DaniApps
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
The Best Android Apps And Games Are Here.📱
For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
♨️ በልጆች መጫዎቻ ሰው ሰራሽ ክንድ የሚሰራው ብልሁ የፈጠራ ሰው

ፖሊሺ ሲንድሮም በተባለው ከባድ በሽታ ከልጅነቱ የተያዘው ዴቪድ እንደ እድሜ እኩዮቹ በሁለቱ እጆቹ ያሻውን ለማድረግ አይችልም ነበር፡፡ ገና ወደዚህች ዓለም ሲቀላቀል የቀኝ ክንዱን የተነጠቀው ይህ ህፃን በእድሜ እኩዮቹ የሚደርስበት እንግልትና ማዋከብ በራሱ ተስፋ እንዲቆርጥ ያደርገው ነበር፡፡ በህጻንነቴ ሁሌ ራሴን በመስታዎት ስመለከት እንደሁሉም ሰዎች ሁለት እጆች ይዤ አለመወለዴ በጣም እንድበሳጭ እና እንዳዝን ያደረግኝ ነበር የሚለው ዴቪድ ይህን ሁኔታ ለመቀየር ብዙ ሃሳቦችን ማውጠንጠን እና ፈጠራዎችን በራሴ ለመስራት ቁጭት አሳደረብኝ ይላል፡፡

ገና ከ9 ዓመቱ ጀምሮ በቤት ውስጥ ለመጫወቻ በተገዛለት የሌጎ ጡቦች ሰው ሰራሽ ክንድ ለመስራት ሲጥር የነበረው ዴቪድ ከብዙ ሙከራዎች በኋላ በቀኝ እጁ ላይ ሊገጠም የሚችል ተጣጣፊ ክንድ መስራት ቻለ፡፡ ዴቪድ የልጆች መጫዎች ከሆኑት የሌጎ ጡቦች ያበለፀገውን ይህን ሰው ሰራሽ ክንድ ይበልጥ እያዳበረ እና እያሳደገ ከመጣ በኋላ ስራውን ከጀመረበት ከዘጠኝ አመታት በኋላ ለተጎዱ ሰዎች በሚገባ ግልጋሎት መሰጥት የሚችል እና አስገራሚ ንድፍ ያለው ሰው ሰራሽ ክንድ ሰርቶ በማቅረብ በ2017 በጊነስ የአለም ሪከርድ ፈጠራውን ሊያስመዘግብ ችሏል፡፡

ከዚህ ዓመት ጀምሮ በሌጎ ጡቦች አማካኝነት ለራሱ የሰራውን ሰው ሰራሽ ክንድ በመጠቅም ሙሉ ጊዜውን መስል ችግር ላለባቸው ሰዎች ፈጠራውን ለማቅረብ ሲሰራ የቆየው ዴቪድ፤ ፖሊሽ ሲንድሮም በተባለው በሽታ ሁለት ክንዶችን ላጣው የስምንት አመት ህጻን ፈጠራውን ሰርቶ ማቅረብ ችሏል፡፡ መጀመሪያ ስሰራቸው ከነበሩት ሰው ሰራሽ ክንዶች አሁን ላይ ያሉት ምቾት ያላቸውና በተገጠመላቸው ኮንትሮል ዩኒት በቀላሉ ትዕዛዝ መቀበል እንዲችሉ ተደርገው መሰራታቸውን የሚናገረው የፈጠራ ባለሙያው ዴቪድ ለስምንት ዓመቱ ህፃን ቤንኩር የሰራውም ሰው ሰራሽ ክንድ በቀላሉ ትዕዛዝ ሊቀበል የሚችል እና የህጻኑን ምቾት የማይነሳ ፈጠራ መሆኑን ይናገራል፡፡

የህጻኑ ቤንኩር ወላጀች ዴቪድ የሚሰራቸውን ሰው ሰራሽ ክንዶች በጊነስ የአለም ሪከርድ ዜና ላይ ከተመለከቱ በኋላ ለልጃቸው የሚሆን ሰው ሰራሽ ክንድ ለማሰራት ከሚኖሩበት ፈረንሳይ ዴቭዲ ወዳለበት አንዶራ 1,300 ኪ.ሜትሮችን ተጉዘው አግኝተውታል፡፡ የፈጠራ ባለሙያው አጭር ጊዜ ወስዶበት ለህጻኑ ማቅርብ የቻለው የሌጎ ሰው ሰራሽ ክንድ የህጻኑን ምቾት በጠበቀ መልኩ የተሰራ ከመሆኑም ባለፈ ትዕዛዝን ተቀብሎ የመፈፀም አቅሙ እጅግ የላቀ ነበር፡፡ ዴቪድ ይህን አስገራሚ የፈጠራ ውጤት ለወላጆቹ ሰርቶ ለማቅረብ የተጠቀማቸው የሌጎ ጡቦች እና አንዳንድ የኤሌክተሮኒክስ ቁሶች በጥቅሉ 18 ዶላር ብቻ መፍጀታቸው ብዙዎችን ያስደነቀ ጉዳይ ነው፡፡

