የዓድዋ ድል በዓል ዛሬ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል
የካቲት 22/2016 ዓ.ም
#አዲስ አበባ
128ኛ የዓድዋ ድል በዓል ዛሬ ፒያሳ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ::
128ኛ የዓድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ መድፍ ተተኩሷል።
የአፍሪካውያን ድል የሆነው "የዓድዋ ድል " ኢትዮጵያውያን የዛሬ 128 ዓመት በወራሪው የፋሺሽት ጣልያን ጦር ላይ የተቀዳጁት አንፀባራቂ ድል ምክንያት በማድረግ በአሉ በየአመቱ ሲከበር ቆይቷል።
የዘንድሮው 128ኛው የዓድዋ ድል በዓልም ዛሬ ፒያሳ በሚገኘው የአድዋ ድል መታሰቢያ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል ፡፡
#አዲስአበባ
#AddisAbaba
#ኢትዮጵያ

የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ
መጋቢት 5/2016 ዓ.ም
#አዲስአበባ
የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የተለያዩ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለፉ ሴቶች ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ ያስችላል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማዕከሉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል የሴቶች ፆታዊ እኩልነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ሴቶችን ማብቃት እና የእኩልነት መብታቸውን ማክበር እና ማስከበር እያረጋገጥን መሔድ እንደሚገባን በምንሠራቸው ሥራዎች ሁሉ ውስጥ የትኩረት አቅጣጫችን መሆኑን የምናሳይበት አንዱ ሥራ ነው ብለዋል።
ዛሬ ይህንን ማዕከል መርቀን ስንከፍት አዲስ የተገነባ ሕንፃን ሥራ ከማስጀመር ባለፈ የተሻለ ነገን፣ ብሩህ ተስፋን፣ ፅናትን እና ሰፊ ሠርቶ የመለወጥ ዕድልን በዘላዊ ፅኑ መሠረት ላይ እየተከልን መሆኑን በማነን ነው ሲሉም አክለዋል።
በርካታ ሴቶች በሚደርስባቸው ፆታዊ አድልኦ፣ ተፅዕኖ እና ጥቃት ለተለያዩ ማኅበራዊ ጫናዎች እና በደሎች ከመጋለጥ በላይ በማኅበረሰባቸው እና ለሀገራቸው ዕድገት አቅማቸው የሚፈቅደውን አስተዋፀኦ ማድረግ እንዳይችሉ ከፍተኛ ውስንነት ውስጥ እንዲያልፉ እንደሚያደርጋቸው አንሥተዋል።
በሀገራችን ይህንን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ለሴቶች ዕድልን ለማስፋት፣ ለማብቃት፣ እኩል ተጠቃሚ እና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን እና አበራታች ውጤቶችም መታየታቸውን ጠቁመዋል።
ዛሬም በርከታ እህቶቻችን እና ልጆቻችን ላይ በሚደርሰው የተወሳሰበ ፆታዊ አድልኦ የኢኮኖሚ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ዕድል ጠባብ መሆን ተጨምሮበት ለኢኮኖሚ ጥገኝነት፣ ለአካላዊ እና ፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው ብለዋል።
በመሆኑንም ይህ የሴቶች ተሃድሶ እና የክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ሁሉን ችግር የሚፈታ ባይሆንም ለጎዳና ሕይወት እና ለወሲብ ጥቃት እንዲሁም ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ የሆኑ እህቶቻችን አማራጭ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ የሚያበቃቸውን እና ብቁ የሚያደርጋቸውን የክህሎት፣ የሥነ-ምግባር፣ የሥራ ባህል፣ የሥራ ስምሪት ጭምር እንዲፈጠርላቸው በማድረግ ነገአቸው ብሩህ ተስፋ የተሞላበት እንዲሆን ለማድረግ እንደሚያስችል እምነታቸውን መግለፃቸው AMN ዘግቧል።
#Ethiopia
#addisababa

🙏4👍2