DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
✅ ዲጂታል ገንዘቦች በ5 ዓመት ውስጥ ብቻ የገንዘብ ኖቶችን ይተካሉ ተባለ
=================
➡️በእውቁ ዓለም አቀፍ የአማካሪ ኩባንያ ዲሎይት አማካኝነት የፋይናንስ ኢንዱስትሪው አንቀሳቃሾችን በማሳተፍ ጭምር የተሰራ አንድ ሰርቬይ የዲጂታል መገበያያ በአምስት ወይም አስር ዓመታት ውስጥ ብቻ የገንዘብ ኖቶችን እንደሚተካና ባንኮችም ይህን አውቀው የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡ የዲሎይት 2021 ዓለም አቀፍ የብሎክቼይን ሰርቬይ ባንኮች የማይቀረው የዲጂታሉን ዓለም መቀበል ያለባቸው መሆኑንና የፋይናንስ ዘርፉ መሪዎችም ከጊዜ ወደ ጊዜ ዲጂታል መገበያያ ገንዘቦች የመጪው ጊዜ ተረካቢዎች መሆናቸውን እየተቀበሉ መምጣታቸውን አመላክቷል፡፡

➡️በጥናቱ ላይ ከተሳተፉት ባለድርሻዎች መካከል 76 በመቶ ያህሉ የዲጂታል ገንዘቦች በቀጣዮቹ ከ5 እስከ 10 ዓመታት ውስጥ የገንዘብ ኖቶችን ሙሉ በሙሉ ይተካሉ አልያም ጠንካራ አማራጭ ሆነው ይወጣሉ ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል፡፡ ይህም የዲጂታል ገንዘብ አብዮቱ ምናልባትም ከሚጠበቀው በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገስግሶ እየመጣ ስለመሆኑና የእርሱን መንገድ ያልተከተሉትንም ከገበያው ውጪ ስለማድረጉ ጠንከር ያለ ማመላከቻ ነው ተብሎለታል፡፡

➡️አሁን ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በዲጂታል መልኩ እየተቀመጠ ሲሆን በዚህም ሳብያ ተቋማትና ኢንቬስተሮች ከሁኔታው ጋር ተላምደው የሚሰሩበትን መንገድ እንዲያፈላልጉ ተገደው ይገኛሉ፡፡ አዲሱ ሪፖርትም ቢሆን የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ባለድርሻዎች ወደዱትም አልወደዱትም ለውጦቹ መምጣታቸው እንደማይቀር ጠንካራ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ ሪፖርቱ እንደሚለው ከሆነ በዘመነ ዲጂታሉ ላይ ተሳታፊ መሆን የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን አይቀሬ ነገር ነውና የዘርፉ አንቀሳቃሾች የዲጂታል መገበያያን እና የአዲሱ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አገልግሎት መሰረተ ልማትን እንዴት ለራሳቸው አድርገው መጠቀም እንዳለባቸው ለመምረጥ ብቻ መገደዳቸውን ያስረዳል፡፡

➡️እንደ አትላንቲክ ካውንስል መረጃ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ከዓለማችን ምጣኔ ሐብት ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን የሚያንቀሳቅሱት 81 ሀገራት የራሳቸውን ብሔራዊ ዲጂታል መገበያያ ለመተግበር ከጥናት አንስቶ እስከ ሙከራና ትግበራ ድረስ በመስራት ላይ ናቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዷ የሆነችው ቻይና ምድሯ ላይ በምታስተናግደው መጪው የበጋ ኦሎምፒክ ላይ የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ለቻይና ህዝባዊ ባንክ የፓስፖርት መረጃቸውን ከሰጡ ዲጂታል ዩሀንን መጠቀም እንዲችሉ አድርጋ እየሰራች ትገኛለች፡፡ ከቻይና ጋር ለመስተካከል ብዙ እርምጃ ቢቀራቸውም አራቱ ግዙፋን የማዕከላዊ ባንኮችም (የአሜሪካን፣ አውሮፓ ህብረት፣ ጃፓን እና እንግሊዝ) እንዲሁ በሩጫው ውስጥ ናቸው፡፡ ከነዚህ ባሻገር ግን ሌሎች 5 የዓለማችን ሀገራት የዲጂታል ገንዘብን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ አውለዋል ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፤ ፊውቸሪዝም እና አትላንቲክ ካውንስል
🆕 ትዊተር ለተጠቃሚዎቹ ገቢ ማስገኛ ስርዓት አዘጋጀ

