልቅ ኮምፒዉተሮች በብርሃን ጨረር (optical pulse) አማካኝነት መረጃን ለማስላት የሚችሉበትን ሙከራ ያደረገበት የምርምር ስራዉ ነዉ።

◽️ ይህ ግኝት ለወደፊቶቹ ኮምፒዉተሮች አሁን ካሉት ማሽኖች እስከ አንድ ሺህ እጥፍ ፍጥነት እንደሚሰጣቸዉ ሲጠበቅ፣ የኤሌክትሪክ ፍጆታንም በእጅጉ ይቆጥባል ተብሏል። የዶክተር ሰለሞን ዋና ግኝት ፎቶዲቴክተር (photodetector) የሚባሉትና የብርሃን ጨረር መልዕክትን (optical signals) አጉልተዉ የሚያስተላልፉ ቁሶች ("amplifiers") እንዴት አድርገዉ መልዕክትን ለማይክሮፕሮሰሰሮች በሚገባ መንገድ በማስተላለፍ ጨረር መልዕክቶችን ወደ (electrical signals) በመቀየር ለኮምፒዉተር አሰራር ጥቅም እንዲዉሉ ማድረግ ነዉ።
✳️ ኤልጂ የ6ጂን ሲግናሎችን ታይቶ በማይታወቅ ርቀት ማስተላለፍ ቻለ
====================
📊 የ5ጂ ቴክኖሎጂ ገና ባደጉት ሀገራት እንኳን በቅጡ ባልተዘረጋበት በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የኮምዩኒኬሽን ኩባንያዎች የቀጣዩ ትውልድ ኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የሆነው 6ጂን ለመስራት በጥድፊያ ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ግዙፉ የኮሪያ ቴክኖሎጂ ኩባንያ ኤልጂ ከጀርመኑ የምርምር ተቋም ፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመተባበር ለቴክኖሎጂው አንድ እምርታ በሆነ መልኩ የ6ጂ ሲግናሎችን በ100 ሜትር ርቀት ውስጥ ማስተላለፍ ችሏል፡፡

📊 የ6ኛው ትውልድ የኮምዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በራሱ እጅግ በጣም ፈጣን ከሆነው ከ5ጂ ጋር እንኳን ሲነፃፀር መረጃን በበይነ መረብ የማስተላለፍ ፍጥነቱ በ50 እጥፍ የላቀ ሲሆን የመረጃዎች የመዘግየት ልኬትንም (latency) በ10 በመቶ እንደሚቀንስና የሚላከው መረጃ ጥራትንም እንደሚያሳድግ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ የቴክኖሎጂው እምርታዎች ተደማምረው ታድያ በቤት ውስጥም ሆነ በስራ ቦታ ከበይነ መረብ ጋር ያለውን ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሳድጉት ተገምቷል፡፡

📊 ሲግናሎቹ በሚተላለፉበት ወቅት የኃይል እጥረት ስለሚያጋጥማቸውና በዚህም ምክንያት የሚጓዙት ርቀት የተገደበ መሆኑ የ6ኛው ትውልድ ቴክኖሎጂን እውን ማድረግ ቀድመው ከነበሩት ትውልዶችም በላይ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ በዚህ ሳብያ ቴክኖሎጂውን በበቂ ሁኔታ አድጎ ለገበያ ሲውል ለማየት ቢያንስ እ.አ.አ ከ2025 እስከ 2029 ድረስ ወይም ከዚያ በላይ መጠበቅ እንደሚገባ የባለድርሻዎች ግምት ነው፡፡

📊 ኤልጂ ከጥቂት ወራት በፊት ሌላኛው ግዙፍ ኮሪያዊ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳምሰንግ የ6ጂ ሲግናሎችን በ15 ሜትር ርቀት ውስጥ በማስተላለፍ የያዘውን ክብረ ወሰን ነው አሁን ላይ ከአንድ ህንፃ ጣርያ ወደ ሌላኛው በማስተላለፍ በከፍተኛ መጠን ያሻሻለው፡፡ እንደ ኩባንያው ከሆነ ሲግናሎቹ ይህን ያህን ርቀት እንዲጓዙለት ያስቻለው ከፍራንሆፈር ጌዜልሻፍት ጋር በመሆን ያበለፀገውና በ155 እና 175 ጊጋ ሀርዝ መካከል ባለ ፍሪኩዌንሲ ውስጥ እስከ 15 ዴሲቤል ሚሊዋት ድረስ የሚለኩ የተረጋጉ ሲግናሎችን መላክ የሚያስችለው አዲስ አምፕሊፋየር ነው፡፡

📊 በተጨማሪም የጋራ ጥናት ቡድኑ እንደተቀባዩ አቀማመጥ መተላለፊያዎችም እንዲለዋወጡ የሚያስችለው የአዳፕቲቭ ቢምፎርሚንግ ሰርተው ያሳዩ ሲሆን የተለያዩ ሲግናሎችን አቀናጅቶ ወደሚፈለገው አንቴና ለመላክ የሚያስችል ስልትንም ተጠቅመዋል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
Elatech
Secure Incoming Call @dani_apps.apk
5.3 MB
👉Secure Incoming Call

✅ ይህ App ሰዉ ሲደዉልላችሁ የደዋዩ ስም እንዳይታይ ማድረግ ትችላላችሁ።