የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.86K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
በአዲስ አበባ የታንዛንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ መታሰቢያ ሐውልት ቆመላቸው

የካቲት 10/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የመታሰቢያ ሐውልቱ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ በሚገኘው የአፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ፊት ለፊት መገንባቱ ተጠቅሷል።

“የታንዛንያ አባት” እየተባሉ የሚጠሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት እንዲላቀቁ በነበረው ትግል ውስጥ ስማቸው በቀዳሚነት ከሚነሱ ሰዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

ታንዛንያ (በወቅቱ ታንጋኒካ) ከብሪታኒያ ቅኝ ግዛት እንድትወጣ ታንጋኒካ አፍሪካን ዩኒየን(Tanganyika African Union) የተሰኘ ፓርቲ በማቋቋም ትግል አድርገዋል።

ጁሊየስ ኔሬሬ “ያለ አንድነት አፍሪካ ምንም መጻኢ እድል የላትም” በሚለው ታዋቂ አባባላቸው ይታወቃሉ።

ትግሉም ፍሬ አፍርቶ እ.አ.አ በ1961 ታንዛንያ ከቅኝ ግዛት የወጣች ሲሆን ኔሬሬም እ.አ.አ በ1964 የመጀመሪያው የታንዛንያ ፕሬዝዳንት በመሆን እስከ እ.አ.አ 1985 አገልግለዋል።

ጁሊየስ ኔሬሬ መምህር (ሙዋሊሙ) የሚል ቅጽል ስም ያላቸው ኔሬሬ የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ ነበሩ።

በስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር መሐመድ ኦውልድ ጋዙዋኒ፣ የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን እንዲሁም የተለያዩ የአፍሪካ አገራት መሪዎች፣ የቀጣናዊ ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
👍3
37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

AMN-የካቲት 11/2016 ዓ.ም
37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 44ኛው የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማን ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጠናከር፣ የትራፊክ ፍሰቱን የተሳለጠ ለማድረግ ግብረ-ኃይሉ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራቱ ለተገኘው ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብሏል መግለጫው።

ለጉባኤው የመጡ እንግዶች በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ እጀባና ጥበቃ ማድረጉን የገለፀው የጋራ ግብረ-ኃይሉ መሪዎቹም በሰላም ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ መሆናቸውን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

መላው የሀገራችን ሕዝብ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች እንግዶችን በክብር ከመቀበል ጀምሮ በየሆቴሎቹ ደረጃውን የጠበቀ መስተንግዶ በማድረግ፣ የሚያልፉባቸው መንገዶች ሲዘጉ በትዕግስት ቅድሚያ ሰጥቶ በማሳለፍ፤ ከፀጥታ ኃይሉ የሚሰጠውን መመሪያ በቅንነት በመቀበል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን በማሳየታቸው፤ የፀጥታና ደህንነት አመራሮችና አባላትም በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመሩ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመወጣታቸው ጉባኤው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላምና በስኬት በመጠናቀቁ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ በመግለጫው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡

አዲስ አበባ፣
የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ.ም
የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል
👍3🔥1
ባለስልጣኑ ከ 2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶች
ገንብቶ በዛሬው እለት ለባለቤቶቹ ቁልፍ አስረከበ።

የካቲት 12/2016 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኮልፌ፣በንፍስ ስልክ፣እና በልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤቶች በጋራ በመሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ላይ የ3 አቅመ ደካማ አባዎራዎች 5 ክፍል ቤት በመገንባት በዛሬው ዕለት የባለስልጣኑ የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት አስመረቀ።

የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክላስተሩን እያስተባበሩ ያሰሩት የኮልፌ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ እንዳሉት የተገነባው መኖሪያ ቤት ከ 2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል

አቶ አበራ በመክፈቻ ንግግራቸው ባለስልጣኑ በክረምት የጀመረው የሰው ተኮር በጎ ተግባራት በበጋም አጠናክሮ መቀጠሉን እና በዚህ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፍ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊዎች ፣ ኦፊሰሮች እና ባለሀብቶችን አመስግነዋል ።

