DaniApps
1.01K subscribers
611 photos
34 videos
537 files
219 links
The Best Android Apps And Games Are Here.📱
For Any Questions ➡️ @DaniappsBot Or Group ➡️ @daniappsgroup
Apps Or Games ➡️ @daniappsstore
Ask Any Apps ➡️ @Daniapps2bot
Website https://daniapps.epizy.com/

https://g.page/r/CYhVwdbaF335EA0/review
Download Telegram
ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ማንቀሳቀስ የሚያስችለው iOS 15

📍በአዲሱ የአፕል ምርት በሆነው አይፎን ስልክ ላይ የተካተተው iOS 15 የተሰኘው ቴክኖሎጂ ከፎቶ ላይ ያለን ጽሁፍ ወደፈለግነው ቦታ ማንቀሳቀስ እንድንችል የሚያደርግ ብቃት እንዳለው ታውቋል፡፡ ይህ የተለያዩ ብቃቶች እንዳሉት የተነገረለት ስርዓት ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም በአንድ ፎቶ ላይ ያሉ ይዘቶችን በመተንተን ተጠቃሚው የሚፈልገውን እንዲያደርግ (copy and paste) ያስችለዋል ተብሏል፡፡

📍ይህ ነገሮችን (ጽሁፎችን) አይቶ የመረዳት ስርዓት ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም እንደ አፕል ማብራሪያ ከሆነ የአሁኑ ቴክኖሎጂ እንደ ከዚህ ቀደሙ ክላውድ ሰርቨር ላይ ያለ ሳሆን ስልኩ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡

📍ይህ ቴክኖሎጂ ከሚሰጠው ጥቅም ውስጥ ተጠቃሚዎች አንድን ጽሁፍ ወይም ገጽ ፎቶ በማንሳት ካነሱት ፎቶ ላይ ያለውን ጽሁፍ በቀላሉ መገልበጥ (copy and paste) ማድረግ መቻሉ ዋነኛው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢዝነስ ካርድ ካሉ የመረጃ ወረቀቶች ላይ የተጻፉ ስልክ ቁጥሮችንና የኢሜል አድራሻዎችን በቀላሉ ፎቶ በማንሳት ስልክ መደወልም ሆነ ኢሜል መላክ ያስችላል፡፡

📍ሌላውና ይህ አዲሱ ቴክኖሎጂ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ውስጥ የእጅ ጽሁፍን በፎቶ አማካኝነት ወደ ዲጂታል መቀየር የሚያስችል መሆኑ ነው፡፡

©️ Techupdates
📺 ፊልም የምናይባቸው ድህረ-ገፆች 📺

1. 🎬https://sflix.to/home

2. 🎬https://myflixertv.to/

3. 🎬http://snehtvnew.ueuo.com/

4. 🎬https://vw1.ffmovies.sc/

5. 🎬https://back.egybest.co/

6. 🎬https://soapgate.org/

7. 🎬https://picaflix.xyz/

8. 🎬https://www.stremio.com/

9. 🎬https://popcorn-time.tw/


©Dani site
😱Mark Zuckerberg's Personal Wealth Has Fallen By Nearly $7 Billion On A Few Hours
Is now No6 In The Billionaire Chart 😂😂😂


ትናንት Facebook, Instagram, Messenger & WhatsApp በመቋረጣቸው ምክንያት Mark Zuckerberg ከሀብቱ ወደ 7ቢሊየን ዶላር አጥቷል

📍አሁን ላይም በሀብታሞቹ ሠንጠረዥ 6ኛ ላይ ይገኛል
📍 ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ 11 ሶፍትዌር መልቀቁን አሳወቀ

ማይክሮሶፍት ለሁሉም የዊንዶውስ 10 ኮምፒዩተሮች የሚሆን የአሰራር ሂደትን በተቀላጠፈ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል አዲስ የዊንዶውስ 11'ን ኦፕሬቲንግ ሲስተም ለገበያ ማቅረቡን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

