"ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” ሀገር አቀፍ የጎዳና ሩጫ ውድድር እየተካሄደ ነው
ሰኔ 30/2016 ዓ.ም
ሰላምን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የ6 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው።
ውድድሩ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!” በሚል መሪ ሀሳብ ከማለዳ 12 ሠዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋና በሌሎች ዋና ዋና የክልል ከተሞች እየተካሄደ ነዉ ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው መርሐ ግብር ታዋቂ አትሌቶችና ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እየተሳተፉ ነው።

👍9👏2
ባለስልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተገለፀ
04-11-2016
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ከማዕከሉ ሰራተኞች ጋር የባለስልጣኑ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት በ2016 በጀት ዓመት በእቅዳችን መሰረት በከተማችን የሚታዩ የደንብ ጥሰቶች በመከላከል፣በመቆጣጠር እና እርምጃ በመውሰድ የተቋም ግንባታን ለማጠናከርና አመራሩንና ሰራተኞችን ለማብቃት በርካታ ተግባራትን በማከናወን በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ መቻሉ ገልፀዋል ።
አክለውም ኃላፊው የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ለቀጣይ የ2017 በጀት ዓመት ለምናከናውነው ሰራዎቸ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ሲሆን የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል በስራዎች ውስጥ የታዩ ክፍተቶችን እና መሰናክሎችን ለማሻሻል የውይይት መድረኩ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
በእለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል ።
በሪፖርቱ በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተፈጸሙ ተግባራት ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ መፍትሔዎች ቀርበዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ የበላይ ሀላፊዎች ምላሽና አስተያየት ተሰጥቶ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

Facebook
A.A City Administration Code Enforcement Authority | Addis Ababa
A.A City Administration Code Enforcement Authority, Addis Ababa, Ethiopia. 4,982 likes · 898 talking about this. Non profit organization (service provider organiza
ኘሬስ ሪሊዝ
ባለስልጣኑ "የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል 6ተኛውን ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በነገው ዕለት ሊያከናውን መሆኑ ተገለፀ
ሐምሌ 05/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ" በሚል መሪ ቃል በነገው እለት 6ተኛውን ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር የከተማው እና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉትን የባለስልጣኑ ሀላፊዎች እና ከ6000 /ስድስት ሺህ/ በላይ ሠራተኞች የሚሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር ይከናወናል።
መርሀ ግብሩ በነገው እለት በሀምሌ 06/2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ መቅዶኒያ የአጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አካባቢ በተዘጋጀው ቦታ ሀገር በቀል እና የፍራፍሬ ችግኞችን ሊተክል መሆኑን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ለ5 ተከታታይ ዓመታት በርካታ የፍራፍሬና ሀገር በቀል ችግኞችን ሲተክልና ፅድቀቱንም ሲከታተል እንደነበረ አስታውሰው፤ለአሁኑ 2016 በጀት ዓመት መርሃ ግብር በርካታ የፍራፍሬና የዛፍ ችግኞች ለመትከል የችግኝ ግዢና የጉድጓድ ቁፋሮ ቅድመ ዝግጅት ቀደም ብሎ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብሩ ከጠዋቱ 12:30 ሠዓት ጀምሮ በነቂስ እንደሚከናወን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።
ዜና ጥቆማው:- የአአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።

👍8