የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.12K subscribers
1.87K photos
4 videos
1 file
54 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ለባህርዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ልምዱንና ተሞክሮውን አጋራ፡፡

ጥር 22/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች ለባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን በተቋም አደረጃጀትና በአሰራር በመመሪያ ዙሪያ ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮውን አጋርቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ-አስኪያጅ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በልምድ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ተቋሙ የከተማዋን እና የተቋሙ ገጽታ ለመቀየር በርካታ ስራዎች ማከናወኑን ገልጸው የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ከዚህ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ባለስልጣኑ ላደረገላቸው ቀና ትብብር አመስግነው በቀጣይነት በሚችለው ሁሉ ከጎናቸው እንዲቆም እና እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል።

ምክትል ስራ-አስኪያጅዋ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙ ለማጠናከር በሚያደርገው እንቅስቃሴዎች በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡

ባለስልጣኑ ከዚህ በፊት ለጅማ፣ለድሬዳዋ እና ለሐረር ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ልዑካን ቡድን ያለውን ልምድና ተሞክሮ ማጋራቱ ይታወቃል፡፡

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
ባለስልጣኑ ከተጠሪ ተቋሙ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አደረገ።

ጥር 23/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት የተሰሩ ስራዎችን የክፍለ ከተማ እና የወረዳ የደንብ ማስከበርና የሰላምና ፀጥታና ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተገኙበት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂዷል ።

የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንደገለፁት የከተማው ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ፣ የአደባባይ በዓላት በሰላም እንዲከበር በማድረግ እና የፀረሰላም ሃይሉ ተልዕኮ በማክሽፍና በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ በስድስት ወራት ውስጥ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱ ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን አያይዘው በጀት ዓመቱ 6 ወራት መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን ወረራን እንዳይፈጸም በመጠበቅ፣ በጎዳና ንግድ እና በሌሎች ተግባራቶች ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል ።

በመድረኩ የሁለቱም ተቋማት የስድስት ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በሁለቱም ተቋሞች በ6ወር ውስጥ የተሰሩ ሰራዎችን በጥንካሬና በክፋተት ተለይተው ቀርበዋል።

በመጨረሻም የውይይቱ ተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እና በሻለቃ ዘሪሁን ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት የቀጣይ የሰራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገባው ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Audio
ባለስልጣኑ በግንዛቤ እና በማስጠንቀቂያ ከድርጊታቸው መቆም ባልቻሉት ህገወጦች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።
1👍1
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ተጠየቀ።

24/05/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የመንግስት ሰራተኞች ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና በኤሊያና ሆቴል የተቋሞቹ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት የመጀመሪያው ክፍል ስልጠና ተሰጠ።

የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከእዳ ወደ ምንዳ ለመሸጋገር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በስልጠናው “ሀብት መፍጠር ማስተዳደር እና ገዥ ትርክት” የሚሉ ሁለት የስልጠናው ሰነዶችን ያቀረቡት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ግዛው ሀገራችን የውጭና የውስጥ ፈተናዎች የነበሩባት ነገር ግን አንድነቷን አስጠብቃ በመቀጠል በለውጥ ጎዳና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር ጥረት ማድረግ ላይ የምትገኝ ሀገር ናት ሲሉ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ በበኩላቸው የአንዱን ክፍተት አንዱ እየሞላ የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ በቀረቡት ሰነዶች ላይ በርካታ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን መድረኩን የመሩት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ፍቅሬ ግዛው እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል።

መረጃው:-የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋናዋና ሃሳቦች (ክፍል ሁለት)

1. የብድር አቅርቦትን በተመለከተ
- ባለፉት ስድስት ወራት ከ170 ቢለዮን ብር በላይ ብድር ተሰጥቷል፡፡ ከዚህም ውስጥ ለግሉ ሴክተር የተሰጠው 83 በመቶ ነው፡፡ በባንኮች ያለው ተቀማጭ ገንዘብም ከ1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል፡፡ይህም በዘርፉ ያለውን ስብራት የቀረፈ ነው፡፡

2. አገራዊ እድገትን በተመለከተ
- ኢትዮጵያ በዓለም ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አገራት አንዷ ናት፡፡ በዘንድሮው ዓመትም በኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ይጠበቃል፡፡ በተለይ በግብርና ዘርፍ እጅግ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል፤ በፊስካልና ሞኒተሪ ፖሊሲ ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችም ከፍተኛ ለውጥ እያስመዘገቡ ነው፡፡

