ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ
15/11/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማችን አዲስ አበባ የደረሰችበትን እድገት ደረጃ ባገናዘበ መልኩ በተሰሩ የአረንጓዴ እና መዝናኛ የልማት ስፍራዎች ላይ በህገ ወጥ መንገድ ደረቅ እና ፈሣሽ ቁሻሻ አወጋገድ ላይ ደንብ የተላለፉ ግለሰቦች ላይ የቅጣት እርማጃዎች መወሰዱን ተገለፀ ፡፡
እርምጃው የተወሰደው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ቸርቸር ጎዳና አካባቢ የጽዳት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት/ማህበር/ የሆነው ይደምቃል ወርቅነሽና ጓደኞቿ ቆሻሻን በአግባቡና በወቅቱ ባለማንሳት 20,000 ብር የተቀጣ ሲሆን በዛው ወረዳ በፍቅር ባርና ሬስቶራንት የ50,000 ብር በመቅጣት የቆሸሸውም ቦታ እንዲያጸዱ ተደርጓል፡፡
በተያያዘ ዜና በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ኦላ ኢነርጂ የነዳጅ ማደያ ያመነጨውን ቆሻሻ በአግባቡ ባለማስወገዱ 50,000 ተቀጥቷል ፡፡
ባለስልጣኑ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እራሱን ከቅጣት እየጠበቀ የተለያዩ የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማውን በማድረስ የከተማዋን ውበት እና ገጽታ በመገንባት የየድርሻውን እንዲወጣ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡
የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል
ዘገባው፡- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሮክቶሬት

❤1