DaniApps™
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
✅The Best Android Apps And Games Are Here.📱
✅For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
✅ Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
✅Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
✅ Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
የ WiFi ፍጥነት ችግር ባሁኑ ጊዜ ሁላችንም የመረረን ነገር ነው። ይህንንም ችግር በቀላሉ ለመፍታት=

1ኛ፦ #Speedfy የሚባል አፕሊኬሽን ዳውንሎድ አድርጎ መጠቀም

አንድ አንድ ግዜ የWiFi አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ሆን ብለው የDownload እና Upload ፍጥነቱን ሊቀንሱ ስለሚችሉ WiFi ኮኔክሽኑ ሊንቀራፈፍ ይችላል፡፡ በዚህ ግዜ #Speedfy አፕሊኬሽን ኮኔክሽኑን ፈጣን ያደርገዋል፡፡በተጨማሪ #Speedfy አፕሊኬሽን እንደ VPNም ስለሚያገለግል ኮኔክሽኑን ፈጣን ያደርገዋል፡፡

2ኛ፦ #Opera ብራውዘር መጠቀም

የWiFi ኮኔክሽናችን በሚንቀራፈፍበት ግዜ #Opera ብራውዘርን ስንጠቀም ኮኔክሽናችን ፈጣን ይሆናል፡፡ ምክንያቱም #Opera ብራውዘር ፈጣን ፕርፎርማንስ እንዲኖረው የራሱ Built-in features ስላሉት።

3ኛ፦ በአንድ ግዜ የከፈትናቸው ብዙ ታቦች(Browser Tabs) ካሉ እነሱን መዝጋት

የተከፈቱ ብዙ ታቦች ካሉ ኮኔክሽናችንን ዝግግግግ… ስለሚያደርጉት የማንፈልጋቸውን ታቦች መዝጋት ኮኔክሽኑን ያሻሽለዋል፡፡

4ኛ፦ ቦታ በመለዋወጥ የተሻለ ኮኔክሽን ልናገኝ እንችላለን።

5ኛ የላፕቶፕ ወይም የስልክ ቻርጀር መሰካት

የላፕቶፓችን ወይም የስልካችን ባትሪ እያለቀ ከሆነ ቻርጀር መሰካት ኮኔክሽኑን ሊያሻሽል ይችላል( ይሄ እንኳን Theory ነው፤ ላይሆን ይችላል)

6ኛ፦ ከጀርባ የሚሮጡ አፕሊኬሽኖችን መዝጋት።

7. VPN መጠቀም። VPN በ ኢንተርኔት ፍጥነት ላይ በጣም አስተዋጽኦ ያደርጋል። አስካሁን ካየሁትም አሪፍ ቪፒኤን super VPN Pro በጣም አሪፍ ነው።

8: የ WiFi DNS መቀየር: የ WiFi DNS መቀየር ለ ዋይፋችን ፍጥነት የጎላ ሚና አለው። የ ዋይፋይ DNS ለመቀየር ትንሽ ፕሮሰሱ በዛ ይላል አና ዩቱዩብ ላይ "How to change WiFi DNS" ብላቹ ሰርች በማረግ ማግነት ትችላላቹ።

9: Background ላይ የሚሮጡ አፕችን መቀነስ: ይህም ማለት ለምሳሌ ቴሌግራም አይተጠቀማቹ ከሆነ Play Store ያለ ፍቃዳቹ ኢንተርኔት እንዳይጠቀም ማገድ ማለት ነው። ይሄንንም ለማረግ አንደ "net guard" ባሉ አፕኦች መተግበር ይችላሉ።

Credit nurutech
🔅 iPhone 13 በ1Tb ስቶሬጅ ይመጣ ይሆን ?🤔

✅ አፕል በኮቪድ ምክንያት ነገ በኦንላይን በሚያደረገው ዝግጅት ላይ የሚጠበቀው አንዱና ትልቁ ነገር iPhone 13 ነው።

✅ አፕል በዚኛው ምርቱ ከዚ ቀደም ከነበሩት በካሜራ ፣በከለር አማራጮች ና በስቶሬጅ ካፓሲቲ በተሻለ ይዞ ይመጣል የሚሉ ወሬዎች እየተናፈሱ ይገኛል ።

✅ እንደ ሚንግ-ቻይ ኩኦ ገለፃ ፣ iPhone 13 Pro እና iPhone 13 Pro Max ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1 ቴራባይት የስቶሬጅ ካፓሲቲ ሊመጡ ይችላሉ ሲል ተናግሯል ። በተጨማሪም iPhone 13 እና iPhone 13 ሚኒ በ 64 ጊባ ፣ በ 256 ጊባ እና በ 512 ጊባ አማራጮች እንደሚገኙ ተነግሯል።

ወደ ባትሪ ደግሞ ስንመጣ ..
✅ ለ iPhone 13 Mini 2,406mAh ባትሪ ፣ ለ iPhone 13 እና ለ iPhone 13 Pro እስከ 3,095 mAh፣ እና ለ iPhone 13 Pro Max 4,325 mAh አቅም ይኖራቸዋል የሚሉ መረጃዎች ከወደ ቻይና እየወጡ ይገኛሉ።

✅ እነዚህ የባትሪ መጠኖች ከ iPhone 12 በየራሳቸው አቅም ላይ የተሻሻሉ ናቸው (ምንም እንኳን አፕል በይፋ የባትሪ ዝርዝሮችን ባይገልጽም)። ሆኖም ፣ የባትሪ ዕድሜ ከባትሪ አቅም ጋር አንድ አይደለም ፣ ስለዚህ የ iPhone 13 የባትሪ መጠን መጨመር ረዘም ያለ የባትሪ ዕድሜ አለው ተብሎ ላይተርጎም ይችላል።

