ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ
15/11/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማችን አዲስ አበባ የደረሰችበትን እድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ በተሰሩ የአረንጓዴ እና መዝናኛ የልማት ስፍራዎች ላይ በህገ ወጥ መንገድ ደረቅ እና ፈሣሽ ቁሻሻ አወጋገድ ላይ ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች ላይ የቅጣት እርማጃዎች መወሰዱን ተገለፀ ፡፡
እርምጃው የተወሰደው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቸርቸር ጎዳና አካባቢ የጽዳት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት/ማህበር/ የሆነው ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት 20,000 ብር የተቀጣ ሲሆን በዛው ወረዳ በፍቅር ባርና ሬስቶራንት የ50,000 ብር በመቅጣት የቆሸሸውም ቦታ እንዲያጸዱ ተደርጓል፡፡
በተያያዘ ዜና በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ 50,000 ተቀጥቷል ፡፡
ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እራሱን ከቅጣት እየጠበቀ የተለያዩ የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማውን በማድረስ የከተማዋን ውበት እና ገጽታ በመገንባት የየድርሻውን እንዲወጣ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል
ዘገባው፡- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሮክቶሬት

❤1
ባለስልጣኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ መፈራረም እና የ2016 እቅድ አፈጻጸም የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ
ሀምሌ 16/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በ2017 በጀት ዓመት በቅንጅት ለመስራት በታቀዱት ተግባራት ላይ በመወያየት የስምምነት ስነድ ስነ-ስርዓት እና የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የእውቅና ሽልማት ፕሮግራም አካሄደ ።
በፕሮግራሙ የሠላም፣የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ፣ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣የባለሥልጣኑ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የማዕከሉ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ፣የባለስልጣኑ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለስልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት ሰፊ እቅዶችን በማቀድ በከተማዋ ከሚገኙ 23 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት አብሮ በመሰራት የጋራ እቅድ በማውጣትና በተለያዩ ጊዜያቶች ሰራዎች በመገምገም ውጤታማ ስራዎችን መከናወኑን ገልፀዋል ።
አክለውም ተቋሙ ባ2016 በጀት ዓመት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የተቋም ግንባታ ሰራውን በማጠናከር ፣ የተቋሙን ሰራና እንቅስቃሴዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ ሰራ በመሰራት ፣ የአመራር ክህሎትን ለማሳደግ ለክ/ከተማ እና ለወረዳ ኃላፊዎች የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት እና ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የክህሎት እና የስነምግባር ስልጠና እና የወታደራዊ ሰልጠና በመሰጠቱ ገልፀው በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመወገቡ አካላት የእውቀናና ሽልማት ማድረግ መቻሉ ለቀጣይ ስራዎች ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ከባለድርሻ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት የተዘጋጀው የ2017 በጀት አመት እቅድ ሰነድ እና የ2016 በጀት ዓመት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የክ/ከተማ እና የማዕከልየምዘና ሂደት በባለስልጣኑ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ቀርቧል ።
የእለቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር የሠላም፣ የፍትህና የመልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ እንደተናገሩት ተቋሙ በየጊዜዉ እያደገና የተሻለ አአፈጻጸም በማስመዝገብ ከተማችንን እንደ ስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ እየከናወነ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ተቋሙ የቅንጅት ስራዎችን በማጠናከር በጋራ መስራት የተሻለ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ካከናወናቸው ሰራዎች በመገንዘብ አጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል።
ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በመድረኩ ከተገኙ የባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት በጋራ ለመስራት የትስስር ሰነድ በመፈራረም በተጨማሪም ተቋሙ በስሩ ካሉ ዘርፎች እና ከክፍለ ከተማዎች ጋር የስምምነት ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል ።
በመጨረሻም በ2016በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የክ/ከተማ እና የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ፣ የማዕከል ዳይሬክቶሬት የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በዚህም መሰረት ከ 11 ክ/ከተማ ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ
2ኛ የካ ክፍለ ከተማ
3ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሲሆኑ
ከ119 ወረዳዎች ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 2
2ኛ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 2
3ኛ ንፋስ ሰልክ ላፍቶክ/ከተማ ወረዳ 10
ከማዕከል ዳይሬክቶሬት ከ1ኛ አስከ 3ኛ የወጡት
1ኛ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት
2ኛ የስልጠናና ጥናት ዳይሬክቶሬት
3ኛ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
በመሆን እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👍1