✅ትዊተር የተባለው የማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ ሱፐር ፎሎውስ የተሰኘ ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ተከታዮቻቸውን እንደ ገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበትን ስርዐት መዘርጋት ማሰቡን ይፋ አድርጓል፡፡ በተለይም በተለያዩ ዘርፎች ከዋክብት የሆኑና ተወዳጅ የሆኑ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተከታይ ያላቸው በመሆኑ ትዊተር እነዚህን ሰዎች አላማ አድርጎ የክፍያ ስርዓቱን ዘርግቷል፡፡
ለምሳሌ ሜካፕ አርቲስቶችና የስፖርት ተንታኞች ‹ከመጋረጃ ጀርባ› የሚባሉ ሁነቶችን ለተከታዮቻቸው ከ3 እስከ 10 ዶላር በሚደርስ ዋጋ እንዲያቀርቡ ሁኔታወችን ትዊተር አመቻችቷል፡፡ በሱፐር ፎሎው የትዊተር ተጠቃሚዎችና ብዙ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ለተከታዮቻቸው የሚቀርቡ የተለያዩ ውይይቶችን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በዚህም ገቢ ማግኘት ይችላሉ፡፡
እንደ ትዊተር መረጃ ከሆነ እንዲህ አይነት እድሎች ሊኖሯቸው የሚችሉ ተጠቃሚዎች አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ሙዚቀኞች፣ ጸሐፊዎች፣ የውበት ሙያተኞችና የመሳሰሉ ታዋቂ ሰዎች ናቸው፡፡ አሁን ላይ ትዊተር አዲሱን ስርዓት በመሞከር ላይ ሲሆን በሰሜን አሜሪካ የተወሰኑ የትዊተር ፈጣሪዎችን (creators) ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ ሌሎች የአፕል ሞባየይልን የሚጠቀሙ የትዊተር ተጠቃሚዎች ሱፐር ፎሎውን በመጭዎቹ ሳምንታት ሊጠቀሙ እንደሚችሊ ተነግሯል፡፡
ትዊተር አንድ ሰው ከተከታዮቹ ከሚያገኘው ከ3 በመቶ በላይ እንደማይወስድ የተናገረ ሲሆን ይህም አንድ ተጠቃሚ በተዘረጋው ፕላት ፎርም 50 ሺህ ዶላር እስኪያገኝ ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡ መሰረቱን በሳንፍራሲስኮ ያደረገው ካምፓኒ ከ50 ሺህ በኋላ ድርሻውን ወደ 20 በመቶ እንደሚሳድግም አሳውቋል፡፡ በዚህም በአሁኑ ሰዓት 200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ድርጅት ብዙ ማስታወቂያዎችን ሳይሰራ ገቢውን ማሳደግ የሚያስችለው አሰራር መዘርጋቱ ተነግሯል፡፡

ምንጭ techxplore
👍1
✅ ወታደራዊ ድሮኖች እና እያደገ የመጣው ግልጋሎታቸው
===================
➡️ ባለንበት ዘመን በድሮኖች አማካኝነት ስለሚከወን ጥቃት መስማት የተለመደ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ሆኖም የዛሬ 20 ዓመት ገደማ በወርሀ መስከረም የኒው ዮርክ መንትያ ህንፃዎች ላይ ከደረሰው ጥቃት ከአንድ ወር በኋላ ነበር አንድ የአሜሪካን አየር ኃይል አብራሪ ዘመናዊ ድሮንን ተጠቅሞ የግድያ ጥቃትን በመሰንዘር የመጀመሪያው ሰው የሆነው፡፡ ከዚህ በኋላ ግን በርካታ ርቀው ባሉ አብራሪዎች የሚንቀሳቀሱ አውሮፕላኖች (RPA) ተመራጭ የውጊያ መሳርያ ወደመሆን ተሸጋግረዋል፡፡ አሜሪካን እንኳን እንደምሳሌ ወስደን ብናይ ከአውሮፓውያኑ 2015 በኋላ በአፍጋኒስታን ውስጥ ብቻ ከ14 ሺህ በላይ የድሮን ጥቃቶችን አድርሳለች፡፡

