DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
TeraBox Cloud Storage Premium _@dani_apps.apk
24.8 MB
🔥TeraBox Cloud Storage: Cloud Backup & Data backup

📌ስልካቹ Storage Full እያለ ላስቸገራቹ እና ስልካቹ ብዙ Storage ለሌለው ለስልካቹ 1024 GB / 1 TB Cloud Storage: በዚህ አፕሊኬሽን ማግኘት ትችላላቹ
​​✳️ Cloud Storage

◽️ ክላውድ ስቶሬጅ የምንለው በኮምፒውተር ወይም በሞባይል ስልክዎት የትኛውም ክፍል ላይ የተቀመጠ ፋይልና ዳታ በሌላ ድርጅት በተዘጋጀ የዳታ ማስቀመጫ ላይ የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የምናስቀምጥበት ነው፡፡

◽️ በአሁን ሰዓት ይሄን አገልግሎት የተለያዮ ድርጅቶች እየሰጡ ሲሆን በዋናነት Microsoft, Google, and Amazon ትልቁን ቦታ በመያዝ የሚጠቀሱ ሲሆኑ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ለማስቀመጫ ድርጅቶቹ ለመጠቀሚያ የሚያስፈልግ ስም እና የይለፍ ቃል በማዘጋጀት የተወሰኑ ፋይሎችን በነፃ እንዲሁም በክፍያ እንድናስቀምጥ ያደርጋል፡፡

◽️ መጠባበቂያ ፋይሎችን እና ዶክመንቶችን ክላውድ ስቶሬጂ አገልግሎትን መጠቀም ፍላጎት እየጨመረ የመጣ እና የተለያዮ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፋይሎች ጥብቅ በሆነ ቦታ መቀመጣቸው፣ የምናስቀምጠውን ፋይል ከየትኛውም ቦታና በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ሆነን መጠቀም እንችላለን እንዲሁም የግል ፋይሎቻችን የተቀመጠበት ኮምፒውተር ቢሰረቅ፣ ቢበላሽ ወይም በእሳት ቢቃጠል ካስቀመጥንበት ድርጂት ፋይሎቹን ካለምንም ችግር እናገኛለን፡፡

◽️ ባክአፕ ክላውድ በመጠቀም ፋይል እና ዳታ ስናስቀምጥ ኮምፒውተራችን የተገናኘበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነት የሚወስነው ይሆናል ትልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለማስቀመጥ ቀናትን ሊፈጅ የሚችል ሲሆን አገልግሎቱን ለመስጠት Amazon S3፣ Google Mozy እና Microsoft Sky Drive የሚሉ ሶፍትዌሮችን አዘጋጅተዋል፡፡

◽️ ማክሮሶፍት ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Sky Driveን በመጠቀም እስከ 25 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡ 

◽️ በተጨማሪም Google ድርጅት ላይ ለማስቀመጥ Google Driveን በመጠቀም እስከ 15 GB በነፃ ማንኛውም ሰው ከስልክዎ ላይ ያሉትን ፎቶና የመሳሰሉት መረጃዎች ማስቀመጥ የሚችል ሲሆን ባጠቃላይ በነፃ ከሰጠን ስቶሬጅ በላይ ለማስቀመጥ ክፍያ የሚያስፈልግ በመሆኑ ክፍያው የሚወሰነው እንደምናስቀምጠው ዳታ መጠን፣ አገልግሎቱን እንደተጠቀምነው ብዛት እንዲሁም የፋይሎቹ ቁጥር ነው፡፡
Abyssiniatech
🧐ታይታኒክ እንዴት ልትሰምጥ ቻለች❓ 🚢

▫️አንድ አዲስ ጥናት ተይታኒክ የተባለችው መርከብ የሰመጠችው በበረዶ ግግር ምክንያት እንዳልሆነ አመለከተ፡፡ መርከቧ በሚያዚያ ወር 1912 ከሳውዝአምፕተን ወደ ኒዮርክ በፍጥነት ጎዞ በማድረግ ላይ ሳለች ካልታሰበ የበረዶ ግግር ጋር ተጋጭታ እንደሰመጠች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ከጊዜ በኋላ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ለመርከቧ መስመጥ ትክክለኛው መንስኤ ፍጥነቷ ወይም የበረዶ ግግር አይደለም የሚሉ ናቸው፡፡

▫️ስለ ታይታኒክ በብዛት በመጻፍ የሚታወቁት አይርላንዳዊ ሴናን ሞሎኒ ለመርከቧ አደጋ መነሻ ምክንያት የሆነው በረዶ ሳይሆን እሳት ነው ይላሉ፡፡ ታይምስ ለተባው መጽሔት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የታሪክ ጸሐፊ መርከቧ የሰመጠችው በእሳት፣ በረዶና ከፍተኛ ቸልተኝነት ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

▫️መርከቧ ከወደቧ ብዙም ሳትርቅ ከከሰል ማንደጃው ውስጥ እሳት መቀጣጠል እንደጀመረ የሚናገሩት ሞሎኒ ይህ እሳት በመርከቧ የውስጠኛ ክፍል የሚገኝን 9 ሜትር የሚረዝም የብረት ምሰሶ እንደለበለበው የሚያሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ስለ መርከቧ መስመጥ አዲስ የተባለው መረጃም ከዚህ ግኝት ጋር የተያዘ ነው፡፡

▫️ይህ እሳት የተነሳበት የመርከቧ ክፍል ደግሞ ከበረዶ ግግሩ ጋር በቀጥታ የተላተመው ክፍል እንደሆነ ይታመናል፡፡ እሳቱ የመርከቧን ተጋላጭ ክፍል አዳክሞት የነበረ በመሆኑ የበረዶው ግግር መርከቧን ሊጎዳት እንደቻለ ሞሎኒ እምነታቸውን አስረድተዋል፡፡ አክለውም እሳቱ ምንም እንኳን ከነመሻው የታወቀ ቢሆንም መርከቧ መነሳት ከነበረባት ሰዓት ለሁለት ጊዜያት ያክል በመዘግየቷ የተማረሩ ተጓዦች ለአደጋ ይጋለጣሉ በሚል ምክንያት ይፋ ሳይደረግ ተደብቆ ቆይቷል ብለዋል፡፡

