ኘሬስ ሪሊዝ
ባለስልጣኑ "የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል 6ተኛውን ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በነገው ዕለት ሊያከናውን መሆኑ ተገለፀ
ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በነገው እለት 6ተኛውን ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር የከተማው እና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉትን የባለስልጣኑ ሀላፊዎች እና ከ6000 /ስድስት ሺህ/ በላይ ሠራተኞች የሚሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ይከናወናል።
መርሀ ግብሩ በነገው እለት በሀምሌ 06/2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መቅዶኒያ የአጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አካባቢ በተዘጋጀው ቦታ ሀገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞችን ሊተክል መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለ5 ተከታታይ ዓመታት በርካታ የፍራፍሬና ሀገር በቀል ችግኞችን ሲተክልና ፅድቀቱንም ሲከታተል እንደነበረ አስታውሰው፤ለአሁኑ 2016 በጀት ዓመት መርሃ ግብር በርካታ የፍራፍሬና የዛፍ ችግኞች ለመትከል የችግኝ ግዢና የጉድጓድ ቁፋሮ ቅድመ ዝግጅት ቀደም ብሎ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ ከጠዋቱ 12:30 ሠዓት ጀምሮ በነቂስ እንደሚከናወን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ዜና ጥቆማው:- የአአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍8