የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.22K subscribers
2.27K photos
5 videos
1 file
56 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ጉድጓድ ውስጥ የወደቀን መንገደኛ በማንሳት መልካም ተግባር ላከናወኑ ኦፊሰሮች የእውቅና ሽልማት ሰጠ

07/02/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን " በጎነታችን የማንነታችን መገለጫ የተቋማችን ድንቅ ተግባር ማሳያ ነው" በሚል መሪ ቃል በጎ ተግባር ላከናወኑ የአቃቂ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለሶስት ኦፊሰሮች የእውቅና ሽልማት መርሐ ግብር አካሂዷል ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ከሚሰራው የደንብ ማስከበር ስራዎች በተጨማሪ መልካም ስነምግባርና ቅን ልብ ያላቸውን ኦፊሰሮች የተቋሙን ገጽታ በመገንባት ለሌሎች አርአያ መሆን በመቻላቸው እንደ ተቋም እውቅና መሰጠቱን ገልጸዋል ።

አክለውም በቀጣይ በስነምግባር በመታነጽ የደንብ መተላለፍ ተግባሮችን በመከላከል ትኩረት እያደረግን ውጤታማ እንድንሆን አደራ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በመድረኩ የተገኙት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሜጀና ደንብ ማስከበር በ7/24 የስራ ባህል በመስራት በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ከማስቻሉም በላይ ቅን ልቦና ባላቸው ኦፊሰሮች አማካኝነት የተቋሙን መገንባት ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል ።

በዚህ በጎ ተግባር ላይ ተሳትፋችሁ ለሌሎች በርካታ ዜጎች ምሳሌ ስለሆናችሁ በራሴ እና በክ/ከተማው ስም ከፍተኛ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አባል የሆኑት ኦፊሰር ተስፋሁን እነ ኦፊሰር ሌንሳ ባከናወኑት በጎ ተግባር አማካኝነት እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ መልካም ተግባር በማሰራጨት ኦፊሰር ይርጋለም የተቋም ግንባታ ስራ በመስራታቸው በጋራ ተሰብስበን የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅና የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ በተገኙበት እውቅና ለመስጠት በዛሬው ዕለት ተገኝተናል ሲሉ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂርፓሳ ተናግረዋል ።

በመድረኩ ቅን ልቦና ላላቸው ኦፊሰሮች ላደረጉት መልካም ተግባር የስማርት ስልክ በስጦታ መልክ ተበርክቶላቸዋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ የእውቀት ሽግግር መድረክ የግጭት ማስተዳደር ስልትን እውቀት አጋራ

  10/02/2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ግጭትን የማስተዳደር ስልት(conflict management styles) በሚል ርዕስ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት እውቀትና ልምድ ተጋርቷል፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሰራተኛው ጤታማ ስራ በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እንደቤተሰብ እየተማማርን መልካም ምኞት በመለዋወጥ እርስ በእርሳችን ምንማማርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበትና የተቋም ግንባታችን የምናጠናክርበት  መድረክ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል ።
በዕለቱ የባለስልጣኑ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ካላቸው ረጅም ልምድ በመነሳት የራሳቸውን የህይወት እና የስራ ተሞክሮና ልምዳቸውን ለሰራተኞች አስተማሪ በሆነ መልኩ አጋርተዋል።

በተጨማሪም ኮለኔል አድማሱ ግጭትን የማስተዳደር ስልት ( conflict management styles )በሚል ለሰራተኛው በተዘጋጀ በሰነድ እውቀት አጋርተዋል ።

ግጭትን አንዱ በሌላው ድርጊት ወይም ግቦች የራሱን ጥቅም አደጋ ላይ ይጥላል ብሎ በሚያምንበት ጊዜ በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚፈጠር አለመጣጣም መሆኑ በሰነዱ ተገልጿል ።

ራስን ሁል ጊዜ በዕውቀት ማዳበር ፣ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ጋር መልካም ግንኙኘት መኖር እንደሚገባና ስራን በትብብር  በአንድነት  መስራት ዉጤታማ እንደሚያደርግ በመድረኩ ገልጸዋል ፡፡

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ  የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳሬክቶሬት ነው፡፡
👍4