▫️ይህ የእሳት መላምት በ2004 በፕሮፌሰር ሮበርት ኢስንሀይ ከተሰራው ምርምር ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ አሁን ላይ ብዙ የታሪክ ተመራማሪዎች መርከቧ ውስጥ እሳት መነሳቱን ቢያምኑም ይህ አዲስ በፎቶግራፍ የተደገፈ ግኝ ግን በትክክል እሳቱ የት ላይ እንደተነሳ እና ከመርከቧ መስመጥ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ የሚያብራራ ነው፡፡
elatech
​​✳️ ውድ የ Dani Apps ቤተሰቦች ዛሬ በትንሹ ስለ Android እናያለን።

🔺Android ምንድን ነው?

◽️ Android Open Source የሆነ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሲሆን በብዛት ለስማርት ስልኮች ያገለግላል።

◽️ ጉግል በ 2003 አንድሮድን ያገኘ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዓለም ላይ ለተንቀሳቃሽ ስልኮች በጣም ታዋቂው ኦፐሬቲንግ ሲስተም ሊሆን ችሏል።

🔺Android ስራው ምንድን ነው?

◽️ አንድሮድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ስለሆነ ዓላማው ተጠቃሚውን እና መሣሪያውን ማገናኘት ወይም ማግባባት ነው።

🔺ለምሳሌ ፣ አንድ ተጠቃሚ Text መላክ በሚፈልግበት ጊዜ አንድሮይድ ለተጠቃሚው የመፃፊያ Keyboard ይሰጣል። ፅፎ ሲጨርስ ደግሞ ተጠቃሚው መላኪያውን በሚነካበት ጊዜ Android መልእክቱ እንዲልክ ስልኩን ይመራዋል።

◽️ Google በየአመቱ ለAndroid System Update ይለቃል። ምንም እንኳን Google ለAndroid እድገት ትልቅ ሚና ቢጫወትም ጉግል የAndroid ኦፐሬቲንግ ሲስተምን ለሞባይል አምራቾች በነፃ ይሰጣል።

◽️ Electric ፣ Samsung ፣ LG ፣ Huawei ፣ Lenevo እና Sony Androidን በሚያመርቷቸው ስልኮች ላይ ከሚጭኑ አምራቾች ጥቂቶቹ ናቸው። በአሁን ሰአት Android Operating System በአንድ ቢሊዮን ሞባይሎች ላይ ተጭኖ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

◽️ብዙ ሰዎች የሚያነሱት አንድ የተለመደ ጥያቄ Android ለምን በተለያዩ ስልኮች ላይ የተለያየ መልክ ይይዛል? የሚል ነው። መልሱም ብዙ የAndroid ስሪቶች አሉ ምክንያቱም Android Open Source ሶፍትዌር ስለሆነ የሞባይል አምራቾች በሶፍትዌሩ ላይ የሚፈልጓቸውን ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ።

🔺Android vs. iOS?

◽️ የAndroid ዋና ተፎካካሪ የሆነው ISO በአይፎን ስልኮች ላይ የሚሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ነው። በAndroid እና iOS የሚያመሳስሉም የሚያለያዩም ነገሮች አሉ። ወደ እሱ ሲመጣ ሁለቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ከ Wi-Fi ጋር መገናኘት ፣ አፖችን ማሰራት ፣ Text መላክ እና ፎቶ ማንሳት ያሉ ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። ሆኖም ግን በመልክ እና በስሜት ረገድ ዋና ዋና ልዩነቶች አሉ።

🔺የAndroid ጥቅሞች

◽️ የAndroid ዋነኛው ጠቀሜታ ተጠቃሚው ብዙ አማራጮች ያሉት መሆኑ ነው። Androidን እንደ ኦፐሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ በሺዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ መሣሪያዎች አሉ። በሌላ በኩል IOSን የሚፈልጉ ከሆነ አይፎን መግዛት ይኖርቦታል።

◽️ ወደ Android አፖች ሲመጣ ተጠቃሚው እንዲሁ ብዙ አማራጮች አሉት። በAndroid የአፖች መደብር ላይ ብዙ ጥራት ያላቸው አፖች አሉ። የAndroid App Store ፕሮግራመሮች የAndroid አፖችን እንዲሰሩ በከፍተኛ ደረጃ ይበረታታሉ። የሚደረግባቸውም ቁጥጥር ከApple ጋር ሲነፃፀር አናሳ ነው።

🔺Google Play / Play Store ምንድን ነው?

◽️ የGoogle Play Store ተጠቃሚዎች ጨዋታዎችን ፣ በአንድሮይድ ኩባንያ የተሰሩ አፖችን ፣ መጻሕፍትን ፣ ፊልሞችን ፣ ሙዚቃን እና ሌሎችንም የሚገዙበት የገበያ ቦታ ነው። በዚህም ምክንያት የPlay Store ለአንድሮይድ መሣሪያ ያለው ጥቅም ትልቅ ነው።

◽️ ያለምንም ጥርጥር Android ለረጅም ጊዜ ያገለግለናል ፡፡ Android በ2000 ዎቹ መጀመሪያ ከነበሩት ቀናት በጣም ረዥም መንገድ መጥቷል። ራሱንም በማዘመን ተደራሽ ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል መሆንም ችሏል።
Abyssiniatech
​​✅ ቴክኖሎጂያዊ እውነታዎች፡

◽️ በ1950ዎቹ ኮምፒውተር አሁን በሚጠራበት ስም ሳይሆን ስሙ "Electronic brain" ነበር::

◽️ በአለማችን የመጀመሪያው 1GB hard disk የተሰራው በ 1980 በ IBM ሲሆን ዋጋውም 40,000$ ነበር።

◽️ Technologyን የመፍራት በሽታ technophobia ይባላል። ሀገራችንም ውስጥ ወጣቱን ጨምሮ ባለስልጣናት፣ ሀብታሞች እንዲሁም ብዙ የህብረተሰብ ክፍል የዚህ በሽታ ተጠቂ ናቸው።