✅ ነገር ግን ከሌሎች ውድ ስልኮች ጋር ሲነጻጸር የአፕል ባትሪዎች አጭር ናቸው። ለምሳሌ በሳምሰንግ ጋላክሲ s 21 ስልኮች ባትሪያቸው ከ 4,000 እስከ 5,000 mAh ይደርሳሉ።
RAM, HARD DISK AND POWER SUPPLY ምንድን ናቸው?
✅RAM
ራም (ራንደም አክሰስ ሜሞሪ) ኮምፒውተር በፍጥነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦኤስ) ፣ Application ፕሮግራሞች እና መረጃዎች በአሁኑ ወቅት በሚቀመጡበት የኮምፒተር መሣሪያ ውስጥ ሃርድዌር ነው ፡፡
#RAM የሚጠቅመው #የተቀሰቀሱ/የተከፈቱ #ፕሮግራሞች #በፍጥነት እንዲሰሩ የሚጠቅም ነው፡፡ የ RAM ተግባር በተለዋጭነቱ ምክንያት ራም ቋሚ መረጃዎችን ማከማቸት አይችልም።
ይህ ሊሆን የሚችለው #ኮምፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ #ፕሮግራሞች ለጊዜው (ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ) ለምሳሌ #HHD ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም #ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ #ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ከፍቷል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ከፍቷል #ፎቶ ወይም ቪዲዮ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና ቪዲዮ #ፕሮግራሞች ከፍቷል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች #እስከተከፈቱ ድረስ #ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር #የኮምፕዩተሩም #ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም፡፡ #ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ቦርድ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

✅Hard_disk

#ዳታዎችን በቋሚነት #ለመያዝ ነው፡፡ #የኮምፒውተሩ አሰራር ሂደት(operating system) #የሚጫንበት እና በአግባቡ ኮምፒውተሩ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ የሚያደርጉትን የአሰራር ሂደት #ፋይሎች(operating system files) የሚቀመጡበት #የኮምፒውተር ክፍል ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ #ሰነድ ጽፈው ለመያዝ ከፈለጉ የሚይዘው #HHD ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው HHD ዋና ቦርድ ላይ የሰካል፡፡ HHD ዳታ ሲያነብና ሲጽፍ #ማግኔታዊ ነው

#Power_Supply

#የኤሌክትሪክ ሃይልን መጥኖ #ለተለያዩ የአካል ክፍሎች ማደል ነው፡፡ ሁሉም #የኮምፕዩተር አካል ክፍሎች #አንድ አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል #(ቮልት) አይጠቀሙም፡፡ ስለዚህ የሃይል #አዳዩ ቮልቱን መጥኖ ለሁሉም ክፍሎች ይልካል፡፡ #ለምሳሌ 12 ቮልት፣ 9 ቮልት፣ 6 ቮልት፣ 48ቮልት ሊሆን ይችላል፡፡ #ፓወር ሳፕላይ እራሱን የቻለ #ማራገቢያ አለው #Power Supply Fan ይባላል፡፡
🔅 ከባድ የሶላር ሱናሜ የአለምን ኢንተርኔት ሊያጠፋ ይችላል

✅ ከፀሀይ የሚነሱ ሞቃት ነፋሳት የሚገድባቸው ነገር እስካላገኙ ድረስ ህዋ ውስጥ ይጉዋዛሉ። እነዚህን ነፋሳት ሊያቆሟቸው የሚችሉት ከሚጉዋዙበት ፍጥነት በበለጠ እና በተቃራኒ አቅጣጫ የሚነፍሱ ነፋሳት ብቻ ናቸው። የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ (magnetic field) ከፀሃይ ውስጠኛ ክፍል በከፍተኛ ፍጥነት የሚመጡትን ሞቃትማ ነፋሳት የሚያግድ ቢሆንም በጥለቁ የህዋ ክፍል የሚገኙ ሌሎች የበይነኮከባዊ ነፋሳት (Interstellar winds) ከፀሀያችን የሚወጡትን ሞቃታማ ነፋሳት የምድራችን ካባቢ አየር ጋር ከመድረሳቸው በፊት ፍጥነታቸውን በእጅጉ እንዲቀንስ ያደርጓቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የብዙ ፕላኔቶች የመግነጢሳዊ መስክ መገኛ በሆነ የህዋ ክፍል የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ የበላይነት ይዞ የሚገኝበት እና በብዙ ሺ ኪሎሜትሮች ምድራችንን ሸፍኖ የሚገኘው ንጣፍ ማግኔቶስፌር (magnetosphere) ተብሎ ይጠራል፡፡

✅ ከባህር ወለል በላይ ብዘ መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ በጥልቁ የህዋ ክፍል እስከ አስረሽ ሺ ኪሎ ሜትሮች ድረስ የሚዘረጋው የማግኔቶስፌር ንጣፍ የምድራችን መግነጢሳዊ መስክ እና ከፀሀያችን የሚነሱ ፕላስማ የተሰኙ ፖርቲክሎች ከፍተኛ ግንኙነት የሚያድረጉበት የህዋ ክልል ነው፡፡ ምድርን ሸፍኖ የሚገኘው የማግኔቶስፌር ንጣፍ ወይም ሌየር ከፀሃይ የሚመጣውን ቻርጅድ ፓርቲክልስ የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ ቢሆንም አልፎ እልፎ በከፍተኛ መጠን የሚመጣው የሶላር ስቶርም ወይም በሳይንሳዊ አጣራሩ (geomagnetic storm) በምድራችን የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ አደጋን ሊያስከትከል ይችላል፡፡

