አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና - አደገኞቹ
201K subscribers
5.16K photos
168 videos
14 files
772 links
ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ቻናል ነው። ይህ ቻናል ሰለ ውዱ ክለባችን ኢትዮጵያ ቡና 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደእናንተ ያደርሳል።

ለማንኛውም አስተያየት እና መረጃ
@UTD14
@Bunnacoffee12

መወያያ ግሩፕ ➲ @BunnaFC
Download Telegram
🔆 #በታማኝነታችን_በተለመደው_ትዕግስታችን_እንቀጥል


🇪🇹☕️1980 አጋማሽ ላይ ለድንቅነሽ(ሉሲ) ዋንጫ ቡና "#ከፈረሰ" በኋላ እንደገና ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሜዳ የሚመጣበት ጊዜ ይፋ ሆነ የመጀሪያውንም ጨዋታ ከአየር መንገድ ጋር ደረሰው

👉 #ቡና_ገበያ ወደ ሜዳ ሲገባ ደጋፊው ገንፍሎበት ቡድኑን እንደገና ሜዳ ላይ በማየቱ በአጥር ዘሎ በመግባት ተጨዋቾቹ እግር ላይ ሳየቀር እየወደቀ ባንደራውን ይዘው

👉 #እያለቀሱ ከሜዳ አንወጣም በሚል ጨዋታው ሳይጀመር ከ30 ደቂቃ በላይ6 ቆየ ደጋፊው መሬትቱን #ይስማል ባንዲራውን ይዘው #የሚጨፍሩ ደጋፊዎችም ነበሩ እርስበእርስ #ተቃቅፈው ያለቅሳሉ ሁሉም ስሜቱን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ነው።

👉#ዳኞቹም ፊሽካ በመንፋት ውድድር ቶሎ እንዲጀመር አላደረጉም በሁኔታው ተገርመው #ይውጣላቸው ብለው ተዋቸው ደጋፊው ውድድሩን አልፈለገም ቡድኑ ዳግም በመመለሱ #ኢትዮጵያ_ቡናን ሜዳ ላይ በማየታቸው ብቻ ተደሰቱ፡፡

አሁንም ያ #ታማኝነት ለክለባችን ያለን #ፍቅር ሳይቀንስ እዚህ ደርሷል እኛም እናስቀጥለዋለን ።
#አይታጠፍም_ቃላችን_ዘላለም_ቡንዬን_ብቻ

©eyobed

👆አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና- አደገኞቹ 👆
👉👉 @coffeefc 👈👈
👉👉 @bunnafc 👈👈
ጊዜው 1986 ነው ::

በወቅቱ በአንድ ቀን ሶስት ጨዋታ ነበረ ይደረግ የነበረው የመጀመሪያውን ጨዋታ በትክክል አላስታውስም ሁለተኛው ጨዋታ ግን ቡና ገበያ ከ ክራይ ቤት 2-2 የተጠናቀቀ ግሩም ጨዋታ ነበረ። የእለቱ የመጨረሻ ጨዋታ ቢራን ከ እርሻ ሰብል ያገናኘው እና በቢራ 1-0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ነበረ።

ጨዋታው ተጠናቆ ጋሼም ከጓደኞቻቸው ተሰናብተው ወደ ቤት ስናመራ አንድ ጥያቄ ጠየቁኝ እንዴት ነበረ ጨዋታዎቹ ብለው? እኔም አሪፍ ነበረ በጣም ደስ ይላል ሚሊዮን በጋሻው እና ሙልጌታ ከበደ ተመችተውኛል አልኩ (በተደጋጋሚ ሲጠራቸው ስማቸውን ስለያዝኩ) በመቀጠል እኔም ፈራ ተባ እያልኩ ጋሼ እኔ ግን ዛሬ ባየሁት ከሆነ ቡኒዎቹን ነው መደገፍ የምፈልገው አልኩ 😔 ሌላ ወሬ ሳናወራ ቤት ደረስን የኔና የጋሼ የስታዲየም ጉዞ በአንድ ቀን ለዘለዓለም ተቋጨ 🤚

ልቤን አሸንፎት አደገኛው ቡና
ስምክን ሳላነሳው ስውል ይለኛል ቅር

በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብሆን የኔ ቡና ቢራን ሲያሸንፍ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም!!

#ቡና_ገበያ_የዘር_ሀረግ

📷 Gediyon Seyoum ገፅ የተወሰደ።
ደሱ ከማን አንሼ ✍️

አረንጓዴ ወርቅ ኢትዮጵያ ቡና-አደገኛ
💛🤎@coffeefc💛🤎
💛🤎@coffeefc💛🤎