◽️ የሰው ልጅ አእምሮ የማሰብ ብቃት በኮምፒውተር CPU ሒሳብ ቢታሰብ 3000Ghz በላይ ፍጥነት አለው።

◽️ 1Petabyte Hard Disk ለ13.3 አመታት ሙሉ HD ቪዲዩ መቅዳት ያስችላል።

🔺1024 GB = 1TB
🔺1024 TB = 1petabyte

◽️ Grand theft auto 5 የተባለው ጌም በሳምንት ውስጥ 1ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያገኘ ሲሆን በአለማችን ላይ ቀዳሚ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

◽️ አንድ ሰው በደቂቃ በአማካኝ 20 ጊዜ አይኑ ይርገበገባል። ይሁንና አንድ ሰው ኮምፒውተር በሚጠቀምበት ጊዜ ግን በአማካኝ በደቂቃ 7 ጊዜ ብቻ ነው አይኑ የሚያርገበግበው።

◽️ Mydoom እስከዛሬ ከተፈጠሩ የኮምፒዩተር ቫይረሶች ቶሎ በመሰራጨትና ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ (38billion $) የሚስተካከለው የለም።

◽️ 92%ቱ የአለማችን ገንዘብ የሚገኘው በኮምፒዩተሮች ላይ ነው፤ በእጃችን የሚገኘው የተቀረው 8% ብቻ ነው።

◽️ ሬዲዮ 50 ሚልዮን አድማጮች ጋር ለመድረስ 38 አመታት ፈጅቶበት ነበር።

◽️ ቴሌቪዥን 50 ሚልዮን ተመልካቾች ጋር ለመድረስ 13 አመታት ነበር የፈጀበት።

◽️ iPhone 50 ሚልዮን ሰዎች እጅ ለመግባት ሶስት አመት ብቻ ፈጅቶበታል።
Abyssiniatech
👍1
TikTok Mod 20.9 @dani_apps.apk
88.9 MB
TikTok 20.9.2 without ads, regional restrictions and with mod downloads
✴️ የሳይበር ጥቃቶች በኢትዮጵያ

🚀 በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ ከ2 ሺህ 800 በላይ የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል። አብዛኛዎቹን ጥቃቶች ማስቆም፣ መቀልበስ እና መከላከል ተችሏል።(#AlAin)
👍1
#ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች

ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ ። 👇👇👇👇

✅ ስያሜው
ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

✅ የጀርባ ማሻ
የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ። ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

✅ የተንጋደደ
ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

✅ ፍየሎች
ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው። አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ። ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

✅ እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

✅ ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

✅ ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

✅ መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

✅ ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

✅ የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

ምንጭ፦BBC AMAHARIC
#የቲውተር_Twitter_አጠቃቀም_አጭር_ማብራሪያ

ቲውተር በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያሉት የማህበራዊ ድህረገፅ አንዱ ነው፡፡ በሃገራችን ኢትዬጲያ በርካታ ተጠቃሚዎች ባይኖሩትም በውጪው አለም ግን በሚሊዬን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችንም የቲውተርን ድረገፅ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡

1. ቅድሚያ የቲውተር አድራሻ እንዲኖረን አካውንት መክፈት ያስፈልጋል፡፡Twitter App ስልካችሁ ላይ ይጫኑ።
አፕሊኬሽነን- ከዚህ ድረገጽ www.twitter.com ላይ ዳውንሎድ ያድርጉ።
✅ በመቀጠልም sign up የሚለውን በመጫን የሚጠይቀውን ሙሉ ስም፣ የኢሜል አድራሻ፣የይለፍ ቃል(password)፣ Username መሙላት
✅ የሚጠይቀውን መጠይቅ ሞልተን ማጠናቀቃችንን ካረጋገጥን ቡሃላ Agree to the Twitter Terms of Service የሚለውን መጫን
✅ በመጨረሻም Sign up for Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት ቻልን ማለት ነው፡፡
✅ አንዳንዴ ለማረጋገጥ በሚል የስልክ ቁጥር እንድናስገባ ሊጠይቀን ይችላል፡፡ ስልክ ቁጥራችን ያለበትን የሃገር ስም በመምረጥ ስልክ ቁጥራችንን እናስገባለን፡፡ በመቀጠልም የማረጋገጫ ኮድ በስልክ ቁጥራችን ይላክልናል፡፡ እሱን በቲውተር አከውንታችን ላይ በማስገባት የቲውተር አካውንት በቀላሉ መክፈት እንችላለን ማለት ነው፡፡

2. የቲውተር አካውንታችን ሙሉ መረጃዎችን እንዲይዝ መሙላት ሌሎች የቲውተር ተጠቃሚ ሰዎች በቀላሉ ከኛ ጋር ለመገናኘት ያስችላቸው ዘንድ ልክ በፌስቡክ ፕሮፋይል እንደምንሞላው ሁሉ በቲውተር ላይም በመሙላት በቀላሉ ከሌሎች ጋር መገናኘት ያስችለናል፡፡

3. ከሌሎች ሰዎች፣ተቋሞች እና ሚዲያዎች ጋር ለመገናኘት የሚከተለውን ማድረግ
✅ የቲውተር አካውንት መጠቀም ስንጀምር የቲውተር ድህረገፅ የራሱን ጥቆማ ያደርግልናል፡፡ ይህንንም Suggestions. የሚለውን በመጫን የምንፈልገውን መርጠን follow ማድረግ እንችላለን፡፡
✅ በራሳችን ለመፈለግም Search. የሚለው ቦታ ላይ የምንፈልገውን ሰው፣ድርጅት ወይም ስም ፅፈን follow ማድረግ እንችላለን ።