3. የአገር ውስጥ ገቢን በተመለከተ
- ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ 265 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡ ይህም ከእቅድ አንጻር 98 በመቶ አፈጻጸም አለው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ካላት አገራዊ ጥቅል ምርት አንጻር የሚገባትን ያህል ገቢ እየሰበሰበች አይደለም፤ በቀጣይ የገቢ አሰባሰብ ስርዓታችንን በማዘመን የተሻለ ገቢ መሰብሰብ አለብን፡፡

4. የስራ እድል ፈጠራና ኢንቨስትመንትን በተመለከተ
- ባለፉት ስድስት ወራት ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡ ከ150 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በውጭ አገራት የስራ እድል ስምሪት ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ኢንቨስትመንትን በማሳብ ረገድም ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል፡፡

5. የእዳ ጫናን በተመለከተ
- የለውጡ መንግስት ከሚኮራባቸው ድሎች አንዱ የእዳ ጫና ቅነሳ ነው፡፡ ባለፉት 5 ዓመታት መንግስት ምንም አይነት የኮሜርሻል ብድር አልወሰደም፡፡ በተቃራኒው ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ 9 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር በድር መክፈል ችላለች፡፡ ከአምስት ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ጫና 32 በመቶ የአገራዊ ጥቅል ምርት(ጂዲፒ) ድርሻ የነበረው ሲሆን፣ይህን ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ ዋናው ፍላጎታችን ከ10 በመቶ በታች ዝቅ ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ መክፈል አለቻለችም በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው፡፡

6. ዲፕሎማሲን በተለመከተ
- ኢትዮጵያ የትኛውንም የባለብዙ ወገድ ድርጅት የምትቀላቀልበት ዋነኛ ዓላማ ብሔራዊ ጥቅሟን ማስከበር ነው፡፡ ብሪክስ የተቀላቀልንበት ዋነኛው ምክንያትም የምዕራቡን ዓለምን በመተው ወደ መስራቁ ለመሄድ ሳይሆን ከሁሉም ጋር በመተባበር ጥቅማችንን ለማስከበር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከምዕራቡም ሆነ ከምስራቁ አገራት ጋር ጥብቅ ወዳጅነት አላት፡፡ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

7. ከሶማሊያ ጋር ያለውን ትብብር በሚመለከት
- የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በደም የተሳሰሩ ናቸው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ለሶማሊያ ሰላም ሞተዋል፡፡ ለሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያን ያህል ዋጋ የከፈለ አገር የለም፡፡ይህም የሶማሊያ ሰላም የኢትዮጵያ ሰላም ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ጥብቅ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ወዳጅ በሆነችው ሶማሊያ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዲደርስ አትሻም፡፡ኢትዮጵያ በታሪኳ በትኛውንም አገር ላይ ወረራ ፈጽማ አታውቅም፡፡ነገር ግን አንዳንድ ሃይሎች ሁለቱን አገራት ለማጋጨት እየጣሩ ነው፡፡ ይህ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም፡፡ የእኛ ጥያቄ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የባህር በር መጠቀም ያስፈልገናል የሚለው ነው፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ ባለፈ ለቀጣናው ትብብርና ትስስር የሚበጅ ነው፡፡

8. ህዳሴ ግድብን በተመለከተ
- ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ለመደራደር ዝግጁ ናት፡፡ የግብጽ ወንድሞቻችን ያላቸው ጥያቄ ለማድመጥና በተቻለ መልኩ ለመፍታት ዝግጁ ነን፤ እነርሱም የእኛን ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን አለባቸው፡፡ ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሊት ስታከናውን በግብጽ ያለው የአሰዋን ግድብ የወሃ መጠን ይቀንሳል በሚል ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ትክክል አለመሆኑ በተግባር ታይቷል፡፡ ውሃ የመሙላት ጉዳይ አሁን ጥያቄ አይመስለኝም፡፡ ኢትዮጵያ በመነጋጋር፣ በመወያየት በትብብር ማደግ ትሻለች፡፡ነገር ግን የእኔ ብቻ የሚለው አካሄድ ግን ብዙም አያዛልቅም፡፡