✅ በፀሃይ የመግነጢሳዊ መስክ ዙሪያ በሚኖር አለመረጋጋት በከፍተኛ መጠን ወደ ህዋ ክፍል የሚሰራጨው በቢሊዮን ቶን የሚለካ ከፍተኛ ሙቀት ያለው ጋዝ ለምድራችን ስጋት ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩት ተመራመሪዎች ይህም ከዚህ ቀድም በተለያዩ ጊዚያት ተከስቶ ለነበረው coronal mass ejection (CME) ዋና ምክንያት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ የሚገኙትና በዚህ ጉዳይ ላይ በቅርቡ የምርምር ጽሁፍ ያሳተሙት ፕሮፌሰር አርቪንና ረዳቶቻቸው እንደሚሉት በተለያየ የጊዜ ኡደት ወደ ህዋ ክፍሎች የሚሰራጨው ከባድ የሶላር ሱናሜ የምድራችንን መግነጢሳዊ መስክ በማጥቃት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈጥረው ችግር የአለማችንን ኢንተርኔት ወይም በይነ-መረብ የማጥፋት አቅም አንዳለው ይናገራሉ፡፡ በተለይም በዓለምችን የበይነመረብ መሠረተ ልማት ውስጥ ወሳኝ አካል የሆኑት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች በሶላር ስቶርም የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስባቸው ከማቻሉ አንጻር የአለምን ኢንተርኔት በቀጥታ የመጥፋት እድል እንደሚኖረው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡

✅ እንዲህ ያሉ ክስተቶች ቀድም ባሉት ጊዜያት አልፎ አልፎ የመከሰት እድል ቢኖራቸውም ኡሁን ባለው ደረጃ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች በአለም ላይ ባለመስፋፋታቸው ጉዳቱን አነስተኛ አንዲሆን ማድረጉን የሚናገሩት ተመራማሪዎች የበይነ-መረብ ዝርጋታ ከመጀመሩ በፊት እንደአውሮፓውያኑ በ1989 የተከሰተው የ coronal mass ejection አደጋ ለብዙ ሰዓታት የኤሌክትሪክ አቅርቦት እንዲቋረጥ ያደረገበት ሁኔታ እንደምሳሌ የሚጠቀስ መሆኑን ያነሳሉ፡፡ አሁን ላይ ለበይነ-መረብ መስፋፋት ከባህር በታች ያሉ የኢንተርኔት ኬብሎች (undersea internet cables) ዋና መሰረተ ልማት ከመሆናቸው አንጻር እነሱ ላይ በቀጥታ ሊደርስ የሚችል አደጋ የሰዎችን የበይነ-መረብ ግንኙነት በማቋረጥ ለአለማችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ትልቅ ጉዳትን ሊያመጣ ይችላል፡፡ በብዙ አመታት አንዴ ሊያጋጥም ይችላል የሚባለው ይህ ከባድ የሶላር ሱናሜ ምድራችንን በ1859፣ በ1921 እና በቅርቡ በ1989 እንዳጠቃት የሚናገሩት ተመራማሪዎች አሁን ካለው የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት መስፋፋፈት ጋር ተያይዞ አደጋው እጅግ የከፋ እንዳይሆን ተገቢውን ትከረት መስጠት እና ምርምሮች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈል ይናገራሉ፡፡
ምንጭ infomance
👍1
🔅 የወደፊቱን የመጓጓዣ ዘርፍ ይቀይራል የተባለለት ሀይፐርሉፕ

✅ ሀይፐርሉፕ የወደፊቱን የሰዎችና የእቃ ማጓጓዣ ስርዓት በእጅጉ ይለውጠዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ በሰዓት 1200 ኪሎሜትሮችን መምዘግዘግ ይችላል የተባለለት ይህ ቴክኖሎጂ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ የዘርፉ ምሁራን በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም 14- 16 ምክክር ይደረግበታል ተብሏል፡፡
✅ሀይፐርሉፕ የተሰኘው የመጓጓዣ ቴክኖሎጂ ሰዎችና የተለያዩ ቁሶች ዙሪያውን ዝግ በሆነ እንደ ሳጥን ባለ ነገር (capsule) ውስጥ ሆነው በከፍኛ ፍጥነት በቶቦ ውስጥ ከቦታ ቦታ እንዲጓዙ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ከመደበኛ ባቡሮች በተቃራኒ ፉርጎዎችን የማይጠቀም ሲሆን በወና ውስጥ በመግነጢሳዊ ሀይል በመታገዝ የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ ይህ ባቡር መሰል መጓጓዣ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለመቆም መግነጢሳዊ ሀይልን ይጠቀማል፡፡ መግነጢሳዊ ሀይሉ የፍትጊያ ሀይልን በመቀነስ ሀይፐርሉፑ በከፍተና ፍጥነት እንዲጓዝ ያስችለዋል፡፡
✅ የመጀመሪያው ቨርጂን ሀይፐርሉፕ የተሰኘው መጓጓዣ በላስቬጋስ በረሃማ ስፍራ መንገደኞችን በማሳፈር የተሳካ ሙከራ ማካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ይህ ከሳይንስ ፊክሽን እንኳን ላቅ ያለ ቴክኖሎጂ በቅርብ እውን የመሆን እድል እንዳለው እየተነገረ ነው፡፡ ሀይፐርሉፕ በጣም ዝቅተኛ የሆነ የካርቦን ተጽዕኖ ያለው መሆኑ እውን የመሆኑን ተስፋ ከፍ አድርጎታል፡፡

Credit tech21et
🔅 ጉግል Android 12ን አንዳንድ ችግሮች ካላጋጠሙት በኦክቶበር 4 ለተጠቃሚዎች ይፋ ሊያደርግ ይችላል !