ፖሊሽ ሲንድሮም በተባለው በሽታ የአካል ጉድለት ላለባቸው ብዙ ሚሊዮኖች ፈጠራውን ማቅረብና መርዳት የሚፈልገው ዴቪድ በቀጣዮቹ አመታት አሁን ካሉት ስራዎች እጅግ የላቀ እና ልክ እንደተፈጥሮ አካል በቀላሉ መንቃሰቀስ የሚችሉ ሰው ሰራሽ ክንዶችን በመላው ዓለም ለማቅረብ እቅድ እንዳለው ይነገራል፡፡ በኔ የደረሰው የህይወት አጋጣሚ ለብዙ ህፃናት ትልቅ ትምህርት እና መነሳሳት እንደሚፈጥር የሚናገረው ዴቪድ ከተለያዩ የተፈጥሮ ወስንነት አደጋዎች ጋር የሚወለዱ ብዙ ሚሊዮን ታዳጊዎች በሰዎች ላይ ጥገኛ ብቻ ሳይሆኑ ለብዙዎች መትረፍ እንደሚችሉ የሚያሳይ ክስተት ነው ይላል፡፡
ምንጭ፡ techgz
▶️ ለተማሪዎች በነጻ የቀረበው የኤሌክተሮኒክ ሲሙሌሽን መተግበሪያ

የተለያዩ የኢንዱስትሪያ ውጤቶችን በኮምፒውተር የሲሙሌሽን ስርዓት ለማበልፀግ እና አዳዲስ የንድፍ ስልቶችን ለመማር የሚያስስችል የ Ansys መተግበሪያ ለተማሪዎች፣ ለሰልጣኞች እና ለትምህርቱ ፈላጊዎች በነፃ መቅረቡ ተነግሯል፡፡ የኤሌክተርሮኒክ ሲሙሌሽን ወይም በሙሉ ስያሜው ኤሌክትሮኒክ ሰርኪዩት ሲሙሌሽን የሂሳብ ሞዴሎችን በመጠቀም መደበኛ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ለማውጣት የሚስችሉ ሲሙሌሽን ወይም አምሳያዎችን በኮምፒውተር አልጎሪዝም አማካኝነት ለማቀናበር እና ለመቅዳት የሚያስችል በምህንድስና ዘርፍ ውስጥ የሚካተት ትምህርት ነው፡፡ በኮምፒውተር ሲስተም አማካኝነት የሚከናወነው ይህ የቴክኖሎጂ መስክ ለዚሁ አገልግሎት ተብለው በበለፀጉ መተግበሪያዎች አማካኝነት ሊተገበር ይችላል፡፡

በቅርቡ Ansys በተባለው የቴክኖሎጂ ኩባንያ በነፃ ያቀረበው አዲስ የኤሌክተሮኒክ ሲሙሌሽን መተግበሪያ ለተማሪዎች እና ለሰልጣኞች አዳዲስ የንድፍ ስልቶችን ለመማር የሚያስችሉ ጠቃሚ የኤሌክተሮኒክ ሲሙሌሽን አሰራሮችን ወይም ቱሎችን በማካትት ከፕሮጀክት እቅድ አንስቶ የሞዴል ፈጠራ እና የኤክስፕርመንቴሽን ትንተና ሂደቶችን በቀላሉ ለማስተማር የቀረበ ነው፡፡ በመተግበሪያው አማካኝነት የሚቀርቡት ጠቃሚ የሲሙሌሽን ክህሎት መማሪያ መሳሪዎች ለማናቸውም የኤሌክትሪካል ምህንድስና አጥኝዎች አልያም እውቀቱን ማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች ጠቃሚ ትምህርቶችን የሚያስገኙ ሲሆን፤ ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ንድፍ ከመስራት አንስቶ ጥራታቸው እጅግ ከፍ ያሉ ሲሙሌሽን ለማበልፀግም የሚረዱ ናቸው፡፡