➡️ ይህ መንግስታት በወታደራዊ ድሮኖች ላይ እያሳዩት የመጡት ከፍተኛ ፍላጎት ታድያ ሦስት አባይት ውጤቶችን አስከትሏል፡፡ የመጀመሪያው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የወታደራዊ ድሮኖች ስርጭት መጨመሩ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ብዙዎቹ የዓለማችን ታላላቅ ብሎም በየአካባቢያቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት ሀገራት ድሮኖችን ለስለላና የአየር ላይ ምልከታ (ISR) አልያም ጥቃትን ለመሰንዘር እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡ ሁለተኛው ውጤት የመጀመሪያውን ተከትሎ የሚመጣ ነው፤ የድሮኖች መብዛትን ተከትሎ እነርሱን ማብረር እንዲችል ተደርጎ የሰለጠነ ወታደር የማፍራት ጉዳይ፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ድሮኖቹ በይበልጥ መሳርያን እየታጠቁ መምጣታቸው ነው፡፡

➡️ ምንም እንኳን ዘመናዊ ድሮኖችን ተጠቅሞ ጥቃት መሰንዘር ከተጀመረ ገና 20 ዓመታት ባያልፉትም ወታደራዊ ድሮኖች ግን የዘመኑ አዲስ ግኝቶች አይደሉም፡፡ እንዲያውም አውሮፕላን ከተፈጠረ ብዙም ሳይቆዩ ነው ድሮኖችም ገና በጠዋቱ በ1920 እና 30ዎቹ (እ.አ.አ) ከርቀት ሆኖ ጥቃትን ለመሰንዘር በማሰብ ወደ መድረኩ ብቅ ያሉት፡፡ ለምሳሌ ሚሳኤሎችም በሰው እየተመሩ ወደ ተልዕኮዋቸው የሚያመሩ ሲሆኑ ነገር ግን ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም የሚሰጡና ምንም አይነት ስለላን የማከናወን ብቃት የሌላቸው ናቸው፡፡ ሆኖም ዘመናዊ ወታደራዊ ድሮኖችን ለየት ከሚያደርጓቸው ውስጥ በመጀመሪያ አብራሪዎቻቸው ከደህንነት ከጥቃት የተጠበቁ መሆናቸው ነው፡፡ ሌላው እነዚህ ዘመናዊ ድሮኖች ኢላማቸውን ጠብቀው ጥቃት መሰንዘር የሚችሉ ስለሆኑ እንደ ሚሳኤል ካሉት አንፃር ጥቃት በሚፈፀምበት ቦታ ላይ አላስፈላጊ ተያያዥ ጉዳቶችን በተሻለ ያስቀራሉ፡፡ በተጨማሪም ለወታደሮቹ እና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎቹ ያለማቋረጥ መረጃን ይሰጣሉ፡፡

➡️ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ድሮኖችን አስመልክቶ ከፍተኛ የሆነ የተሳሳተ ግንዛቤ ይታያል፤ በተለይም ድሮኖቹ እንዴት ይንቀሳቀሳሉ በሚለውና በአብራሪዎቹ ላይ፡፡ ድሮኖች የሚበሩት እነርሱን ለማብረር በማሰብ ተመልምለው በሰለጠኑ ወታደሮች አማካኝነት ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አብራሪዎች እንደ ማንኛውም የአውሮፕላን አብራሪ ሁሉ ለሚከውኗቸው ተግባራት ኃላፊነትና ተጠያቂነት ቢኖርባቸውም በማህበረሰብም ሆነ በሌሎች ወታደሮች ዘንድ ግን በመልካም አይታዩም፡፡ ለምሳሌ ድሮኖችን ማብረር የቪዲዮ ጌሞችን ከመጫወት ጋር በማያያዝ የሚቀለድ ሲሆን አብራሪዎቹም ቢሆን ከሌሎች የአውሮፕላን አብራሪዎች አንፃር የስራ እድልን ሲከለከሉ ይታያል፡፡ ይህም የድሮን አብራሪዎች እጥረትን አስከትሏል፡፡ በሌላ መልኩ የድሮን አብራሪዎች ከአንድ አደጋ በኋላ የሚከሰት የጭንቀት በሽታ (Post traumatic stress disorder) ምልክት ቢታይባቸውም በወታደራዊ ተቋማቱ ጭምር የምር ተወስዶላቸው ህክምና ሲያገኙ አይስተዋልም፡፡

➡️ በሌላ መልኩ ጥቃት በሚፈፅሙበት ጊዜ ተያይዘው የተከሰቱ የንፁሀን ሞት በማህበረሰብ ዘንድ በመጥፎ እንዳይታዩ አድርጓቸዋል፡፡
#NASA