✅ጉግል ባለፈው ሳምንት የAndroid 12 5ኛና የመጨረሻ ቤታን ለPixel ስልኮች ማውጣቱ ይታወቃል።

✅ጉግል "እኛ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ዋናውን update ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደምናደርግ እንጠብቃለን " ምንም እንኳን ጉግል ትክክለኛውን ቀን ይፋ ባይደረግም አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በኦክቶበር መጀመሪያ ላይ ሊሆን ይችላል ።

✅ከዚህ ቀደም ከነበሩት ስሪቶች ጋር ስናነፃፅረው በርግጥ ይሄኛው ዘግይቷል ፤ ሆኖም Google ሁሉም ነገር በትክክል መሥራቱን ማረጋገጥ ስለሚፈልግ ተጨማሪ ጊዜም ሊወስድ ይችላል ።

Credit ፦ XDA Dev
Adobe PhotoShop #Shortcuts
#YouTube news

✅ ከዚህ ቀደም YouTube community ለማስጀመር 1000 subscriber ይጠይቀን ነበር አሁን ግን ከ October 12/2021 ጀምሮ በ500 subscriber መጀመር እንደሚቻል youtube ተናግሯል።
ኢንተርኔትን በብርሃን ጨረሮች ተደራሽ የማድረግ ሙከራ

የሌዘር ጨረር ሥርዓት ላይ በመመስረት ኢንተርኔትን ተደራሽ የማድረግ ሙከራ በስኬት መከናወኑ ተገለፀ፡፡

ሙከራው የተከናወነው የኮንጎ ወንዝ በሚያካፍላቸው ብራዛቪል እና ኪንሻሳ ከተሞች መካከል መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

ኤክስ በተባለው የአልፋቤት የምርምር ተቋም ለሶስት ዓመታት ሲበለፅግ የቆየው አዲስ ሥርዓት ለአይን የማይታዩ የብርሃን ጨረሮችን በመጠቀም ፈጣን ኢንተርኔትን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ታውቋል፡፡

በዚህ ገመድ አልባ የግንኙነት መንገድ 99.9 በመቶ አስተማማኝነት 7 መቶ ቴራባይት የሚጠጋ ዳታ በ20 ቀናት ውስጥ ማቅረብ እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

የኮንጎ ወንዝ ቆርጦ በሚያልፋቸው ሁለቱ ከተሞች መካከል ገመድን መሰረት ያደረገ ፈጣን የብሮድባንድ ኢንተርኔት ለማቅረብ ቢሞከር አምስት እጥፍ ውድ እንደሚሆን ተዘግቧል፡፡

ፍሪ ስፔስ ኦፕቲካል ኮምዩኒኬሽንስ የሚል መጠሪያ በተሰጠው በዚህ ቴክኖሎጂ በቀጣይ ከሰሐራ በታች ያሉ ሀገራትን የፈጣን ኢንተርኔት ተጠቃሚ ለማድረግ ኩባንያው ማቀዱ ተነግሯል፡፡
ላፕቶፕ ሲገዙ ማወቅ ያልብዎት ነገሮች!

✅አዲስ laptop ለመግዛት አስበዉ ነገር ግን ምን አይነት laptop እንደሚገዙ ግራ ከተጋቡ🤔 ይችን ምክር ያገንቡቧት።


✅ አዲስ ላፕቶፕ ከመግዛት በፊት ሊያገናዝቧቸው የሚገቡ ነገሮች

📝 በዋናነት ሁለት አይነት Laptop አለ!

📌በWindows OS የሚሰራ
📌በMac OS(ለApple ብቻ)
(Kali linux, ubuntu...እራሳችን የምንጭናቸው Custom OS ስለሆኑ ብዛት እነዚ OS ያላቸውን ላፕቶፖች ገበያ ላይ አናገኝም!)

📌በብዛት በWindows OS የሚሰሩ የLaptop ዝርዝር👇
🔺Hp
🔺Dell
🔺Accer
🔺Toshiba
🔺Asus
🔺LG
🔺SONY....ወዘተ

📌በMac OS(ለApple ብቻ)
🚩Macbook Pro
🚩Macbook Air
🚩Macbook Retina

✅አዲስ Computer ሲገዙ ማየት ያለብዎት ነገሮች
👇👇👇👇
1⃣#RAM (Random Access Memory)

✅RAM ማለት አሁን አየተጠቀምንበት ያለዉ application ወይም System Process የሚቀመጥበት ቦታ ነዉ።

✅በአንድ ጊዜ ብዙ Application ከፍተዉ ለመጠቀም ኮምፒተርዎ ብዙ RAM ቢኖረዉ ይመረጣል።

✅ምንም እንኳን window 10 ለ 32 bit 1GB እና ለ64 bit 2GB (macOS minimum 2GB ያስፈልገዋል) minimum ቢያስፈልገዉም ስራችንን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስራት ይህ RAM አይበቃንም።