የኦፕሬቲንግ ሲስተም ዝመናው ቀደም ብሎ ጥቅም ላይ ከዋለው ከ ዊንዶውስ 10 በኋላ በተሻሻለ መልኩ የቀረበ ሲሆን ሶፍትዌሩ የዊንዶውስ 10 ተጠቃሚ የነበረ የትኛውም ኮምፒዩተር ላይ መጫን የሚችል ነው። ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ለማግኘት በቀጥታ ቀድሞ ይጠቀሙበት የነበረው ዊንዶውስ መቼት ላይ ማዘመኛውን (windows update software) በመጠቀም ማግኘት እንደሚቻልም አሳውቋል።
በህንድ ሲም የሚቀበል ነጠላ ጫማን ለኩረጃ ሊያውሉ የነበሩ ተፈታኞች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

📍በህንድ ራጃስታን ግዛት ከዚህ ቀድም ከፍተኛ ጥቅም ያስገኛል የተባለውን የመምህራን ፈተናን ለመስጠት በሚል ኢንተርኔት ቢቋረጥም የኩረጃ መልኩ ተቀይሯል።ነጠላ ጫማን በብሉቱዝ በማገናኘት ፈተናውን ቀድመው ተፈትነው የወጡ ተፈታኞች ውስጥ ላሉ ጓደኞቻቸው መልስ እንዲነግሩ ተደርጎ ተመቻችቷል።

📍በዚህም መሰረት ነጠላ ጫማው ሲም የሚቀበል ሲሆን በአይን ለማየት እጅግ አዳጋች የሆነ ቀጭን የጆሮ ማዳመጫ በጆሮዋቸው በማድረግ ወደ መፈተኛ ክፍል ያመራሉ።አንዳንዶቹ የጆሮ ማዳመጫውን በጊዜያዊነት በጆሮዋቸው ውስጥ ለማስቀበር ሲሞክሩ እንደነበረም ተሰምቷል።ከውጪ ስልኩ ሲደወልላቸው በእግር ጣታቸው ስልኩን ያነሳሉ።

📍ለአንድ ነጠላ ጫማ 600ሺ ሩፒ ወይም 8ሺ ዶላር ይጠየቅበታል።በዚህ ድርጊት እጃቸው አለበት የተባሉ አደገኛ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል።ህንድ ተፈታኞች ነጠላ ጫማ አድርገው ወደ መፈተኛ ክፍሎች እንዳይገቡ ከልክላለች።

©ethio techs
🎦ብዙ እየተወራለት ያለው SQUID GAME በ Dani Movies Store ላይ ይገኛል አሁኑኑ አውርደው ይኮምኩሙት 👇👇👇

📥 DOWNLOAD NOW
📌በትናንትናው እለት የፌስቡክ ፣ዋትስአፕ እና ኢንስታግራም ገፆች ለ6 ሰአት ሲቋረጥ ቴሌግራም ላይ 70 ሚልየን አዲስ ተጠቃሚዎች ጨምሯል::

©️ FACTS_FOR_KNOWLEDGE
ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ተሳትፈውባት የነበረችው ሶፊያ ሮቦት በዚህ ዓመት በብዛት ልትመረት ነው

📍መቀመጫውን በሆንኮግ ኮንግ ባደረገው እና ሀንሰን ሮቦቲክስ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በዋና መሪነት የተሰራችው ሶፍያ ሮቦት ከ50 የሚበልጡ የፊት ገለጻዎችን ማሳየት የምትችል መሆኗ ለየት ያደርጋታል። ሶፍያ ይህን ለማድረግ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (artificial intelligence) የሚባለውን ግሩም ቴክኖሎጂ ከማካተቷ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎች አሻራቻን ያሳረፉባት አስገራሚ የቴክኖሎጂ ግኝት ናት። ከአመታት በፊት አይኮግ ላብስ በተባለው ድርጅት የታቀፉ ኢትዮጵያውን ባለሙያዎች የሮቦቷን አካል ከሰራው ሀንሰን ሮቦቲክስ ኩባንያ ጋር በመተባባር ለሶፍያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቀመሮችን በማዘጋጀት ስራ ላይ በዋናነት ሲሰራ መቆዩታቸው የሚታወቅ ሲሆን ሮቦቷን ወደ ውጤት በማምጣት ሂደት ላይም የራሳቸውን ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