በዚህ ወር ምድርን የሚያሻግረው ሦስተኛው አስትሮይድ 2021 NY1 ይባላል። á‹­áˆ… የአስትሮይድ ዲያሜትር ከ 127 እስከ 284 ሜትር ነው ፣ ይህም በግምት የትምህርት ቤት አውቶቡስ መጠን ነው። á‰ áˆ˜áˆľáŠ¨áˆ¨áˆ 22 በ 1.5 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምድር ትበርራለች። á‹¨áŠ“áˆł የጄት ፕሮፕሉሽን ላቦራቶሪ ከምድር ጋር ባለው የቅርብ መተላለፊያ ምክንያት 2021 NY1 ን “ሊደርስ የሚችል አደገኛ አስቴሮይድ” ብሎ ፈርጆታል።
አፕል ኩባንያ iPhone 13ትን በመስከረም 4 ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

አፕል "California Streaming " ብሎ ስያሜ በሰጠው ዝግጅት ላይ iPhone 13ን ይፋ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ።

አፕል በ 2021 iPhone ስልኮች ላይ ለተሻለ ካሜራዎች ከፍተኛ የማደሻ መጠንን ጨምሮ በርካታ አዳዲስ ባህሪያትን ያስተዋውቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም አፕል በዝግጅቱ ላይ ከiphone 13 በተጨማሪ Apple Watch Series 7 እንዲሁም አዲሱን #ipad እና #Airpads ይፋ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል ።
ደምብ አስከባሪው ሮቦት በሲንጋፖር ጎዳኖች

በሲንጋፖር የእግረኛ እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ ሥርዓተ አልበኝነትን እየተዘዋወረ የሚቆጣጠር ዣቪየር የተባለ ሮቦት ከሰሞኑ የሙከራ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡

ዣቪየር የሙከራ ስራውን ቶያ ፓዮሕ በተባለው የከተማው ማዕከላዊ ክፍል ለሶስት ሳምንታት እንደሚያከናውን ማሼብል ዘግቧል፡፡

ሮቦቱ በጎዳናዎች እየተዘዋወረ ከአምስት በላይ የሆኑ የሰዎች ስብስብን፣ ባልተፈቀደ አካባቢ ሲጃራ ማጨስ፣ ሕገ-ወጥ የጎዳ ላይ ንግድ ፣ያለአግባብ የቆሙ ብስክሌቶችን እና በእግረኛ መንገድ ሕገ-ወጥ የባለ ሞተር ተሸከርካሪ እንቅስቃሴዎችን ይቆጣጠራል፡፡

እርስዎም ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን ፈፅመው ቢገኙ ሮቦቱ በቀጥታ የቪዲዮ ስርጭቱ ወደ ማዕከላዊ የመቆጣጠሪያ ጣቢያው ሁኔታውን ያሳውቃል፡፡ ለተላለፉት ደንብም አግባብ የሆነውን የማስጠንቀቂያ መልዕክት በተገጠመለት ስክሪን እና ድምጽ ማጉያ ያስተላልፋል፡፡
ሶሻል ሚዲያ ላይ ያየነውን እና ያነበብነውን ሁሉ #ማመን_የለብንም!!
የኮምፒውተራችን እድሜ ስንት እንደሆነ ለማወቅ👇

1. System information በመጠቀም
👉Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ

👉 ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ

2. CMD በመጠቀም

🔅አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ

✅ open CMD

🔅CMD ሲከፍት systeminfo.exe ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒውተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ::
Channel photo updated
#Samsung_Phones

የሳምሰንግ ሊለጠጥ የሚችል ማሳያ 2 ዲ ይዘትን ወደ ተንቀሳቃሽ 3 ዲ ትዕይንቶች ሊለውጥ ይችላል

ከኮሪያ አውትሌት ኢቲ ኒውስ ዘገባ መሠረት ፣ ሳምሰንግ ዲስፕሌይ 13 ኢንች የሚዘልቅ የቅርብ ጊዜውን ሊለጠጥ የሚችል ዲስፕሌይን አሳይቷል። ርዕሱ እንደሚጠቆመው ፣ በዲስፕሌዩ ላይ የበለጠ ጠለቅ ያለ የይዘት ተወካይ ለማቅረብ ማያ ገጹ ሊዘረጋ እና ሊዝል ይችላል። ሳምሰንግ እንደሰጠው ምሳሌ ከሆነ እንደ ሚንሳፈፍ ላቫ Plume ፣ ማያ ገጹ በአካል ይነሳል እና ይወድቃል ፣ በትዕይንት ላይ የ 2 ዲ ይዘትን 3 ዲ ውክልና በማምረት ይችላል።
Šplus ethio
🔅 ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ማድረጓ መነጋገሪያ ሆኗል
=======================
✅ አለም የቢትኮይን ጥቅምና ጉዳት ላይ ገና ክርክሩን ጨርሶ ባላጠናቀቀበት ሁኔታ ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ አድርጋ መወሰኗ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ከትናትና ዕለት አንስቶ የንግድ ልውውጦችና ክፍያዎች በዲጂታል ገንዘብ እንዲሆን እያስገደደ ያለው የሃገሪቱ መንግስት ዜጎች የቢትኮይን ዲጂታል ዋሌት መተግበሪያ እንዲያወርዱና በምትኩ 30 ዶላር ዋጋ እንዲከፍሉ የሚያዝ መመሪያ አስቀምጧል፡፡