አክለውም የደንብ ጥሰቶችን እንዳይከሰት አስቀድሞ የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት እና ተከስቶም ሲገኝ አስፈላጊውን እርምጃ እየተወሰደ በዛው ጎን ለጎን በሰው ተኮር ስራዎች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በተለያዩ የበጎ ስራዎች ተቋማችን እንደሚሳተፍ አስታውቀው አሁን ያሰረከብነውን የቤት ግንባታ በመፍጠንና በመፍጠር ላይ ሆነን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን ለቤት ባለቤቶቹ እንዳስረከቡ አስታውቀዋል::

የዕለቱ የክብር እንግዳ ሆነው የተገኙት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ሀብታሟ ባልቻ እንዳሉት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ እንደዚህ አይነት ሰው ተኮር ተግባራት ላይ ሲሳተፍ የመጀመሪያው እንዳልሆነ እና በዛሬው ዕለት ለ 3 አባወራዎች ቤት ገንብቶ ማስረከቡ የሚበረታታ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

በዛሬው እለት የቤት ቁልፍ ከተረከቡት የቤት ባለቤቶች አቶ ባዮ ደሜ እንዳሉት ከዚህ ቀደም ክረምት በመጣ ቁጥር በችግር ሲኖሩ እንደነበር ገልፀው አሁን በተደረገለቸው በጎ ተግባር እንደተደሰቱ ገልፀው ለባለስልጣን መስሪያ ቤት እና ተግባሩ ላስተባበሩ አካላት ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በስራው ላይ ጉልዕ አስተዋፅኦ ላደረጉ ክፍለ ከተሞች እና ግለሰቦች የምስጋና የምስክር ወረቀትና ስጦታ በማበርከት ለቤቱ ለባለቤቶቹ ቁልፍ በማስረከብ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement

የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
ባለስልጣኑ ከ 2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶች
ገንብቶ በዛሬው እለት ለባለቤቶቹ ቁልፍ አስረከበ።

የካቲት 12/2016 ዓ.ም
*አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኮልፌ፣በንፍስ ስልክ፣እና በልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤቶች በጋራ በመሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ላይ የ3 አቅመ ደካማ አባዎራዎች 5 ክፍል ቤት በመገንባት በዛሬው ዕለት የባለስልጣኑ የክፍለ ከተማ አመራሮች በተገኙበት አስመረቀ።

የዕለቱን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክላስተሩን እያስተባበሩ ያሰሩት የኮልፌ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ እንዳሉት የተገነባው መኖሪያ ቤት ከ 2.2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ገልፀዋል።

አክለውም የደንብ ጥሰቶችን እንዳይከሰት አስቀድሞ የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት እና ተከስቶም ሲገኝ አስፈላጊውን እርምጃ እየተወሰደ በዛው ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ ስራዎች ተቋማችን እንደሚሳተፍ አስታውቀው አሁን ያሰረከብነውን የቤት ግንባታ በመፍጠንና በመፍጠር ላይ ሆነን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን ለቤት ባለቤቶቹ እንዳስረከቡ አስታውቀዋል።

በዛሬው እለት የቤት ቁልፍ ከተረከቡት የቤት ባለቤቶች አቶ ባዮ ደሜ እንዳሉት ከዚህ ቀደም ክረምት በመጣ ቁጥር በችግር ሲኖሩ እንደነበር ገልፀው አሁን በተደረገለቸው በጎ ተግባር እንደተደሰቱ ገልፀው ለባለስልጣን መስሪያ ቤት እና ተግባሩ ላስተባበሩ አካላት ከፍ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በስራው ላይ ጉልዕ አስተዋፅኦ ላደረጉ ክፍለ ከተሞች እና ግለሰቦች የምስጋና የምስክር ወረቀትና ስጦታ በማበርከት ለቤቱ ለባለቤቶቹ ቁልፍ በማስረከብ ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid

የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement

የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT

የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen

ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ
👍3😁1
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ስለተቋማችን ባለድርሻ አካላት በተመለከተ የታተመው አምድ
👍5
ለመላው የተቋማችን አመራሮች፣ ሰራተኞችና አጋሮቻችን በሙሉ፦

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን በሀላፊነትና ተግባራት በብቃት እየተወጣ ይገኛል።

ሆኖም የተቋሙን እና የከተማ አስተዳደሩ ስም በሚያጠለሽ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት በሶሻል ሚዲያ የተለቀቀውን መረጃ ተቋሙ በማስረጃነት በመያዝ ድርጊቱን የፈፀሙ አካላት በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በሂደት ላይ ይገኛል።