📍እንደአውሮፓውያኑ በ2016 ለአለም የተዋወቀችው ይህች ሮቦት የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከሚባሉት የምትመደብ ቢሆንም ከሷ በፊትና ከሷ በኋላ ከተሰሩት ማሽኖች እጅግ የሚለይ ባህሪዎችና ገፅታዎች የተላበሰች ሮቦት ናት፡፡ እስካሁን በዚህ ዘርፍ ከተሰሩት ማሽኖች ከሰዎች ጋር ባላት ግንኙነት እና እንደየሁኔታው በሚያጋጥሟት ክስተቶች እንደ መቆጣት፣ ማዘን እና መደሰት ያሉ ሰውኛ ባህሪዎችን ለመሳየት መቻሏ ሶፊያን ከሌሎች የማህበራዊ ሚና ካላቸው ሮቦቶች ለየት የሚደርጋት ነው፡፡ ሶፊያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያላት እና በማህበራዊ ሚና ላይ ለሰዎች ይበልጥ የቀረበች ሮቦት ብትሆንም በብዛት የመመረት እድል ስላልነበራት ወደብዙዎች መድረስ አለመቻሏን የሚያስረዱት የሀንሰን ሮቦቲክስ መስራች ዴቪድ ሃንሰን አሁን ላይ ከኮቪድ መምጣት ጋር ተያይዞ ሮቦቷን በብዛት አምርቶ ወደገበያ ለማቅርብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

📍ከወራት በፊት ይህን እቅድ በመሬት ላይ በማውረድ በብዙዎች የምትታወቀውን የሶፍያ ሮቦት እስከአመቱ መጨረሻ በሺዎች በመማረት ለገበያ ለማቅርብ እየሰራ መሆኑን የሚናገሩት ዴቪድ ሃንሰን አሁን ባለንበት አለም እንደሶፊያ ያሉ ማህበራዊ ሚና ያላቸው አውቶሜትድ ማሽኖች አቅመ ደካሞችን ያለመሰልቸት ለመርዳት እና የታመሙ ሰዎችንም ለማገዝ ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ያነሳሉ፡፡ አሁን ላይ ብዙ በሮቦቲክስ ዙሪያ የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶችን በብዛት በማምረት ላይ የሚገኙ ሲሆን እንደ ሃዩንዳይ ያሉ ትልልቅ ኩባንያዎች ሳይቀር በዘርፉ ላይ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

📍ከዚህ በፊት የተሰሩ እንደ ሚሎ ያሉ የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከኦቲዝም ጋር የተያያዘ የጤና እክል ያለባቸው ህጻናትን ስሜቶቻቸውን አውጥተው አንዲናገሩ በማስቻል የተግባቦት አቅማቸውን ሊያስድጉ መቻላቸውን የሚናገሩት የዘርፉ ባለሙያዎች መሰል የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች በየቀኑ ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን ያለመስለቸት በመስራት የታመሙ ሰዎች ለመርዳት እና አቅመ ደካሞችን ለማገዝ ጥሩ አማራጭ መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሰፊ እውቅና ያላት የሶፍያ ሮቦት እንዲህ ያሉ ማህበራዊ ተግባሮችን ለመከወን የሚስችል የስሜት ተለዋዋጭነት እና የበዛ የቋንቋ ክህሎት የታከለባት ሮቦት እንደመሆኗ መጠን ተቀባይነቷን እንደሚጨምረው የባለሙያዎች አስተያየት ነው፡፡
©️elatech
📍የሳምንቱ Technology News And Fact

Facebook በገጠመው የSystem ችግር ምክንያት ለ6 ሰአት በአለም ዙሪያ ቆሞ ነበር በቆመ በ 6 ሰአት ውስጥ  7ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሞኛል አለ የFacebook መስራቹ Zuckerberg በገጠመው ኪሳራ በ ሃብት ደረጃ ወደ 5ተኛ ዝቅ ብሏል።

አንድ ግለሰብ የGoogleን Company ሙሉውን ልግዛ ቢል አሁን ላይ 1ትሪሊዮን ዶላር ሊኖረው ይገባል 😳🤭

የቀድሞ የአሜሪካ ፕረዚዳንት Donald Trump ከ ማህበራዊ ሚዲያ ግጭት ቀስቃሽ ነገሮችን ይለቃል በሚል ከነ Twitter ከመሳሰሉ ታግዶ (Bun) ተደርጎ ነበር የሚገርመው ነገር የራሴን የ Social-Media አቋቁሟለሁ ሲል ዝተዋል። ያለው ማማሩ 😁

የGoogle Company የሆነው (Android) Android 12 የሚባል አዲስ Version የያዘ OS አውጥቷል በጣም የገረመኝ ነገር ሚኖር ይዞ ከመጣው አዲስ ነገሮች ውስጥ ከinternet Game Download እያደረግን መጫወት እንችላለን ይገርማል Downloadዱ ሳያልቅ እንዴት ? እኔ በጣም አስገርሞኛል ሌላም ብዙ አዲስ Features  ይዞ መትዋል 🔥

Microsoft Window 11 ድን እንዳወጣ ዘግቧል ይህ መረጃ ትንሽ ቆየት ቢልም ለWindow ለተጠቃሚዎች Officially Download አድርገው እንዲጠቀሙ የተፈቀደው ከ 1ድ ቀን በፊት ትላንት October 5 ነው Download አድርጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ Window 10 የምትጠቀሙ ወደ 11 Upgrade ማድረግ ይቻላል.

Telegram በአንድ ቀን ብቻ 70ሚሊዮን አዲስ ተጠቃሚ አግኝትዋል ይህም ሊሆን የቻለው
Facebook WhatsAppና Instagram ለ 6 ሰዓት በአለም ደረጃ በመቋረጡ ነው።

©️tech21
ቻይናዊያን ተማሪዎች ለረጅም ሰዓት የምትበር ድሮን በመስራት ክብረ ወሰን
ሰበሩ


📍 በቻይናዊያን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች መሳርያ አልባ ድሮን ያለ እረፍት
ለረጅም ሰዓት የበረረች ድሮን በመባል የዓለም ክብረ ወሰንን ሰብራለች፡፡

📍 ፌንግ አርዩ 3-100 የተሰኘችው ይህች በቤጂንግ የኤሮናቲክስ እና አስትሮናቲክስ
ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተሰራች ድሮን ያለ ማቋረጥ ለ80 ሰዓት ከ46 ደቂቃ
ከ35 ሴኮንድ በመብረር ነው ቀድሞ በቦይንግ ስር በሚተዳደረው ኦሪዮን በተሰኘ ተቋም በ80 ሰዓት፣ ከ2 ደቂቃ ከ52 ሴኮንድ ተይዞ የነበረውን ክብረ
ወሰን ያሻሻለችው፡፡

📍 የክንፍ ርዝማኔዋ 10 ሜትር የሆነው ድሮኗ በጋዝ ሞተር አማካኝነት የምትንቀሳቀስና ጠቅላላ ክብደቷም (የተሞላባትን ነዳጅ ጨምሮ) 60 ኪ.ግ
ነው፡፡ ስያሜዋም የቻይና አቪዬሽን ኢንዱስትሪ አባት ከሚባሉት ከፌንግ ሩ የተወረሰ ነው፡፡