✅ስለዚህ አዲስ Computer ሲገዙ 8 GB እና ከዚያ በላይ RAM የለዉ ቢሆን ይመከራል።

2⃣Processor

✅Cori 3 chips:ይህ Processor ዝቅተኛ ሀይል  እና እርካሽ ዋጋያለዉ ነዉ።

✅Cori 5 chips:ይኸ ተመጣጣኝ ዋጋ እና perforance የያዘ ነዉ ።

✅ተመጣጣኝ ዋጋ እና በቂ speed ያለዉ Computer ከፈለጉ ይኽን ይምረጡ።

✅Cori i7 : የገንዘቡ ነገር እማያሳስቦ ምርጥ ኮምፒውተር መግዛት ከፈለጉ ከ Cori i7 በታች አይምረጡ።

3⃣Storage  ባሁኑ ሰአት ሁለት አይነት የኮምፒዉተር Storage አሉ HDD(hard disk drive) እና SSD(solid state drive)
HDDs  መረጃዎችን ለማስቀመጥ በፍጥነት የሚሽከረከሩ Magnetic Disk'ችን(Platters) ሲጠቀም flash memory ይጠቀማል።

✅SSD ያላቸው ኮምፒውተሮች የመጻፍ እና የማንበብ rate'አቸዉ HDD ካላቸዉ ኮምፒውተሮች በጣም ፈጣን ነው።

✅SSDs ምንም የሚንቀሰቀሱ part ስለሌላቸዉ lighter,cooler,quiter, more efficient and harder to damage ስለሆኑ ከ HDD ይልቅ ተመራጭ ናቸው።

4⃣Screen size

✅የ እስክሪን መጠን በብዛት የምንመርጠዉ #Laptoo ስንገዛ ነዉ።
ላፕቶፖች ከ 11-17 #inch መጠን አላቸዉ።

✅ብዙ #window ባንዴ የምንጠቀም ከሆነ ትልቅ እስክሪን መጠን የለዉ #Laptop ብንገዛ አሪፍ ነዉ።

✅ነገር ግን ትልቅ የእስክሪን መጠን ያላቸዉ ላፕቶፖች ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ ያስቸግራሉ እንዲሁም ትንሽ የባትሪ እድሜ አላቸዉ።

✅ዴስክቶፕ ላይ #Portability እና የባትሪ እድሜ ችግር የለዉም ነገር ግን ብዙ ሰዎች 24-inch ወይም ከዚያ በላይ #Monitor ይመርጣሉ።

4⃣ Resolution

✅  Resolution እንደናተ ምርጫ እና ገንዘብ ይወሰናል።

✅ምንም አይነት ሳይዝ ቢኖረዉ የእስክሪኑ #display ጥራት የሚወሰነዉ በ #Resolution ነዉ።

✅አብዛኞቹ ላፕቶፖች በ 720p resolution ለትንሽ display size ይመጣሉ።

✅ከፍተኛ ላፕቶፖች #Ultra HD/4K display የመጣሉ ነገር ግን ዋጋቸዉ በጣም ወድ ነዉ።

5⃣Size and Weight

✅አሁንም ሳይዝ እና ዉፍረት ለ #desktop ብዙም ችግር የለዉም ነገር ግን ላፕቶፕ #portability ሊኖረዉ ይገባል።

✅ላፕቶፕዎን እንደፈለጉ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ 12-inch #Screen size ወይም ከዚያ በታች ይምረጡ።

6⃣Operating Syatem

✅Windows ብዚ ጊዜ በስራ ቦታ እና ብዙ ሰዉ በምቾት የሚጠቀምበት #Operating System ነዉ።

✅የApple ኮምፒዉተር ከገዙ Mac Operating System ይጠቀማሉ።

7⃣ Generation
✅ማወቅ ያለብዎ latest generation ምን ጊዜም efficient እና powerful ናቸዉ።
5th, 6th, 7th, 8th.....

8️⃣ Graphics Card
Graphics Card ማለት ከ ፎቶ እና ቪዲዮ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ነገሮች በምንጠቀምበት ሰአት ፈጣን እና ከፍተኛ ጥራት ባለው መንገድ አቀናብሮ መስራት የሚያስችል የ ማትስ ቀመር የሚጠቀም Hardware Device ነው።

✅ a single, high-powered graphics card ያለው ይምረጡ ይህም ኮምፒውተሮ ላይ በ3D የሚሰሩ ለሶፍትዌሮችን ማለትም እንደ AutoCad አይነት እንዲሁም ጌም የሚጫወቱ ከሆነ ይጠቅሞታል
9️⃣ ኮምፒውተሮን ሲገዙ አብረው external hard drive ይግዙ ይህም ዳታዎችዎን ባክ አፕ (መጠባበቂያ) ለማረግ ነው::

🔟 Battery (ባትሪ) የስአት ቆይታው ቢያንስ ከ4 ሰአት በላይ ቢሆን ይመረጣል!
- 10,000 mAh
- 20,000 mAh
- 30,000 mAh
Website You Never Heard Of
Link: 2050.earth

This Website will show you How Some Cities would look like on the Future [ 2030, 2040, 2050 ].

You can see a 360 degree by sliding the screen.

