የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለአማራ ክልል ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

ሀምሌ 18/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች በሰነድ እና በጉብኝት በተደገፈ መረጃ ለአማራ ክልል የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በልምድ ማጋራቱ ወቅት የተቋሙ አደረጃጀት እና ያጋጠሙ ችግሮች ከሚመለከተው አካል በመነጋገር የተፈታበት ሂደት እና ተቋሙ በማጠናከር የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ሂደት በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ በበኩላቸው የተቋሙን አሰራሮች እና ተሞክሮዎች የገለጹ ሲሆን የአማራ ክልል አስተዳደር ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት ገልጸዋል፡፡

አማራ ክልል የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከከተማ አስተዳደሩ እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና በክልላቸው ልምዱን ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2
ባለስልጣኑ በተሰሩ የልማት  የደንብ መተላለፍ በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ የሚወስደው እርምጃ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ ገለፀ

ትናንት ሀምሌ 19/2016 በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ ግለሰቦች በደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ክትትልና ህዝቡ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በደንብ ጥሰት ተቀጥተዋል።

በዚህም መሰረት ፦                       
               
1.ቦሌ ክ/ከተማ

የኮቨርስቶን መንገድ የሠበረ  አንድ ተሽከርካሪ  5,000  ብር ተቀጥቷል። እንዲሁም በዚሁ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ተረፈ ምርት (ቆሻሻ) በዋና መንገድ ላይ ያወረደ ተሽከርካሪ  50,000 ብር ተቀጥቷል።

2. ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሞተር ሳይክል በእግረኛ መንገድ ላይ ያቆመ ግለሰብ 3,000 ብር ተቀጥቷል።

አካባቢያቸዉን ያቆሸሹ ሁለት ሱቆች በአጠቃላይ 20,000 ብር ሲቀጡ፣ አከባቢውን ያቆሸሸ አንድ የፅዳት ማህበር 20,000 ብር ተቀጥቷል።

3. ልደታ ክ/ከተማ ደግሞ አንድ ተሽከርካሪ መንገድ የማበላሸት ተግባር በመፈፀሙ 50,000 ብር ተቀጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልማት ስራም ሆነ በመሰረተ ልማት ጥበቃ ዙሪያ ከከተማው ነዋሪ ጋር እጅና ጓንት በመሆን  ፅዱ፣ ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች አዲስ አበባን እውን ለማድረግ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
👍14👏3