በመሆኑም ማንኛውም አይነት የተቋሙን እና የከተማ አስተዳደሩ ስም የሚያጠለሽ ሀሰተኛ መረጃ በሶሻል ሚዲያ ሲመለከቱ የሦስት ነጥብ ምልክቱን በመጫን ለሶሻል ሚዲያው ሪፖርት እዲያደርጉ ተቋሙን መልዕቱ ያስተላልፋል ።

የደንብ መተላለፎችን በጋራ እንከላከል!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
👍124
የዓድዋ ድል በዓል ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል

የካቲት 22/2016 ዓ.ም
  #አዲስ አበባ

128ኛ የዓድዋ ድል በዓል ዛሬ ፒያሳ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ::

128ኛ የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ መድፍ ተተኩሷል።

የአፍሪካውያን ድል የሆነው  "የዓድዋ ድል " ኢትዮጵያውያን የዛሬ 128 ዓመት በወራሪው የፋሺሽት ጣልያን ጦር ላይ የተቀዳጁት አንፀባራቂ ድል ምክንያት በማድረግ በአሉ በየአመቱ ሲከበር ቆይቷል።

የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓልም ዛሬ ፒያሳ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ፡፡
#አዲስአበባ
#AddisAbaba
#ኢትዮጵያ
በህገ-ወጥ መንገድ ሲሰሩ በነበሩ ስጋ ቤቶች እና ግለሰቦች ላይ እርምጃ ተወሰደ

      27/06/2016 ዓ.ም
      #አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፣ ንግድ ቢሮ እና ከከተማ ግብርና ኮሚሽን ጋር በመሆን በህገ-ወጥ መንገድ ሲሰሩ በነበሩ ስጋ ቤቶች እና ግለሰቦች ላይ ከየካቲት 12 እስከ ከየካቲት 24 በተደረገው የክትትል ስራ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ።

በክትትል ስራው አጠቃላይ በከተማው ከ11 ክፍለ ከተሞች 226 ቤቶች ክትትል ተደረጎባቸው ከነዚህ  ውስጥ ከደረሰኝ እና በህገወጥ እርድ ጋር በተያያዘ 45 ስጋ ቤቶች የታሸጉ መሆኑ ተገልጿል።

በተደረገው የክትትል ስራው  የተለያዮ ለህገወጥ እርድ የተዘጋጁ እንስሳቶች የተወረሱ ሲሆን 5,293 ኪሎ ግራም ስጋ እንዲወገድ ለቄራዎች ድርጀት ገቢ በማድረግ ህግ በተላለፉት ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ እንደ ጥፋታቸው የተቀጡ ሲሆን ከቅጣቱ 450,000 ብር ገቢ ማድረግ ተችሏል።

በህገ-ወጥ እርድ ስጋ ለማህበረሰቡ በማቅረብ የማህበረሰቡ ጤና አደጋ ላይ በሚጥሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ላይ እርምጃው የሚቀጥል መሆኑ  በክትትል አባላቱ ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችን ፎሎው፣ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
የፌስ ቡክ ገፃችን፦
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082525711518&mibextid
የቴሌግራም ቻናላችን
https://t.me/codeenforcement
የዩቱብ ቻናላችን
https://youtube.com/@A.A.C.ACODEENFORCEMENT
የቲክቶክ አካውንታችን
https://www.tiktok.com/@addisababacodeenforcemen
ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ!
የከተማዬን ጽዳት በመጠበቅ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ በሚል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ

የካቲት 30/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች፣ዳይሬክተሮች እና ኦፊሰሮች የተሳተፉበት የጽዳት ዘመቻ "የከተማዬን ጽዳት በመጠበቅ የአመራርነት ሚናየን እወጣለሁ" በሚል በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ ።

በዘመቻው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከተማዋን የጽዳት ተምሳሌት ለማድረግ ህብረተሰቡ ጽዳትን ባህል አድርጎ ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 በተካሄደው የጽዳት ዘመቻ የከተማው እና የክፍለ ከተማዉ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን ከንግግር ባለፈ ስራው በተግባር የምናሳይበት መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉም ህብረተሰቡ ጽዳትን የእለት ተእለት ተግባሩ እንዲያደርገዉ ጠይቀዋል፡፡

አዲስ አበባ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በአይን የሚታዩ ሁለንተናዊ ለዉጦችን እያስመዘገበች ትገኛለችና
ከነዚህ ለዉጦች ዉስጥ ደግሞ ጽዳት ተጠቃሽ ነው ተብሏል ።
👍6