📍 በረራው የተከናወነው ባሳለፍነው ግንቦት ወር በቻይና ሄናን ግዛት ውስጥ ነበር፡፡ ሆኖም ክብረ ወሰኑ ገና ባሳለፍነው እሁድ ነው በዓለም አቀፉ የኤሮናቲክስ ፌደሬሽን (FAI) እውቅና የተሰጠው፡፡

📍 በበረራው ወቅት ድሮኗ በ300 ሜትር
ከፍታ ላይ ስትጓዝ የነበረች ሲሆን በአየር ላይ እያለችም ምንም አይነት ተጨማሪ ነዳጅ እንዳይሞላላት ተከልክላ ነበር፡፡ እንደ ዩኒቨርሲቲው መረጃ ከሆነ ድሮኗን የሰራው የተማሪዎቹ ቡድን 25 ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ያቀፈ ነው፡ የተማሪዎቹ አማካኝ ዕድሜም ከ20 ዓመት በታች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፤ ሺኑዋ
#DV_2023_እንዴት_ራሳችን_መሙላት_እንችላለን?

በጥያቄያችሁ መሰረት ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ

📍በመጀመሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2023 Program: Online Registration
DV-2023 Program: The online registration period for the DV-2023 Program begins on Wednesday, October 7, 2021 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2021 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2023 Program Instructions

📍የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦

እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም

• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም

• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም

www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት

›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል

1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።

2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።

3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።

4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ

5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር

6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ

7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል

* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት

9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ

10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል

11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት

12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ

13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ

14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።

» በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2023 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2023 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ ።

© Muhammed computer technology
DaniApps pinned «#DV_2023_እንዴት_ራሳችን_መሙላት_እንችላለን? በጥያቄያችሁ መሰረት ዲቪ 2023 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ 📍በመጀመሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2014 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2021 ጀምሮ ህዳር 09/2021 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው። DV-2023 Program: Online Registration DV-2023 Program: The online…»
#የጥንቃቄ_መልእክት_ለሞባይል_ባንኪንግ_ተጠቃሚወች

ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን ከዚህ ጥፋት እንታደግ!

አጭበርባሪወች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥር በተለያየ መንገድ ካገኙ በኋላ ፤ የባንክ ቁጠባ እድለኞች ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል ሜሴጅ ይልካሉ ፤

በተጨማሪም ወድያውኑ በስልካቸው ደውለው እርስዎ የወሩ የባንካችን እድለኛ ነዎት በመሆኑም በሽልማት የደረሰዎት 300,000 ሺ ብር በአካውንትዎ ገቢ እንዲሆንልዎ መጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆኑ *889# ብለው ያስገቡ በመቀጠል ስንደውልልዎ የራስዎን ሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስገቡ በሚል አጭበርባሪወች እራሳቸው የባንክ ሰራተኛ መስለው ካልኩሌሽኑን በስልክ ይመራሉ ፤

በመቀጠል በግለሰቦች አካውንት ያለውን ገንዘብ በሙሉ ወደ እራሳቸው አካውንት በማዞርና ወዲያውኑ ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ በማውጣት እየተሰወሩ ከፍተኛ ዘረፋ እየፈፀሙ ስለሆነ ፤ ማንኛውም ሰው ባንክ እየገባ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ በስልክ ጥሪ ብቻ እየተታለለ ገንዘቡን እንዳይበላና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን ።
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
(ምንጭ Muhammad Computer Technology
ታዋቂ የ ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች በደረጃ
✳️ስፔስ ኤክስ ከ 100 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማካበት አሁን የአለም ሁለተኛው በጣም ዋጋ ያለው የግል ኩባንያ ሆኗል !

