የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.1K subscribers
1.79K photos
4 videos
1 file
53 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት ዓመቱ ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በቅንጅት ያከናወናቸውን ስራዎች ገመገመ

11/10/2016ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሰላምና ፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ እና አባላት፣የባለስልጣኑ አመራሮች እና የባለድርሻ ተቋማት ሀላፊዎች በተገኙ በዛሬው ዕለት ውይይት አካሄደ።

የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት በዛሬው ዕለት በአመቱ በጋራ በመሆን የሰራናቸውን ስራዎች የምንገመግምበት መድረክ መሆኑ ተናግረዋል።

አክለውም ስራ አስኪያጁ እንዳሉት ከተማችንን ውብ፣ፅዱ እና ማራኪ ለማድረግ እንዲሁም የህዝብ ሀብት የሆነውን መሬት ከመጠበቅ አንፃር በዘንድሮ ዓመት በርካታ ውጤታማ ስራዎችን መሰራታቸውን ገልፀዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን መድረኩን የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት የሰላምና ፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ዶ/ር መሀመድ ገልማ እና የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ መርተውታል።

ባለድርሻ አካላትም በዚህ ልክ ውይይት በማድረጋችን ጥሩና ቀጣይ ውጤት በማምጣት በስምምነት ሰነዱ መሰረት ሊሰራ ይገባል ነገር ግን ይህ ሳይሆን ሲቀር ተጠያቂነት ማሳረፍ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም በተከበሪ ዶ/ር መሀመድ ገልማ እና በባለስልጣኑ አመራሮች ከባለድርሻ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማጠቃለያ እንዲሁም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
👍9
ባለስልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

ሰኔ 12/2016Vዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸሙ ከባለስልጣኑ የማዕከል ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ጋር ውይይት አደረገ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እንደገለጹት ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ በተሰጠው ተልዕኮ መሰረት በከተማችን የሚታዩ የደንብ ጥሰቶችን ከማዕከል አስከ ወረዳ በመናበብ ባለድርሻ አካላት እና ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።

አያይዘውም ተቋሙ ከተማችን እንደስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ የራሱን አስተዋፅኦ ማድረግ መቻሉንና በቀጣይም ሰራዎቻችን በማጠናከር የደንብ ጥሰቶች ከዚህም በተሻለ እንዲቀንስ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

ባለስልጣኑ ከሚሰራው ዋና ዋና ተግባራት ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ መልካም ተግባር ማድረጉንና ቢሮውን ለሰራተኞች እና ለተገልጋዩ ምቹ ማድረግ መቻሉን ኃላፊው ተናግረዋል ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

በሪፖርቱም በበጀት ዓመቱ ታቅደው የተፈጸሙ ክንውኖች ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራቶች ፣ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተከናወኑ ተግባራትና መፍትሔዎች በሰነድ ቀርበዋል።

በሰነዱ በ2016 በጀት ዓመት ቅድመ መከላከልን መሠረት ያደረጉ የግንዛቤ ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን በከተማችን መሬት ባንክ የገቡ መሬቶች በመጠበቅ ምንም አይነት ወረራ እንዳይፈጸም መከላከል መቻሉ ተገልጿል ።

በመጨረሻም የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሽቴ እና የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ከተሳታፊዎች በቀረበው ሀሳብ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መልስ በመስጠትና የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የትኩረትን ነጥቦች በማስቀመጥ የተዘጋጀው መድረክ ተጠናቋል ።
👍1
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ

15/10/2016ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ላደረጉ አካላት የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም አካሄደ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበጀት ዓመቱ በክፍለ ከተማው ከደንብ ማስከበር ተቋም ጋር በርካታ የፀጥታ እና የደንብ ማስከበር ተግባራት መከናወናቸውን በመግለፅ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም ክ/ከተማው የንግድ እና የሰዎች እንቅስቃሴ የሚበዛበት በመሆኑ በቀጣይ ብዙ የሚቀሩ ስራዎች ስላሉ ለማስተካከልና በቀጣይ አብሮ ለመስራት እንዲሁም ለፅ/ቤቱ በሚያስፈልገው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸው ገልፀዋል።

በመድረኩ የእንኳን መጣቹ ንግግር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ደረጄ ነገሮ በበጀት አመቱ በደንብ መተላለፎች በግንዛቤ እና በቁጥጥር ተግባራት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ፕሮግራሙ የተዘጋጀው በ2016 በጀት አመት ለተሰሩ ውጤታማ ስራዎች አመራሮች እና ኦፊሰሮች ለማመስገን የተዘጋጀ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም መሆኑና በቀጣይ በጀት ዓመት በጥንካሬ ያገኘናቸውን ለማስቀጠል ክፍተቶቹ ለመሙላት መነቃቃትን ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ገልፀዋል።

የመድረኩ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በንግግራቸው በከተማችን ደንብ መተላለፎች ከመከታተል እና ከመቆጣጠር ባሻገር እንደስሟ አዲስና ውብ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል።

በመጨረሻም በበጀት አመቱ በፅ/ቤቱ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና በመስጠት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።
👍5