የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
992 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በቅድሚያ የረዳን ፈጣሪ ይመስገን
እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ,!

በደቡብ ኮሪያ ሴኡል ከተማ የ2024 ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ ሽልማት ከ72 ሀገሮችን እና ከ115 አቻ ከተሞች አስተዳደር ከንቲባዎች መካከል ምርጥ የአመራር ሸልማት በማግኘታችን በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

ይህ ያስመዘገብነው ውጤት በከተማችን በተሰሩ እና በህዝባችን ተሳትፎ እና ቅንጅት የተገኘ ውጤት በመሆኑ ለዚህ ወጤት መገኘት አስተዋፅኦ ያደረጉ አካላትን ሁሉ እያመሰገንኩ፣ በደቡብ ኮሪያ 2024 ሴኡል ስማርት ሲቲ ሊደርሺፕ የእውቅና ሸልማት ስለተበረከተልንም እናመሰግናለን።

ለህዝባችን ሰርተን በምናገኘው እውቅና ሁሉ ተመስጋኙ ሁሌም ከጎናችን በመሆን የልማቱ ዘዋሪ እና ተጠቃሚ የሆናችሁ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናችሁን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ።
በድጋሚ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባረክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ሲፈጥር የነበረው የጦር ሃይሎች አደባባይ ድልድይ ስር ህገ-ወጥ ንግድ መፅዳቱ ተገለፀ

03/02/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በጦር ኃይሎች አደባባይ ድልድይ ስር የነበሩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ቦታውን ለእግረኛ ምቹ በማድረግ ህገወጥነት እንዲቀነስ ማድረጉን የክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አስታወቀ።

ክፍለ ከተማው ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ተወካይ አቶ አብረሀም የአካባቢው ገጽታ ሲያበላሽ፣ መንገድ ሲያጨናንቅና የትራፊክ አደጋ ሲፈጥር የነበረውን ችግር አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ቦታውን በማጽዳት ለእንቅስቃሴ ምቹ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል ።

የኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 9 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛ ካራ እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ቦታው ላይ ህገወጥ ንግድ በሰፊው የነበረበት በመሆኑ የእግረኛ መንገድና ድልድይ ውስጥ ከፍተኛ የመንገድ መጨናነቅ ሲፈጥር የነበረው መሆኑ ገልፀዋል።

በተግባሩ የተሳተፉ የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ በአዋጅ በተሰጣቸው ሀላፊነት መሰረት የተሰራው ልማት ለታለመለት አላማ እንዲውል ደንብ የማስከበሩን ስራ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው ከዚህ በፊት ቦታው ህገወጥ ንግድ እግረኛ ተሽከርካሪ ለመተላለፍ ሲቸገሩ እንደነበር ገልፀው አሁን በነፃነት እንድንሄድ ላደረጉት ለደንብ ማስከበር አባላት አመስግነዋል።

ዘገባው:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ኦፊሰሮች 17ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን እየተከበረ ይገኛል

       ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም

ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ለሉዓላዊነታችን ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚከበረው የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በክፍለ ከተሞች ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኦፊሰሮች ወታደራዊ ሰልፍ ታጅቦ እየተከበረ ይገኛል ።
ባለስልጣኑ ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የኦፊሰር የአቅም ግንቦት ስልጠና በተቀመጠው ፕሮግራም መሰረት በስኬት አጠናቀቀ

04/02/2017ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ለሚገኙ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቋል።

በሶስት ቀን በቆየው ስልጠና ለኦፊሰሩ በስነምግባርና ጸረ ሙስና፣በስነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 3/2015ዓ.ም ላይ ፣ በተሻሽው በደንብ ቁጥር 167/2016ዓ.ም ፣ ፣ በመረጃ አያያዝና ትንተና ፣ በደንብ ቁጥር 167/2016 አና የሀገር ፍቅር ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል ።

በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉሉ በስልጠናው ማጠቃለያው ተገኝተው ስልጠው ከኦፊሰሩ የዕለት ከዕለት ተግባር ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ግንዛቤ የሚጨመር መሆኑ በመግለፅ ቀጣይነት ያለው መሆኑ ጠቁመዋ።

ስልጠናው የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በስነምግባር የታነጹ እንዲሆንና በተቋሙ ሁለንተናዊ ለውጥ አንዲያመጡና በተሰማሩበት ቦታ ሁሉ ህብረተሰቡን በቀናነት እንዲያገለግሉ የተዘጋጀ የአቅም ማጎልበቻ መሆኑን የስልጠናው አስተባባሪ ወሮ ላቀች ሀይሌ ተናግረዋል ።

በስልጠናው ተሳትፊ የነበሩት ኦፊሰሮች ስልጠናው ራሳቸውን ከብልሹ አሰራር በማራቅ የተቋሙን ግብ ለማሳካት ያለቸውን አቅም በመጠቀም በትጋት እንደሚሰሩ ግንዛቤ መፍጠሩ ገልፀዋል ።

ስልጠናው በተለይ ከስራችን ጋር የተያያዙ ህግና መመርያን እንድናውቅና የምናውቃቸውን በስራችን አጠናክረን እንድንቀጥልና አሰራሩን ተረድተን በስራ ላይ ለሚገጥሙን የአሰራር ክፍተቶችን ለመሙላት አቅም ፈጥሮልናል ብለዋል ፡፡

ባለስልጣኑ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች እየሰጠ ያለው ስልጠና ይበል የሚሰኝና ለኦፊሰሩ መብትና ግዴታውን በማወቅ ስራውን እንዲሰራ፣የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለማጠንከር ግንዛቤ የተጨበጠበት መሆኑና ገልፀዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከስልጠናው ተሳታፊዎች በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በከተማውና በክፍለ ከተማው ሀላፊዎችና ተወካዮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

ዘገባው ፦ የአዲስ አባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።