4. ቲውተር ላይ ፖስት ለማድረግ
✅ በቲውተር ላይ ፖስት ማድረግ የሚቻለው በ 140 ቃላቶች ብቻ የተዋቀረን መልዕክት ነው፡:
✅ ሃሳባችንን ወይም መልዕክታችንን ባጭሩ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ የምንጠቀምበትን አይነት ሳጥን ጋር በመጻፍ Tweet የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን::
✅ በፌስቡክ ፖስት ስናደርግ ታግ እንደምናደረገው ሁሉ በቲውተር ላይም “@” የሚለውን ፊደል ከምንፈልገው የሰው ስም ወይም ተቋም ስያሜ ቀድመን በመፃፍ ታግ
ማድረግ እንችላለን
✅ በቱውተር ላይም በፎቶ የተሰሩ ነገሮችን ፖስት ማድረግ የሚቻል ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ፖስት እንድናደርግበት በተዘጋጀው ሳጥን ስር በግራ በኩል ADD PHOTO የሚል እናገኛለን፡፡ እሱን በመጫን ከምንፈልግበት ቦታ ፎቶውን በመምረጥ ማስገባት እንችላለን፡፡ ታግ ማድረግ ከፈለግንም ወይንም ከፎቶ በተጨማሪ ፖስት ከምናደርገው ፎቶ ጋር መልዕክት ማስገባት ከፈለግን ፖስት ለማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ላይ በመፃፍ አንድ ላይ TWEET የሚለውን በመጫን ፖስት ማድረግ እንችላለን
✅ በቀላሉ መልዕክቶች አንድ ቦታ እንዲሰባሰቡ ከተፈለገም ሃሽታግ መጠቀም እንችላለን፡፡ የምንፈልገውን መልዕክት ወይም ቃላት ፊት ይህን የመሰላል ምልክት (#) በማስገባት መልዕክቶቻችን በአለም ዙሪያ አንድ ቦታ ተሰባስበው እንዲቀመጡ ማድረግ ይቻላል፡፡

5. ቲውተርን ላይ የምናገኛቸው ቃላቶች እና
አጠቃቀማቸው
✅ Follow፡ ይህ ማለት ልክ በፌስቡክ ፖስት የሚደረጉ ነገሮችን ለመከታተል አድ ፍሬንድ ለማድረግ የምንጠቀምበት ሲሆን follow የሚለውን በመጫን ብቻ የፈለግነውን ሰው ወይም ተቋም የሚለቃቸውን መረጃዎች እና መልዕክቶች በቀላሉ መከታተል ያስችለናል፡፡
✅ Following:- ይህ ማለት Follow እያደርግናቸው ያሉ ሰዎችን እና ተቋማትን የማናገኝበት ምርጫ ነው፡፡
✅ Followers:-ይህ ማለት እኛን Follow እያደረጉ የሚገኙ ሰዎችን ዝርዝር የምናገኝበት ምርጫ ነው፡፡
✅ Replies.፡- ይህን የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ወይም ቲውት ባደረገው ነገር ላይ ሲሆን ምልክቱም ወደ ግራ የታጠፈ የቀስት ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም ልክ
በፌስቡክ ኮሜንት እንደምንለው ነው፡፡ አስተያየት ወይም ምላሽ ለመስጠት Replies. የሚለውን በመጫን ምላሽ
ወይም አስተያየት መስጠን እንችላለን፡
✅ TWEET፡-ይህ በፌስቡክ ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ Post የሚለውን ምርጫ እንደምንጫን ሁሉ በቲውትር ላይም ፖስት ለማድረግ ስንፈልግ TWEET የሚለውን በመጫን ይሆናል፡፡
✅ Retweets.፡- ይህንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በኩል መሃል ላይ ሲሆን ምልክቱም ሁለት ቀስቶች ወደላይ እና ወደታች ያሉበት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ሼር ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ አንድ ሰው ፖስት ያደረገውን ሼር ለማድረግ ስንፈልግ Retweet የሚለውን በመጫን ሼር ማድረግ እንችላለን
✅ Favorites.፡ ይህንንም የምናገኘው አንድ ሰው ፖስት ባደረገው ነገር ላይ ከስር በቀኝ በኩል ሲሆን ምልክቱም የኮከብ ምልክት ነው፡፡ አገልግሎቱም በፌስቡክ ላይክ ለማድረግ እንደምንጠቀመው ነው፡፡ ፖስት የተደረገውን ነገር ላይክ ለማድረግ Favorit የሚለውን በመጫን ላይክ ማድረግ እንችላለን፡፡
✅ More:- በዚህ ስር ደግሞ ፖስት የተደረገውን ነገር በግል የቲውተር ሜሴጅ ለመላክ፣ በኢሜል ለመላክ እንዲሁም ፖስት ያደረገውን ሰው ብሎክ ለማድረግ
የምንጠቀምባቸውን ምርጫዎች የያዘ ነው፡፡
✅ Messages.፡ ይህ ምርጫ በቲውተር Follow እያደረግነው ከምንገኘው ሰው ጋር በውስጥ በኩል መልዕክት ለመለዋወጥ የምንጠቀምበት ምርጫ ነው፡፡

6. የፌስቡክ አካውንታችንን እና የቲውተር አካውንታችን አንድ ጊዜ በጋራ እንዴት እንጠቀም ይህን ለማድረግ በቀላሉ የፌስቡክ አካውንታችንን ከቲውተር አካውንታችን ጋር በማገናኘት በአንድ ፖስት ሁለቱም ጋር ፖስት ማድረግ ያስችለናል፡፡ ይህ ለማድረግ ሁለት ምርጫዎች ይኖሩናል::

✅. በፌስቡክ ፖስት የምናደረገውን ነገር በቲውተራችንም ላይ ፖስት እንዲሆን ማድረግ፡፡

ይህን ለማድረግም የሚከተለውን Step
ይከተሉ፡
✅ -በቅድሚያ በፌስቡክ Setting የሚለው
ውስጥ ይግቡ
✅ -በመቀጠልም በSetting ውስጥ
የተዘረዘሩት መካከል Followers የሚለውን
ይጫኑ
✅ -በመቀጠልም Followers የሚለውን
ሲከፍቱ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል
አምስተኛውን "Link my Profile to
Twitter. የሚለውን በመጫን የቲውተር
አድራሻችንን በማስገባት በቀላሉ ከፌስቡክ
አካውንታችን ጋር ማገናኘት እንችላለን፡፡
✅ -ከላይ የተጠቀሰውን በቀላሉ ለማግኘት ይህን
ሊንክ www.facebook.com/twitter በመጫን ማግኘት ይችላሉ
Credit Dotcomtvshow
✳️ የመጀመሪያው ብራውዘር Browser ማን ነው የፈጠረው?