እ.ኤ.አ. በ 2002 የተቋቋመው ስፔስ ኤክስ ሳተላይቶችን ወደ ምህዋር በመክፈት ጠፈርተኞችን ወደ ዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሚያጓጉዙ ሲሆን ኩባንያው አሁን ከ100 ሚ ዶላር በላይ በማካበት የአለም ሁለተኛው በጣም ዋጋ ያለው የግል ኩባንያ መሆን ችሏል ።  

በቅርቡ ሙሉበሙሉ በአማተር ጠፈርተኞች ያደረገውን ጉዞ በስኬት ማጠናቁ ይታወሳል ።
✳️ ፈረንጆች ሞባይላቸው ብዙ ብር ሲቆጥርባቸው ቢል ሾክ(Bill Shock) ይሉታል። እርስዎ ሳይጠቀሙበት ሞባይልዎ ብዙ ብር የሚቆጥር ከሆነ አላስፈላጊ ወጪ ለመቀነስ የሚከተሉትን ምክሮች እናካፍል።

1. እንተርኔት በማይጠቀሙበት ጊዜ የሞባይል ዳታ ያጥፉ (turn of mobile data when not in use)
2. ትልቅ መጠን ያላቸዉን አፕልኬሽኖች ለመጫን wifi ይጠቀሙ
3. አንዳንድ አፕልኬሽኖች እርስዎ ሳያቁ ዳታ ሊያወርዱ ስለሚችሉ አፕዴት እንዳያደርጉ መከልከል (restrict background data)
4.የተጠቀሙትን የዳታ መጠን ሊያሳይ የሚችል አፕልኬሽን ይጫኑ
5. ኢመል አካዉንትዎ በራሱ ጊዜ አዳዲስ መልእክቶች መኖራቸዉንና አለመኖራቸዉን እንዳያደርግ መከልከል (Adjust account sync settings)
©tech com
ጎግል ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ ነው
==========================
በሳይበር ምህዳሩ ዘርፍ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት በሃከሮች ዋና ኢላማ እየተደረጉ ከመምጣታቸው አንጻር ጎግል በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ለእነዚህ ተጠቃሚዎቹ የማስጠንቀቂያ መልዕክት እና አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም (APP) የተባለውን የቅርብ ጊዜ የደህንነት ሲስተም እንዲተገብሩ ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁንና በቅርብ ወራት ውስጥ ከፍተኛ ተከታይ ባላቸው የፖለቲካ መሪዎች፣ የሰብኣዊ መብት አክቲቪስቶች እና ሌሎች ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ባለባቸው አካላት ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የሳይበር ወንጀል፤ ሌሎች የደህንነት አሰራረሮችን ለመተግበር እያስገደደው እንደመጣ ያስታወቀው ጎግል አሁን ላይ 10ሺ ለሚጠጉ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው ተጠቃሚዎች አዲስ የደህንነት ቁልፍ ሊሰጥ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

በ2021 ብቻ ውስብስብ የሳይበር ጥቃት እየተፈፀማባቸው የሚገኙ እና የሃገር መንግስታት ድጋፍ የሚደርጉላቸው ሃከሮች የሚሞክሩትን የሳይበር ጥቃት ለማክሸፍ አድቫንስ ፐሮቴክሽን ፕሮግራም የተባለውን የደህንነት ስርዓት ተጠቃሚዎች እንዲተግበሩ ጎግል ሲሳስብ ቆይቷል፡፡ ይሁንና ይህንን ሳያደርጉ የቆዩና በመስከረም ወር የማጣራት ሂደት ብቻ ከፍተኛ የሳይበር ሙከራ በተደረገባቸው 14 ሺ በላይ የጂሜል ተጠቃሚዎች የማስጠንቀቂያ መልክት መላኩን የተናገሩት በድርጅቱ ውስጥ የስጋት ትንተና ቡድን ሃላፊ የሆኑት ሚስተር ሃንትሊ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው አካላት የኦንላይን አጠቃቀማቸው ላይ የሚታየውን ተጋላጭነት በፍጥነት እንዲሞሉ ተዳጋገሚ ማሳሰቢያ መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