በምህንድስናው ዘርፍ የኮምፒውተር ሲሙሌሽን ትግበራዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ባሉበት በአሁን ሰዓት የእውነተኛውን አለም ችግር በአነስተኛ ወጪ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለመፍታት የሚስችሉ የሲሙሌሽን ቴክኒኮችን ለመማር በዘርፉ ተቋማት የሚቀርቡ የመተግበሪያ አማራጮችን መጠቀም ትልቅ ጥቅም ሊያስገኝ ይችላል፡፡

በዚህ የኤሌክተሮኒክ ሲሙሌሽን የትግበራ ዘርፍ ውስጥ በበይነ-መረብ የሚገኙ ብዛት ያላቸው የኦንላይን ወይም የኦፍላይን መተግበሪያዎች ቢኖሩም ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ኖሯቸው ለሰልጣኞች ወይም ለተማሪዎች አስፈላጊውን የክህሎት ስልጠና የሚሰጡት አማራጮች እጀግ አነስተኛ ናቸው፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ Ansys ያሉ የኤሌክተሮኒክ ሲሙሌሽን መተግበሪያ አማራጮች በሙያው ረዥም ርቀት መጓዝ ለሚፍልጉ ሰልጣኞችና ተማሪዎች ደረጃው እጅግ ከፍ ያለ የሲሙሌሽን ቴክኒክ እና ተያያዥ እውቀቶችን ለማግኘት ትክክለኛው ቦታ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ምንጭ፡ techgz
የመተግበሪያው ሊንክ https://www.ansys.com/academic/students/ansys-electronics-desktop-student?utm_campaign=academic&utm_medium=paid-trade&utm_source=interesting-engineering%20&utm_content=partner_electronics_web-banner-aedt-student_product-page_download_sponsored-content_en_global&campaignID=7013g000000HRcDAAW
♨️ ሎካል ዲስክን እንዴት ወደ ሁለት ክፍል ወይም partition መከፋፈል እንችላለን።

ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ክፍሎች እንዴት እንከፍላለን

🔆 ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል:

1⃣. right click on My computer

2⃣. በመቀጠል Manage የሚለውን እንነካለን

3⃣. ቀጥሎ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ ውን
በመምረጥ right click እናደርጋለን።

4⃣. ከዚያም shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል።

5⃣. በመቀጠል የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን Click አድርጎ መጠበቅ...

6⃣. በመጨረሻም በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ

7⃣. click on "New simple volume
አሁን next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::

ℹ️ ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም፤ ግን ደግሞ
#Backup ብንይዝ ይመረጣል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😱ኮኔክት የተደረገልንን ዋይ-ፋይ ስልካችንን ሩት ሳናደርግ በቀላሉ #Password ለማየት የሚረዳ ቪዲዮ ነው

‼️አንድሮይድ ቨርዥናችሁ ከ 9 በላይ ቢሆን ይመረጣል👌
ከዚያ በታች ከሆነ ሩት ማድረግ አለበለዚያም Hacker Keybord የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖችን በመጠቀም የዋይ-ፋይ #Password ማየት ይቻላል።
✴️ አማዞን አዲስ ሮቦት አስተዋወቀ፡፡

🔻አስትሮ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውል ሮቦት በአማዞን ቀረበ፡፡

🔻አሌክሳ በተባለው የኩባንያው የስማርት ቤት ቴክኖሎጂ አማካኝነት የቀረበው ሮቦት የቤት ደህንነትን ጨምሮ ቤት የሚወሉ አዛውንቶችን ለማዝናናት እንዲሁም በቪዲዮ ጥሪ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ያስችላል ሲል ሲኔት ዘግቧል፡፡

🔻ሮቦቱ በራሱ እና በርቀት መቆጣጠሪያ የቤትዎን ሁኔታ መከታተል የሚያስችል ሲሆን እንግዳ እንቅስቃሴ ከተመለከተ ለባለቤቶቹ እንደሚያሳውቅ ተገልጿል፡፡

🔻የድምፅ ትዕዛዛትን የሚቀበለው ሮቦት የአካባቢውን ሁለንተናዊ ገፅታ መቃኘት እንዲያስችለው እንደ አንቴና ተዘርጊ ካሜራ ተገጥሞለታል፡፡