የመጀመሪያው የድር አሳሽ(ብራውዘር) በቲም በርነርስ ሊ(ሰር) በ1990 ላይ ( GC)ነው የተፈጠረው። ይህ ብራውዘር ስሙ ወርልድ ዋይድዌብ (WorldWideWeb) ተብሎ ይጠራል ፡፡

ቲም በርነርስሊ( Tim Berners Lee) በተጨማሪ የድርን ልማት የሚቆጣጠር ዓለም አቀፍ የድር ጥምረት( World Wide Web consortium) ዳይሬክተርም ናቸው ፡፡ በአሁኑ ወቅት በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒተር ሳይንስ እና በማሳቹሴትስ የቴክኖሎጂ ተቋም ፕሮፌሰር ናቸው ፡፡

ቲም ፕሮግራሙን ወይም የመጀመርያ ድር አሳሽ ለመስራት የስቲቭ ጆብስ (Steve Jobs) ከቀድሞዎቹ ምርት አንዱ የሆነውን NeXT Computer (ኔክስት ኮምፒተርን) ተጠቅሟል ፡፡

የመጀመርያውን አሳሽ ከሰራ በኋላ የስም መጠርያው ከወርልድ ዋይድዌብ (WorldWideWeb) ጋር ግርታን እነዳይፈጥር የአሳሹ ወይም ብራወዘሩ ስም ወደ Nexus ተለውጧል ፡፡

እንደ ዛሬ ብዙ ብራውዘሮች ሳይፈጠሩ ለምሳሌ (Firefox, Google Chrome , Microsoft Internet Explorer etc) Nexus በግዜው ብቸኛው የድር አሳሽ (ዌብ ብራውዘር) ነበር ፡፡በኋላ ላይ በ1994 ተቋርጧል። አግልግሎት መስጠት አቁሟል።
💎አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን ከመጠቀማችን በፊት መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
አዲስ ኮምፒዉተሮችን ከኢንተርኔት ጋር ግንኙነት ከመፍጠራችን በፊት ማድረግ ያሉብን የደህንነት ጥንቃቄዎች የትኞቹ ናቸው?
👉 የኮምፒዉተር ደህንነትን መጠበቅ እጅግ አስፈላጊ የሆነበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም አዲስ የገዛናቸዉን ኮምፒዉተሮች መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ማድረግ ያሉብን የደህንነት ጥንቃቄዎች አሉ፡፡
👉 ከእነዚህ ጥንቃቄዎች መካከል፡-
👉 የኔትዎርክ ማገናኛ መሳሪያ የሆነውን የራዉተር(router) ደህንነት መጠበቅ.
👉 ኮምፒዉተራችንን ከኢንተርኔት ጋር በምናገናኝበት ወቅት በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሌሎች ኮምፒውተሮች ጋር ተገናኘን ማለት
ነዉ::
👉🏻 ታዲያ ይህ ሲሆን የራዉተርን ደህንነት መጠበቅ እጅግ ወሳኝ ነዉ፡፡ ምክንያቱም የኢንተርኔት ግንኙነቱ የመጀመሪያ መዳረሻ ራውተር በመሆኑ፡፡
👉🏽 የፋየርወል(firewall) ደህንነት ማስተካከያን ወይም ዲቫይስን
👉 መጠቀም፡- ፋየርወሎች የኮምፒዉተራችን ግንኙነት ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችል በመሆኑ አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን
ከበይነ-መረብ ጋር ከማገናኘታቸን በፊት
👉🏻 የፋየርወል ማስተካከያዎችን ማድረግ ጠቃሚ ነዉ:: በተለይ የኮምፒዉተር ፋየርወልን ኦንና ኦፍ (on & off) አማራጮችን 'ኦን' ማድረግ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚፈልግ ጉዳይ ነዉ።
👉🏼 ፀረ-ቫይረስ (antivirus) ሶፍትዌሮችን በቅድሚያ መጫን፡- አዳዲስ ኮምፒዉተሮችን ከበይነ-መረብ(internet) ጋር ከማገናኘታችን በፊት ፀረ-ቫይረሶችን እና ፀረ-ማልዌሮችን (anti malware) ጭነን ቢሆን
👉 ለኮምፒዉተራችን ደህንነት ተመራጭ ነዉ፡፡
እነዚህ ጸረ-ቫይረስ እና ማልዌሮችን በየጊዜዉ ማዘመን መዘንጋት አይገባም፡፡
👉 አላስፈላጊ የሆኑ ሶፍትዌሮችን ማጥፋት
Habeshatech
🆕 ዛሬ የምነግራቹ ያገለገለ ስልክ ከ ሰው ላይ ስትገዙ ማድረግ ያለባችሁን ጥንቃቄ እና ማረጋገጥ ያለባችሁን ነገሮች ናቸው....

