የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን Addis Ababa Code Enforcement Authority
1.09K subscribers
1.75K photos
4 videos
1 file
52 links
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
Download Telegram
ባለስልጣኑ ኮሪደር ልማት በመኪና ጉዳት ያደረሰው ሻሞ የመኪና ኪራይ ድርጅት 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ

03/09/2017 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ምሽት 2:ዐዐ ሰአት አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ በኮርደር ልማት ላይ ጉዳት በማድረስ የደንብ መተላለፍ የፈፀመ ሻሞ የመኪና ኪራይ ድርጅት 100,000/አንድ መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ አስታወቀ።

የደንብ መተላለፉ አዲስ በተስራው በኮርደር ልማት የብስክሌት መንገድ በመኪነና በመሄድ በህዝብ ሀብት ላይ በተሰራው ልማት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ድርጊቱ ከቅጣቱ ባለፈ በህግ ተጠያቂነትንም ስለሚያስከትል አሽከርካሪው ለጊዜው ቢሰወርም በህግ ቁጥጥር ስር ይውል ዘንድ ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

በሰዓቱ የተመደቡ ሁለት ኦፊሰሮች በቀጠናው ስራ ላይ ቢኖሩም አፋጣኝ እርምጃ ባለመውሰዳቸው የአንድ ወር ደሞዝ እንዲቀጡ ተደርጓል።

ባለስልጣኑ የህብረተሰቡ የጋራ ሀብት የሆኑ የኮርደር ልማትና በሌሎች አካባቢ የማገኙ መሠረተ ልማቶችን፣ለህዝብ የተሰሩ አረንጓዴ ስፍራዎች እና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ደህንነት በመጠበቅ በሀላፊነት እንዲገለገል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በከተማዋ ደንብ የሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍132
''ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቋምና አፈፃጸሙ በማሳደግ ተዓምራዊ ለውጥ በማምጣት ላይ ይገኛል" የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የሰላም፣ የፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ

ግንቦት 4/2017
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም የፍትህ መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴዎች የከተማ አስተዳደሩ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት 9 ወራት የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የመስክ ምልከታ በማድረግ አፈፃፀሙ ገመገሙ፡፡

በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሰላም ፍትህና መልካም አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን በማሳደግ ተምራዊ ለውጥ በማምጣት የከተማ አስተዳደሩን ደንብ ጥሰቶች በመከላከል አዳስ የወጡ ደንቦችን የማስተግበር ትልቅ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀው ይህንንም ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ በሎም ማዕከል ላይ በተደረገ የመስክ ምልከታ እና ሱፐር ቭዥን መመልከታቸውን ተናግረዋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ3ሺህ በላይ ለሚሆኑ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የደመወዝ ልዮነትና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች መስተካከል መቻሉ ፤ ከድግሪ በላይ የሆኑ 2000 ምልምል የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠና ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

አያይዘውም ባለስልጣኑ ለሀገሪቱ ክልል ከተሞች ደንብ የማስከበር ተሞክሮ የመስጠት አስተዎፆ እያደረጉ መሆኑን እና በከተማ አሰተዳደሩ ከሚገኙ አብዛኛው ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ደንብን የማስከበር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የ2017 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተስፋሁን አሉላ ቀርቧል ።

በሪፖርቱ በርካታ የተቋም ግንባታ ስራዎች መሰራታቸው ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸውን ፣ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድና ሰው ተኮር ሰራዎችን በስፋት መስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን በሪፖርቱ ቀርቦል፡፡

ከቋሚ ኮሚቴው አባላት ባለስልጣኑ ከዕለት ወደ እለት እራሱን በማሻሻል አዳዲስ ስራዎችን በቁርጠኝነት በመስራት የተለወጠ ደንብ ማሳየት መቻሉን ፣ ስራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳየ ያለውን መሻሻል ይበል የሚሰኝ ተግባር መሆኑን በመግለፅ በተለይም መድረኮች ሲኖሩ ቋሚ ኮሚቴውን በመጋበዝ የሚነሱ ችግሮችን ቀጥታ ቋሚ ኮሚቴው ከሚመለከተው አካል እንዲወስድ የማድረግ ስራ መሰራቱን የቋሚ ኮሚቴው ተወካዮች ገልፀዋል።