#የጠሚሩምላሾች
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋናዋና ሃሳቦች (ክፍል 1)

1. ሰላምን በተመለከተ
- ሰላም ሁሌም በውድ ዋጋ የሚገኝ ነው ፡፡በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 50 ዓመታት ሃሳብን አደራጅቶ የፖለቲካ ፍላጎትን ከማሳካት ይልቅ ጠመንጃን አማራጭ የማድረጉ ልምምድ ለሰላም እንቅፋት ፈጥሯል፤ወንድም ወንድሙን ገድሎ ምን አሳካ ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምንም የሚለው ይሆናል፡፡ ችግሮች የሚፈቱትም በውይይት ብቻ ነው፡፡

2. ሸኔን በተመለከተ
- ጠመንጃ ታጥቆ የራስን ህዝብ እያሰቃዩ እታገልልሃለሁ ማለት ትርጉም የሌለው አካሄድ ነው፡፡ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል እያደረገ ያለውም ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ውስጥ በሰላም፣ በዴሞክራሲና በምርጫ ካልሆነ ጠመንጃ ይዞ ወደ ስልጣን መምጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡

3. በአማራ ክልል ያለውን ሁኔታ በተመለከተ
- በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ባደረግነው ውይይት ከህዝቡ ሶስት ዋና ጥያቄዎች ተነስተውልናል፡፡ እነርሱም የልማት፣ የህገ መንግስት ማሻሻልና የወሰን ጥያቄዎች ናቸው፡፡ መንግስት በአማራ ክልል የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ብዙ ርቀት ሄዷል፤ ለአብነትም 2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አውጥተን በአባይ ወንዝ ላይ በአይነቱ ልዩ የሆነ ድልድይ ገንብተናል፡፡ በጎርጎራ ፕሮጀክት አማካኝነትም የክልሉን ቱሪዝም የሚያነቃቃ ስራ ተከናውኗል፡፡ በአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኩል ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ የሚሰራ ይሆናል፡፡

4. በአማራ ክልል የሚነሳውን የወሰን ጥያቄን በተመለከተ
- መንግስት ከአስተዳደር ወሰን ጋር የሚነሱ ጥያቄዎች በውይይትና ዘላቂ ሰላም በሚያመጣ አግባብ እንዲፈታ በጽኑ ይፈልጋል።

#የጠሚሩምላሾች
ባለስልጣኑ የስራ ቦታ የአድራሻ ለውጥ በማድረግ አገልግሎቱን በቀየረው ህንፃ መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

01/06/2016 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የማዕከል ሰራተኞች የስራ ቦታ የአድራሻ ለውጥ መደረጉን በማስመልከት በቀጣይ ለህብረተሰቡ ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት አሠራሮች ዙርያ የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደረገ።

ባለስልጣኑ ቀድሞ ቦሌ በሚገኘው ደንበል ሲቲ ሴንተር ሲጠቀምበት የነበረውን የስራ ቦታ ለቆ ፒያሳ በተለምዶ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ EMA ታወር ላይ ስራ ጀምሯል።

በውይይቱ ለተገልጋይ ማህበረሰቡና ለሠራተኛው ምቹ የሆነ የስራ አካባቢ ለመፍጠር በማሰብ ተቋሙ የአድራሻ ለውጥ ማድረጉንና አገልግሎት እንዳይቋረጥ በማሰብ በጥቂት ቀናት ውስጥ እቃዎችን በማጓጓዝ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ፉፋ ገልፀዋል።

የባለስልጣኑ የማዕከል ሰራተኞች በውይይቱ ከዚህ በፊት የነበረው የስራ ቦታ ለተገልጋይና ለሠራተኛው ምቹ እንዳልነበረ በመግለፅ ተቋሙ የሰራተኛው ጥያቄ ለመመለስ ላደረገው ጥረት ለተቋሙ አመራሮች እና ትብብር ላደረጉት ተቋማት ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

በመድረኩ ሰራተኞች የአድራሻ ለውጥ የተደረገበት ምክንያት ለተገልጋይና ለሠራተኛው የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት መሆኑ በመረዳት ከምንጊዜውም በላይ ህብረተሰቡ ለማገልገል መትጋት እንዳለባቸው በመግለፅ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል።

ዘገባው፦የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

👉ለማንኛውም የደንብ መተላለፍ ጥቆማ ነፃ የተቋሙን የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።