❗️ከስር የዘረዘርኳቸው ነገሮች በ እናንተ ፍላጎት ልትተዋቸውም ትችላላቹ

🔅በመጀመሪያ ከስልኩ Screen ጀምሩ ና የፊት screen ኑ አለመሰበሩን ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ

🔅በመቀጠል የፊት ካሜራው ላይ ጉዳት አለመድረሱን አጣሩ / ጥራቱን ሳይሆን ከተሰበረ ምናምን

🔅 አሁን ወደ ጎን ሂዱና የጎን volume እና power buttons መታዘዝ አለመታዘዛቸውን አረጋግጡ

🔅በመቀጠል ወደ ኀላ ዙሩና ከኀላ ያሉትን እንደበፊቱ አጣሩ

🔅ቀጣይ ስልኩ የ sim card በትክክል መቀበሉን, Sd card, Earphone እና በተጨማሪም USB የሚቀበል መሆኑን አጣሩ/ ይሄ ሊቀርም ይችላል ግን ቢሰራ በጣም ጥሩ ነው በቀላሉ በ Connector usb flash በስልካቹ መጠቀም ትችላላቹ። ስልኩን የ ኀላ ክዳን የሚከፈት ከሆነም የ ባትሪ power ስንት እንደሆነ ማየት ትችላላቹ።የማይከፈት ከሆነ ወይም ካልተፃፈ ቡሀላ መፍትሄውን ነግራቹአለው።

🔅በቀጣይም ወደ ውስጥ እንግባ የ lock screen check አድርጉ ወደ ውስጥ ገብታችሁም Call, sms,WiFi አጣሩ
🔅አሁን የስልኩን camera, ቅድም ያስገባቹትን sd card ማንበቡን አረጋግጡ

🔅አሁን ከዚህ ቡሀላ ያለውን ሙሉ ነገር ለማጣራት አንድ አኘ ብቻ ስልኩ ላይ መጫን ይበቃል።Device info ይባላል በጣም ገራሚ አኘ ነው ከሌሎች አፓች በተለየ መልኩ ሁሉንም የስልኩን መረጃ ማረጋገጥ ያስችላችኀል።ቅድም ያልኳችሁንም Battery States በዚህ አኘ ማየት ትችላላቹ።

🔅ምናልባት ሰውየው አኘ በ xender ስትላላኩ እንዳይደብረው በቀላሉ አፑን መጀመሪያ memory card ላይ copy አርጋቹ አስቀምጡ በመቀጠልም Memory check ለማረግ ስታስገቡ install አርጋቹ ማየት ነው።አፑ ሁሉንም ነገር ያሳያል

🔱 አሁን አንድ የማቀር ነገር አለ የምትገዙት ስልክ Original ወይስ copy መሆኑን ማረጋገጥ።ይሄም በፍላጎታችሁ ላይ ይወሰናል 👇👇👇

▶️መጀመሪያ ስልኩ ላይ *#06# አስገቡ እና የ ስልኩን imei no አግኙ/ያዙ

▶️ http://www.imei.info ወደ ዚህ Website ሂዱ እና የ ስልኩን Imei no አስገቡ

▶️ ከዛ search አርጎ ያመጣው የዛን ስልክ information ከሆነ original ✅ ነው ማለት ለው የ ሌላ ስልክ info ካመጣ ደሞ FAKE


✅ አሁን ሙሉ መረጃውን አውቃችኀል ስልኩን መግዛትም መተውም ትችላላችሁ።
🔱 የማሽን ለርኒንግ አስፈላጊነት

ማሽን ለርኒንግ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አንዱ ንዑስ ክፍል ሲሆን በግብዓትነት ከሚሰጠው ዳታ መማር የሚችል ስልተ-ቀመርን መሰረት ያደረገ ሥርዓት ነው፡፡

የተለመዱት የኮምፒዩተር ሥርዓቶች በሌላ በኩል ሕግን መሰረት ያደረገ የትግበራ ሥርዓት (rules-based programming) ይከተላሉ፡፡

በማሽን ለርኒንግ የሚበለፅጉ ሥርዓቶች የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር የነገሮችን ንድፍ (pattern) የመለየት፣ ውሳኔ እና ትንበያዎችን የመስጠት አቅምን እንደሚያጎለብቱ ቢዩልትኢን ድረ-ገፅ ያትታል፡፡

ይህን ሥርዓት ያነገቡ ማሽኖች በተሰማሩበት ዘርፍ ያለስህተት ስራዎችን በማከናወን እና በሰው ልጅ ቢተገበር በተለያየ ምክንያት ሊፈጠር የሚችል ክፍተትን በማስወገድ ወይም በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ ውጤታማ ስራን ማከናወን ይችላሉ፡፡

ተግባራዊ ማሳያዎች

ኔትፍሊክስ፡- የእርስዎን ዝንባሌ መሠረት ያደረጉ የፊልም ጥቆማዎች
ታዋቂው የፊልም መመልከቻ መተግበሪያ ኔትፍሊክስ ከ200 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ መተግበሪያው የማሽን ለርኒንግ ስልተ-ቀመርን በመጠቀም እና የዕይታ ልማድን መሠረት በማድረግ እንደየግለሰቡ ዝንባሌ የመዝናኛ ጥቆማ ያቀርባል፡፡

ሾፌር አልባ ተሽከርካሪዎች፡- ከባቢያቸውን የመረዳት አቅም
ለራስ-ገዝ ተሽከርካሪዎች እውን መሆን የማሽን ለርኒንግ ሚና ቁልፍ መሆኑ ይታመናል፡፡ መሰል ተሽከርካሪዎች በካሜራዎቻቸው እና መጠቆሚያቸው አማካኝነት ከከባቢያቸው የሚሰበስቡትን መረጃ ምንነት የሚረዱት እንዲሁም ውሳኔን የሚያሳልፉት የማሽን ለርኒግ እውቀትን መሠረት አድርገው ነው፡፡
#Facts

✔ዛሬ ከ3.8 ቢሊዮን በላይ ሰዎች Internet ይጠቀማሉ ይህም ከዓለም ህዝብ 40
በመቶው ነው።
✔በየ57 ደቂቃው ከ570 በላይ አዳዲስ Websites ይፈጠራሉ።
✔በየቀኑ ከ3.5 ቢሊዮን በላይ Google Search ይደረጋል።
✔በ2020 ቪዲዮ ከሁሉም ከInternet ትራፊክ 80% ያህሉን ይይዛል።
✔40,000 የTweeter ትዊቶች በደቂቃ ይላካሉ በቀን 500 ሚሊዮን ትዊቶች ማለት
ነው።
✔በAmerica ከሚደረጉ ከ7 ፍቺዎች መካከል ለአንዱ ፌስቡክ ተጠያቂ ነው።
✔በ2020 ከ8.2 ቢሊዮን በላይ መረጃዎች ተሰርቀዋል ወይም Hack ተደርገዋል።
✅ አዲሱ የአይፎን ስልክ የሳተላይት ግንኙነትን አካቷል፣ ይህ ምን ማለት ይሆን ❓