✅በሰኔ ወር መጀመሪያ ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ የሚያስችል አወዛጋቢ የህግ ረቂቅ ያሳለፈችው ሃገሪቱ ከመስከረም 7 ጀምሮ ደግሞ ህጉ የሚፀናበት ቀን እንደሚሆን አስቀምጣ ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ከትላንት ጀምሮ ስራ ላይ የሚውለው ይህ መመሪያ 4 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላትን ኤልሳልቫዶር ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ያደረገች ብቸኛ ሀገር ያደርጋታል፡፡

✅ህጉ ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላ የሃገሪቱ ዜጎች በቀላሉ የንግድ ልውውጥ ለማድረግ እንዲመቻቸው የቢትኮይን ሳንቲምን ወደ ዶላር የሚቀይሩ 200 የኤት ኤ ኤም ማሽኖችን ያስገጠመው የሃገሪቱ መንግስት በመደበኛው ገንዘብ ሲተመን 21 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ 400 የቢትኮይን ዲጂታል ገንዘብ ከአለም አቀፍ ገበያው እንደገዛም ተዘግቧል፡፡ የኤልሳልቫዶር ፕሬዝዳንት ናይብ ቡኬሌ ቢትኮይንን የሃገሪቱ መገበያያ የማድረጉ ውሳኔ በረሚታንስ የኢኮኖሚ ዘርፉ ላይ ትልቅ መሻሻሎችን እንደሚያመጣ ቢናገሩም በውሳኔው ላይ አስተያየት የተጠየቁ ብዙ የሃገሪቱ ዜጎች ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ የማድረጉ እርምጃ ግራ ኣጋቢ እንደሆነባቸው እንስተዋል፡፡

✅አወዛጋቢ በሆነው የቢትኮይን ገበያ ብዙ የአለም መንገስታት ዲጂታል ገንዘቡን ለማስተዳደር የሚያስችሉ ማዕቀቦችን እና ልዩ አሰራሮችን እያበጁ ቢሆንም በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ መንግስታት ደግሞ ይህን የዲጂታል ገንዘብ እንደ ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ መወሰናቸው ክርክሮችን እያስነሳ ይገኛል፡፡ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት የቢትኮይን ገበያ ቁጥጥር ውስጥ ለማድረግ እየሰሩ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የኤልሳልቫዶርን ውሳኔ ተከትለው ቢትኮይንን ህጋዊ መገበያያ ለማድረግ እየጣሩ ያሉት ፓራጓይ እና ኩባ በአለም አቀፍ መድረክ ትልቅ መነጋገሪያ አድርጓቸዋል፡፡
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼
የምልክት ቋንቋን ወደ ድምፅ ተርጓሚው የጆሮ ማዳመጫ

በኒውዮርክ የሚገኘው ቡፋሎ ዪኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን የጆሮ ማዳመጫን ከስማርት ስልክ ጋር በማገናኘት የምልክት ቋንቋን ወደ ድምፅ መተርጎም ወደሚችል መሣሪያ መቀየራቸው ተነገረ፡፡

መሣሪያው ዶፕለር የተባለውን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በመዋል የድምጽ ሞገድን በመልቀቅ የምልክት ቋንቋን ከሚያሳየው ሰው እጅ ላይ ነጥረው የሚመጡ የድምፅ ሞገዶችን ቅርፅ መተርጎም ማስቻሉን ቴክ ኤክስፕሎር አስነብቧል፡፡

ሶኒክኤ.ኤስ.ኤል በሚል ስያሜ በተጠራው በዚህ መሳሪያ ለጊዜው የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ተጠቅሞ በቤት ውስጥ በተደረገ ሙከራ 93.8 በመቶ ውጤታማ መሆን መቻሉ ተዘግቧል፡፡