ጎግል አሁን ላይ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የሚያቀርበው የደህንነት ቁልፍ በኮምፒውተራቸው ላይ በሚሰኩ የሃርድዌር ዩኤስቢ መሳሪዎች አማካኝነት የሚሰሩ ሲሆን በዋናነት የተጠቃሚዎችን አካውንት ለመጥለፍ የሚያስችሉ የተለያዩ የሳይበር ጥቃቶችን በሚገባ ለመከላከል የሚግዝ ነው፡፡ ታይታን ብሎ የሰየመውን የድህንነት ቁልፉ ለተጠቃሚዎች ለማሰራጨት ጎግል ከብዙ የቴክኖሎጂ ድጅቶች ጋር እየሰራ መሆኑን ያስታወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት ከከቀረቡት ባለሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (two-factor authentication) አሰራሮች በተጨማሪ ከፍተኛ የሳይበር ስጋት ላለባቸው 10 ሺ ተጠቃሚዎች የቀረበው ይህ የደህንነት ቁልፍ እየተባባሰ የመጠውን የሳይበር ወንጀል ለመከላከል በእጅጉ እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
ቴሌግራም hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?

✔️መፍትሄውን እነሆ👇

ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatts app,viber, imo,tango.....etc
ቴሌግራም እንደ whatsapp,viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

✴️ሌሎችም hack ማድረጊያ አፕሊኬሽኖች አሉ
ማለትም 👉desktop app
👉android app አሉ።
እናም በነዚህ👆 የሀኪንግ አይነቶች አካውንታቹ ሌላ ስልክ ላይ ወይም ሌላ #pc ላይ ሊኖር ይችላል

1⃣.በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session 👉 ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

⚠️Note: እራስዎ በሌላ #አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል መርጠው መርጠው ነው።

✴️ ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት፤ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ 📱 የእናንተን #አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

2⃣.Security ደግሞ ለማጠናከር👇

seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password *..

⚠️ግን የ #gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

✴️ ይህ👆 ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

✔️የሚጠቅመው #እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ📲 ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።

✔️ ሌላ ሰው #በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።

✴️ ማንም ሰው ለመግባት #በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም፥፥

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት::
✴️ ሀከሮች የሚጠቀሙባቸዉ አሪፍ ቱሎች

🧩1. Kali linux:- ካሊ ሊኑክስ የላቀ የፔንቴሬቲንግ ፍተሻ እና የደህንነት ማረጋገጫ ኦፍ ሴተሮችን መሠረት ያደረገ Debian መሰረት ያደረገ የLinux ስርጭት ነው. ካሊ ለበርካታ የመረጃ ደህንነት ተግባራት ማለትም እንደ penetration testing, የደህንነት ምርምር, ኮምፕዩኒኬሽን እና የተራቀቀ ኢንጂነሪንግ ያሉ በርካታ መቶ መሳሪያዎችን ይዟል !

🧩 2. Black box BackBox ኔትቡክን መሰረት ያደረገ የLinux ስርጭት እና የኔትወርክ እና ኢንፎርሜሽን ስርዓቶች ትንታኔ መሳሪያዎችን የሚያቀርብ የዳሰሳ ጥናት እና የደህንነት ግምገማ ነው. ለደህንነት ምርመራዎች የሚያስፈልጉትን የተሟላ መሳሪያዎች ያካትታል.

🧩 3. Parrot security 
parrot linux ኮምፒውተር ጥበቃ ላይ ትኩረት በማድረግ የደቢያን ስርጭት ስር ነው. ለዳሰሳ ሙከራ, ተጋላጭነት ግምገማ እና ማቃለያ, ኮምፒዩቲን ጠንቋዮች እና ስም-አልባ የድር አሰሳ ተብሎ የተዘጋጀ ነው።

©️ Amesi Tech