➠አፕል በቅርቡ ይፋ የሚያደርገው የአይፎን ስልክ የሳተላይት ግንኙነትን የሚያስቸል በመሆኑ ለስልኩ ተጠቃሚዎች አስፈላጊው የአውታር-መረብ ሽፋን (cellular coverage) በሌለባቸው ቦታዎች መደበኛ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚስችል ነው፡፡ የማክሩመርስ ዘጋቢ ሚንግ ቺኩዎ እንደጠቀሰው አይፎን 13 የተባለው አዲሱ የአፕል ስልክ በተካተተለት የሳተላይት ግንኙነት ገፅታ የኔትወርክ ሽፋን አስቸጋሪ በሚሆንባቸው አካባቢዎች ተጣቃሚዎች ስልክ መደውል እንዲችሉ እና መልዕክት መላላክ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ብሏል፡፡

➠አዲሱ የአፕል ምርት የ4ጂ፣ 5ጂ እና ሌሎች የኔትዎርክ ሽፋኖች በሌሉባቸው ቦታዎች እንደ ስልክ መደውል እና መልዕክት መላላክ ያሉ መደበኛ አገልግሎቶችን ተጠቃሚዎች እንዲያገኙ የሚያስችለው በቀድሞ የገመድ ስልኮች ይገጠም የነበረ የዘመነ ሃንድሴት ሃርድዌር በማከሉ ነው፡፡ በአይፎን 13 ስልክ ላይ የሚገጠመው የዘመነ የሃንድሴት ሃርድዌር ዝቅተኛ የምድር ምህዋር ሳተላይቶች (low-Earth orbiting satellites) ጋር በቀላሉ ለመገናኛት ስለሚያስችለው የአውታር-መረብ ሽፋን (cellular coverage) በሌለባቸው ቦታዎች መደበኛ አገልግሎት አንዲሰጥ ያደርገዋል፡፡ የሳተላይት ግንኙነቱ ከስልኩ ጋር በደንብ እንዲግባባ Qualcomm X60 የተሰኘ የቤዝባንድ ቺፕ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የግንኙነት ስርኣቱን የሚያፋጥንና የሚደግፍ ይሆናል፡፡

➠ዝቅተኛ የምድር ምህዋር ሳተላይቶች ላይ የሚሰራው ግሎባል ስታር የተሰኘው የሳተላይት ግንኙነት አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት አፕል በቅርቡ ይፋ ለሚያደርገው የስልክ ምርት የቴክኖሎጂና የኔትወርክ ሽፋን በመስጠት በጋራ የሚሰራ ነው፡፡ ግሎባል ስታር ዝቅተኛ የምድር ምህዋር (LEO) ላይ ብዙ ሳተላይቶችን በማሰማራት አገልግሎቱ ለሚያስፈልጋቸው ድርጅቶች ለብዙ አመታት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ ድርጅት እንደነበር በዘገባው ተገልጿል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኘው የስፔስ ኤክስ ኩባንያ የኔትወርክ ሽፋን ባልተሟላላቸው በሁሉም የአለማችን ክፍሎች የ LEO ሳተላይቶችን በስፋት ጥቅም ላይ በማዋል በየትም ቦታ አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ዘጋቢው ሚንግ ቺኩዎ ተናግሯል፡፡

➠አንዲህ ያሉ የቃጣይ ትውልድ የቴክኖሎጂ አማራጮች የኔተዎርክ ሽፋን በሌለባቸው ቦታዎች የሚኖሩ ብዙ ሚሊዮን ሰዎችን በእጅጉ የሚረዳ እና በብዙ የአለማችን ክፍሎች በግንኙነት እጥረት ምክንያት አስፈላጊውን እርዳታ ለማያገኙ ሰዎች ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ይሁንና በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች ይፋ ይደረጋል የሚባለው አይፎን 13 በተሟላ ሁኔታ የተባለውን አገልግሎት ለመስጠት ጊዜ እንደሚወስድበት የሚናገሩ አንዳንድ ባለሙያዎች የአገልግሎት አይነቱ መልክዕክት በመላክ የተወሰነ እና በተለይም አንደ አውሮፕላን አደጋ፣ የመርከብ መስጠምና ሌሎች ከባድ አደጋዎች ሲደርሱ በአጭር የፅሁፍ መልክት ለማሳወቅ የሚያስችል ብቻ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡
ምንጭ፡ macrumors
ሳፋሪኮም ቴሌኮምዩኒኬሽንስ በኢትዮጵያ የንግድ ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉትን ዝግጅቶች መጀመሩን አስታወቀ

ነሀሴ 28፤ 2013 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ_አዲስ አበባ) ሳፋሪኮም ቴሌኮምዩኒኬሽንስ በኢትዮጵያ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ አንደሚገኝ በዛሬው ዕለት አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ሀላፊዎች ለመገናኛ ብዙሃን ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ሳፋሪኮም ቴሌኮምዩኒኬሽንስ የኢትዮጵያዉን ቢሮ የሚመሩ የስራ ሀላፊዎችን የመመደብ፤ የሰራተኛ ቅጥርና ቁሳቁስ የማሟላት ስራዎችን እየሰራ አንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት 1000 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የዘርፉ ባለሙያዎችን የመቅጠር ሂደት አንደተጀመረ ተገልጿል፡፡

በተለይም ኩባንያው የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ባለሞያዎችን በቴክኖሎጂ፣ ንግድ እና ሌሎች የኮርፖሬሽን ዘርፎች ላይ ከአዲስ ምሩቃን እስከ ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የስራ እርከኖች ላይ መቅጠር እንደጀመረ ተናግረዋል።