🔻በተገባደደው የአውሮፓውያኑ 2021 መጨረሻ በአንድ ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለገበያ እንደሚቀርብ የተነገረለት አስትሮ በስሪቱ ላይ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጉልህ ሚና እንደነበረው በዘገባው ተገልጿል፡፡

🔻አማዞን በአስር ዓመት ውስጥ ቢያንስ ከአምስት ቤት በአንዱ አጋዥ ሮቦት እንዲኖር አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

©Arteficial intelligence center ethiopia
════❁✿❁ ═══════
News Time

🛩ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙ ድሮኖችን ለቀረፃ መጠቀምና ማብረር በህግ ያስጠይቃል። -የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

🚨ማንኛውም ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰቦች ማንኛውንም አይነት ድሮኖች ከመጠቀማቸው በፊት ለፍቃድ ሰጪ ድርጅቶች ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፤ ፈቃድ ሰጪ ድርጅቶቹ ፈቃድ ስለሰጡት የድሮን ባለቤትና የድሮን አይነት 24 ሰአት ቀደም ብለው ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል።

‼️ማንኛውም አካል ፍቃድ ሳያገኝ እያበረረ ቢገኝ በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
ኮምፒዩተራችን ሲከፍት ወይንም ጌም እና ሌሎች አፕሊኬሽኖችን ስንከፍት ስታክ ሚያደርግብን ከሆነ ይህን ስቴፕ በመጠቀም ማስተካከል እንችላለል

🔻 Win + R
🔻 msconfig ብለን መፃፍ ከዛም Ok
🔻 Boot የሚለውነ ጋር እንገባለን
🔻 Advanced Options የሚለውን እንነካለን
🔻ከዛም Number Of Processor On ካረግን በኋላ Maximum ወይንም 4 ላይ አርገን Ok ከዛም Apply ካልነው በኋላ Restart ሚለውን ነክተን Restart
በመጨረሻም ኮምፒውተራችን Smoothly Run ያደርግልናል
ግብፅ ዩቲዩበሮችን ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ ማቀዷ መነጋገሪያ ሆኗል😳

👉 በግብፅ ዩቲዩበሮች ግብር እንዲከፍሉ የወጣዉ ዕቅድ የተለያዩ የድጋፍ እና የተቃዉሞ አስተያየቶች እንዲደመጡ አድርጓል፡፡የግብጽ የግብር ባለስልጣን ዩቲዩበሮች እና ጦማሪያን ዓመታዊ ገቢያቸውን እንዲያስመዘገቡ እና እንዲያሳውቁ ጠይቋል።

👉 መንግስት በዋናነት ትኩረት ያደረገዉ በየዓመቱ ከ32,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያገኙትን እንደሆነም ተነግሯል፡፡በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ሰዎች አዲሱን የግብር መመሪያ ሲደግፉ ተስተዉለዋል፡፡

👉 በማህበራዊ ገጽ ትስስር ላይ እየተንሸራሸሩ ካሉ ሀሳቦች መካከል አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ የአትክልት ሻጮች ግብር ይከፍላሉ እኛ ሀብታሞቹ ዩቲበሮች ግብር ልንከፍል ይገባል ያሉም ተገኝተዋል፡፡የግብጽ የታክስ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ መሐመድ አል ጌይርን በበኩላቸዉ በግብፅ ውስጥ ትርፍ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው የሥራው መስክ ምንም ይሁን ምን በትክክል ግብር ይከፈልበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

👉 ሌሎች ደግሞ የበይነመረብ ወጪዎችን በመጥቀስ እርምጃውን ይቃወማሉ ፣መንግስት ዩቲዩቦችን ቀረጥ እንዲከፍሉ ከፈለገ ቢያንስ የተሻለ የበይነመረብ አገልግሎት ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ተችተዋል፡፡
☝️☝️☝️ Programming Languages እና ጥቅማቸው
የኢሜል password ብንረሳዉስ🙈?
የኢሜል ፓስዋርዳችሁ ከጠፋባችሁ ከዚህ በታች ያሉትን እስቴፖች በመከተል የጠፋባችሁን የኢሜል ፓስዋርድ
አጥፍታችሁ #reset በማድረግ በአዲስ መቀየር ትችላላችሁ ።
👇👇
1⃣ ይከከን ማስፈንጠሪያ