ምርምሩ ከዚህ ቀደም በአጋዥ ቴክኖሎጂዎች አሊያም በተጨማሪ የሰው ኃይል የምልክት ቋንቋዎችን ለመተርጎም የሚደረገውን ጥረት ወደ አዲስ ምዕራፍ እንደሚወስድ ይጠበቃል፡፡

መሣሪያው መስማት በተሳናቸው እና በሌሎች ሰዎች መካከል የሚደረግ ተግባቦትን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያቃልል የተመራማሪዎቹ እምነት ነው፡፡

የዓለም መስማት የተሳናቸው ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ መሰረት ሶስት መቶ የተለያዩ የምልክት ቋንቋዎችን የሚናገሩ 72 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፡፡
Credit Tech 21
#Samsung_New_Camera

ሳምሰንግ እ.ኤ.አ. በ 2025 576 ሜጋ ፒክስል የምስል ሴንሰሮችን ወደ ገበያ ሊያመጣ ይችላል።

በ SEMI አውሮፓ ጉባኤ ላይ በ Samsung ከፍተኛ አውቶሞቲቭ ዳሳሽ VP ፣ Haechang Lee ላይ በቀረበው ስላይድ መሠረት ሳምሰንግ 576 ሜጋ ፒክስል የሚኖረውን ስልክ በመስራት ላይ እንዳለ አስተዋውቋል።
ፌስቡክ ለኩባንያው የመጀመሪያውን ስማርት መነፅር ይፋ አደረገ !

ፌስቡክ የመጀመሪያውን ስማርት መነፅር ይፋ ሲያደርግ ስማርት መነፅሩ ፎቶግራፎችን እና ቪዲዮዎችን ለማንሳት በካሜራ ጥንድ ፣ ፖድካስቶችን ለማዳመጥ ማይክሮፎን እና ድምጽ ማጉያ ፣ እና ሁሉንም ነገር ከእጅ ነፃ እንዲያደርጉ የሚያስችል የድምፅ ረዳት የተገጠመለት ነው ።

በመነፅሩ ክንፎች ላይ ፎቶዎችንና ቪዲዮችን ለማንሳት 5ሜጋፒክስል ካሜራዎች የተገጠመላቸው ሲሆን በረጅሙ ወይንም በአጭሩ በተኖቹን በመንካት እስከ 30ሰከንድ የሚደርሱ ቪዲዮዎችንም ማስቀረት ይችላል ።

ኩባንያው ከሬይ-ባን ጋር በጥምረት የሰራው ነው ተብሏል ፣ በመነፅሩ ላይ ክላሲክ ዌይፋሬር ሃርዴዌር የተቀረፀበት ፣ እና መሣሪያው በመጀመሪያ እንደ ሬይ-ባን ምርት ምልክት ይደረግበታልም ተብሏል ። ሬይ-ባን የተባለው ኩባንያ በ1936 የተመሰረተ ሲሆን ቅንጡ መነፅሮችን በማምረት ዝናን ያተረፈ ነው ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#የሞባይል_ሚስጥራዊ_ኮዶች!

1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#ይደውሉ

2ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#

3ኛ. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት ላይ አልዋለም እንዲልላችሁ ከፈለጋቹ!
ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ!
ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910654321 ከሆነ ወደ *21*091065432# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ!

➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክቶች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ
*21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል

4ኛ. ስልክዎ ቢዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ

5ኛ. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ

6ኛ. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!

7ኛ. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል
ከ 74 Million በላይ ተከታይ ያለው የስፔን ላሊጋ ፔጅ ለኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ አመት ብሏል።
👉 ሲም ካርድ ምንድን ነው?
🔷 ሲም ማለት ነው የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል.SIM stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል ፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-based access module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (a small portable memory chip) ፣ የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው ፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ / የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው።

✅ የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ፣ ማይክሮ እና ናኖ ፡፡ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው ፡፡ ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል ፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡

✅ የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና
CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው።

✅ GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡
CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም።

✅ eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡


✅ ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡
🔷 1. VCC ( Power Supply )
የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል ፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC(Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡

🔷 2. RST ( Reset )

የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

🔷 3. CLK ( Clock ) ሰዓት-ሲምውን ለprocessor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡
🔷 4. GND (Ground) ሲም የIntegrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል ፡፡
🔷 5. VPP ( Voltage Programming Power )
ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡
🔷 6. SIM Data I/O Pin

ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የdata ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