በተጨማሪም የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተናበው ሰራዎችን ከሰባዊነት ጋር በመስራቱ ለውጦች መመጣታቸውን ጠቁመው በምዘናው አብዛኛው በጥንካሬ አንደሚወሰድ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተቋም ግንባታ እና አዲስ የስገነባውን የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ስቱዲዮ በመጉብኝት ምዘናው ተጠናቋል ።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍2
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ደንብ የተላለፉ ተቋማት 1.5 ሚሊየን ብር ተቀጡ

04/09/2017 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፋለ ከተማ ወረዳ 03 ኖህ ሪል እስቴት ከተቋሙ ግቢ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከወንዝ ጋር በቀጥታ በማገናኘታቸው በተደጋጋሚ በተፈጠረላቸው በግንዛቤ እና በተወሰደባቸው የገንዘብ መቀጮ ተምረው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እና ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ባለመቻላቸው በዛሬው እለት ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሰላም ፀጥታ እና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት በሪከርድ የጥፋቱ እጥፍ 800,000 ብር መቀጣቱ አስታወቀ።

በተመሳሳይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሁለት ተቋማት ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በመገኘታቸው 700,000 በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

በአጠቃላይ በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው ደንብ ቁጥር 180/2017 ተላልፈው በተገኙ ሶስት ተቋማት ላይ በተወሰደ እርምጃ 1,500,000 ብር መቀጣታቸው ገልጿል።

ባለስልጣኑ በከተማው ከአሁን በፊት ተቀጥተው ከድርጊታቸው የማይቆጠቡ ተቋምና ግለሰቦችን በሪከርድ የቅጣቱ እጥፍ በመቅጣት የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ተቋሙ ለከተማው ነዋሪዎች ማንኛውም የደንብ መተላለፎች ሲያጋጥሙ ለደንብ ማስከበር ባለስልጣን በነጻ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሮክቶሬት ነው።
👍4
ባለስልጣኑ የደንብ ጥሰት የፈጸመውን የከተማ አብቶቢስ አሽከርካሪ መቅጣቱን አስታወቀ

07/09/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በለገሀር አከባቢ የከተማ አውቶቢስ ሹፌር ከመኪናው የጠረገውን ደረቅ ቆሻሻን አስፓልት ላይ በመጣሉ በደንብ ቁጥር 167/2016 መሰረት አምስት ሺህ ብር በመቅጣት ለመንግስት ገቢ ማድረጉን አስታወቀ ።

ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ በጊዜው ተሸከርካሪዉን ይዞ ከቦታዉ ቢሰወርም በተደረገዉ ክትትል በዛሬዉ እለት የካ
ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ላይ ሹፈሩን ከነተሸከርካሪው በቁጥጥር ሰር በማዋል መንገድ በማቆሸሸ ለተላለፈዉ የደንብ ጥሰት የገንዘብ ቅጣት በመቅጣት ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ለሰጠው ጥቆማ ከልብ እያመሠገነ ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች መረጃ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪውን ያቀርባል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
👍17
ባለስልጣኑ ልምዱን እና ተሞክሮውን ለሐረሪ ከተማ አስተዳደር ልዑካን ቡድን አባላት አጋራ

            12-09- 2017 ዓ.ም
          አዲስ  አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሐረሪ ከተማ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት በተቋም አደረጃጀት፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በገጽታ ግንባታ ፣ በሰው ሃይል አደረጃጀት እና ከባለድርሻ  አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ  አጋርቷል፡፡


በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እንደየስራ ክፍል አሰራሮችን እና የተቋሙ ተሞክሮዎች ን የገለጹ ሲሆን የሐረሪ ከተማ አስተዳደር  ከተቋሙ ልምድ በመውሰድ እና ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ለልዑካን ቡድኑ አባላት አስረድተዋል፡፡

ባለስልጣኑ ሀረሪ  ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ተቋሙን ለማጠናከር በሚያደርገው  እንቅስቃሴዎች  በሚችለው ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል።

የልዑካን ቡድን አባላት ተቋሙ የተደራጀበት እና ከባለድርሻ ተቋማት ጋር በመነጋገር እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራዎች አድንቀው የወሰዱት ተሞክሮ ጠቃሚ እና ልምዱን በከተማቸው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ለማንኛውም የደንብ መተላለፎች ጥቆማ ነፃ የስልክ መስመር 9995 ይጠቀሙ።

ዘገባው :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
👍1