https://accounts.google.com/signin/recovery

ተጭናችሁ ወደ #Google account recovery ፔጅ ግቡ።

2⃣ፖስዋርዱ የጠፋባችሁን ኢሜል አድራሻ (email address) አስገብታችሁ #forget password የሚለዉን በተን ተጫኑ።

3⃣የምታስታዉሱትን የ ኢሜል ፓስዋርድ እንድታስገቡ ይጠይቃችሗል።

እዚህ ላይ ያስታወስችሁትን የጠፋዉን ፖስዋርድ አስገቡ እና #Next የሚለዉን በተን ተጫኑ።

ብትሳሳቱም አትጨነቁ አካዉንታችሁን አይዘገሠዉም።

4⃣ከዛ #Google የሜረጋገጫ #Verification code
ኢሜሉን ስትከፍቱ ባስገባችሁት ስልክ ቁጥር ይልክላችሗል።

በምን ይልካል?

#Text or Call የሚል ሲመጣ የሚፈልጉትን የመቀበያ መንገድ ይምረጡ።

5⃣የተላከላችሁን ባለ 6 #digit የማረጋገጫ ኮድ አስገቡ።

6⃣ከዛ አዲስ ፖስዋርድ እንድታስጋቡ ይጠይቃችሗላ።

የፈለጉትን ፖስዋርድ እና ኮንፌርሜሽን ፓስዋርድ(መጀመሪያ ያስገባችሁትን ደግማችሁ አስገቡ) አስገብታችሁ
#Next የሚለዉን ሲጫኑ የጠፋዉ ፖስዋርድ በአዲስ ፓስወርድ ተቀየረ ማለት ነዉ።


Join & Share @dani_apps
EBC ሀክ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ይፋዊ ፌስቡክ ገፅ #ሀክ መደረጉ /መጠለፉ/ ተገልጿል።

በገፁ ላይ የሚሰራጩት መረጃዎችም የተቋሙ አይደሉም ተብሏል።
#Update

የEBC ገፅ ተመለሰ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፥ " በጠላፊዎች ተወስዶ የነበረው የኢብኮ የፌስቡክ ገጽ በሳይበር ባለሞያዎቻችን እጅ ገብቷል " ሲል አሳውቋል።
ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መስራት አቁመዋል።

በፌስቡክ ስር የሚገኙት መተግበሪያዎቹ በተለያዩ የዓለም ሀገራት መስራት አቁመዋል። ኢትዮጵያ ውስጥም አገልግሎቶቹ ተቋርጠዋል።

መተግበሪያዎቹ በበርካታ አገራት መቋረጣቸውን ዓለም ዐቀፉ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቆጣጣሪ ተቋም ኔትብሎክስ አሳውቋል።

ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ፌስቡክ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

⚠️ በ VPNም እየሰራ አይደለም
ውድ ደንበኞቻችን
ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር በአሁኑ ወቅት አገልግሎታቸው የተቋረጠ መሆኑን እየገለጽን ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል በትዕግስት እንድትጠብቁ እንጠይቃለን።

Ethio Telecom
#Facebook

የተቋረጠው የፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እና ሜሴንጀር አገልግሎት ችግሩ በአገልግሎት ሰጪዎቹ በኩል እስኪስተካከል ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኢትዮ ቴሌኮም መልእክት አስተላልፏል።

ፌስቡክ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባሰራጨው መልዕክት በተቻለ ፍጥነት ነገሮችን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ እየሰራን መሆኑን አሳውቋል፤ ለተፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግር ይቅርታ ጠይቋል።
😁😂😂

በአለም ዙሪያ ብዙ ሰዎች በአሁኑ ሰአት ቴሌግራምን እየተጠቀሙ ይገኛል
በዚህም ምክንያት ቴሌግራም BUSY እየሆነ ነው
#Update

ከ6 ሰዓታት በላይ ተቋርጠው የቆዩት ፌስቡክ ፣ ዋትስአፕ ፣ ኢንስታግራም እንዲሁም ሜሴንጀር ወደ አገልግሎት ተመልሰዋል።

ፌስቡክ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ከመጠየቅ ውጭ እስካሁን ችግሩ በምን ምክንያት እንደተፈጠረ ማብራሪያ አልሰጠም።

እንደብሉምበርግ ዘገባ ከሆነ በፌስቡክ መቋረጥ በ5 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የማርክ ዙከርበርግ የግል ሃብት በ7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዝቅ ብሏል።

@dani_apps