የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.86K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
የአድዋ ድል መታሰቢያ ኢትዮጵያ በሁሉም ተጋድሎ የፀናች ሀገር መሆኗን  የሚያሳይ  መሆኑ ተገለፀ

      የካቲት 2/2016 ዓ.ም
      *አዲስ አበባ*

የአድዋ ድል መታሰቢያ ኢትዮጵያ በሁሉም ተጋድሎ የፀናች ሀገር መሆኗን  የሚያሳይ ነው ሲሉ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ምሁር ተናገሩ፡፡

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ሀላፊና መምህር ተማማ ሐጅአደም( ዶ/ር) ለአዲስ ልሳን ጋዜጣ እንደገለፁት የዓድዋ ሙዚየም ፕሮጀክት በዚህ መልኩ መገንባቱ ያለው ሀገራዊ ፋይዳ ትልቅ ነው። መታሰቢያው የአንድነታችን ተምሳሌት ነው።

ምክንያቱም የዓድዋ ድል ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በእምነት፣ በባህል እና በቋንቋ ሳይለያዩ ከሁሉም አቅጣጫ የተሳተፉበትና ታላቅ መስዋዕትነት ከፍለው ያስገኙት ድል ነው፡፡ በመሆኑም የዓድዋ  ሙዚየም ኢትዮጵያ በሁሉም ተጋድሎ የፀናች ሀገር መሆኗን  የሚያሳይ  እንደሆነ ተናረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቆመችው በሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እና ሁለንተናዊ ማንነቶች ህብረት ነው፡፡ የዓድዋ ድል ደግሞ ለዚህ ትልቅ ተምሳሌት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ይህ ድልና መታሰቢያ የሚያመላክተው ኢትዮጵያ በሁሉም ተጋድሎ የፀናች ሀገር መሆኗን ነው፡፡ የተማረም፣ ያልተማረም፣ ገበሬውም፣ ወንዶችም፣ ሴቶችም…. ሁሉም የተሳተፉበት ነው፡፡

ፕሮጀክቱ  በኢትዮጵያውያን የሚመራ በመሆኑ ከተማችን በኪነ ሕንፃ ጥበብ ከፍ ማለቷን፣ ኢትዮጵያውያን ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በብቃት መስራት እንደሚችሉ የሚያሳይና የጀመሩትን የመጨረስ ብቃት እንዳላቸው የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከስነ ልቦናም አንፃር የሚኖረው አወንታዊ ሚና ከፍ ያለ ስለመሆኑ ተማማ ሐጅአደም (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡

       መረጃው፦AMN ነው።
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን እየጎበኙ ነው

የካቲት 3/2016 ዓ.ም
የዓድዋ ድል መታሰቢያ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ነው።

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓድዋ ድል መታሰቢያን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

በጉብኝቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
👏1
ትስስር ብቻውን ውጤት አይሆንም!
በስሜነህ ደስታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተዘጋጀው አምድ የተወሰደ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዲስ መልክ መደራጀቱን ተከትሎ ባለስልጣኑ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባራት በተሟላ መልኩ ማሳካት ይቻለው ዘንድ የባለ ድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያምናል፡፡

በትስስር ከተሠሩ ሥራዎች ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፣ ከመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በከተማው ውስጥ የሚገኙ መሬቶች ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ በማድረግ በደንብ ተላላፊዎች የሚፈፀሙ መሬት ወረራዎችን የመከላከል እና የመቆጣጠር አቅምን በማሳደግ ውስን የሆነውን የመሬት ሀብት ከደንብ ተላላፊዎች መከላከል ተችሏል፡፡

ከትምህርት ቢሮን ወክለው የመጡት የተቋሙ ሀላፊ ወይዘሮ አበበች የትስስር ስምምነት ተፈራረሞ መቀመጥ ግብ አይሆንም ስለዚህ በቅንጅት በመሥራት አሠራራችን ምን ይመስላል ብሎ መገማገም እንዲሁም መወያየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የመማር ማስተማርን የሚያውኩ ንግድ ቤቶች ከትምህርት ቤቶች እንዲርቁ መደረጉ ጥሩ ሆኖ ሳለ ሁለት መቶ ሜትር ብቻ እንዲርቁ መደረጉ የሚያንስ ስለሆነ ችግር እንዳይፈጥር መመሪያው እንደገና ተፈትሾ የሚስካከልበት መንገድ ቢፈለግ በማለት አንስተዋል፡፡

ከንግድ ቢሮ የተሳተፉት የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን ባለስልጣኑ ላይ እየታዩ ያሉ ለውጦች በጣም አስገራሚ መሆናቸውን ገልጸው በጋራ የሚሠሩ ሥራዎች በጣም አመርቂ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡ ሌሎችም ተሳታፊ ባለድርሻ አካላትም ገንቢ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ መጨረሻም የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተሰጡትን አስተያየቶች እንደግባት በመውሰድ ለቀጣይ ስድስት ወር በተሻለ ሁኔታ ለመተግበር ባለስልጣኑ ተግቶ እንደሚሠራ ቃል በመግባት አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
👍1
ህብረተሰቡ እንደሁልጊዜው ለፀጥታ አካላት ሥራ ተባባሪ እዲሆን ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ በሰላምና በስኬት ለማጠናቀቅ እንዲቻል በሚከናወነው የፀጥታ ስራ እና የትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ እንዲሆን አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀ ፡-
• ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ -ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ -ኤርፖርት
• ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሔራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ ፡-
• ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር -ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶቹ እንግዶች ሲያልፉ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለእንግዶቹ ቅድሚያ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑ እና ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ እያሳሰበ ፡-
• ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር
• መረጃ ለመስጠት በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11፣ 011-5-52-63-03 ፣ 011-5-52-40-77 ፣ 011-5-54-36-78 ፣ 011-5-54-36-81 እንዲሁም 987 ፣ 991 እና 916 ነፃ የስልክ መስመሮችን መጠቀም እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆ ለጉባኤው በሰላም መጠናቀቅ መላው ሠላም ወዳድ ህዝባችን ለሚያደርገው ቅን ተባባሪነት ፖሊስ አስቀድሞ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
👏3👍2
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባዔው "ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ስርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ፣ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው።

በጉባኤው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማህማት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶችና የሕብረቱ ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል።

የመሪዎቹ ጉባኤ የካቲት 6 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም 44ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት በመደበኛ ስብሰባ በተወያየባቸው አጀንዳዎች ላይ በስፋት የሚመክርም ይሆናል።

አህጉራዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ንግድና ትስስር፣ ተቋማዊ ማሻሻያዎች፣ ትምህርት፣ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ ስርዓተ ጾታና ወጣቶችን ማብቃት እንዲሁም የተቋማትና አደረጃጀቶች ምርጫ ውይይት የሚደረግባቸው ዋነኛ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገልጿል።
👍1