እየተካሄደ ካለው የስራ ቅጥር ሂደትም ቅጥራቸው የተረጋገጠ 11 የኤግዚክዩቲቭ ኮሚቴ አባላቱን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

የሳፋሪኮም ፐብሊክ ሊሚትድ ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፒተር ንዴግዋ ባለ አክስዮኖቹ ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለነዋያቸውን ለማፍሰስ እንዲሁም የዲጂታል ኢትዮጵያ ዓላማዎች እውን ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያን ዓላማዎች ማሳካት በሚያስችል መልኩ በ10 ዓመታት ውስጥ 8.5 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት አንደሚያደርግ ሀላፊዎቹ አስታዉቀዋል፡፡

ምንጭ፡አዲስ ዘይቤ
🆕 ዊንዶው 11 ቀን ተቆረጠለት

✅ የዊንዶው 10 ተከታይ የሆነው ዊንዶው 11 የተሰኘው መጠቀሚያ በመጪው የፈረንጆቹ ጥቅምት 5 ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተነገረ፡፡ ላለፉት ጥቂት ወራት ሙከራ ሲደረግበት የነበረው ይህ ፕላትፎርም ከዚህ በፊት የነበረንን መጠቀሚያዎች ለማሻሻልና እንደ ዴል፣ ሌኔቮ ሌሎች የኮምፒውተር አይነቶች ላይ ተጭኖ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡

✅በቀጠሮው እለት የሚቀርበውን ማሻሻያ የተደረገበትን የዊንዶው አይነት እንደቀድሞው (አሁን ላይ ጥቅም እየሰጠ ያለው ዊንዶው 10) ተመሳሳይ ማሻሻሎች (updates) ያሉት ሲሆን የቫይረስ ተጋላጭነቱ ዝቅተኛ ነው ሲል ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡ ወደ ዊንዶው 11 ማሳደጊያውም በነጻ የቀረበ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

✅ዊንዶው 11 እንደሚጫንበት የኮምፒውተር አይነት የተለያየ ቢሆንም ሁሉም የኮምፒውተር አይነቶች በነጻ የቀረበውን ማሳደጊያ እስከ 2022 አጋማሽ ድረስ መጠቀም እንደሚችሉ ይፋ ተደርጓል፡፡ የምንጠቀመው ኮምፒውተር ለአዲሱ ዊንዶው የተፈቀደለት ከሆነ በማይክሮሶፍት በኩል ማሳወቂያ ይላካል ተብሏል፡፡

✅ይሁን እንጂ ሰዎች አዲሱን ዊንዶው መጠቀም ካልቻሉ ዊንዶው 10 እስከ ጥቅምት 2025 ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጥ ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡ ተቋሙ አክሎም የተለያዩ የአንዲሮይድ መተግበሪያዎችን ከዊንዶው 11 ጋር ለማቀናጀት ከአማዞንና ከኢንቴል ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አሳውቋል፡፡
Credit techhabesha
#ቴክኖሎጂ_በመቃብር_ስፍራ

በጃፓን በአንዳንድ የመቃብር ስፍራዎች የሚገኙ ኃውልቶች ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት QR CODE ተገጥሞላቸዋል።
የኮዶቹ ጥቅም QR ኮዱን በስልክ ስካን ሲደረግ ስለ ሟቹ ማንነት ዝርዝር መረጃ ይሰጣል ።
✅ ሳምሰንግ በGalaxy A ስልኮች ላይ አዲስ ቴክኖሎጂ ሊጠቀም ነው!

✅ አዲስ በሚወጡ ሪፖርቶች መሠረት የደቡብ ኮሪያ ኩባንያ በ 2022 በሚመጣው የሳምሰንግ ጋላክሲ ኤ ስልኮች ላይ OIS ን እንደሚያካትት ይጠቁማሉ።

✅ የኦፕቲካል ምስል ማረጋጊያ ወይም የኦአይኤስ ባህሪ በአብዛኛዎቹ ዋና መሣሪያዎች ላይ መገኘቱ ይታወቃል። áˆˆá‰Şá‹˛á‹Žá‹Žá‰š መረጋጋትን ይሰጣል እንዲሁም በፎቶዎች ውስጥ በእጅ መንቀጥቀጥ ምክንያት የሚፈጠር ብዥታን ይቀንሳል። á‰Łáˆ…áˆŞá‹ በዋናነት በዋናው ክፍል ውስጥ የሚገኝ ቢሆንም ሳምሰንግ እ.ኤ.አ. በ 2022 በሚመጡ የ Galaxy A ተከታታይ መሣሪያዎች ላይ OIS ን ያካትታል ።ሳምሰንግ በዚህ ዓመት በጥቂት የ Galaxy A ስልኮች ዋና ካሜራዎች ላይ OIS ን አስተዋውቋል። áŠĽáŠá‹šáˆ… ጋላክሲ A52 ን እንዲሁም ጋላክሲ A72 ን ያካትታሉ። á‰ áˆšá‰€áŒĽáˆˆá‹ ዓመት ነገሮች የሚሻሻሉ ይመስላል።

✅ ሳምሰንግ እ.ኤ.አ. በ 2022 ሊጀምረው ወደሚፈልጉት ሁሉም የ Galaxy A- ሞዴሎች ዋና ካሜራዎች OIS ን ሊጨምር ይችላል ይላል።

✅ ሪፖርቱ በተጨማሪም ኦአይኤስ ያለው ካሜራ ከሌለው ከሌላው ይልቅ 15% ያህል ይበልጣል ፣ እና ኦአይኤስን በስልክ የሂሳብ ዕቃዎች ላይ ማከል የሚያስከትለው ውጤት 3% ያህል ነው። 

✅ ይህም ሳምሰንግ በ Xiaomi ስልኮች ላይ የበላይነቱን እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል።
Credit plus ethio
#Pegasus_Spyware

በሰከንዶች ውስጥ ስልክዎ እርስዎ የሚያደርጉትን ሁሉ በሚከታተል በፔጋሱስ ስፓይዌር ሊበከል ይችላል።

#Pegasus_Spyware ምን ምን እንደሚያደርግ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ነው።