Unfortunately they didn't do much for each Country But the rest is Amazing.
📌ቴሌግራም ለሳይበር ወንጀለኞች ጥቃት ተጋላጭ እየሆነ መምጣቱን አንድ ጥናት አመለከተ‼️

ቴሌግራም የተሰረቁ መረጃዎች መገበያያ ማዕከል እየሆነ መጥቷል ያለው ጥናቱ መተግበሪያው የሳይበር ወንጀለኞች የሚተራመሱበት ሌላኛው ‘ዳርክ ዌብ’ እየሆነ መጥቷልም ብሏል፡፡

‘ዳርክ ዌብ’ ባለሙያዎች ብቻ ሊጠቀሙና ሊደርሱ የሚችሉበት ድብቅ የበይነ መረብ ግንኙነት ስፍራ ነው፡፡ ‘ሳይበሪንት’ በተባለው የሳይበር ደህንነት ቡድን እና በፋይናንሽያል ታይምስ ጋዜጣ ትብብር የተካሄደው ጥናትም ቴሌግራም ለእንዲህ ዓይነት ባለሙያዎች ይበልጥ እየተጋለጠ መምጣቱን አረጋግጧል፡፡

የተሰረቁ መረጃዎችን ብዙዎች በሚጠቀሙበት በዚህ መተግበሪያ ላይ ለተዋቀሩና በሺዎች የሚቆጠሩ አባላት ላሏቸው ቡድኖች የሚያጋሩ፣ለግዢ እና ሽያጭ የሚያቀርቡ በርካታ መረጃ መንታፊዎች (ሃከርስ) መኖራቸውንም ነው ጥናቱ ያመለከተው፡፡
ይህ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነው ቴሌግራም ላይ ያሉ የቁጥጥር መንገዶች ከመላላታቸው የመጣ ነው እንደ አጥኚዎቹ ገለጻ፡፡
ከ47 ሺ በላይ አባላት ባሉት እና “ኮምቦ ሊስት” በተባለ አንድ ‘ፐብሊክ ቻናል’ ሃከሮች የይለፍ ቃላትን ጭምር የያዙ እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ያፈተለኩ መረጃዎችን ለሽያጭ አቅርበዋል ሲሉም በማሳያነት ያስቀምጣሉ፡፡

ለክፍያ አገልግሎት የሚውሉ ካርዶች፣ የግለሰቦች የባንክ መረጃ እንዲሁም የፓስፖርት ቅጂዎች በመተግበሪያው መጠቀሚዎች ለሽያጭ ከሚቀርቡት መካከል ናቸው እንደ ዘገባዎች ገለጻ፡፡
የሰዎችን መረጃ ለመበርበር የሚያገለግሉ መተግበሪያዎች እና መመሪያዎች በወንጀለኞቹ እንደሚቀርቡም ጥናቱ አመልክቷል፡፡
አጥኚዎቹ “ቴሌግራም የሳይበር ወንጀለኞች መጠቀሚያ እየሆነ መምጣቱን በልበ ሙሉነት እንናገራለን” ብለዋል፡፡

በተለይ ሚስጥራዊ መረጃዎች የሚጋሩበት የመተግበሪያው የአገልግሎት ክፍል፤ የተሰረቁ መረጃዎችን በድብቅ መሸጥ ለሚፈልጉ ሃከሮች ይበልጥ እየተመቸ መምጣቱን ነው በሳይበሪንት የሳይበር አደጋዎች ተንታኙ ታል ሳምራ የተናገረው፡፡
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2013 ስራ የጀመረው ቴሌግራም ለመለዋወጥ ምቹ እና ቀላል የሆኑ ነጻና ፈጣን የኦንላይን መልዕክቶች አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ከ500 ሚሊዬን የሚልቁ ተጠቃሚዎችም አሉት፡፡
ሆኖም የወንጀለኞቹ መበራከት መቀመጫውን የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ዱባይ አድርጎ በመስራት ላይ የሚገኘውን ተቋም በአሰራሮቹ ላይ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ ሊያስገድዱት እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡

#አል_ዓይን
☝️Which Camera Is Better For You

Samsung? OR iPhone?
🆕 ጨረቃ ላይ ውሃ እንዳለ ተረጋገጠ

▶️የፀሐይ ብርሃን የሚያገኙ የጨረቃ ክፍሎች ላይ ውሃ እንደሚገኝ ተመራማሪዎች አሳወቁ፡፡ ከዚህ በፊት በተሰሩ ምርምሮች ጨረቃ ላይ ውሃ ሊኖር እንደሚችል የሚያመላክቱ መረጃዎች ተገኝተው እንደነበር ያመለክታሉ፡፡ ይሄኛው ግኝት ደግሞ ሶፊያ በተባለችው ቴሌስኮፕ በመታገዝ የተሰራ ምርምር ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረውን ግምት እውነትነት የሚያጠናክር እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

▶️ይህ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የተገኘው የውሃ ሞሎኪዩል በቋሚነት በዚህ ስፍራ ብቻ የሚገኝ ላይሆን ስለሚችል ተጨማሪ ምርምሮችና ፍለጋዎች መሰራት አለባቸው ብለው እንደሚያምኑ የናሳው ተመራማሪ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ግኝቱ ለወደፊት ወደ ጨረቃ ለሚሄዱ ተጓዦችና ተመራማሪዎች እንደ ግብዓት ሊጠቅም ይችላል የሚል ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

▶️ሶፊያ (SOFIA) የተሰኘችው ቴሌስኮፕ በናሳ እና በጀርመን ኤሮስፔስ ማዕከል ጥቅም ላይ የምትውል ባለ 2.5 ሜትር እና በህዋ ላይ ግልጽ ምስሎችን ለመመልከት የምታስችል መሳሪያ ናት፡፡ ተመራማሪዎቹ በዚህች ቴሌስኮፕ በመታገዝ የተመለከቱት ምስል የውሃ ሞሎኪዩሎችን በፀሐይ ጨረሮች አማካኝነት ሲሆን ከዚህም በመነሳት ጨረቃ ላይ በተለያዩ ነገሮች ተሸፍኖ ውሃ እንዳለ መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህ ውሃም በጊዜ ሂደት ጨረቃ ላይ በፀሐይ ብርሃን አማካኝነት የተፈጠረ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ Science news
ALERT❗️ ለሞባይል_ባንኪንግ_ተጠቃሚወች

ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን ከዚህ ጥፋት እንታደግ!

