የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
995 subscribers
1.5K photos
4 videos
1 file
51 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመግታት ባለሙያን በእውቀትና በስነ-ምግባር ማነፅ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

09/02/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2ኛ ዙር ሙያዊ ተላብሰው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ከ2100 በላይ ለፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች የስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 3/2015 እና በፀረ ሙስና ላይ የአቅም የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።

ባለስልጣኑ ለመሚያስተዳድራቸው ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስነ-ምግባር መመሪያ እና ብልሹ አሰራር በሀገር ላይ የሚያደርሱ ጉዳቶች በተመለከተ ስልጠና በመስጠትና ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በብልሹ አሰራር ተግባር ውስጥ ገብተው የተገኙ ኦፊሰሮች ላይ ጠንከር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

የባለስልጣኑ የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመግታት ባለሙያን በእውቀትና በስነ-ምግባር ማነፅ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ሰልጣኞች በሰለጠኑት መሰረት ህብረተሰቡን በመመሪያው መሰረት በሙያዊ ስነምግባር ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

ስልጠናው በሦስት ዙር የሚሰጥ ሲሆን መጀመሪያው በተሰጠው የስነ-ምግባር መመሪያ ስልጠና 2000በላይ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠናው የወሰዱ ሲሆን በቀጣይ 3ኛ ዙር ለ2100 ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ዘገባው ፦ የአዲስ አባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።