#FactCheck
ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ እንደተደረገ የሚጠቁም መልዕክት ደርሶናል፣ በርካቶች ደግሞ አንድ ኮድን በመጠቀም በነፃ የኢንተርኔት ፓኬጅ ማግኘት እንደቻሉ ሲፅፉ ተመልክተናል።
በዚህ ዙርያ ኢትዮጵያ ቼክ የድርጅቱን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩን አናግሯል። የሰጡን መረጃ በዚህ መልኩ ይቀርባል:
"ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ አልተደረገም። ስራችን ሳይቋረጥ አዳዲስ አገልግሎቶች ላይ ማስተካከያ (configuration) እያረግን ነው። በዚህ ምክንያት ጥቂት ደንበኞቻችን አንዳንድ አገልግሎቶችን [በነፃ] ሊወስዱ/ሊያገኙ ችለዋል። ሁኔታውን እኛም አውቀነው እየሰራንበት ነው፣ በቁጥጥራችን ስር ነው" ብለዋል።
ድርጅቱ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው መረጃ በመጪው 2014 ዓ.ም ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ የሆኑ አዳዲስ አሰራሮችን እተገብራለሁ ብሏል። ከዚህም አንዱ ደንበኞች ፓኬጅ ሲጠቀሙ የ20 በመቶ ቅናሽ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን በአዲስ አመት ደግሞ ለአንድ ወር የሚቆይ አደይ አበባ የተሰኘ የሞባይል ፓኬጅ አገልገሎት 44 በመቶ ቅናሽ ተደርጎበት ስራ ላይ ይውላል ብሏል።
ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት 70 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት እንዲሁም የደንበኞቹን ቁጥር 64 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን ኢዜአ አስነብቧል።

👍1