⭕️አጭበርባሪወች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥር በተለያየ መንገድ ካገኙ በኋላ ፤ የባንክ ቁጠባ እድለኞች ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል ሜሴጅ ይልካሉ ፤

⭕️በተጨማሪም ወድያውኑ በስልካቸው ደውለው እርስዎ የወሩ የባንካችን እድለኛ ነዎት በመሆኑም በሽልማት የደረሰዎት 300,000 ሺ ብር በአካውንትዎ ገቢ እንዲሆንልዎ መጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆኑ *889# ብለው ያስገቡ በመቀጠል ስንደውልልዎ የራስዎን ሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስገቡ በሚል አጭበርባሪወች እራሳቸው የባንክ ሰራተኛ መስለው ካልኩሌሽኑን በስልክ ይመራሉ ፤

⭕️በመቀጠል በግለሰቦች አካውንት ያለውን ገንዘብ በሙሉ ወደ እራሳቸው አካውንት በማዞርና ወዲያውኑ ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ በማውጣት እየተሰወሩ ከፍተኛ ዘረፋ እየፈፀሙ ስለሆነ ፤ ማንኛውም ሰው ባንክ እየገባ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ በስልክ ጥሪ ብቻ እየተታለለ ገንዘቡን እንዳይበላና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን ።

ምንጭ dotcom tv show
​​✅ በአለማችን ትልቁ የCreation Software Developing ካምፓኒ Adobe ሲሆን የአዶቤን ሶፍትዌር የማይጠቀም ፕሮዲውሰር ፣ Studio ፣ ዲዛይነር ፣ TV Company የለም ማለት ይቻላል። ከትላልቆቹ Hollywood እስከ ጀማሪዎቹ Art ባለሙያዎች ሁሉም ስፘቸውን የሚሰሩት በAdobe ነው።

✳️ በአለም ዙሪያ ብዙ ተጠቃሚ ያላቸውና በብዙ ሰዎች የሚወደዱ የAdobe ሶፍትዌሮች፡

🔻Adobe Photoshop | ፎቶና ግራፊክስ መስሪያና ማቀናበሪያ
🔻Adobe Premiere Pro | ቪዲዮ ማቀናበሪያ
🔻Adobe After effect | Motional ግራፊክስ መስሪያ
🔻Adobe Lightroom | የፎቶ ከለር ማቀናበሪያ
🔻Adobe illustrator | ዲጂታል ስዕልና ሎጎ መስሪያ
🔻Adobe xD | interface ዲዛይን ማድረጊያ
🔻Adobe InDesign | Logo, Banner, Mesh መስሪያ
🔻Adobe Premiere Rush | all In one ቪዲዮ ማቀናበሪያ
🔻Adobe Dimension | 2D እና 3D ነገሮች Design ማድረጊያ
🔻Adobe Character Animator | 2D Animation መስሪያ
🔻Adobe Bridge | file organize ማድረጊያ
🔻Adobe Dreamweaver | ዌብሳይት መስሪያ
🔻Adobe Acrobat | Pdf መፍጠሪያና ማቀናበሪያ
🔻Adobe Animate | Vector ግራፊክስ እና Animation መስሪያ
🔻Adobe Audition | ድምፅ ማቀናበሪያ

Credit Amesi_Tech
እንኳን አደረሳችሁ መልካም በዐል
✴️ የስልካችንን ባትሪ እድሜ እንዴት ማርዘም
እንችላለን የሚለውን ነው ተከታተሉን።

1⃣. በመጀመሪያ #ባትሪዎን በጣም የሚመጠውን አፕ ለይቶ ማወቅና uninstall ማድረግ።

2⃣. e-mail, Twitter, Instagram, messenger....የመሣሰሉትን ከፍቶ አለመተው

3⃣. Bluetooth, WiFi, GPS
እነዚህን በስልክዎ ሲጠቀሙ ስልክዎ ሁልጊዜ search ስለሚያደርግ ባትሪዎን ይገሉታል።
🔻በተለይ GPS ለብዙ ሰአት መጠቀም ከሁሉም የበለጠ አደገኛ ነው።

4️⃣. ስልክዎን📱 በማይጠቀሙበት ጊዜ ultra power saving የሚለውን ማብራት ስልክዎ ስልክ ከመደወልና ሜሴጅ ከመቀበል በቀር ሌላ አገልግሎት እንዳይሰጥ ⚠ ስለሚያደርግ
#ባትሪዎን ለረጅም ሰአት መጠቀም ይችላሉ።

5⃣. background process የሚያደርጉ አፖችን ማስቆም።

6⃣. animated የሆነ wallpaper አይጠቀሙ።

7⃣. የስልክዎን brightness 🔆🔅🔅 ይቀንሱ።

8⃣. ያሉበት ቦታ ኔትወርክ በደንብ የሌለበት ከሆነ ስልክዎት የሚበቃውን ያህል signal 📶 strength ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት የስልክዎ ባትሪ ቶሎ ❌ ያልቃል።

9⃣. ስልክዎ ላይ ሙሉ ቀን ሙጭጭ🤳 አይበሉ።

1⃣0⃣. ኦርጅናል 📱
#ባትሪ ይጠቀሙ።

1⃣1⃣. battery case መግዛት የሚችሉ ከሆነ ይጠቀሙ።

1⃣2⃣. የስልክዎ 📱 የቻርጅ መጠን ከ 40-90% ቢሆን የተሻለ ነው።

1⃣3⃣ስልኮ 100% እስኪሆን ቻርጅ አለማድረግ ከ40% በታችም ሲሆን አለመጠቀም መልካም ነው።
⚠️ እነዚህን መፍትሄዎች ተግብረውም ለውጥ ከሌለው ባትሪ ይቀይሩ ወይም ችግሩ የ power ic ሊሆን ስለሚችል ለባለሙያ ያሳዩት።
▶️ የኮምፒዉተራችን storage space ሲሞላብን እንዴት ማስለቀቅ እንችላለን?
የኮምፒዉተርዎ storage space ሞልቶበት ተቸግረዋል፡፡ እንግዲያዉስ የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ
✅ ለብዙዎች እፎይታን የሰጠ መፍትሔ ሲሆን የኮምፒዉተራችንን ስቶሬጅ የሞሉብንን የተለያዩ ፋይሎች በማጥፋት ብዙ ትርፍ storage space እንዲኖረን ያስችለናል፡፡ ኮምፒዉተራችን ላይ የማንጠቀምባቸዉ እና የማይጠቅሙን ጊዜያዊ ፋይሎችን (temporary files) በማጥፋት ኮምፒዉተራችን ላይ ብዙ ቦታ እንዲኖረን ያስችለናል፡፡

✅ Delete unnecessary temporary file
Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን
የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት
አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።
እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።
✅ የማንጠቀምባቸዉን ፕሮግራሞች Uninstall ማድረግ
አብዛኞቹ ኮምፒዉተር ተጠቃሚዎች የኮምፒዉተራቸዉን ቦታ የሚያጣብባቸዉ የጫኗቸዉ ሶፍትዌሮች እና ጌሞች ናቸዉ፡፡ የማንጠቀምባቸዉን ሶፍትዌሮች Uninstall በማድረግ ቦታ መቆጠብ እንችላለን፡፡ ከኮምፒዉተሮ ላይ የማይፈልጉትን ሶፍትዌር ለማጥፋት የሚከተሉትን ቅደምተከተሎች ይከተሉ፡-

1. Start -> Control Panel -> Uninstall a program
2. ብዙ ቦታ የያዘዉን ሶፍትዌር ለማወቅ በ size ቅደም ተከተል ይደርድሯቸዉ፡፡
3. ማጥፋት የፈለጉትን ሶፍትዌር መርጠዉ Uninstall የሚለዉን ይጫኑ፡፡
3. የተደጋገሙ ፋይሎችን ያጥፉ
ዊንዶዉስ በራሱ የተደገሙ ፋይሎችን ለይቶ የሚያጠፋ ሲስተም የለዉም ስለዚህ ይህንን ስራ የሚሰሩ ሶፍትዌሮችን መጫን ይኖርብናል፡፡ ይህንን የሚያደርጉ የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ከነዚህም ዉስጥ Duplicate Sweeper አንዱ ነዉ፡፡ Duplicate Sweeper ኮምፒዉተራችን ላይ ያሉ የተደጋገሙ ፋይሎችን scan አድርጎ ያቀርብልናል፡፡ እኛም ከዘ ዉስጥ የተደገሙ መሆናቸዉን እያረጋገጥን ማጥፋት እንችላለን፡፡
4. ጊዜያዊ ፋይሎች (Temporary Files)
በ Windows Disk Cleanup አማካኝነት ጊዜያዊ ፋይሎችን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አይተናል፡፡ ነገርግን Windows Disk Cleanup ሊያገኛቸዉ የማይችሉ እንደ browser ያሉ የጫንናቸዉ ሶፍትዌሮች የፈጠሩትን ጊዜያዊ ፋይሎች ለማጥፋት የሚያስችለን ሌላ መንገድ Google Chrome ን እንደ ምሳሌ በመዉሰድ እናያለን፡፡
1. Google Chrome ን ይክፈቱ
2. settings menu ይክፈቱ
3. More tools የሚለዉን ይምረጡ
4.Clear Browsing data የሚለዉ ዉስጥ በመግባት ማጥፋት የሚፈልጉትን ጊዜያዊ ፋይል
መርጠዉ ያጥፉ
5. Recycle Bin ዉስጥ ያሉ ፋይሎችን ያጥፉ
ከኮምፒዉተራችን ላይ ያጠፋናቸዉ ፋይሎች permanently delete ካላደረግናቸዉ መልሰን ብንፈልጋቸዉ ማግኘት እንድንችል Recycle Bin ዉስጥ ይቀመጣሉ፡፡ ከላይ ባሉት መንገዶች ያጠፋናቸዉ ፋይሎችም Recycle Bin ዉስጥ ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ Recycle Bin ያሉ ፋይሎች ግን ከኮምፒዉተራችን ላይ የያዙትን storage space እንደያዙ ነዉ የሚቆዩት፡፡ ስለዚህ storage space ለማስለቀቅ እነዚህን የማንፈልጋቸዉ ፋይሎች ከRecycle Bin ዉስጥ ማጥፋት ይኖርብናል።

Mametech
✅ 23ኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው ጎግል ከዛሬ ጀምሮ ‘አሮጌ’ አንድሮይዶችን በሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ላይ አይሰራም

✅ አንድሮይድ 2.3 እና ከዚያ በታች የሚጠቀሙ ስልኮች ከዛሬ ጀምሮ የጎግል ማፕ፣ ዩ ቲዩብ እና የጂ ሜይል አግልግሎቶቹን እንደማያገኙም ኩባንያው አስታውቋል
@Dani_apps
👍1